Archive | January 4, 2014

የግንቦት 7 ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ

የግንቦት 7 ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ

ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው በ“አንድ ለአምስት” አደረጃጀት እያደራጀው ነው። ይህ አደረጃጀት ስታሊን ለሠላሳ ዓመታት ሶቭየት ኅብረትን፤ ኤንቨር ሆዣ ደግሞ ለአርባ ዓመታት አልባኒያን ጠፍረው የገዙበት ስልት ነው። በዚህ የአገዛዝ ስልት መሠረት እያንዳንዱ ሰው በመዋቅር ተይዞ አራቱ ለአንዱ መረጃ የሚያቀብሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።
ginbot 7
ሕዝብን በድርጅት አባልነት ስም በመዋቅር ማስገባት ለአንባገነኖች የሚሰጠው ዋነኛ ጥቅም የማኅበረሰብን ስነልቦና መስበሩ ነው። ይህ አወቃቀር ዜጎች የአምባገነኑን መንግሥት ኃይል ከመጠን በላይ አግዝፈው፤ እራሳቸውን ደግሞ አንኳሰው እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል። ዜጎች፣ “መንግሥት እያንዳንዱን ነገር አብጠርጥሮ ያውቃል” በሚል የፍራቻ ቆፈን እንዲያዙ ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ጓደኛውን እንዲጠረጥር በማድረግ አምባገነኖች የስለላ ተቋማቸዉ ጠንካራና ሁሉን-አዋቂ እንዲመስል ያደርጉታል።

ይሁን እንጂ የማኅበረሰብ ስነልቦና ካልተሰበረ፤ በፍራቻ ፋንታ በራስ መተማመን ከዳበረ ማንም ያደራጀው ማን ነፃ ህሊና ያላቸው አባላት ድርጅቱን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ይጠቀሙበታል። አሁን በደረስንበት ሁኔታ ይህንን በአገራችን ተግባራዊ የማድረግ ሰፊ እድል አለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ፍራቻ እራሱን ነፃ እያወጣ ነው። ወያኔ ከስታሊንም ሆነ ከኤንቨር ሆዣ በተለየ መንገድየአመለካከትና የርዕዮተዓለም ጉዳይ የሚያሳስበዉ ሀይል አይደለም።ቢያሳስበውም የሕዝብን ቀልብ የሚይይዝበት ምንም ነገር የለውም። ይህ ባህሪይዉ ነዉ ነው ወያኔ በእጅጉ የተጠላ ኃይል እንዲሆን ያደረገው።

እንዲህ በግዴታ እንጂ በእምነት ያልተሰባሰቡ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ተመሳሳይ ፀረ-ወያኔ አቋም ያላቸው ሰዎች በአንድ “አንድ ለአምስት” ሕዋስ ውስጥ የመገኘታቸው አጋጣሚ የጎላ ነው። እነዚህ አባላት በግልጽ ከተነጋገሩበት ሕዋሱን ለፀረ-ወያኔ ትግል ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በመሆኑም ወያኔን ለመጨቆኛ መሣሪያነት ያዋቀረውን “አንድ ለአምስት” ራሱ ወያኔን መታገያ ብሎም ማዳከሚያ መሣሪያ ማድረግ ይቻላል። “አንድ ለአምስትን” በሽፋንነት በመጠቀም ውስጥ ውስጡን መጀራጀት በስፋት ልንይዘዉና ልንሰራበት የሚገባ ስትራቴጄ ነው።

የወያኔ “አንድ ለአምስት” የኑሯችን አካል እየሆነ መጥቷል። በአንዳንድ ቦታዎች አለመደራጀት ሥራ የሚያሳጣ እየሆነ ነው። በማናቸውም ምክንያት ራሳቸውን ወያኔ ጉያ ውስጥ ያገኙ የሕዝብ ወገኖች ካሁን በኋላ መሥራት ያለባቸው ወያኔን ከውስጥ ሆኖ የማዳከምን ሥራ ማፋጠን ነው። ለዚህ ደግሞ እንደ “አንድ ለአምስት” አመቺ የሆነ መዋቅር አይገኝም።

በአሁኑ ሰዓት ግንቦት 7 ሕዋሳቶቹን በሁሉም ቦታ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤በዚህም መሠረት የግንቦት 7 ሕዋሶች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢ ባልተማከለ መልኩ በብዛት እየተመሠረቱ ነው። ከዚህ ህዋሳቶችን ከመዘርጋት ሥራ ጎን ለጎን ህዝቡ በያለበት የወያኔንየራሱንመዋቅር በመጠቀም ወያኔንና ስርዐቱን መገዝገዝ አለበት።

ይህንን ለማድረግ የግንቦት 7ን መመሪያ መጠበቅ አያስፈልግም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ መንገድ ተግባራዊ ሊያደርገው የ የሚችለዉ ነገር ነው።

በመሆኑም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ “አንድ ለአምስቶችን” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው የሚል ጥሪ ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

oLF Militery

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ  ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ሲያሰቃዩ መቆየታቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

አንድ ሹፌር ለኢሳት እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳፋሪዎችን ከመኪና ላይ በማስወረድ ድብደባ እንደፈጸሙባቸውና እርሳቸውም በጥፊ እንደተመቱ ተናግረዋል

“እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም” የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን  ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።

ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል።

ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ልዩ ጉባኤው የአቋም መግለጫ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ልዩ ጉባኤው የአቋም መግለጫ

UDJዛሬ በደረስንበት 21ኛው ክፍለዘመን በአለማችን የሚገኘው ሕዝብ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ በተከበሩበት ሁኔታ መመራት ይሻል፡፡ በዚህ ዘመን አምባገነን መሪዎችና መንግስታት በየትኛውም መስፈርት ስልጣን ላይ የመቆየት እድል የላቸውም፡፡ በዚህ ረገድ በቅርብ አመታት ውስጥ የማይደፈሩና እንደ ፈርኦን ይመለኩ የነበሩ አምባገነን መንግስታት በህዝባዊ ማዕበል ተጥለቅልቀውና ተንጠው መቀመቅ ሲወርዱ የአለም ህዝብ ሁሉ አስተውሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የዲሞክራሲና የነፃነት ጥየቄ ከዳቦ ጥያቄ ይበልጥ አንገብጋቢ እየሆነ መጥቷል፡፡

የአለማችን አንድ አካል የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት የስልጣኔ ጉዞዋ የምድራችን ቁንጮ የታሪክ ባለቤት ያደርጋታል፡፡ በየዘመናቱ የተነሱ ገዢዎቻችን ሲጭኑብን የቆዩት የአገዛዝ ቀንበር ወገባችንን ቢያጎብጠውም የኢትዮጵያ አንድነትና ሉኣላዊነት ፍፁም ሳይሸራረፍ ተጠብቆ ዘመን እንዲሻገርና ለትውልድ እንዲተላለፍ የማይሻ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡

ወታደራዊው ደርግ ከሥልጣን በተወገደ ማግስት ዲሞክራሲና ነፃነት የሰፈነበት የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩባትን ኢትዮጵያ ለማየት ያልጓጓ ኢትዮጵያዊ አልነበረም፡፡ ህልማችን በእውነት ሳይፈታ ቀረ፣ ተስፋ ያደረግነው ነገር ከዓመት ዓመት እየጨለመ መጣ፡፡ ኢህአዴግ ባለፉት 23 ዓመታት የምኒሊክን ቤተመንግስት ቢቆጣጠርም የአገርን ህልውና ከመጠበቅና የህዝብ እንባን ከማበስ ይልቅ ዜጎችን መውጪያ መግቢያእያሳጣና የመከራን ገፈት እያስጨለጠ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ስደቱ፣ እንግልቱ፣ ግርፋቱ፣ እስራቱ፣ ግድያው፣ አፈናው፣ ስቃዩ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው እየከፋ ይገኛል፡፡

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ይህን ቀንበር ለመስበር እንደ መርፌ ቀዳዳ በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ እየተንቀሳቀሰ በመላው አገሪቱ ህዝብን ለትግል እያሰለፈ ይገኛል፡፡
ይህን እልህ አስጨራሽ ትግል ለመምራት ትልቁ የስልጣን አካል የሆነው ይህ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 19 እና 20 / 2006 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረገው ከፍተኛ ስብሰባ አያሌ አገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይቷል፡፡ የፓርቲውን ምክር ቤት ፣ የሥራ አስፈፃሚና የኦዲት ኮሚሽንን ሪፖርት በማድመጥ ጠንካራ ውይይት አካሂዷል፡፡

በመጨረሻም የአገልግሎት ዘመናቸውን ባጠናቀቁት የፓርቲው ፕሬዚደንት የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምትክ የተከበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን ፍፁም ግልፅና ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተክቷል፡፡ የፓርቲውን ብሔራዊ ምክር ቤት እና የኦዲት ኮሚሽን አባላትንም በመምረጥ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

አባላቱ በጉባኤው ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚከተለውን የአቋም መግለጫና ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡

1ኛ. ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በአገሪቱ የሚደረገውን የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ለማኮላሸት ነጋ ጠባ የሚያጠነጠነው እኩይ ሴራ የህዝቡን ስሜት ወደ ሌላ አቅጣጫ እና ጥግ እየገፋው ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፓርቲያችን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጀመረው የሰላማዊ ትግል ጉዞ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለመብት ለማድረግ እስከመጨረሻው እንጥፍጣፊ በጥብቅ መታገል እንደሚኖርበት ይታመናል፡፡ በመሆኑም እኛ ከመላው አገሪቱ በዚህ ጉባኤ ላይ የታደምን የፓርቲ አባላትና አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ለሰላማዊ ትግሉ ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
2ኛ. አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የፓርቲያችንን እንቅስቃሴዎች እግር በእግር እየተከታተለና በሀሰት ውንጀላ በማጠልሸት በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳናገኝ ጠቅልሎ በያዘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሰፊ የሆነ አፍራሽ ተልዕኮን እያስተጋባ ይገኛል፡፡ይህ ጉዳይ ህገ መንግስቱ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ያመቻቸውን መንገድ ሙሉ ለሙሉ የሚጠቅም ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አገር እየመራሁኝ ነው የሚለው ኢህአዴግ ፓርቲያችንን ከሽብር ድርጊት ከአሸባሪዎች ጋር ለማቆራኘት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡

