Archive | January 2014

ወያኔን ያሸበረው የግንቦት 7 መንገድ ምንድነው?

የትግራይን ሕዝብ ከብሄር ጭቆና ነጻ አወጣለሁ በሚል ጠባብ ዓላማ ተደራጅቶና ታጥቆ ለበትረ ሥልጣን የበቃው ህወሃት ወይም ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረ 23 አመት ሊሞላው እነሆ ጥቂት ወራቶች ብቻ ቀርተውታል።

ለጋራ ቤታችን ለሆነቺው አገራችን ኢትዮጵያና በአስተዳደር በደል ለከፋ ድህነት ለተዳረገው መላው ሕዝቦቿ የሚሆን አንዳችም ራዕይ ሳይኖረው ለመንግሥትነት ሥልጣን የበቃው ይህ ቡድን ላለፉት 23 ዓመታት ከግል ኑሮአቸው አሻግረው የአገርንና የወገንን ጥቅም ማየት የማይችሉ ወይም የማይፈልጉትን በዙሪያው አሰባስቦ እያካሄደ ካለው ዘርፈ ብዙ የሃብት ምዝበራ ወንጀል በተጨማሪ እየፈጸመ ያለው የመብት ጥሰትና አፈና ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።

ሰሞኑን እያፈተለኩ በመውጣት ላይ ከሚገኙ ምስጥራዊ የድምጽ መረጃዎች ለማረጋገጥ እንደተቻለው ደግሞ ለጥቂቶች የሃብትና የብልጽግና ምንጭ የሆነው ሥልጣን ከእጃቸው እንዳይወጣ በአንድ በኩል በምርጫ ስም እንዴት አድርገው ሕዝቡን ቀፍድደው የምርጫው ተሳታፊ ማድረግ እንደሚችሉ ሲዶልቱና በሌላ በኩል ደግሞ በቁጥጥራቸው ሥር የሌሉትንና ለሥልጣናቸው ያሰጉናል ያሉዋቸውን የደሃዉን ልጅ በማጋፈጥ እንዴት በጦርነት እንደሚጨፈልቁዋቸው ሲመክሩ ተሰምተዋል።

ከወያኔው ቁንጮ አንዱ የሆነው በረከት ስሞን በየደረጃው ላሉት የአገዛዙ ሹሞችና ካድሬዎች ባደረገው ገለፃ መሬትን የመንግሥት ባደረገው ኮሚኒስታዊ አዋጅ ምክንያት የመንግሥት ጭሰኛ ለመሆን የተፈረደበትን ሰፊውን አርሶ አደር “ተኛ ስንለው ይተኛል፤ ቁም ስንለው ይቆማል ፤ እንደፈለግን ብንበድለው እንኳ አያማርረንም ” እያለ ሲዘባበትበት ተደምጦአል ። በአንድ ለአምስት ኮሚንስታዊ አደረጃጀት ተጠርንፎ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ብቻ የሚያቀርቡትን ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ያለውዴታው እንዲራገፍበትና ከአቅሙ በላይ ዕዳ እንዲቀፈቅፍ የተፈረደበት የኢትዮጵያ አርሶ አደር በዚህ አይነት ንቀት ደረጃ የሚዘባበትበትን መሪ ከወያኔው በረከት ስሞን በፊት ገጥሞት አያውቅም ። ለወደፊትም ሊያይ አይፈልግም ። ወያኔን ሥልጣን ላይ ለማምጣት የሰሜኑ ክፍለአገራችን አርሶ አደር የተጫወተው ሚና ተዘንግቶ በበረከት ስሞን እንዲህ መዋረዱ እጅግ ያሳዝናል። ለነገሩ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ ለድል ያበቃው የትግራይ ሕዝብ ቁም ስቅሉን እያየ አይደል?

ሌላው አስገራሚ ክስተት በአገር ደህንነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ባደረጉት ዝግ ስብሰባ ታማኝነታችን ለአገራችን ነው ወይስ የሥርዓቱን አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም? ብለው ላነሱት ጥያቄ የጠቅላይ ሚንስትር ተብዬው የህግ አማካሪ ጌታቸው ረዳ የሰጠው መልስ ነው። ደህንነት ብቻ ሳይሆን የመከላኪያ ሠራዊትና ፖሊስ ጭማር ታማኝነታቸውና ግዴታቸው ሥርዓቱን ሥልጣን ላይ ማቆየት መሆን አለበት ሲል ጌታቸው እንቅቹን ነግሮአቸዋል ። በምላሹ “ላለፉት 23 አመታት እያደረግነው ያለው ይሄው ሆኖ ሳለ አሁን ምን ብታስቡ ነው ጥያቄ ያነሳችሁ?” የሚል ይመስላል ። ይባስ ብሎም ሥርአቱን ለመጠበቅ ያልቻለና በግንቦት 7 መንገድ የሚጓዝ ደህንነት ሠራተኛ የተስፋየ ገብረስላሴን ያህል የደህንነት እውቀት ቢኖረውም ሆነ እስራኤል አገር የዓመታት ስልጠና ያገኘ ቢሆን ዋጋ የለውም ብሏቸዋል።

ለመሆኑ ወያኔዎች እንደመርገም የቆጠሩትና ተከታዮቻቸውን የሚያስፈራሩበት የግንቦት 7 መንገድ ምንድ ነው።?

