አዲሳባ ስልክ ደውዬ ነበር…


577634_559213234123423_137929150_n
አዲሳባ ስልክ ደውዬ ነበር፡፡ “የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም እባክዎ ትንሽ ቆይተው ይሞክሩ” አለችኝ፡፡ ይቺ ሴትዮ ውጤት ተኮር ስራ እንድትሰራ ምናለበት እባክዎ ቆይተው ይሞክሩ ካለች በኋላ ጨመር አድርጋ… “ካልሆነልዎ ደግሞ መልክት ካልዎ ላድርስልዎ እንዴ…” እንድትል ቢያደርጓት… ለማንኛውም እሺ የኔ እመቤት ብዬ ትንሽ ቆይቼ ሞከርኩ፡፡ thenetworkisbusynowpleasediallatter አለችኝ ሌላዋ ደግሞ space በሌለው እንግሊዘኛ፡፡ የዝችኛዋ ደግሞ ንግግሯ በጣም ነው የሚያበሽቀው… የምር ግን ምናለ በየ ቃላቷ መሃል ትንሽ ንትፋሽ እንድትወስድ ቢያደርጓት ብዬ እያሰብኩ እንግዲህ እንዲህ ትንፋሽ የሚያሳጧት ከአንዱ ባለስልጣን ጋር የተቀያየመች ሴትዮ ትሆናለች ስል አስቤ አሳዘነችኝ…

በስንት መከራ ሲሰራልኝ የመጀመሪያው ጥያቄዬ፤ ስልኩ ምን ሆኖ ነው… የሚል ነበር፡፡
ከዛኛው መስመር… ምን ሆነ ቶሎ ሰራልህ እንዴ…
እኔ…. አረ አልሰራ አለኝ!
ከዛኛው መስመር….. ታድያ የኛ ስልክ እኮ ምን ሆነ የሚባለው ሲሰራ ነው እንጂ አለመስራትማ ስራው ነው፡፡

በገና ዋዜማ በርካታ አዲሳቤዎች መብራት ጠፍቶባቸዋል፡፡ ስልክም አብሮ ጠፍቷል፡፡ ዶሮ ጠፍቷል ሳይሆን አጥፍቷል ይሻላል አሉ፡፡ ስጋን እንጃባቱ… ግዜው የስጋት እንጂ የስጋ አይደለም ብለው የሚያሽሟጥጡ መበራከታቸውን ግን ሰምቻለሁ!!! አይሻልህም ግዜው የባዳ ነው እንጂ የስጋ አይደለም….! የሚል ድምፅ ይሰማኛል!

በዚህ ሁሉ መሃል እንኳን ለገና በዓል በሰላም አአደረሳችሁ!

One thought on “አዲሳባ ስልክ ደውዬ ነበር…

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s