3ኛ. በዚህ ልዩ ጉባኤ ወቅት በአካል በመቅረብ በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ አርቡር ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው የ 8 ዓመቷ ህፃን ስለእናት ማስረሻ ጥላሁን የደረሰባትን እጅግ ዘግናኝና ሰቅጣጭ የአካል ጉዳትአሳይታለች፣ ሁኔታው የጉባኤውን አባላት ክፉኛ ያስቆጣ ሆኗል፡፡ አባቷን እና የቤት እንስሳትን በጥይት ገድለው ህፃን ስለእናትን በጥይት አረር እጇን የቆረጡ እኝህ እኩያን ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
4ኛ. የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የአመራር ዘመን አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ የተዋረደችበትና ሉኣላዊነቷ የተደፈረበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዜጎች የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይደርስባቸዋል፣ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፣ ይገደላሉ፣ ይሰደዳሉ ወዘተርፈ፡፡
ለስደት በተዳረጉባቸው አገራትም ዜጎቻችን በግፍ ሲገደሉና ሲደበደቡ እያን ነው፡፡ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያና ሰሞኑን ደግሞ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ሞትና ስቃይ የእያንዳንዳችንን ልብ የሰበረ ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህም ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡
በመሆኑም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በመላው ዓለም እንደ ወንዝ ዳር አሸዋ ተበትነው ለሚንገላቱ ዜጎች ጉዳይ በአፅንኦት እየተከታተለ እንዲታደግና የመንግስትነት ግዴታውን ባግባቡ እንዲወጣ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
5ኛ. በአሁኑ ወቅት የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ጥቂት ሹማምንት እጆቻቸውን እያስረዘሙ የአገርን ሀብት እየዘረፉ ናቸው፣ ሥርዓቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ በሙስና የተጨማለቀ መሆኑን እየተጋለጠ ነው፡፡ ዜጎች ዛሬ የዕለት ጉርሳቸውን አጥተው ሲራቡና ሲጠሙ፣ወጣቶች የሥራ ዕድል ተነፍጓቸው በአሳፋሪ ሁኔታ ከአገር ሲሰደዱ፣ የኑሮ ውድነቱ ትውልዱን ግራ እያጋባ ነው፣ ህዝቡ ፍትህና መልካም አስተዳደር በማጣት ነጋ ጠባ የዜግነቱ ጉዳይ ጥያቄ በፈጠረበት ሁኔታ የነገዋን ኃያልና የበለፀገች ኢትዮጵያን አይደለም ማየት ይቅርና የህልውናዋ ጉዳይም አጣብቂኝ ውስጥ የገባበት ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡ በአገሪቱም አስከፊ ብሔራዊ ቀውስ ይፈጠራል ብለን እንሰጋለን፡፡
ከዚህ አንፃር ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብሔራዊ መግባባትን የሚያሰፍን መድረክ እንዲያዘጋጅ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
6ኛ. ኢቴቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልሳንነቱን እርግፍ አድርጎ በመተው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ መሆኑን የትኛውም ኢትዮጵዊ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ፕሮግራም ላይ በመላው አገሪቱ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባዎችን በጠራበት ወቅት ኢቴቪ ጅሃዳዊ ሃረካት ፊልምን አቀናብሮ ፓርቲያችንን ከአሸባሪዎች ተርታ ሲፈርጀው ቆይቷል፡፡ ሌላው ቀርቶ ጉባኤያችንን ባከናወንበት ታህሳስ 19 ምሽት ኢቴቪ ያንኑ ፊልም በድጋሚ በማቅረብ አንድነት ፓርቲ በደሴ፣ በጎንደር፣ በአርባምንጭ፣ በጂንካ፣ በባህርዳር ወዘተ ካደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎችና በፓርላማ የፓርቲያችን ብቸኛው ተወካይ ስለ ፀረ ሽብር ህጉ አፋኝነት ያነሱትን ሀሳብ ከሽብር ጋር በማያያዝ ከንቱ ዲስኩር ሲያቀርብ ተመልክተናል፡፡ ኢቴቪ የአንድ ድርጅት መሆኑ አብቅቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዋይታና ብሶት የሚያስተጋባ ግዙፍ የብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንዲሆን አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
7ኛ. ፓርቲያችን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ ከኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ጋር በብርቱ እየተናነቀ መሪዎቹ እየታሰሩበትና እየተደበደቡበት መዋቅሩን በመላው አገሪቱ ዘርግቶ አመርቂ የትግል ውጤት እያመጣ ቢሆንም የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚቀረው ጉዞ እጅግ ረጅም ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ፓርቲያችን ይህ ታላቅ ጉባኤ የወሰናቸውን ውሳኔዎችና መርሃ ግብሮች በአግባቡ እየተወጣ ታሪክ ይሰራ ዘንድ አጥብቀን እናስገነዝባለን፡፡
በቀጣይ ዓመታት ፓርቲውን በበላይነት እንዲመሩ የተመረጡ አመራሮች ከመቼውም ግዜ በበለጠ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ (ሄኖክ የሺጥላ)

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ (ሄኖክ የሺጥላ)

January 4, 2014

ሄኖክ የሺጥላ

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ

ብቸኛው ልቤ ሰው  በመውደዴ

ነው  ያለው ኣረጋሃኝ ወራሽ ኣሁን እንደሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሰራውን ሁሉ በመናድ : የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው። እኔ እንኳ በዘመኔ ስንት ኣየሁ። ኣሁን ማን ይሙት ኣደይ ትርሃስ በፍራሽ መዋጥ ለሁለት ዕየከፈሉ ያጸኑት ሹሩባ የሚረሳ ሆኖ ነው “ቢዮንሴ ሄር ስታይለር ምናምን ምንምን በሚል ሰጋቱራ ሃገሩን ያጥለቀለቅነው።” እስኪ ኣሁን ምን ትውልድ ኣለ። ድሮ ቡና እንኩዋ እስከ ሶስተኛ ነበር የሚጠጣው፤ ኣሁን ግን ኢኮኖሚው በ ፲፩ ፐርሰንት ኣድጎ ቡና እንኩዋ የሚያቆመው ሰባተኛ ምናምን ላይ ነው። በውነት ፕሮፌሰር ኣልማርያም እንደሚሉት ይሄ ትውልድ ኣቦ ሸማኔ ሳይሆን ኣቦል ሸማኔ ነው። ኣያቶቻችን ለኣድዋ ጦርነት ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሲሉ፤ መለከት: ጥሩንባ ሲነፉ  ነው ታሪክ የሚነግረን። ዛሬ ግን የመለከት እና የእንቢልታ ሪሚክስ  በየ ስርጣ ስርጡ ሺሻ መንፋት ሆኖዋል ግብራችን። የሰሞኑ መፈክር ኪንግ ኣብደላ ሼም ኦን ዩ፤ ሼም ሼም ሼም፤ ነበር ኣይደል፤ ምነው ሺሻው ተረሳ ታዲያ፤  ኣጎቶቻችን  ባርነትና ውርደት ብቻ ሳይሆን ሱሰኝነቱንም ኣወረሱን።Ethiopian poet Henok Yeshitla

እንግሊዚኣዊው  ጋዜጠኛና ጠሃፊ Grham Hancook The sign and the Seal (The Quest for The Lost Arc of the Covenant)  በሚለው መጥሃፉ ላይ The Ethiopian slept a thousand years forgetting the world by whom they were forgotten by  ይላል :: በነገራችን ላይ የላይኛውን የኣነባበብ ዘዬ (style ) ኣንድ ነገርን ኣስታወሰኝ :: ባንድ ወቅት በስድስት ኪሎ (university ) ያስተምሩ የነበሩ መምህር  ስለ ጆነፍ ኬንዲ ሞት ለተማሪዎቻቸው ሲያስተምሩ (During the time and death of Jonneif Kennedy everybody was shocken) ኣሉ በዚህን ጊዜ ኣንድ የቅዱስ ዮሴፍ ተማሪ ሳቁን ለሞአቆጣጠር ሲታገል  ያስተዋሉ እኝሁ መምህር በነገሩ በስጨት ይሉና “ምን ያስቅሃል ሾካካ!!!” ኣሉ ኣሉ። እንግዲህ ያዙልኝ ሾክን ሾካካ ከሚለው ነው የመጣው ማለት ነው። እሺ ይሁን  ሾክንስ ከሾካካ ነው እንበል፤ ኣድርባይነት፤ ባንዳነት፤ ሆዳምነት፤ ታሪክ ሸቃይነት፤ እነዚህስ?  ኣንድ ወዳጄን በጣም በስጨት ብዬ ኣረ ባክህ እኔ ኣልገባኝም ይሄ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መናቅ ከየት የመጣ ባህል ነው ስለው፤ ፈገግ ብሎ በርግጠኝነት ከቻይና ኣይደለም፤ ከቻይና ቢሆን ይህን ሁሉ ዘመን ኣብሮን ኣይቆይም ነበር፤ ማናልባት ከጣልያን ይሆን እንዴ ኣለኝ። ወይ ኢትዮጵይ፤ ልጆችሽ ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም የሚለውን ዘፈን  በየስብሰባው እና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ደጋግመው በማቀንቀናቸው ዘፈኑ ራሱ ሰልችቶት ልጆቼ ሃያ ሶስት ኣመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ተዘፈንኩላችሁ በሉ ኣሁን ሌላ ዘፈን ፈልጉ፤ እናንተን እንዳየሁዋችሁ ከሆነ ፤ እኔን እንደ ልደት ዘፈን በሻማ ከባችሁ ከማልቀስ ውጪ  ምንም የምታመጡ ኣይመስለኝም፤ እና ጡረታዬን ጠብቁልኝና እስኪ ደሞ ይቺ የቀረችው ጊዜዬን እፎይ ብዬ ልኑር ኣለ ኣሉታዲያ ምን ይዋጠን፤ ኣንቺም ዜሮ ዜሮ እንዳንል ዘፋኙ እንጀራው ላይ የቅንድብ ጠጉር ተገኝቶበት ገበያውን ገደለው፤ ምን ይበጀን፤ ምን ይሻለን።  ከማቀንቀን ውጪ ሌላ ነገር ለማድረግ ዛሬም በቅጡ የተዘጋጁ ኣይመስልም፤ በየ ዝግጅቱ ላይ ኣበው ኣባቶቻችንን በ ፩ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ከማሰብ ውጪ ሰምሮላቸው የተሻለ ነገር ሲያደርጉ ዛሬም ኣናይም።

ወደ ግራሃም ሃንኩክ ልመለስ…ኣዎ “The Ethiopian Slept…. A 1000 years forgetting the world by whom they were forgotten by.”