ግንቦት 7 የፍትህና፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራችን ኢትዮጵያ የእያንዳንዱ ዜጋ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት የተከበረባት፤ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ፤ የዜጎች ሕይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረባት እና የሕዝቧ አንድነትና ትስስር የጠነከረባት ሃገር ሆና ማየትን ብቸኛ ራዕይ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ ደግሞ እስከ ዛሬ በጠመንጃ ኃይልና በጉልበተኖች ጡንቻ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈራረቀው የመንግሥት ና የፖለቲካ ሥልጣን በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትን ፤ የሃገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበት፤ ማኅበራዊና የፖለቲካ ችግሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈቱበት እና ዲሞክራሲያዊ ባህል የሚበለፅግበት ብሄራዊ የፖለቲካዊ ሥርዓት መገንባት አማራጭ የሌለው ነው ብሎ ያምናል።

ይህ ደግሞ ያለምክንያት አይደለም። ወያኔ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ በሩን ከፈት አድርጎ በነበረበት ምርጫ 97 ወቅት ከተገኘው ልምድና ከተመዘገበው ውጤት ሕዝባችን በአምባገነኖችና በከፋፋዮች ለመገዛት አለመፈለጉን በግልጽ አስመስክሮአል።

ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ሕዝባችን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በነቂስ ወጥቶ መሪዎቹን የመረጠበትንና ድሉን የተነጠቀመበትን ታሪካዊ የግንቦት 7 1997ን ቀን ምን ጊዜም አይረሳም። መጠሪያ ስሙንም በዚያ ታሪካዊ ቀን የሰየመው ሕዝብ የተነጠቀውን ድል በማስመለስ ፍትህ የሰፈነባት፤ የበለጸገችና የተከበረች አገር ባለቤት እንሆን ዘንድ ነው። ሁላችንም አትራፊ እንጂ ተጎጂ ለማንሆንበት ለዚህ ቅን አለማና ራዕይ ደንቃራ ሆኖ የተገኘው ወያኔና ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከወያኔ ጋር የተጣበቁ አንዳንድ ባዕዳን አገሮች ናቸው።

ወያኔ የግንቦት 7 መንገድ የሚለው ለዚህ ክቡር ዓላማ ሲባል እንቅፋት የሆነውን ሥርዓቱን በሁለ- ገብ ትግል አስገድዶ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር አካል ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ በተባበረ ትግል አስወግዶ በምትኩ በሕዝብ ለሕዝብ ከሕዝብ የሚመጣ ሰላማዊ የመንግሥት ሥርዓት መመሥረትን ነው። ይህንን የተቀደስ አላማ ለማክሸፍና የተጀመረውን ትግል ለመጨፍለቅ ሲባልም ወደ ሥልጣን ለመምጣት በጦርነት ማግዶ ካስጨረሳቸው የደሃ ልጆች በእጥፍ የሚበልጡትን መልምሎ በጸረ ሽምቅ ውጊያ ከማሰልጠን ጎን ለጎን ለግንባታ ቢውል ስንት ፋይዳ ሊያስገኝ ይችል የነበረ በርካታ ገንዘብ በማፍሰስ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ድምጽ ለማፈንና ለመሰለል እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለአገራችን ሉአላዊነት ጠቀሜታው እስከዛሬ ምንም ባልታወቀ ጦርነት ወደ መቶ ሺ የሚጠጉትን ያስጨፈጨፈ፤ የተልዕኮ ጦርነት ለማካሄድ በመንግሥት አልባዋ ጎረቤት ሱማሌ እስከዛሬ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ወገን ያስፈጀ ፤ ለሥራ ፍለጋ ውትድርና የገቡትን ወጣቶች ለይቶ በሰላም አስከባሪ ስም በድንበር ዘለል ጦርነቶች እየማገደ ገንዘብ የሚቀበል፤ ስለአገርና ስለወገን ምን ሊገደው ይችላል?

ትናንት ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት የቀደምቶቹ መንግስታት ልጆቻቸውን ለትምህረት ወደ ፈረንጅ አገር እየላኩ የደሃውን ልጅ በጦርነት ይማግዳሉ በማለት በጅምላ ሲከስ የኖረ ዛሬ በተራቸው ልጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን ዘርማንዘሮቻቸውን ታይቶ በማይታወቅ ብዛት ወደ ፈረንጅ አገር ለትምህርት እየላኩ ለነጻነታችንና ለክብራችን የምንታገለውን እርስ በርስ ለማጨራረስ ሲዶልቱ ዝም ብሎ መመልከት ከየትኛውም ቅን ዜጋ የሚጠበቅ አይሆንም።

ስለሆነም የበላይ አዛዦቻቸው በሚሰርቁት የሕዝብ ገንዘብ ፎቅ ላይ ፎቅ እየገነቡ ሃብት በሚያካብቱት አገር ሠራዊቱን እረፍት ለመንሳት ሆን ተብለው በሚቀሰቂሱት ግጭቶች ከአንዱ ማዕዘን ወደ ሌላው ማዕዘን ያለ ዕረፍት እየተንከራተተ ያለው የመከላኪያ ሠራዊት ፤ የፖሊስና የደህንነት ኃይል ለአገዛዙ አልታዘዝም በማለት ተገዶ ሥልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክብ የማድረግ ወገናዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ግንቦት 7 የፍትህ የነትጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።

የግንቦት 7 መንገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት የተጠማውን ፍትህ እኩልነትና ነጻነት በአገራችን ለማስፈን አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የጎጠኞችና የዘራፊዎች ስብስብ በማስገደድ ወይም በማስወገድ ሰላማዊ ህጋዊና ዲሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ማድረግ ነው። ይህንን ደግሞ የሚፈሩት በሥልጣን ቱርፋትና በሃብት ዘረፋ የሰከሩ ብቻ ናቸው።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

posted by Alemayehu Tibebu

Ethiopia – Land for Sale(cheapest price per hectar) Al Jazeera

 Just a few decades ago, Ethiopia was a country defined by its famines, particularly between 1983-1985 when in excess of half a million people starved to death as a consequence of drought, crop failure and a brutal civil war.

