Archive | January 7, 2014

ዘመንን ለማሰር (በልጅግ ዓሊ)

Ethiopian Flag

 

ይህን 77 እስሩት በገመድ፣

ወደ 78 እንዳይረማመድ።

ይህች አነስተኛ ስንኝ የሰማኋት እንደ ሃገራቸን አቆጣጠር በ1978 ዓ.ም  ላይ ነበር። መቼም የማይረሳ የለም አሥረኛው የአብዮት በዓልም ተረሳ። ያኔ እነ “ጓድ መንግሥቱ“ ድርቁን ደብቀው አሥረኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ለማክበር ውስኪ በመርከብ ያስገቡበትና የተራጩበት ዘመን ነበር። ያኔ እነ “ብጻይ መለስ“ በድርቁ ስም በተገኘው ገንዘብ ጠብመንጃ የገዙበት ዘመን ነበር። የማይረሳ የለም በዚያ ዘመን በድርቅ ያለቀው ወገናችንም ተረሳ። የሕዝብ ገንዘብ ለውስኪና ለጠብመንጃ ያዋሉት ትንሽ ቆይተው ስልጣን ተቀያየሩ። 1977 ማሰር አቅቶን 1983 ከድጡ ወደ ማጡ አነጎደን።

በደርግ ዘመን የደረሰውን ድርቅ ለመከላከል በሰሜን የሚኖሩትን ዜጎቻችንን(ከሰሜን እየታፈሱ የመጡት ዜጎቻችን በድርቁ ምክንያት ይሁን በሌላ ወደፊት አዋቂዎች ይጽፉት ይሆናል)  ወደ ምዕራብ ማስፈር ተጀምሮ ነበር። ማስፈሩ ሁለት መልክ ነበረው። ሠፈራ የሚባለው ሰው ባልሰፈረበት አካባቢ ወስዶ ማስፈር ሲሆን ስግሰጋ የሚባለው ደግሞ በሕዝብ ቁጥር የሳሱትን ወረዳዎች በሰፋሪዎች መሰግሰግ ነበር። ሠፈራና ስግሰጋ የራሱ የሆነ በሰፊው የሚተረክለት ታሪክ አለው።

ከሰሜን ኢትዮጵያ ለሠፈራና ለስግሰጋ ወደ ኢሉባቡር የመጡ አንድ ሽማግሌ ገበሬ ነበሩ ይህችን ከላይ የሰፈረችውን ስንኝ ለመጀመሪያ ጊዜ  የነገሩኝ። ይህች ስንኝ ሁለት ትርጉም ይዛለች። አንደኛው 1978 ከ 1977 ይብሳልና አይሸጋገር የሚል ሲሆን ሁለተኛው 1977 ያየነው ችግር ወደ 1978 እንዳያልፍ የሚል ነው። ሽማግሌው እንዳስረዱኝ የመጀመሪው ነው ትክክሉ።   ከጊዜ በኋላም አንድ የምቀርበው የወረኢሉ ሰው ስለነ መንግሥቴ ደፋር ፣ ስለነ ብሩኬ ስንጫወት  ይህችን ግጥም አስተወሰኝና ማስታወሻ ላይ ጽፌ ይዣት ቆይቼ ለዛሬው መነሻ ሆነችኝ። (መንግሥቴ ደፋርና ብሩኬ በወረኢሉና ሰሜን ሸዋ ሃገር ያንቀጠቀጡ “ሽፍቶች“ ነበሩ። ቀን ሲሞላ የሚጻፍ ታላቅ ታሪክ አላቸው።)