(ይህንን ፈረንጅኛ በኣማርኛ ብናራምደው ወይም ወደ ኣማርኛ ብንቀዳው) ኢትዮጵያዊያኖች ኣለምን ረስተው ኣለምም እነሱን ረስታ ለሺ ኣመተታት ኣንቀላፉ)ማለት ይሆናል።  ታዲያ የዚህን ሰውዬ ኣባባል የነብይ ግብር ለመስጠት ኢስቲመስል ድረስ ዛሬ ሃገሪቱ ኣልጋ በኣልጋ ሆናላች። ኣዎ ለኢሃዲግ መራዡ (ይቅርታ መራሹ መንግስት ኣልጋ ባልጋ) ከዚህ ካለሁበት ኣማሪካም ይሁን ከኣውሮጳና ከሩቅ ምስራቅ ሃገራት ለሳምንታት ተንፍሰው መምጣት ለሚፈልጉት  ኣቦ ሸማኔዎችም ኣልጋ በኣልጋ። ኣንቺ ሃገር ያለው ዘፋኝ ማን ነበር። ማንስ ቢሆን ምን ዋጋ ኣለው።

ታላቁ የኢሃዲግ መንግስት ከሚከበርበትና ከሚወደስበት የቀለበት መንገድ በተጨማሪ (ግድቢ ኣደይ ሃዳስ (የእማማ  ሃዳስ ግድብ) (ለመሃል ኣገር ሰው ይስማማ ዘንድ የህዳሴውን ግድብ እየተባለ የሚነገረውን  ሳይጨምር…) ከሚታወቅበት ኣንዱ እንቅልፍን ያለ ገደብ መፍቀዱ ነው።  በነገራችን ላይ ያባይ ቦንድ የብዙ ኣባወራዎችን ትዳር በማፍረሱ ያባይ ቦንብ የሚል ስም ሊሰጠው እንደሆነ ጥቃት ያደረሱትም ጥቃት የደረሰባቸውም እየተናገሩ ነው:: የዚህ ያባይ ቦንብ የሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑት ሰዋች እንደሚሉት ከሆነ ኣማሪካ ቢሆን disability  ክሌም ኣርገን እንደ ኣካፋ ዝቆ በሚያነሳ ኣውቶብስ ፈልሰስ እያልን እንኖር ነበር፤  እኛ ግን ከጥቃታችን ሳናገግም፤ ተገድቦ የት ያደርሰናል ያልነው ኣባይ ጉሮሮዋችንን ገድቦ ይስረቀረቃል ብለዋል። ለነገሩ ኣባይ ኣፍ የለውም እንጂ ቢጠይቁት የደደቢት ድርዬዎች ሃንግ ኣረጉኝ ብሎ ለኣውሽና ቦርከና ይናገር ነበር። ምን ያረጋል ታዲያ ኣባይ እንኩዋን ኣፍ ማደሪያ የለውም። ኣባይ በስምሽ ስንት ታሪክ ተሰራ። ትገርሚያለሽ፤ በቃ ግንዱ ኣልበቃ ብሎሽ የዲያስቦራን ዶላር ትጠርጊ ጀመር፤ ለነገሩ ኣንቺ ምን ታረጊ፤ ሆዶ ነው ቁም ነገረኛ ያረገሽ እዚህ ዛሬ ከኛ ጋ ተቃውሞ ማታ ደሞ እትዮጵያ ደውሎ፤ እንዴት ነው ቦንዱ፤ ግድቡ እያለቀ ነው፤ ምን ይጠበቅብኛል ጌቶች የሚለው፤ ይሄ ሁለት ቢላ ህዝብ ኣባይዬ በናትህ በጣና ይሁንብህ፤ ይህንንማ ውስክስክ ላፍልኝ፤ መቅኖ ኣስቀረው፤ ኣላርፍ ያለ ዲያስፖራ ያባይ ቦንድ ይገዛል ኣሉ።

የጎጃም ገበሬ እንኩዋ  ዛሬ ቦንድ ካልገዛህ ኣባይ ኣጠገብ ዋሽንት መንፋት ኣትችልም ሊባል እንደሆነ ሰምቼኣለሁ፤ ዋሽንቱስ ይሁን፤ ቢያንስ ውሃ ሽንት ይፍቀዱላቸው።

በኣባይ ቦንድ መሸወዳቸው የገባቸው ኣንዳንድ ግለሰቦች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው  ሲናገሩ እንደሰማነው ከሆነ “ቦምብን በቦንድ ስም መንግስት ሲያስታጥቀን ዝም ብሎ የተመለከተው ሰማያዊ ፓርቲ ይጠየቅልን ብለዋል።” ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው መንግስትም ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ኣፍራሽ ድርጊቱ ካልተቆተበ ኣሸባሪ ተብሎ ከነግንቦት ሰባትና መሰል ድርጅቶች ተርታ ሊፈረጅ እንደሚችል ኣስምሮበት ኣልፉዋል ይልቁንም ሰማያዊ ፓርቲ በኣባይ ቦንድ እና በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ ኣስተያየት ከመስጠት ታቅቦ፤ ልማታዊ ጉዳዮች ላይ ቢያተኩር በማለት የመንግስት ቃል ኣቀባይ የሆኑት ኣቶ ኣከሌ ተናግረዋል (ኣከሌ ያልኩበት ምክንያት ከመለስ ሞት ወዲህ ሰው ኣጥፊ ብቻ ሳይሆን ኣላፊና ጠፊ እንደህነ ስለተረዳሁ ነው)፤ ኣያይዘውም ሰማያዊ ስሙ ከኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ጋም የተያያዘ ስለሆነ፤ የህገ-መንገስት የበላይነት እና የእምነት እኩልነት በሰፈነበት ሃገር ፓርቲያቸው ኢሃዲግ እንዲህ ኣይነት መድሎ ስለማይቀበል፤ ሰማያዊ በሚለው ላይ ተቀጽላ ጨምሮ (ሰማያዊ ኣል ረካት) ብሎ እንዲያስተካክለው እናሳስባለን፤ ይህ ባይሆን ግን ፤ ህገ መንግስቱ በሚፈቀደው መሰረት፤ ህጋዊ እርምጃ እንደምንወስድ እናሳስባለን። በነገረችን ላይ ይሄ የኣሸባሪነት ህግ ከመጠን በላይ መናፈስ በጀመረበት ዘመን የልጅ ልጃቸውን ማየት የቻሉ ኣያት፤ ልጃቸው እማ ልጄን ማን ልበልው ብላ ለጠየቀቻቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፤ ማንስ ብትይው ምን ዋጋ ኣለው፤  ገና ሳይወልድ እኮ ነው መንግስት ስም ያወጣለት፤ ስለዚህ ኣድጎ ግራ ከሚገባው ኣንድ ፊቱን ኣሸብር በይው ኣሉዋት። ኣረ እቴ፦

በነገራችን ላይ የጎጃም ገበሬ ነው ኣሉ፤ ስለ ኣዲሱ የኣደይ ሃዳስ ግድብ  ወይም ህዳሴ ግድብ ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፤ እናንተ የኢትዮጵያን ባህልና ወግ ለመናድ ስትታገሉ፤ ኣባይ ደሞ የኣማራ ኣፈርን ሲንድ፤ ነው የማወቀው፤ እንግዲህ ዛሬ ኣባይ ከዚህ ጸያፍ ድርጊቱ ታቅቦ፤ እንደ ሴተኛ ኣዳሪ እዚህም እዚያም ከማስካካት እናንተ ባበጃችሁለት ቦይ ለመንዶልዶል መወሰኑ ጥሩ ጅምር ነው፤ ዋናው ቁም ነገር ግን መንግስት ከዚህ ግድብ ምን ይማራል ነው፤ ይህ የሺህ ኣመት ቦዘኔ፤ ጨርቄን ማቄን ሳይል፤ ጉዋዙን ጠቅሎ  እዚሁ የተፈጠረበት ሃገር ለመስተር መሞከሩ፤ መንግስትን ምን ያስተምረዋል፤ የገዛ ሃገራቸውን ኣንጡራ ሃብት ለባ፤ኣዳን የሚቸበችቡ ኣሻጥረኞች ከዚህ ምን ይማራሉ ነው። ብሎ ኣስተያየቱን ሰትቶ ኣልፎዋል።

ሲታረስ ሳያምር ሲታጨድ ሳያምር

ዋራን ኣሳመረው የድንጋይ ቤት ክምር

ያለው ማን ነበር

ሲነገር ሳያምር ሲወራ ሳያምር

ደለል ሻኛ ሆነው የጭቃ ቤት ክምር

ብለን ለኣባይ መሳ ግጥም ገጥመን እንለፋ።

እና ስለ እንቅልፍ ተመልሰን እናውራ….