Against this backdrop, it is impressive that in recent years, Ethiopia has been experiencing stellar economic growth. The headline statistics are certainly remarkable: the country is creating millionaires faster than any other in Africa; output from farming, Ethiopia’s dominant industry, has tripled in a decade; the capital Addis Ababa is experiencing a massive construction boom; and the last six years have seen the nation’s GDP grow by a staggering 108 percent.

But it is not all positive news, because for all the good figures there are still plenty of bad ones.

Around 90 percent of the population of 87 million still suffers from numerous deprivations, ranging from insufficient access to education to inadequate health care; average incomes are still well below $1500 a year; and more than 30 million people still face chronic food shortages.

Ethiopian farmer in Gambella region
And while there are a number of positive and genuine reasons for the growth spurt – business and legislative reforms, more professional governance, the achievements of a thriving service sector – many critics say that the growth seen in agriculture, which accounts for almost half of Ethiopia’s economic activity and a great deal of its recent success, is actually being driven by an out of control ‘land grab’, as multinational companies and private speculators vie to lease millions of acres of the country’s most fertile territory from the government at bargain basement prices.

At the ministry of agriculture in Addis Ababa, this land-lease programme is often described as a “win-win” because it brings in new technologies and employment and, supposedly, makes it easier to improve health care, education and other services in rural areas.

“Ethiopia needs to develop to fight poverty, increase food supplies and improve livelihoods and is doing so in a sustainable way,” said one official.

But according to a host of NGO’s and policy advocates, including Oxfam, Human Rights Watch and the Oakland Institute, the true consequences of the land grabs are almost all negative. They say that in order to make such huge areas available for foreign investors to grow foodstuffs and bio-fuels for export – and in direct contravention of Ethiopia’s obligations under international law – the authorities are displacing hundreds of thousands of indigenous peoples, abusing their human rights, destroying their traditions, trashing the environment, and making them more dependent on food aid than ever before.

“The benefits for the local populations are very little,” said renowned Ethiopian sociologist Dessalegn Rahmato. “They’ve taken away their land. They’ve taken away their natural resource, because these investors are clearing the land, destroying the forest, cutting down the trees. The government claims that one of the aims of this investment was to enable local areas to benefit by investing in infrastructure, social services … but these benefits are not included in the contract. It’s only left up to the magnanimity of the investor.”

And those investors, he continued, are simply not interested in anything other than serving their own needs: “They can grow any crop they want, when they want it, they can sell in any market they want, whether it’s a global market or a local market. In fact most of them are not interested in the local markets.”

He cited as an example a massive Saudi-owned plantation in the fertile Gambella region of south west Ethiopia, a prime target area for investors: “They have 10,000 hectares and they are producing rice. This rice is going to be exported to the Middle East, to Saudi Arabia and other places. The local people in that area don’t eat rice.”

But the most controversial element of the government’s programme is known as ‘villagisation’ – the displacement of people from land they have occupied for generations and their subsequent resettlement in artificial communities.

In Gambella, where two ethnic groups, the Anuaks and the Nuers, predominate, it has meant tens of thousands of people have been forced to abandon a traditional way of life. One such is Moot, an Anuak farmer who now lives in a government village far from his home.

“When investors showed up, we were told to pack up our things and to go to the village. If we had decided not to go, they would have destroyed our crops, our houses and our belongings. We couldn’t even claim compensation because the government decided that those lands belonged to the investors. We were scared … if you get upset and say that someone stole your land, you are put in prison. If you complain about being arrested, they will kill you. It’s not our land anymore; we have been deprived of our rights.”

Despite growing internal opposition and international criticism, the Ethiopian government shows no sign of scaling the programme back. According to the Oakland Institute, since 2008, an area the size of France has already been handed over to foreign corporations. Over the next few years an area twice that size is thought to be earmarked for leasing to investors.

So what does all this mean for the people on the ground? In Ethiopia – Land for Sale, filmmakers Veronique Mauduy and Romain Pelleray try and find out.

Source: Al Jazeera

ኢትዮጵያን ለማዳን ወቅቱ አሁን ነው!!! የተከበሩ አቶ ልዑል ቀስቅስ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ሊቀመንበር/MP. Leul Keskis EPPFGuard chairman