እናላችሁ  መተኛት ለሚፈልግ ከምግብና መጠጥ ሌላ ሁሉም ይሞዋላለታል። እንኩዋን ሰዉ ዛፍ እንኩዋ እንቅልፍ ለምዱዋል። መወዛወዝ የል፤ ቅርንጫፍ ማፋጨት የለ፤ ዘነበ ኣልዘነብ የለ፤ ከሰው ጉንጭ ውስጥ ገብቶ ለጥ። ማ ወንድ ነው የዘንድሮን ዛፍ የሚቀሰቅሰው። ስሙስ ቢሆን ኣሱም እንደ ቢዮንሴ ሄር ስታይለር …ተቀይሮ። ድሮ ኣባቶቻችን ሰለ ዛፍ ሲያወሩ፤ ዝግባ፤ ዋንዛ፤ ቀርቀሮ፤ ጥድ፤ የባህር ዛፍ፤ ወይራ፤ ኣር ስንቱ፤ የዘንድሮ ዛፍ ለስለስ ያለ ስም ነው ያለው፤ ለስለስ ያለ እጅም ነው የሚይዘው። የዘንድሮ ዛፍ ምንጣፍ ተነጥፎለት ነው ቤት የሚገባው እንጂ በኣህያ ጀርባ ተጭኖም ኣይደል። ከትግራይ ውጭ በኣራቱም ማእዘናት ይበላል፤ ኣወዳይ ወይም በፈረንጅኛው  (I will die) ገለምሶ፤ በለጬ ፤ ጉራጌ ገለመኔ ነው ስሙ። የዚህ የእንቅልፋም  ትውልድ ቀርቀሮና ዝግባ።  ይሄ ትውልድ በእውነትም እንቅልፋም ነው።

ደጉ መንግስቴ በክርስትና ስሙ (የዘመናት ብሶት የወረሰው፤ ወይም የወረረው) (በዳቦ ስሙ ባለ ራእዩ መንግስቴ)…  የኣቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ኣፍርሶ (ነቅሎ)፤ ቁልቁል ሲንደረደር በተኛበት ቤቱ የፈረሰበት ሰው ነው ኣሉ እንዴ ይሄ ባቡር ሳይገባ ገጭቶ የጨረሰን ሲገባ ምን ልንሆን ነው ኣለ ኣሉ። ሲገባማ ምን ችግር ኣለው፤ ያባልነት መታወቂያ ከያዝክ እንቅልፍህን ትራንሰፈር ታደርገው ዘንድ በርህ ላይ ቆሜ እየጠበቑ ነው የሚል ኣይመስልሕም።

ባለ ራአይ ስል…. የቀድሞ የሳውዝ ኣፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኔልሰን ማንዴላን የቀብር ስነ ስርኣት በተሌቪዥን ሲከታተል የነበረ  ኣንድ ታጋይ (በሃደግ)ለማንዴላ እንደኛ ባለ ሯዩ መሪ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ሴተኛ ኣዳሪዎች ያላለቁሱለት ለምንድን ነው ኣለ ኣሉ። ስላልወለዳቸው እናም ስላላገባቸው ልበልህ። ምን ልበል እኛ በህግ የተመዘገበ፤  ህገ መንግሱ የሚያውቃት ልጃቸው ቢሊየነሩዋን ሰማኸል መለስን ነበር፤ ታዲያ ጆቢራው ሲሞት ባንዴ (ባሌ ባሌ፥ ኣባቴ ኣባቴ ባዩ መብዛቱ) ድሮም  ሾፌርና የእንትን ወንድ ይሉ ነበር ዘመዶቼ::

ማን ነበር ሎዚች ጦላ ሎጦሞቆ ሴት ሙተኛት ነበር ያለው። ኣይ ሃገር፤ ቡና ቤት ኣረጉሽ፤ ኣይ ትውልድ ቁመን ኣየንሽ።

ሲታረስ ሳያምር ሲታጨድ ሳያምር

ዋራን ኣሳመረው የድንጋይ ቤት ክምር

ያለው ማን ነበር

ሲፈጥረው ሳያምር

ሲገለው ሳያምር

ክፋት ግብር ሆነው የደደቢት ንስር።

ብዬ ለኣባባ መልስ እኔ ወዲ ሃድጊው በጎዳ ልጆች ስም ግጥም ባበረክትስ።

ቸር ይግጠመን

የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር! ኢቲቪ ስለ ኢሳት

ማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር! ኢቲቪ ስለ ኢሳት

January 4, 2014

ቢታኒያ አለማየሁ፣ አዲስ አበባ

ዶክመንታሪ ብሎ ዝም! አስቡት እስኪ ኢሃዲግን በሚያክል አፋኝ መንግስት በኢቲቪ ኢሳት ሲብጠለጠል፣’ኢሳት ማለት የኢትዮጵያ ህይዝብ እውነተኛ የመረጃ ወፍጮ ነው!’Ethiopian Satellite Television (ESAT)

ለምን ግን በዚህ ሰአት ስለ ኢሳት ዶክመንታሪ መስራት አስፈለገ?

-ኢሳት ከተመሰረተ አንስቶ እስካሁን ድረስ በእውነተኛ መረጃ ምንጭነት በመላው የኢትዮጵያ አንጀት ውስጥ ተደላድሎ መቀመጡን ስልሚያውቁ!

-ይከስማል ይጠፋል አቅሙ ይዳከማል ሲሉት እንደ ወይን ጠጅ ከለት እለት እየበሰለና እየጎመራ መምጣቱን ስላዩ!

-በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ተምልካቾች ለኢሳት በመደወል በሚሰጡት አስተያየት ህዝቡ በሚገባ እየተከታተለው መሆኑን ስላረጋገጡ!

-ከዚህ ቀደም ከሰባት ጊዜ በላይ ጃም በማደርግ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት ቢያቛርጡም ኢሳት ግን የተለያዩ የሳተላይት አማራጮችን በመጠቀም ከአንድ አመት በላይ(እስካሁን) ያለ ምንም ችግር ወደ ኢትዮጵያ ማሰራጨ ስለቻለና አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ጃም ማድረግ ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ!

-ህዝብን አደንቁሮ በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ ብቻ የህዝብን አምሮ ለማደደብ በሚደርገው ጥረት ኢሳት ነጻ ሃሳብ በማነሸራሸር እንቅፋት ስለሆነ!
ባጠቃላይ ኢሳት ለህዝብ እውነትን በመግለጽ ለስረአቱ የእግር እሳት መሆኑ ስለታመነበት:- የኢሳትን ይዘት ተንትኖ እና እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ኢሳት ግን እንዲህ ይላል በሚል አመክኖዋዊ አስተሳሰብ ከመሞገት ይልቅ፣ ግንቦት ሰባት አሸባሪነው ኢሳት ደግሞ የግንቦት ሰባት ነው ስለዚህ ኢሳት አሸባሪ ነው ብለው ከደመደሙ በኋላ ህዝቡ አሳትን መከታተል እንደ ሽብርትኛነት አድርጎ ቆጥሮት መከታተሉን እንዲያቆም ለማግባባት ቀጥሎም ለማስገደድ ያመች ዘንድ የተሰራ ድራማ ነው! የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሳ ነው ትል ነበር አያቴ! የሚገርመው ግን አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት “ግንቦት ሰባት በቅዠትላይ የተመሰረተ ድርጅት” ከሆነ ይህን ያክል ተከታታይ ድራማዎች በመስራት ምን አደከማቸው? በራሱ ጊዜ ከእንቅሉ ይባንንላቸው የለም እንዴ?

እናንት አሸባሪ ኢሳቶች ሆይ ህዝብን እልል እያስባላችሁ አንባገነኖችን እያሸበራችሁ ነውና በርቱ! በርቱ! በርቱ!

ቢታኒያ አለማየሁ

ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ – “አርጅቻለሁ፤ በቃኝ”

 

negaso-gidada

በቅርቡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባደረገው ምርጫ ስልጣናቸውን ለኢንጂነር ግዛቸው ያስረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲያቸው አንድነት የመስራች ጉባኤውን በአዲስ ቪው ሆቴል እያደረገ ባለበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ቀጣይ የፖለቲካ ህይወታቸውን አስመልክቶ የደረሱበትን ውሳኔ አሳወቁ። የፓርቲውን የመመስረቻ ጉባዬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው የአንድነት ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹ከአሁን በኋላ ከየትኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሴን አግልያለሁ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ዕድሜዬ 70 መድረሱ ነው፡፡ትግሉን ወጣቶች መምራት እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ስለዚህ በቀሪው ህይወቴ ገለልተኛ በመሆን አገሪን ለማገልገል እሰራለሁ፡፡በአንድነት አዲሱ ብሄራዊ ምክር ቤት ከ65ቱ ውስጥ 47 ወጣቶች መሆናቸው አስደሳች ነገር ነው፡፡አዲሱ ፕሬዘዳንት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ከ65% በላይ ወጣቶች እንደሚሆኑ መናገራቸውም ያስደስተኛል፡፡›› ማለታቸውን የአንድነት ፓርቲ ሚድያዎች ዘግበዋል። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ኢሕአዴግን ሲለቁ አቶ መለስ ዜናዊን “አሁንስ መንግስቱ ኃይለማርያም መሰልከኝ” በሚል በቃኝ ያሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ በቃኝ ያሉት በእድሜ መግፋት ነው። ዛሬ በአዲስ ቪው ሆቴል ኢንጂነር ግዛቸው በአብዛኛው በወጣት የተያዘውን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። ዝርዝራቸውም የሚከተሉት ናቸው፦ 1) አቶ ተክሌ በቀለ ——- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት 2) አቶ በላይ ፈቃዱ ——– ምክትል ፕሬዘዳንት 3) አቶ ስዩም መንገሻ ——– ዋና ጸሀፊ 4) አቶ ዳንኤል ተፈራ ——– የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ 5)አቶ ሃብታሙ አያሌው ——- የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ 6)አቶ ዘለቀ ረዲ ——— የውጪ ጉዳይ ሀላፊ 7) አቶ አስቻለው ከተማ ——- የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ 8)አቶ ሰለሞን ስዮም ——– የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ 9) አቶ ዳዊት አስራደ ——– የኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ 10)አቶ አለነ ማህጸንቱ ——- የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ 11) ወ/ሮ የትናየት ቱጂ ——- የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ 12) አቶ ትእግስቱ አወሉ ——- (የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ በመሆናቸው በቀጥታ የካቢኔ አባል ሆነዋል)