1528716_385228011613166_627076728_n

MP. Leul Keskis EPPFGuard chairman Interview
አቶ ልዑል ቀስቅስ አስታጥቄ በጎንደር ከተማ ተወልደው የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ከተማ ውስጥ በሚገኘው ፃድቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአፄ ፋሲለደስ መለስተኛ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡
ከዚያም የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት በመቀላቀል ሁርሶ መኮንኖች ማሰልጠኛ በመግባት የሁለት አመት ወታደራዊ አካዳሚ ትምህርታቸውን ጨርሰው በመቶ አለቅነት ማዕረግ ተመርቀዋል፡፡
በመቀጠልም ኤርትራ ውስጥ በነበረው 2ኛው አብዮታዊ ሰራዊት ተመድበው በሻለቃ አዛዥነት እንዲሁም በዘርያድረስ 27ኛ መካናይዝድ ብርጌድ አመራር በመሆን በርካታ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎችን አድርገዋል፡፡ ለሀገራቸው ከፍተኛ መስወዓትነት ከፍለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በህግ ትምህርት በዲፕሎም ተመርቀዋል በማዕከላዊ እስታስቲክስ መስርያ ቤት ተቀጥረው ለ11 ዓመት ሰርተዋል፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል በማለት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላም እና ዴሞክራሲ ለማምጣት በተቋቋሙት የሰላም ታጋይ ድርጅቶች ውስጥ በመግባት ቅንጅትን ቅንጅት ካደረጉት ግንባር ቀደም የሀገራችን ውድ ልጆች መካከል አንዱ ሆኑ ፡፡ በቡዙዎች የሀገራችን ሕዝቦች ዘንድ ታላቅ ተስፋን ሰጥቶ በነበረው ሆኖም በወያኔ ቡድን በተጨናገፈው የ1997 ዓ.ምረቱ ሀገራዊ ምርጫ በጎንደር ከተማ ቅንጅትን በመወከል ተወዳድረውና ሰፊ የህዝብ ድጋፍ አግኝተው የኢትዮጵያ የፓርላማ አባል በመሆን ለተወሰነ ጊዜ አማራጭ ሲጠፋ ገብተው ለተወሰነ ጊዜ እንደቆዩ ፓርላማው የወያኔ ፓርላማ እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደማይወክል ተረድተው እና የተገነዘቡትንም ችግር ለሪፖርተር ጋዜጣ መግለጫ ሰጥተው ፓርላማውን ትተው በረሀ ገቡ፡፡
አንባገነኖችን በትጥቅ ትግል ካልሆነ በስተቀር በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አምነው ስልጣናቸውን ለህዝብ እንደማያስረክቡ ያረጋገጡት አቶ ልዕል በወቅቱ ኤርትራ ውስጥ ይገኝ የነበረውን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተቀላቀሉ፡፡ ለ10 ወራትም የትጥቅ ትግል ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
ወደውጭ በመውጣት በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት እና በማደራጀት ቢሰሩ ይበልጥ ውጤታማ ሊሆኑ እና ለድርጅቱም ከፍተኛ ጥቅም መሆኑን የተገነዘበው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወደ ውጭ እንዲወጡ አደረገ፡፡ ላለፉት 3 ዓመታትም በውጭ ሀገር የግንባሩ ተወካይና የአለም አቀፍ ኮሚቴው ሊቀመንበር በመሆን የሚጠበቅባቸውን ከፍተኛ ተግባር በብቃት እየተወጡ ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ
ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ (EPPFG) ሊቀመንበር ናቸው፡፡
በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና በድርጅቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ከድርጅቱ መጽሔት ጋር አጨር ቆይታ አድርገዋል፡፡ መልካም ንባብ
ጎህ፡- የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ከሁለት ዓመት በፊት የደርጅቱን ፕሮግራም እና ህገ ደንቡን በማሻሻል እንዲሁም ከ6
ዓመት በፊት ተመስርቶ ወያኔን ያንቀጠቀጠውን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ዘብ ጋር በመዋሀድ በአንድ መጠሪያ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በሚል ትግሉን በማካሔድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የተደረገበት ምክን ት ምንድነው ከሚለው ብንጀምርስ?
አቶ ልዑል፡- ድርጅቱ ከበፊቱ ሥያሜው የተለየ ብዙም ነገር የለውም፡፡ ሆኖም ለፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጠናከር ሲባል እንዲሁም አጠቃላይ ለድርጅቱ አደጋ የሆኑ ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል ሲባል የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ (EPPFG) የሚል ስያሜ የውህደት ሥያሜ ተሰጥቶታል፡፡
በአጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ የድርጅቱን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ሲባል ይህም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች ቀደም ብለው እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም የሁሉንም አባላት ድጋፍ አግኝቶ ከፍተኛ አመራሩ ባደረገው የመጨረሻ ሥብሰባ ውሳኔ ተሰቶበት ፀድቋል፡፡
ጎህ፡-በአሁኑ ሰዓት የድርጅቱ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?
አቶ ልዑል፡- ከላይ እንደጠቀስኩት ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ጠንካራ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ በአገር ውስጥ በሁሉም የሀገራችን ክልሎች በየስፍራው በመግባት ለውጥ ፈላጊውን ህብረተሰብ እያገዘና እያሳተፈ በህዕቡና በግልፅ እየተንቀሳቀሰ አምባገነኖችን እየታገለ ይገኛል፡፡ የድርጅት አባላትንና ደጋፊዎችን ለማሥፋት በተደረገው የተጠናከረ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት የአገር ውስጥ አባላትና ደጋፊዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን
ይህም ድርጅቱ ምን ያህል ለህዝብ ጠቃሚ አጀንዳ ያለው መሆኑ ህብረተሰቡ መረዳቱን ያመላክታል፡፡ በውጭ አገርም ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በውጭ አገር የሚኖረው ዲያስፖራ ያገሩ ጉዳይ ይመለከተዋል፡፡ ተገቢም ነው፡፡ ሆኖም በጋራ ሆኖ ትግሉን ለማካሄድ ጠንካራ ድርጅት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም የኛ ድርጅት ለውጥ ፈላጊውን በውጭ አገር የሚገኝ የኢትዮጵያ ህዝብ በማሰባሰብ ድጅታዊ ድጋፍ የመሥጠት ሚናውን እየተወጣ ነው የሚገኛው፡፡ ለዚህም በየጊዜው እየጨመረ የመጣው አባላት ቁጥር አንድ ማሳያ ነው፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖረው ህዝብ ይበልጥ የተገነዘበበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
ጎህ፡- ወያኔን ከሚታገሉ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ ምን ይመስላል?
አቶ ልዑል፡- አላማችንና አጀንዳችን አንድ ነው፡፡ ይህም አምባገነኑን የወያኔ ቡድን ማሥወገድ ነው፡፡ እናም በጋራ እየተወያየን እየሰራን እንገኛለን፡፡ በያለንበት የፖለቲካ ድርጅት ለህዝብ የሚጠቅም ሥራ እያከናወንን እንገኛለን፡፡ ትግሉን ፊሬአማ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን አንዳንድ ጠጠር እንዲወረውር እንጠይቃለን፡፡ „ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ“የሚለው የህዝባችን ወቅታዊ መፈክር ትክክል መሆኑን ተረድተን ከመጠላለፍና ከመዘላለፍ እንዲሁም ጎራ ለይቶ
ከመፋለም ይልቅ እየተነጋገሩ የወያኔን ሥርዓት ግባ ከመሬት ለማፍጠን አማራጭ የሌለው ጥያቄ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ያለብንን ክፍተቶች ለመድፈን እና አብሮ ለመስራት በተለይ በአመራር ደረጃ ላይ ያለን እየተገናኘን እየተወያየን እንገኛለን፡፡ በተለይ በአሁን ሰዓት በቅርብ በተመሰረተውና በውስጡ በርካታ ድርጅቶችን ባቀፈው ሸንጎ ጋር በጋራ ለመሥራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንገኛለን፡፡ ባለፈው መጋቢት 1/2013
ፍራንክፈርት ውስጥ በተካሄደው ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ሸንጎ የበኩሉን የድጋፍ መልዕክት መላኩ በሀገራችን ጉዳይ በመተሳሰብና በጋራ ለመሥራት ያለውን መልካም ጅምር የሚያመላክት ነው፡፡ በአቶ ጥአሁን ገላው የሚመራው ድርጅት ጋርም በጋራ እየሰራን እንገኛለን፡፡
ጎህ፡- በአሁኑ ሰዓት ያለውን የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዴት ይመለከቱታል?
አቶ ልዑል፡- የአሁኑ የወያኔ ሥራ አዲስ አይደለም፡፡ የቆየ ደብቅ አላማው ነው፡፡ እንደምንታዘበው ዘር በማጥፋትና የውጭ ሃይሎች ሎሌ በመሆን አገራችንን እያተራመሰ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ ዓመት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ እናስታውሳለን፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በቤኒሻንጉል ጉምዝ አካባቢ የሚገኙ አማራዎች የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም በሚል እያፈናቀለ ሜዳ ላይ እየጣላቸው ይገኛል፡፡ ይህም ድብቅ የቆየ የህዘብ
ጠላትነቱን ያሳየ ተግባር ነው፡፡ ሌላው በሃይማኖት ላይ የሚያካሄደው የሀገር ማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ዛሬ እየደረሰበት የሚገኘው ግፍና በደልም መግለፅ ከሚቻለው በላይ ነው፡፡ እንዲሁም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ እየደረሰ ያለው ተግባር የወያኔን እኩይ ተግባር ያረጋገጠ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ወያኔ ሃይማኖታዊው ሥርዓት በማይፈቅደው መንገድ የራሱን ፖለቲካ ጳጳስ በመሾም ለ22 ዓመት ሃይመኖትን ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት ሲያተራምስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንዲሁ ከዚህ ተግባሩ አልወጣም፡፡ የምዕመኑን ድምፅ በማፈን ፖለቲከኛ ጳጳስ ሾሟል፡፡ ይህም የሚያመለክተው ሀገር አፍራሽ ወሮበላ ቡድን መሆኑን ነው፡፡
ጎህ፡- አቶ ልዑል ይህ ሁሉ ተባለ፡፡ እንዲያው እስካሁን ባሳለፉት የትግል ጉዞና ተሞክሮ በመነሳት የወያኔን ቡድን እንዴት ይገልፁታል?
አቶ ልዑል፡- በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ ወያኔ በመሰረቱ አመሰራረቱ ሻዕብያ በትከሻው ተሸክሞ ከሳህል በረሃ ደደቢት አምጥቶት ያገባው የሻዕብያ ተላላኪ ቡድን ነው፡፡ ተላላኪነቱን ያመለከተውም እንደምታሥታውሱት ሻዕብያና ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩ ሻዕብያ ለሰባት አመት ኢትዮጵያን እንዲዘርፍ የፈቀደለት ራሱ ወያኔ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ክፍለ ሀገር የኢትዮጵያን ቡና በወያኔ ተባባሪነት በመዝረፍ ሜድ ኢን ኤርትራ እያለች ለውጭ ኤክስፖርት ታደርግ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡
ጎህ፡- ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ሶስት የባህር በሮች ነበሯት፡፡ በአሁን ሰዓት ከሶስቱም የባህር በሮች አንድ እንኳ የላትም ይህን ጉዳይ ድርጅታችሁ እንዴት ያየዋል? ወደፊትስ አገሪቱ የባህር በር እንዲኖራት ምን መደረግ አለበት ብሎ ያምናል?
አቶ ልዑል፡- አሁንም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሶስት ወደቦች እንደነበራት ግልፅ ነው፡፡ ጅቡቲ፣ አሰብና ምፅዋ ሶስቱ የባህር በሮቻችን ነበሩ፡፡ የጅቡቲ ጉዳይ አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን ለማሳደግ ከነበራቸው ከፍተኛ ዕራይ የተነሳ የተፈፀመ ጉዳይ ነው፡፡ የአሰብና የምፅዋ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የኛ ድንበር ቀይባህር ነው፡፡ ኤርትራ በወያኔና ሻብያ ህገ ወጥ ፈቃድ ብቻ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ፍላጎት ሳይኖርበት የተፈፀመ ህገ ወጥ ሥራ ነው፡፡ ያም ቢሆን አሰብ በሰሜን ምስርቅ ኢትዮጵያ የሚገኝ የሀገራችን ክፍል ነው፡፡ እንጂ የኤርትራ አካል አይደለም፡፡ ይህንንም ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አሰብ የኢትዮጵያ ወደብ ነች፡፡ የሚያሻማ ጉዳይ አይደለም፡፡ ወደፊት በኢትዮጵያ ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ሲመሰረት ኢትዮጵያ ህጋዊ በሆነ መንገድ አሰብን የማስመለስ ህጋዊ መብት አላት፡፡ ምንም ይሁን ምን የሁለቱ ሀገር ህዝቦች ወንድማማቾች ናቸው የሚጣሉት ሁለቱ የወሮበላ ቡድኖች ናቸው፡፡
ጎህ፡- በመጨረሻም የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለዎት?
አቶ ልዑል፡- „ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ“ የሚለው የህዝባችን ወቅታዊ መፈክር ትክክል መሆኑን ተረድተን ከመጠላለፍና ከመዘላለፍ እንዲሁም ጎራ ለይቶ ከመፋለም ይልቅ እየተነጋገሩ የወያኔን ሥርዓት ግባ ከመሬት ለማፍጠን አማራጭ የሌለው ጥያቄ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን
እናስተላልፋለን፡፡
ጎህ፡- ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን፡፡
አቶ ልዑል፡- እኔም አመሰግናለሁ፡