ህገመንግስትን የሚቃረን አንቀጽ ከፀረሙስና አዋጅ እንዲሰረዝ ተወሰነ

ህገመንግስትን የሚቃረን አንቀጽ ከፀረሙስና አዋጅ እንዲሰረዝ ተወሰነ

አዲስ አድማስ ታህሳስ 26 2006

 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፓርላማ የወጣውን ህግ ሲያሻሽል አሁን የመጀመሪይው ነው፡፡ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጐባቸው ነበር፡፡ “በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ላይ የቀረበው የሙስና ክስ መታየት ያለበት በከፍተኛ ፍ/ቤት ነው ወይስ በጠቅላይ ፍ/ቤትን” በሚል ለተነሳው ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ለሰዓታት የተከራከሩ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት፤ የሚኒስትሮች ክስ በጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲታይ የሚደነግገው አንቀጽ ከፀረ ሙስና አዋጁ እንዲሰረዝ በ76 የድጋፍና በ8 የተቃውሞ ድምጽ ወሰኑ፡፡ የሙስና ክሶችን በቀዳሚነት የመዳኘት ስልጣን የከፍተኛ ፍ/ቤት እንደሆነ የሚገልፀው የፀረሙስና አዋጅ፣ ሚኒስትሮች ሊከሰሱ ግን በቀጥታ ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ ይገልፃል፡፡ በ1993 ዓ.ም ኢህአዴግ ውስጥ በተከሰተው ፀብ ከፓርቲው አመራርነት የተባረሩት የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ስዬ አብርሃ፣ በወቅቱ በሙስና መከሰሳቸው የሚታወቅ ሊሆን፣ ጉዳያቸው በቀጥታ በጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲታይ መደረጉን ተቃውመው እንደነበር ይታወሳል፡፡ እንደሌሎች ተከሳሾች የአቶ ስዬ ክስ በከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲታይ መከራከሪያ ያቀረቡት ጠበቃ፤ አለበለዚያ ግን ይግባኝ የመጠየቅ የተከሳሽ ህገመንግስታዊ መብትን የሚጥስ ይሆናል ብለዋል፡፡ በፀረ ሙስና አዋጅ የተካተተው አንቀጽ ህገመንግስቱን ስለሚቃረን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት የአቶ ስዬ ጠበቃ ቢከራከሩም፤ ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ጥያቄው እንደገና ፍ/ቤት ውስጥ የተነሳው ከአስር አመታት በኋላ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ ሃላፊዎች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ በአንድ በኩል ዋና ዳሬክተሩ አቶ መላኩ ፈንታ በሚኒስትርነት ማዕረግ የተሾሙ በመሆናቸው፣ በፀረ ሙስና አዋጁ መሰረት ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍ/ቤት መታየት ይገባዋል የሚል አስተያየት ቀርቧል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህጐች፣ በበኩላቸው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እንደሆነ በህገመንግስት ውስጥ በግልጽ ስለሰፈረ፣ የሁሉም ተከሳሾች ጉዳይ በከፍተኛ ፍ/ቤት መታየት አለበት በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍ/ቤቱም፤ የአዋጁ አንቀፆች ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጋጩ ወይም እንደማይጋይጩ የመወሰንና ለዚህ ክርክር እልባት የመስጠት ስልጣን እንደሌለው በመግለጽ ነው፣ ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ም/ቤት ያስተላለፈው፡፡ በፌደሬሽን ምክር ቤት ስር የተቋቋመው የህገመንግስት ጉዳዮች የአጣሪ ጉባኤ፣ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የውሣኔ ሃሳብ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ አባላት ለበርካታ ሰዓታት ተከራክረውበታል፡፡ “በፀረ ሙስና አዋጅ የተካተተው አንቀጽ ህገ መንግስቱን ስለማይፃረር ባለበት ይቀጥል፤ እንዲያውም ህገመንግስቱን የሚያስከብር ነው” በማለት አስተያየት የሰነዘሩ አባላት፤ “ባለስልጣናት በሙስና ሲባልጉ አምነው የተቀበሉትን ህገመንግስት ስለሚጥሱ ይግባኝ በሌለበት ሁኔታ ፍርዳቸው መታየቱ ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ጉዳዩ ክብደትና እና ጥልቀት ያለው መሆኑን በመጠቆም ጉዳዩን ለማጤን የተሰጠው ጊዜ አጭር ነው የሚል ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ በሌላ በኩል፤ “የይግባኝ መብት የሚጣሰው የአቶ መላኩ ብቻ ሳይሆን የአቃቤ ህግም ነው” በማለት የተከራከሩ አባላት፣ ጉዳዩ በከፍተኛው ፍ/ቤት መታየቱ ሁለቱንም ይጠቅማል ብለዋል፡፡ ይግባኝ በሌለበት ሁኔታ ፍርዳቸው መታየት አለበት በሚል የተሰነዘረውን ሃሳብ በመቃወም ምላሽ የሰጡት የአጣሪ ጉባኤው አባል አቶ ሚሊዮን አሰፋ “የሚኒስትሮች ክስ ከሌላው ሰው ተነጥሎ ይታይ” የሚል ሃሳብ በዜጐች መካከል የመደብ ልዩነት መኖሩን ከሚያመላክት ፊውዳላዊ አስተሳሰብ የሚመነጭ በመሆኑ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ በመጨረሻም፤ አከራካሪው አንቀጽ ህገመንግስቱን ስለሚቃረን ከፀረ ሙስና አዋጅ እንዲሰረዝ በ76 የድጋፍና በ8 የተቃውሞ ድምፅ የተወሰነ ሆን፣ እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ ለምክር ቤቱ የመጀመሪያው መሆኑን በመጠቆም ታሪካዊ ውሳኔ ነው በማለት አፈጉባኤው አቶ ካሳ ተክለብርሃን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ለሳዑዲ ተመላሾች የሚውል ድጋፍ ሰጡ

ኢትዮጵያዊያን ለሳዑዲ ተመላሾች የሚውል ድጋፍ ሰጡ

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መብቶች መከበር የሚሟገተው ዓለምአቀፍ ጥምረት የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት – አይኦኤም ዛሬ አበረከተ፡፡
sa
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መብቶች መከበር የሚሟገተው ዓለምአቀፍ ጥምረት የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት – አይኦኤም ዛሬ አበረከተ፡፡

ሥጦታውን ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የአይኦም ፅ/ቤት ተገኝተው ያበረከቱት የጥምረቱ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ፣ የጥምረቱ የዲፕሎማሲና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር አክሎግ ቢራራ፣ የጥምረቱ የበላይ አማካሪ አቶ ንአምን ዘለቀ፤ የገንዘብ መምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሂሩት ልሣነወርቅ ናቸው፡፡ሥጦታውን የተረከቡት የአይአኤም የዋሽንግተን ዲ.ሲ. ቢሮ የውጭ ግንኙነቶች ኃላፊ ማሪያ ማሪኖ ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ቀውሱን በማስወገድ ላይ እየሠራ ያለ ድርጅታቸው እስከአሁን 140 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ከሳዑዲ አረቢያ ማውጣቱን አመልክተው በአሁኑ ጊዜ የቅድሚያ ትኩረት እየሰጡ ያሉት ለሴቶችና ለሕፃናት መሆኑን አስረድተዋል፡፡አይኦኤም ለድጋፍ ከጠየቀው የ15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እስካሁን ያገኘው 2.5 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ሞሪኖ ጠቁመው የአሁኑን የኢትዮጵያዊያኑን ዓይነት ድጋፍ ድርጅታቸው እንደሚያደንቅና ማንኛውምንም እርዳታ እንደሚቀበል ከተረጂዎች ጋርም እየሠራ ያለው በቀጥታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

አይ ስብሐት ነጋ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

አይ ስብሐት ነጋ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

January 4, 2014

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

Download

Prof. Mesfin Woldemariam

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን ‹‹አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት፤ ስለሆነም ነበር ከፍተኛ ጥበቃ አልፈን የገባነው፤›› ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ በከባድ ጥያቄም ቢሆን የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ ማረጋገጡ በተማሪዎቹም ቢሆን ውሎ አድሮ ትዝብት ላይ ይጥለዋል።

ዶር. በድሉ ዋቅጂራ ስለስብሐት ነጋ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ በሚል በጻፈው ላይ ዶር. ዳኛቸውን እንደሚከተለው ይጠቅሳል፤ ‹‹ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት፤ በቃ በአጭሩ (ኢትዮጵያዊ ሆኖ)ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው፤›› በቅንፍ ውስጥ ያለው የኔ ነው፤ ልክ ነው፤ አንድ ግለሰብ በማናቸውም ምክንያት ከኢትዮጵያዊነት ቢወድቅ ኢትዮጵያዊነቱ የከሸፈ ነው ለማለት ይቻላል፤ ነገር ግን ከኢትዮጵያዊነት መውደቅንና ኢትዮጵያዊነትን መጣልን ለይተን ማየት ያስፈልጋል፤ አንድ ሰው በማናቸውም ምክንያት ከፍተኛውን የኢትዮጰያዊነት ባሕርይና ግዴታ መሸከም አቅቶት ቢወድቅ ለዚያ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ከሸፈ፤ ለስብሐት ነጋና ለጓደኞቹ ከከሸፈባቸው የቆየ ይመስለኛል፤ ከራሱ አልፎ የሌሎችን ኢትዮጵያዊነት ለማክሸፍ የሚሞክር ደሞ ከመክሸፍ አልፎአል፤ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት የከሸፈ ኢትዮጵያዊነት ነው ማለት ነው።

ስብሐት ነጋ ዋና ዓላማው በሙሉ ነጻነት የመጣለትን እንደመጣለት መናገር ነው፤ ምሳሌዎችን እንጥቀስ፤– ሀ) ‹‹ከኢትዮጵያ ሕዝብ በላይ የኤርትራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት አለው፤›› ስብሐት ነጋ ስለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ስለኤርትራ ሕዝብ፣ ስለኢትዮጵያዊነት ያለው እውቀት የሚባል ነገር እንዲህ ያለው መዘባረቅ ነው፤ ስብሐት ነጋ ጨረቃ ከጸሐይ የበለጠ ትሞቃለች ቢልም አይደንቀኝም፤ አልከራከረውም፤ ስብሐት ነጋም ብቻውን መናገር እንጂ መከራከር አይፈልግም፤ ለ) ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኤርትራ ሕዝብ የበለጠ የኤርትራን መሬት ይፈልጋል፤›› እንደምሳሌ ያነሣው አሰብን ነው፤ ባድመን አላነሣም!  እሱና ጓደኞቹ የኢትዮጵያን ወጣቶች በከሸፈ ጦርነት ውስጥ የማገዱት ባድመ ለሚባል መንደር ነው እንጂ አሰብ ለሚባል ወደብ አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ ጦርነቱን በመቃወም ድምጼን ያሰማሁት ኢትዮጵያዊ ወይም ኤርትራዊ ሆኜ አልነበረም፤ ሰው ሆኜ ነው፤ ዛሬ ስብሐት ነጋ ሲዘላብድ ኢትዮጵያዊነት የማይታይበትን ያህል ኤርትራዊነትም አይታይበትም፤ በዚህም ጉዳይ ላይ መከራከር አይፈልግም፤ ሐ) ‹‹ለማንኛውም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ መከልከላቸው የማውቀው ብዙ ነገር የለኝም፤ ይከልከሉም አልልም፤ አይከልከሉም አልልም፤ መብታቸው ነው፤›› ይህ መዘላበድ ካልሆነ ምንድን ነው? ምን ቁም-ነገር ይዞ ነው ይህንን የተናገረው? የገለባ ክምር ውስጥ አንድ ፍሬ መፈለግ ይቀላል።

አንድ ሌላ የስብሐት ነጋ ዘዴ (ዘዴ ካልነው!) ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ እንደመጣለት ይናገርና ‹‹አላውቅም›› ይላል! የማያውቀውን መዘባረቅ ግን ይችላል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የምን ፓርቲ እንደሆነ አይታወቅም፤ የእስላም ፓርቲ ነው?›› ስብሐት ነጋ እውቀትን የሚሻ ቢሆን ለፓርቲዎች እውቅናን የሚሰጠውን መሥሪያ ቤት ያውቀዋል፤ ለምን ብሎ ይጠይቅ? ለምን ብሎ እውነቱን በማወቅ ይታሰር? ትክክለኛ መረጃ ባለማወቅ እንደልብ የመናገርን ነጻነት ይገድባልና ‹‹አላውቅም›› ማለት ለመዘላበድ ይጠቅማል፤ ምንም እንኳን የሰላዮች ሠራዊት እንዳለው ብናውቅም ስለእስላሞችና ስለሰማያዊ ፓርቲ የተናገረውን እንደፖሊቲካ ከወሰደው ደረጃውን ከማሳየት አያልፍም፤ ሰማያዊ ፓርቲን በሁሉም ዘንድ ለማስጠላት የሚከተለውን ይላል፤ ‹‹እስላሞች ወንድሞቻችን የሚሉት ደግሞ የት ያውቁናል? ሲቀጠቅጡን የነበሩ፤ ተራ ሕዝቡም አይወዳቸውም፤›› የጤፍ ቅንጣት የምታህል የማሰብ ተግባር ቢኖርበት ስብሐት የተናገረው ያልተጠረነፉትን እስላሞች በሙሉ የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት ይችል ነበር።

ስብሐት ነጋ አንድ መቶ ሃያ ዓመታት ያህል ወደኋላ ቢሄድ ኤርትራ የሚባል አገር አያገኝም፤ በዚያ መሬት ያሉ ሰዎች ላላቸው ወይም ለሌላቸው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የስብሐት ነጋን ምስክርነት እንደማይፈልጉ በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፤ ለሌሎቻችን ኢትዮጵያዊነትም ቢሆን የስብሐት ነጋ ምስክርነት አያሻንም፤ አሰብን አንሥቶ ብዙ ወጣቶች ያለቁበትን ባድመን ሳያነሣ መቅረቱ በአንድ በኩል፣ አሰብንም ሆነ ባድመን ከሚፈልጉ ወገኖች መሀል እሱ መውጣቱን በጣም ግልጽ አደረገ፤ ወዴት እንደገባ ግን ገና አልነገረንም!!!

Download (1)

 

The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire

1383955_727118837316235_2074903103_n

In March 1896 a well-disciplined and massive Ethiopian army did the unthinkable—it routed an invading Italian force and brought Italy’s war of conquest in Africa to an end. In an age of relentless European expansion, Ethiopia had successfully defended its independence and cast doubt upon an unshakable certainty of the age—that sooner or later all Africans would fall under the rule of Europeans. This event opened a breach that would lead, in the aftermath of world war fifty years later, to the continent’s painful struggle for freedom from colonial rule.

 

Raymond Jonas offers the first comprehensive account of this singular episode in modern world history. The narrative is peopled by the ambitious and vain, the creative and the coarse, across Africa, Europe, and the Americas—personalities like Menelik, a biblically inspired provincial monarch who consolidated Ethiopia’s throne; Taytu, his quick-witted and aggressive wife; and the Swiss engineer Alfred Ilg, the emperor’s close advisor. The Ethiopians’ brilliant gamesmanship and savvy public relations campaign helped roll back the Europeanization of Africa.

 

Figures throughout the African diaspora immediately grasped the significance of Adwa, Menelik, and an independent Ethiopia. Writing deftly from a transnational perspective, Jonas puts Adwa in the context of manifest destiny and Jim Crow, signaling a challenge to the very concept of white dominance. By reopening seemingly settled questions of race and empire, the Battle of Adwa was thus a harbinger of the global, unsettled century about to unfold.

 

ያዋረደን ማነወ ? ? ?