ከጎህ መፅሔት ኤፕሪል 2013 ዓ.ም አንደኛ አመት ቁጥር 2 የተወሰደ

Leul Keskis
Chair person in EPPFG

Posted By Alemayehu Tibebu

ማንነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher

በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ጽሑፌ ውስጥ ‹‹ማንነት ምንድን ነው፤ በሚል ንዑስ ርእስ ስር ከገጽ 98 ጀምሮ በተቻለኝ መጠን አፍታትቻለሁ፤ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ይህንን ለማንበብ ጊዜ አላገኘም፤ ወይም የተገለጠለት ዱሽ ቅንጫቢ በቅቶት ይሆናል፤ የምጠቅሰውም ለሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው፡፡

በቅርቡ በፌስቡክ ላይ አንድ አውቀቱ ይሁን ጤንነቱ፣ ወይም ኪሱ የተቃወሰበት ሰው በትግርኛ ስለማንነት ጽፎ ነበር፤ ከዚህ በፊትም ጽፎ አስተሳሰቡ ሁሌም የተወላገደ በመሆኑ አልፌው ነበር፤ አሁን ደግሞ ሲጽፍና በአንዳንድ የሱ ቢጤዎች አበጀህ! አበጀህ! ሲባል ሳይ አደገኛነቱን ተገነዘብሁ፤ አንዱን ጎባጣ ሀሳብ ቶሎ ካላስተካከሉት ብዙ ጎባጦችን ያፈራል፤ የተጣራና ቀና የሆነ ሀሳብን ለመግለጽ በጣም ያስቸግራል፤ ማሰብ መጨነቅን፣ ማበጠርን፣ ማጣራትን ይጠይቃል፤ አፍ እንዳመጣ መልቀቅ ቀላል ነው፤ በተለይ የሚዳኝ ከሌለ!

በመጀመሪያ ሀሳብን ለመግለጽ የተመረጠው ቋንቋ ጠበብ ያለና የተፈለጉ አድናቂዎች ዘንድ ለመድረስ ብቻ ከተፈለገ ሀሳቡም እንደቋንቋው ለተወሰኑ ሰዎች የተመጠነ ይሆናል፤ በዚህ ዓይነት የቀረበው ቅንጣቢ ሀሳብ በሌላ ቋንቋ ሊተረጎም አይቻልም፤ ደንቆሮነትን ማጋለጥ ይሆናል፤ ለምሳሌ በትግርኛ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› የሚለውን ‹‹ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤›› በማለት፣ በእንግሊዝኛ ደግሞ ‹‹There is no identity called Ethiopian.›› ተብሎ ሊተረጎም ነው፤ እንግዲህ ይህ አወቀች፤ አወቀች ሲሏት መጽሐፉን አጠበች እንደተባለችው ሴትዮ፣ ወይም ደግሞ አላዋቂ ሳሚ እንትን ይለቀልቃል! የሚባል ነው፤ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› ብሎ በትግርኛ የጻፈው ሰው የአለማወቁ አዘቅት ዓለምን በሙሉ የሚያናጋ መሆኑን አልተገነዘበም፤ (አሜሪካን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ኢጣልያን … የሚባል ማንነት የለም ሊለን ነው፤) የመንደር ማንነትን በሁለት እጆቹ ይዞ፣ አእምሮውን በመንደር ማንነት ጨቅጭቆ በየፓስፖርቱ ላይ የማንነት መግለጫ ተብሎ የተሰየመውንና በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀውን ማንነት ካደው፡፡

በፍጹም ያልገባውን የፈረንሳዩን ፈላስፋ፣ የሩሶን ሀሳብ አበለሻሽቶ ከቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያገኘው ቡትቶ ሊያደርገው ይከጅላል! ከጥራዝ-ነጠቅም አጉል ጥራዝ-ነጠቅ! ትግራይን የመገንጠል ዓላማ ያለው ሰው በእውነትና በግልጽ ዓላማውን ቢያራምድ በበኩሌ አልደግፈውም እንጂ አልቃወምም፤ መብቱ ነው፤ ነገር ግን በሰንካላ አስተሳሰብና በተንኮል ወጣቶችን ለመመረዝ የሚፈልገውን ሰው አጥብቄ እቃወማለሁ፤ ትግራይን እንደኤርትራ ካስገነጠለ በኋላ እንደኤርትራ ለትግራይም የኢትዮጵያዊነት ማንነትንን ማገድ ይቻላል፤ ከዚያ በፊት ግን ተንኮል ይቅር፡፡

ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚደረገው ሙከራ አዲስ ኤደለም፤ ኢጣልያኖች በሰፊው ዘርተውት የሄዱት ጉዳይ ስለሆነ የአባቶቻቸውን ውርስ የሚከተሉ ዛሬም ይኖራሉ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ብዙ ገንዘብና ሌላም የሚከፍሉ ብዙ የተለያዩ ድርጅቶች መኖራቸው የታወቀ ነው፤ ዱሮ የኢጣልያ ወኪሎች ተጠቅመውበታል፤ ዛሬ ደግሞ ሌሎችም ተጨምረው ያንኑ ተልእኮ የሚያራምዱ አሉ፤ በየዋህነት እንደበፊቱ እንዳናስተናግዳቸው እንጠንቀቅ!