ያዋረደን ማነወ ? ? ?
ቅጥረኝነተ፤ የስልጣን ልክፍት፤ ዝቅተኝነትና እብደት፤ ቡድነኝነትና ጎጠኝነት፤ ዘራፊነት፤ ነፍሰገዳይና
ጨካኝነት አፋኝነትና አሸባሪነት፤ በታኝነትና ከፋፋይነት፤ ሗላቀርነትና ምቀኝነት፤ እምነት የለሺ
የታሪክና አገር ካሐዲነት ወዘተ…የተሰኙት ቃላት ወያኔንና የሺፍታ ስርዓቱን በሚገባ ይገልፁታል። እኛ
ኢትዮጵያውያን ውርደታችን የሚጀምረው በዚህ ጨካኘና ካሐዲ ቡድን መዳፍ ስር ከወደቅንበት ጊዜ
ጀምሮ ነው። ወያኔና መሰሎቹ በኢትዮጵያና በሕዝባችን ላይ ባለፉት 22 አመታት የፈፀሙት ወንጀለኛ
ተግባሮቻቸው ዋንኛ መለኪያና ማረጋገጫችን ነው።
በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ እንደተመዘገበው መንግስትን ገልብጦ መንግሰት ማቋቋም ያለና የነበረ
አለማቀፋዊ ክስተት ነው። ነገርግን ወያኔንና የሺፍታ ስርዓቱን ከዓለማችን ታሪካዊ መዘውር ውስጥ
ልዩ የሚያደርገውውና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ምስቅልቅል ስርዓቱም የሚጠቁመው
የገለበጠው አላፊውንና ጠፊወን ምድራዊ የኮሎኔል መንግስቱ ሐ/ማሪያምን መንግስት ሳይሆን ይልቁንም
የነበረውንና ወደፊትም የሚኖረውን የጋራ አገር፤ የጋራ ሕዝብ የጋራ ታሪካችንና ባሕልላችን ሆኖ
መገኘቱ ነው። ለዚሕም ነው ወያኔ ተፈጥሮዋዊ ውልደቱና እድገቱ መንግስት ተብሎ ለመጠራት
መመዘኛውን የማያሟላው። ይሕ ጎደሎው የመንግስትነት ስነምግባርና ሺፍታዊ መታወቂያው በመሆኑ
ብሔራዊ ሐላፊነት የማይሰማው ሐገርንና ሕዝብን ያዋረደ የጥቂት ሺፍቶች ማፍያ ቡድን ነው ብልን
አፋችን ሞልተን እንድንናገር የምንገደደው። የብሔራዊ ውርደታችን ምንጭም እራሱ ወያኔና አጋሮቹ
ለመሆናቸው ከተግባር የበለጠ ሌላ ገላጭ ቋንቋ ስለሌለ ማንንም የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም
የወያኔውም አፈጣጠር ለዚሕ ጥፋት ታስቦና ተመቻችቶ ነው።
ቆምነገሩ ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው ምስራቅ አፍሪካዊት አገር ውስጥ ሐገሪቱን እንደሐገር
ሕዝቡን እንደህዝብ የሚያስከብር መንግሰት አለን ወይ ብሎ ለሚጠይቅ ዜጋ መልሱ የለንም ማለታችን
ብቻ ሳይሆን በዚሕ በኩል የነበረው እድል በ 4 ነጥብ መዘጋቱ ነው። ባንፃሩ ስናይ እኛን ኢትዮጵያንን
ያዋረደን ማነው የሚለውን ሰሞነኛ ጥያቄ ለመመለስ ወያኔ ነውና ደረታችን ነፍተን ከመናገር ውጭ
ከቶውንም ማነንም ቅን ዜጋ አያሳፍረውም። ሰሞኑን ደግሞ ያረጀ ጡርንባ እየተነፋ አየሩ ተበክሎል።
በውጭና በውስጥ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ያረጀ ካርድ ተመዞ የተሰጠን አጀንዳ አለ። እሱም
በዘመናዊ የባሪያ ፍንገላ ስልት በራሱ በወያኔው ተሺጠው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ስርተው በሚያድሩ
ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ እልቂትና ውርደት አንዱ ሲሆን ሁለተኛው የአማራውን ሕዝብ
ከኦረሞው ጋር የማጋጨቱ የቆየው የወያኔ አጀንዳ በቴዲ አፍሮ ዘፈን ምክንያት እንደገና በአዲስ መልክ
ተቀስቅሶ በውስጥም በውጭም በምንኖረው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ አቧራው ጨሰ የተሰኘውን ወያኔዊ
የፕሮፓጋንዳ ሺብር አስከትሎ አጀንዳውን ጀባ ተብለናል።
ታዲያ የሰሞኑ አቧራው ጨሰ ወያኔዊ ሺብርተኛ ፕሮፖጋንዳ አጀንዳ ሚስጥሩ ምንድነው ብሎ መጠየቅ
ብልሕነት ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔው የጥፋት ውሳኔ መሰረት
ኢትዮጵያ የምትባል ሐገርና የዜግነት መብት የለህም ተብሎ በሕዋ ላይ መኖር ከጀመረ ይኸውና 22
ዓመታትን አስቆጥሮል።ኢትዮጵያዊነቱንና ሰው በመሆኑ ብቻ ነፃነቱን የጠየቀው ሕዝብ በወያኔና
መሰሎቹ በገዛ ሐገሩ ይገደላል፤የደበደባል፤ይታሰራል፤ ይሰደዳል፤ሐብትና ንብረቱን ይነጠቃል፤ትውልድ
ቦታውን በማስለቀቅ እንዲጋዝ ይፈረድበታል፤ በእምነቱ የማመን ነፃነቱ ይገፈፋል፤ ፍትህን ፍለጋ
ወደሰማይ እያነባ ያንጋጥጣል፤እራሐብና እርዛት ለሱ የተሰጠ ፀጋ ሆኖበታል፤ አኩሪ ባሕሉ ቆሺሾል፤
መጋባቱ መዋለዱ ተገድቦ ፈጣሪው የቸረውን ነፃነት ተነጥቆል፤ እርስበርሱ የመደጋገፍ ተስፋው
ተሟጧል፤ በየመንደሩ በተሰገሰጉ የወያኔ ጀሮ ጠቢውች እንዳይናገር ልሳኑ ተዘግቶል፤ የዘራፊወች የበይ
ተመልካች ሆኖ በራሐብ አለንጋ ይጠበሳል፤ ቤተሰቡን ማስተዳደር ተስኖታል፤ ባልተለመደ መልክ
ስብዕናን ለሚሸጡ የወያኔ ደላላወች ልጆቹን አሳልፎ እዲሰጥ ተገዷል፤ በየቀኑና በየደቂቃው ወያኔው
ለራሱ ህልውና ይጠቅሙኛል ብሎ በሕዘቡ ውስጥ በሚቀሰቅሳቸው ግጭቶችና ሺብር የመኖር
ዋስትናው ተናግቶ ተሰላችቶል፤ የወያኔው የውሸት ነፃ አውጭነት ፕሮፓጋንዳ ነጋ ጠባ ሆዱን ነፍቶ
አቅለሺልሾታል።
በዚሕ አይነት የወያኔው የግፍ ቀንበር ተጭኖት ሕዝባዊ ብሶቱ ለአመታት ተጠራቅሞ ቆይቶ ዛሬ
በሐገሪቱ የትኛውም ማእዘናት ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። ታዲያ ይህ ብሶት የወለደው ሕዝባዊ ማዕበል
ማንም ሊገታው በማችል መልኩ ሊከሰት እንደሚችል ማመላከቱ ብቻ ሳይሆን ወያኔንና መሰሎቹን
መግቢያና መውጫ አሳጥቶ የሚጠራርግ ሕዝባዊ ማዕበል መሆኑ አይቀሬ ነው። ይሕ አይቀሬ የሆነው
የታሪክ ሒደት ወያኔን አስጨንቆ አሳብዶ የራስምታት በሺታ ጥሎበታል አባኖታል አንቀዠቅዦታል
የባህሩ ሞገድ ከድንጋይ ከቋጥኙ ጋር እያንከባለለ ያላትመዋል። የሕዝባዊ ብሶቱ የአደጋ ጥሪም በመረዋ
ድምፁ ተንቆርቁሮ ተዋርደን አንቀርም የሚለው ጩኸቱ ከወያኔው ጀሮ በመድረሱ የሚጨብጠውን
አሳጥቶታል። በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እዲሉ ወያኔው በራሱ ውስጠ ሕይወት የተፈጠረው ታሞ
የማይድን አስተዳደራዊይ ግማቱ ታክሎበት አቀጣጣይ ክብሪቱን ለመለኮስ ተቀጣጣይ ቤንዚሉን
አርከፍክፎ የህዝባዊ ብሶቱን ቦንብ የመፈንዳት ፍጥነት እዲጨምር የበለጠ እየገፋው ነው።
ታዲያ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ዛሬ ብለጣብልጡ ውያኔ ከተፈጠረበት ከፍተኛ እራስ
ምታት በሺታ የሚያድነው መዳሕኔት ባያገኝም ለጊዜውም ቢሆን ሊውጠው ሊሰለቅጠው የተቃረበውን
ሕዝባዊ ማእብል ለመግታት ማስታገሻ ኪኒን ይሆነኛል ያለውን ወያኔ ሰራሺ ኬሚስትሪ ማፈላለጉ
አልቀረም። ዘመድ ከዘመዱ አሕያ ካመዱ ሆነና አቅፈውና ደግፈው በቅጥረኝነት ያሰለፉትን አረቦች
ተመልሶ እጅ መንሳቱ ግድ ስለሆነበት የሜንጫ ፖለቲካ አራማጅ የሆኑ ኤጀንቶችን ከሲያድባሬ አክራሪ
እስላሚስት መኮንኖች ተውሶ ኦረሞ ፈርስት የተባለውን ቋንቋ ካረጁና ተስፋ ከቆረጡ ጥቂት የኦነግ
ሚሺነሪወች በማዳቀል በጀት መድቦ ጮሌ ካድሬወችን ቀጥሮ በሚቆጣጠራቸውና አዳዲስ በፈጠራቸው
ሚዲያወች በመጠቀም በውጭም በውስጥም እያተራመሰ ነው። ፈውስ ባያገኝም በጠና ከታመመበት
የእራስ ምታት በሺታ ለጊዜውም ቢሆን ጊዜ ለመግዛት ማስታገሻ ኪኒን እየወሰደ ነው። ደሮውንም
ወያኔ ሲወጠርና ሲጨነቅ ኮንዶሞቹን እንደደባል እቃ ማውጣትና ማግባት ዛሬ የተከሰተ ባለመሆኑ
ለሐገር ወዳዱ ሕዝባችን አዲስ ነገር አይሆንበትም በወያኔ ላይ ያነሳውን ሕዝባዊ አመፅ የሚያስቆም
አንዳችም ምድራዊ ሐይል የለም። የልቁንም የምስራቁ በረኛ የደጃዝማች ዑመር ሰመተርንና የደጃዝማች
ባልቻ አባ ነፍሶን የነራስ ጉብና ዳጨውንና የነ አፃ ምኔልክን የነ ራስ አበበ አረጋይንና የነ ጀኔራል
ኤጃማ ኬሎን የነ ጀኔራል ታደሰ በሩንና የነ ጀኔራል ደምሴ ቡልቱን የመሳሰሉ ጀግኖቻችን ያቆዩንን
ኢትዮጵያ አገራችን መዳፈር የዘመናት ታሪካችን አለማወቅ ይመስለኛል። ወያኔና ቅጥረኞቹ በአሁኑ
ወቅት እየደረሰባቸው ካለው ሕዝባዊ ማዕበል ለማገገም የቻሉ እየመሰላቸው አቧራው ጨሰ የተሰኘውን
የወያኔ ሰራሺ ሺብረተኛ ፕሮፖጋንዳ አጀነዳ አዲስ ግኝት አስመስለው በማራገብ ሕዝባዊ ጀግኖቻችን
ማዋረድና ማንቓሺ የወያኔውን ግባተ መሬት መቃብሩን ቁፈራ ቢያፋጥነው እንጅ ከቶውንም
ለጣረሞቱ ማስታገሻ ኪኒን ሆኖ አያገለግለውም። በውስጥም በውስጥም የምንኖር ቀለም ቀመስ
ኢትዮጵያውያን ሆይ!! ሕዝባቸህን ብሶቱ ገንፍሎ ወያኔንና ጀሌወቹን ከራሱ ላይ ለማውረድ እየታገለ
መሆኑን እናውቃለን ስለዚህ ሳናመነታ ሞላች ጎደለች ሳንጫወት የወያኔ የጥፋት ፕሮፖጋንዳ ማራገፊያ
ሳንሆን መከራ ተቀባይ የሆነውን ሕሕባችእንና ታሪካዊት ሕገራችን ከሺብርተኛ ቡድኖች ጥፋት
እንከላከል፤ እናድን!!
አገራችን በጎሳ ስም ዳግም ስልጣን ከሚናፍቁ ሺብርተኞችና
ሚሺነሪወች ጥፋት እንጠብቅ !!
መሰረት ቀለመወርቅ
አውሰተራሊያ

ያዋረደን ማነወ ? ? ?