“በጥይት ትመታላችሁ፣ መትረየስ ጠምደን እንፈጃችኋለን” እያሉ እያስፈራሩን ነው ጎንደር በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄዎች ተወጥራለች

በመጪው እሁድ ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር መካከለል ጉዳይ ለሕዝብ ግልፅ አለመሆኑን በመቃወም ሰልፍ የጠራ ሲሆን፤
በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ዙሪያ የሚኖሩ የቅማንት ብሔረሰብ አባላት ማንነታችን አልተከበረም በሚል ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄአቸውን ለማቅረብ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ
አቅርበዋል። ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ለሁለቱም ወገኖች ለሰላማዊ ሰልፉ መካሄድ ማረጋገጫ አለማግኘታቸውን እየተናገሩ ነው።
ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ለማስተባበር ወደስፍራው የላከውን የፓርቲውን አመራር ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አስተባባሪዎች ታስረው መፈታታቸውን ገልጿል። ሆኖም ሰልፉን
ለማካሄድና የማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማው አስተዳደር ቢያቀርቡም አስተዳደሩ ደብዳቤውን ባለመቀበሉ ጠረጴዛ ላይ ትተው መውጣታቸውን የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት
አስታውቋል። እስካሁን የከተማው አስተዳደር ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉ እንደተፈቀደ በመቁጠር ሰልፉን ለማካሄድ በዛሬው ዕለት 12 የአመራር
አባላት ያሉት ቡድን ወደ ጎንደር እንደሚሄድ አስታውቋል። በሌላ በኩል በበርካታ ጊዜያት የቅማንት ብሔረሰብ የቋንቋ፣ የባህልና የማንነት መብቱ
አልተጠበቀም የሚሉ ወገኖች በተመሳሳይ ቀን (ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም) ጥያቄአቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ሰልፍ መጥራታቸውን የቅማንት ብሔረሰብ የማንነት የራስ
አስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አበራ አለማየሁ ለሰንደቅ ጋዜጣ አስታውቀዋል።
የኮሚቴው ሊቀመንበር የጎንደር ከተማ በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። አስተዳደሩም የእነሱ ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ እንጂ የፖለቲካ አይደለም። ነገር
ግን እናንተ ጥያቄ ካቀረባችሁ በኋላ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል በማለት አጀንዳችሁ ተመሳሳይ ነው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው አጀንዳችን የተለያየ መሆኑን
ብንገልጽም፤ “በጥይት ትመታላችሁ፣ መትረየስ ጠምደን እንፈጃችኋለን” እያሉ እያስፈራሩን ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ጥር 4 ቀን 2006 ዓ.ም በጅልጋ ወረዳ አይከል ከተማ ላይ ከ70 ሺህ በላይ ሕዝብ የተገኘበት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ያስታወሱት አቶ አበራ፤ በዚያን ጊዜም
“በመትረየስ እንፈጃችኋለን” ቢሉንም ሕዝቡ ነቅሎ መውጣቱን ተናግረዋል። አሁንም በጎንደር ከተማ ከሰማያዊ ፓርቲ ቀድመው ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቢዘጋጁም
በየቀበሌው ሕዝቡን በስብሰባ በመጥራት ወደ ሰልፉ እንዳይወጡ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ያለውን ጫና ተቀቁመው ሰልፉን ለማካሄድ ወደኋላ
እንደማይመለሱ ተናግረዋል።
እንደ አቶ አበራ ገለፃ፤ እነሱ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘው በተመሳሳይ ቀን ሰማያዊ ፓርቲ በሌላ አጀንዳ ሰልፍ በመጥራቱ እኛም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር አብረን
እንደምንሰራ ተደርጎ ታይቶብናል ብለዋል። ይሁን እንጂ የእኛ ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ እንጂ የፖለቲካ ወይም የድንበር አይደለም ብለዋል።
የቅማንት ብሔረሰብ በአማራ ክልል በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች የሚኖር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አበራ፤ የሕዝብ ብዛቱም አንድ ሚሊዮን እንደሚሆን፣ የቋንቋው ተናጋሪዎችም
ከ20 ሺህ በላይ እንደሚሆኑ ገልፀው፤ ሕዝቡ እራሱን በቻለ ዞን ለመተዳደር ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ብለዋል። በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ጥያቄውን
ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ ውሳኔ አለማግኘቱንም ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረን በስልክ አግኝተን በዚሁ ጉዳይ ላይ የአስተዳደራቸውን አቋም እንዲያብራሩልን
ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
የሰንደቅ ዜናዎች (ጥር 21/2006)

posted by Alemayehu Tibebu

በጎንደር የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች ታሰሩ

blue-party-gonder-flyer

 የፊታችን እሁድ በጎንደር ከተማ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ወጥቶ ለሱዳን በሚሰጠው መሪት ዙሪያ ድርጊቱን እንዲቃወም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ከተማ መታሰራቸው ተሰማ።