ያዋረደን ማነወ ? ? ?
ቅጥረኝነተ፤ የስልጣን ልክፍት፤ ዝቅተኝነትና እብደት፤ ቡድነኝነትና ጎጠኝነት፤ ዘራፊነት፤ ነፍሰገዳይና
ጨካኝነት አፋኝነትና አሸባሪነት፤ በታኝነትና ከፋፋይነት፤ ሗላቀርነትና ምቀኝነት፤ እምነት የለሺ
የታሪክና አገር ካሐዲነት ወዘተ…የተሰኙት ቃላት ወያኔንና የሺፍታ ስርዓቱን በሚገባ ይገልፁታል። እኛ
ኢትዮጵያውያን ውርደታችን የሚጀምረው በዚህ ጨካኘና ካሐዲ ቡድን መዳፍ ስር ከወደቅንበት ጊዜ
ጀምሮ ነው። ወያኔና መሰሎቹ በኢትዮጵያና በሕዝባችን ላይ ባለፉት 22 አመታት የፈፀሙት ወንጀለኛ
ተግባሮቻቸው ዋንኛ መለኪያና ማረጋገጫችን ነው።
በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ እንደተመዘገበው መንግስትን ገልብጦ መንግሰት ማቋቋም ያለና የነበረ
አለማቀፋዊ ክስተት ነው። ነገርግን ወያኔንና የሺፍታ ስርዓቱን ከዓለማችን ታሪካዊ መዘውር ውስጥ
ልዩ የሚያደርገውውና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ምስቅልቅል ስርዓቱም የሚጠቁመው
የገለበጠው አላፊውንና ጠፊወን ምድራዊ የኮሎኔል መንግስቱ ሐ/ማሪያምን መንግስት ሳይሆን ይልቁንም
የነበረውንና ወደፊትም የሚኖረውን የጋራ አገር፤ የጋራ ሕዝብ የጋራ ታሪካችንና ባሕልላችን ሆኖ
መገኘቱ ነው። ለዚሕም ነው ወያኔ ተፈጥሮዋዊ ውልደቱና እድገቱ መንግስት ተብሎ ለመጠራት
መመዘኛውን የማያሟላው። ይሕ ጎደሎው የመንግስትነት ስነምግባርና ሺፍታዊ መታወቂያው በመሆኑ
ብሔራዊ ሐላፊነት የማይሰማው ሐገርንና ሕዝብን ያዋረደ የጥቂት ሺፍቶች ማፍያ ቡድን ነው ብልን
አፋችን ሞልተን እንድንናገር የምንገደደው። የብሔራዊ ውርደታችን ምንጭም እራሱ ወያኔና አጋሮቹ
ለመሆናቸው ከተግባር የበለጠ ሌላ ገላጭ ቋንቋ ስለሌለ ማንንም የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም
የወያኔውም አፈጣጠር ለዚሕ ጥፋት ታስቦና ተመቻችቶ ነው።
ቆምነገሩ ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው ምስራቅ አፍሪካዊት አገር ውስጥ ሐገሪቱን እንደሐገር
ሕዝቡን እንደህዝብ የሚያስከብር መንግሰት አለን ወይ ብሎ ለሚጠይቅ ዜጋ መልሱ የለንም ማለታችን
ብቻ ሳይሆን በዚሕ በኩል የነበረው እድል በ 4 ነጥብ መዘጋቱ ነው። ባንፃሩ ስናይ እኛን ኢትዮጵያንን
ያዋረደን ማነው የሚለውን ሰሞነኛ ጥያቄ ለመመለስ ወያኔ ነውና ደረታችን ነፍተን ከመናገር ውጭ
ከቶውንም ማነንም ቅን ዜጋ አያሳፍረውም። ሰሞኑን ደግሞ ያረጀ ጡርንባ እየተነፋ አየሩ ተበክሎል።
በውጭና በውስጥ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ያረጀ ካርድ ተመዞ የተሰጠን አጀንዳ አለ። እሱም
በዘመናዊ የባሪያ ፍንገላ ስልት በራሱ በወያኔው ተሺጠው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ስርተው በሚያድሩ
ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ እልቂትና ውርደት አንዱ ሲሆን ሁለተኛው የአማራውን ሕዝብ
ከኦረሞው ጋር የማጋጨቱ የቆየው የወያኔ አጀንዳ በቴዲ አፍሮ ዘፈን ምክንያት እንደገና በአዲስ መልክ
ተቀስቅሶ በውስጥም በውጭም በምንኖረው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ አቧራው ጨሰ የተሰኘውን ወያኔዊ
የፕሮፓጋንዳ ሺብር አስከትሎ አጀንዳውን ጀባ ተብለናል።
ታዲያ የሰሞኑ አቧራው ጨሰ ወያኔዊ ሺብርተኛ ፕሮፖጋንዳ አጀንዳ ሚስጥሩ ምንድነው ብሎ መጠየቅ
ብልሕነት ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔው የጥፋት ውሳኔ መሰረት
ኢትዮጵያ የምትባል ሐገርና የዜግነት መብት የለህም ተብሎ በሕዋ ላይ መኖር ከጀመረ ይኸውና 22
ዓመታትን አስቆጥሮል።ኢትዮጵያዊነቱንና ሰው በመሆኑ ብቻ ነፃነቱን የጠየቀው ሕዝብ በወያኔና
መሰሎቹ በገዛ ሐገሩ ይገደላል፤የደበደባል፤ይታሰራል፤ ይሰደዳል፤ሐብትና ንብረቱን ይነጠቃል፤ትውልድ
ቦታውን በማስለቀቅ እንዲጋዝ ይፈረድበታል፤ በእምነቱ የማመን ነፃነቱ ይገፈፋል፤ ፍትህን ፍለጋ
ወደሰማይ እያነባ ያንጋጥጣል፤እራሐብና እርዛት ለሱ የተሰጠ ፀጋ ሆኖበታል፤ አኩሪ ባሕሉ ቆሺሾል፤
መጋባቱ መዋለዱ ተገድቦ ፈጣሪው የቸረውን ነፃነት ተነጥቆል፤ እርስበርሱ የመደጋገፍ ተስፋው
ተሟጧል፤ በየመንደሩ በተሰገሰጉ የወያኔ ጀሮ ጠቢውች እንዳይናገር ልሳኑ ተዘግቶል፤ የዘራፊወች የበይ
ተመልካች ሆኖ በራሐብ አለንጋ ይጠበሳል፤ ቤተሰቡን ማስተዳደር ተስኖታል፤ ባልተለመደ መልክ
ስብዕናን ለሚሸጡ የወያኔ ደላላወች ልጆቹን አሳልፎ እዲሰጥ ተገዷል፤ በየቀኑና በየደቂቃው ወያኔው
ለራሱ ህልውና ይጠቅሙኛል ብሎ በሕዘቡ ውስጥ በሚቀሰቅሳቸው ግጭቶችና ሺብር የመኖር
ዋስትናው ተናግቶ ተሰላችቶል፤ የወያኔው የውሸት ነፃ አውጭነት ፕሮፓጋንዳ ነጋ ጠባ ሆዱን ነፍቶ
አቅለሺልሾታል።
በዚሕ አይነት የወያኔው የግፍ ቀንበር ተጭኖት ሕዝባዊ ብሶቱ ለአመታት ተጠራቅሞ ቆይቶ ዛሬ
በሐገሪቱ የትኛውም ማእዘናት ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። ታዲያ ይህ ብሶት የወለደው ሕዝባዊ ማዕበል
ማንም ሊገታው በማችል መልኩ ሊከሰት እንደሚችል ማመላከቱ ብቻ ሳይሆን ወያኔንና መሰሎቹን
መግቢያና መውጫ አሳጥቶ የሚጠራርግ ሕዝባዊ ማዕበል መሆኑ አይቀሬ ነው። ይሕ አይቀሬ የሆነው
የታሪክ ሒደት ወያኔን አስጨንቆ አሳብዶ የራስምታት በሺታ ጥሎበታል አባኖታል አንቀዠቅዦታል
የባህሩ ሞገድ ከድንጋይ ከቋጥኙ ጋር እያንከባለለ ያላትመዋል። የሕዝባዊ ብሶቱ የአደጋ ጥሪም በመረዋ
ድምፁ ተንቆርቁሮ ተዋርደን አንቀርም የሚለው ጩኸቱ ከወያኔው ጀሮ በመድረሱ የሚጨብጠውን
አሳጥቶታል። በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እዲሉ ወያኔው በራሱ ውስጠ ሕይወት የተፈጠረው ታሞ
የማይድን አስተዳደራዊይ ግማቱ ታክሎበት አቀጣጣይ ክብሪቱን ለመለኮስ ተቀጣጣይ ቤንዚሉን
አርከፍክፎ የህዝባዊ ብሶቱን ቦንብ የመፈንዳት ፍጥነት እዲጨምር የበለጠ እየገፋው ነው።
ታዲያ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ዛሬ ብለጣብልጡ ውያኔ ከተፈጠረበት ከፍተኛ እራስ
ምታት በሺታ የሚያድነው መዳሕኔት ባያገኝም ለጊዜውም ቢሆን ሊውጠው ሊሰለቅጠው የተቃረበውን
ሕዝባዊ ማእብል ለመግታት ማስታገሻ ኪኒን ይሆነኛል ያለውን ወያኔ ሰራሺ ኬሚስትሪ ማፈላለጉ
አልቀረም። ዘመድ ከዘመዱ አሕያ ካመዱ ሆነና አቅፈውና ደግፈው በቅጥረኝነት ያሰለፉትን አረቦች
ተመልሶ እጅ መንሳቱ ግድ ስለሆነበት የሜንጫ ፖለቲካ አራማጅ የሆኑ ኤጀንቶችን ከሲያድባሬ አክራሪ
እስላሚስት መኮንኖች ተውሶ ኦረሞ ፈርስት የተባለውን ቋንቋ ካረጁና ተስፋ ከቆረጡ ጥቂት የኦነግ
ሚሺነሪወች በማዳቀል በጀት መድቦ ጮሌ ካድሬወችን ቀጥሮ በሚቆጣጠራቸውና አዳዲስ በፈጠራቸው
ሚዲያወች በመጠቀም በውጭም በውስጥም እያተራመሰ ነው። ፈውስ ባያገኝም በጠና ከታመመበት
የእራስ ምታት በሺታ ለጊዜውም ቢሆን ጊዜ ለመግዛት ማስታገሻ ኪኒን እየወሰደ ነው። ደሮውንም
ወያኔ ሲወጠርና ሲጨነቅ ኮንዶሞቹን እንደደባል እቃ ማውጣትና ማግባት ዛሬ የተከሰተ ባለመሆኑ
ለሐገር ወዳዱ ሕዝባችን አዲስ ነገር አይሆንበትም በወያኔ ላይ ያነሳውን ሕዝባዊ አመፅ የሚያስቆም
አንዳችም ምድራዊ ሐይል የለም። የልቁንም የምስራቁ በረኛ የደጃዝማች ዑመር ሰመተርንና የደጃዝማች
ባልቻ አባ ነፍሶን የነራስ ጉብና ዳጨውንና የነ አፃ ምኔልክን የነ ራስ አበበ አረጋይንና የነ ጀኔራል
ኤጃማ ኬሎን የነ ጀኔራል ታደሰ በሩንና የነ ጀኔራል ደምሴ ቡልቱን የመሳሰሉ ጀግኖቻችን ያቆዩንን
ኢትዮጵያ አገራችን መዳፈር የዘመናት ታሪካችን አለማወቅ ይመስለኛል። ወያኔና ቅጥረኞቹ በአሁኑ
ወቅት እየደረሰባቸው ካለው ሕዝባዊ ማዕበል ለማገገም የቻሉ እየመሰላቸው አቧራው ጨሰ የተሰኘውን
የወያኔ ሰራሺ ሺብረተኛ ፕሮፖጋንዳ አጀነዳ አዲስ ግኝት አስመስለው በማራገብ ሕዝባዊ ጀግኖቻችን
ማዋረድና ማንቓሺ የወያኔውን ግባተ መሬት መቃብሩን ቁፈራ ቢያፋጥነው እንጅ ከቶውንም
ለጣረሞቱ ማስታገሻ ኪኒን ሆኖ አያገለግለውም። በውስጥም በውስጥም የምንኖር ቀለም ቀመስ
ኢትዮጵያውያን ሆይ!! ሕዝባቸህን ብሶቱ ገንፍሎ ወያኔንና ጀሌወቹን ከራሱ ላይ ለማውረድ እየታገለ
መሆኑን እናውቃለን ስለዚህ ሳናመነታ ሞላች ጎደለች ሳንጫወት የወያኔ የጥፋት ፕሮፖጋንዳ ማራገፊያ
ሳንሆን መከራ ተቀባይ የሆነውን ሕሕባችእንና ታሪካዊት ሕገራችን ከሺብርተኛ ቡድኖች ጥፋት
እንከላከል፤ እናድን!!
አገራችን በጎሳ ስም ዳግም ስልጣን ከሚናፍቁ ሺብርተኞችና
ሚሺነሪወች ጥፋት እንጠብቅ !!
መሰረት ቀለመወርቅ
አውሰተራሊያ