 ከሰማያዊ ፓርቲ አካባቢ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።

ፖሊስ የሰልፉን ቀስቃሶች ካሜራ እና ላፕቶፖችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን መውሰዱን የጠቆመው ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘው መረጃ ፖሊስ ዛሬ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን “እሁድ የሚደረገው ሰልፍ ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌለው መቀስቀስ አትችሉም” ያላቸው ሲሆን አስተባባሪዎችም “በሕገመንግስቱ መሠረት ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀድ የለብንም። ቀድመን ማሳወቅ እንጂ። ይህን ደግሞ አድርገናል” ቢሉም ፖሊስ ማስተዋወቅ አትችሉም በሚለው አቋሙ ጸንቶ መደብደብ መጀምሩም ተሰምቷል።

የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ደጋፊዎች ከድብደባው በኋላ ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው መታሰራቸውንና ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አለመፈታታቸውም ታውቋል።

አስገራሚ ዜና – ሽመልስ ከማል ተሳደቡ፣ አስፈራሩ


“በአብዛኛዎቹ የህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ማስታወቂያ
እንጥል እቆርጣለሁ፣ ግግ እቧጥጣለሁ የሚል የአንድ ደብተራ ማስታወቂያ ነው” አቶ ሽመልስ ከማል

መንግስት የህትመት ውጤቶች አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፍንጭ ሰጠ

በዘሪሁን ሙሉጌታ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በሀገሪቱ ውስጥ ፈርጀ ብዙ ኀሳቦች ለህብረተሰቡ እንዳይደርስ እያደረጉ ነው ባሉዋቸው የጋዜጣና መፅሔት አከፋፋዮች ላይ መንግስት በፍጥነት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቁ።
ሚኒስትር ዴኤታው ይሄህን የተናገሩት “የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስትና የመገናኛ ብዙኃን ግንኙነት” በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት በኢንተርኮንቲነታል ሆቴል ሰሞኑን ባዘጋጀው የአንድ ቀን ሲምፖዚየም መዝጊያ ላይ ነው።
የፕሬስ ነፃነት አፈና ሲነሳ በአከፋፋዮች አማካኝነት የሚደረግ አፈና አንዱ መሆኑን በመጥቀስ ጥቂት መፅሔቶችንና ጋዜጦችን በባለቤትነት የያዙ ግለሰቦች የማከፋፈል ስራውን በሞኖፖል ይዘው የአመለካከት ፈርጀ ብዙነት እንዳይኖር በማድረግ፣ በርካታ ህትመቶችን በለጋነታቸው ለሞት እንዲበቁ በማድረግ የአፈና ስራ ውስጥ የገቡ ወገኖች አሰራራቸው በፍጥነት መስተካከል አለበት ብለዋል።
“ሚዲያን የመደጎምና የማስተካከሉ ስራ መንግስት በአግባቡ በተጠና ሁኔታ መግባት እንዳለበት ያምናል” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በሚዲያ የኀሳብ ገበያ ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን በማዘጋጀት ለኢንዱስትሪው ቀና እድገት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል። በአከፋፋዮች በኩል በርካታ ችግሮች ተለይተው እየተጠኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የህትመት ሚዲያው ብቻ ሳይሆን የሕዝብ የመገናኛ ብዙኀን አውታሮች ከችግሮች ነፃ አለመውጣታቸውንም የጠቀሱት አቶ ሽመልስ መንግስት ፈጣን መረጃ የሚሰጥ የሚዲያ ስርዓት እንዲፈጠር እንደሚፈልግ ገልጸዋል። መንግስት መረጃዎችን በገፍ የሚያቀርብ፣ ጥራት ባለውና ወቅታዊ በሆነ መንገድ የሚሰራ የሚዲያ ስርዓት እንዲገነባ ይፈልጋልም ብለዋል።
ብሔራዊ የሚዲያ ፖሊሲው በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የህብረተሰቡን የፖለቲካ ብዙሃነት፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ፈርጀብዙነት ከመቀበል የሚነሳ መሆኑ አስታውሰው፤ ነገር ግን ሚዲያው በማንኛውም የባለቤትነት ውስጥ ቢሆንም ብሔራዊ መግባባትን ለማስረፅ መተኪያ የሌለው ቀዳሚ ሚና እንዲጫወት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል። ሚዲያው በብሔራ ዊ መግባባት ላይ እንዲሰራ መንግስት ቢፈልግም ከማንኛውም ርዕዮተዓለም ተፅዕኖ ነፃ እንዲሆን ይፈልጋል ብለዋል።
አሁን ያለው የሚዲያ ችግር በንግድ ሚዲያ መርህ ወይም በገበያ መርህ መንቀሳቀስ አለመቻል መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሽመልስ አብዛኛዎቹ ሚዲያዎቻቸው ገበያቸውን ከማስታወቂያ የሚሸፍኑ አይደሉም ብለዋል።
“በአብዛኛዎቹ የህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ማስታወቂያ “እንጥል እቆርጣለሁ፣ ግግ እቧጥጣለሁ” የሚል የአንድ ደብተራ ማስታወቂያ ነው። ከዚህ ውጪ ሌላ ማስታወቂያ የላቸውም። ኮሜርሺያል አይደሉም፤ ኮሜሪሻያል ካልሆኑ ይደጎማሉ። በድጎማ የሚተዳደሩ ከሆነ ታማኝ አንባቢ ነው ያላቸው። ከተወሰኑ ርዕዮተአለማዊ አጥሮች አልፈው መጓዝ አይፈልጉም። ስለሆነም የህትመት ሚዲያ እድገት ላይ አንድ ትልቅ ጋሬጣ የሆነው ከነፃ ሚዲያ ህግጋት ውጪ ተንጋዶ የበቀለ የሚዲያ አካሄድ ነው” ያሉት አቶ ሽመልስ ይህንን ለማስተካከል መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ሊተባበሩ ይገባል ብለዋል።
የሰንደቅ ዜናዎች (ጥር 21/2006)