ድርቅ ከሳይንስ በተቃረነ መልኩ በአገራቸን ሁል ጊዜ ዱብ እዳ ነው የሚሆነው። 1966 የደረሰውም ይሁን 1977 የተደገመው ድርቅ እንደው ሳንሰማው ነው በድንገት ያየነው። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 80ኛ ዓመት በተከበረ ማግሥት ድርቅ “ሳይታሰብ“ መጣ። ደርግም ሕዝብ ሲራብ የንጉሡ ባለሥልጣናት  ኬክ ይበሉ ነበር በማለት ቅስቀሳ አድርጎ ነበር ወደ ስልጣን የመጣው። ደርግ ይባስ ብሎ  የአሥረኛውን አብዮት በዓል እስከሚያልፍ ድርቁን ደብቆ፣ በዓሉ  ባለቀ ማግስት ድርቅ እንደ ዱብ እዳ፤  እንደ ተምች ከሰማይ እንደወደቀ ነገረን። በ1966 ዓ.ም. እንደ ሃገራችን አቆጣጠር የደረሰው ድርቅ  እንደ ወንጀል ተቆጥሮ 60ዎቹን ባለሥልጣናት የገደለው መንግሥቱ በእሱ ዘመን ለተደበቀው ድርቅ ራሱን ሳይገድል መቅረቱ ፍትህ አልባነት ነው ማለት ይቻል ይሆን?

በዛ ዘመን ካለ መንግሥቱ አመራር ምንም ነገር የሚሆን አልነበረምና በዓሉ ካለቀ በኋላ ሁላችንም ስለድርቁ ተነግሮን ዝግጅት እንድናደርግ ታዘዝን። ከግብርና ሚኒስቴር እስከ ታች እስከ ወረዳ ድረስ  ከግብርና ጋር ግንኙነት ያለን በሙሉ ክተቱ ተባልን። የኢሠፓ አባላት መሪዎቻችን ሆነው እኛ የእርሻ ኤክስፐርቶቹ ተመሪ ሆነን ሥራውን ጀመርን። ቀርፋፋዋ ኢሊባቡር ከአዝጋሚነት ወጥታ እንቅስቃሴ በእንቅስቃሴ ሆነች። በየመሥሪያ ቤቱ ያሉ መኪናዎች ከእኛ ተወስደው ለኢሠፓዎቹ መጓጓዣ ሆኑ። እኛ ወደ ሞተር ባይስክልና ወደ ትራክተር ተዘዋወርን።

በዚያ ወቅት ኢሊባቡር ነበርኩና እኔም ለዚህ “ሳይታሰብ በድንገት“ ከሰማይ የመጣብንን እዳ ለመቋቋም በየቦታው መራወጥ ጀመርን።  በጋምቤላ ለሰፋሪዎች ቦታ መዘጋጀት ጀመረ። በሌላ በኩል ደግሞ በሕዝብ ቁጥር የሳሱ የገበሬ ማህበራት ውስጥ ከሰፋሪዎቹ ውስጥ እየተወሰዱ ይሰገሰጉ ጀመር። እኔ ጎሬ አካባቢ በሚገኝ ወረዳ ለሚሰገሰጉት ገበሬዎች ጎጆ ለመስራት ተመደብኩ። ዛሬ ያገኘሁት ትንሽ የየቀኑን ሁኔታ የምዘግብበት ማስታወሻ አንዲት ጎሬ ለምትኖር አንዲት ወይዘሪት የተጻፈ ደብደቤ ላይ የደብዳቤውን ብዙው ዝባዝብኬ ተቀንሶለት እንዲህ የሚል የተጠቀሰ ጉዳይ ይገኝበታል። ።

 

 ውዷ

ጓጆ ቤት መሥራት ቀርቶ ጎጆ ቤት ውስጥ አድሬ አላውቅም። ይህ የምሰራው ጎጆ (ጎጆ ከተባለ) የሚገርም ነው። ከላይ ሳር ጣል ተደርጎ ይከደንና ግንድግዳው በዘንባባ ይሸፈናል። የኛን አዛዥ አላፊ ካድሬዎችን ለመሆኑ ይህ የምንሰራው ቤት ከምን ይከላከላል? ብዬ ጠይቄ ነበር። የተሰጠኝ መልስ ለጊዜው ማረፊያ ካገኙ  ሰፋሪዎቹ ሲመጡ ያሻሽሉታል የሚል ነበር። በድርቅ የተጎዳ ሰው እውን ቤት መስራት ይችል ይሆን? የሚገርም ነው። ለማንኛውም ሥራውን እያጣደፍነው ነው። ስራው አልቆ ጎሬ ለመምጣት ቸኩያለሁ።

ይላል። በዛ ወቅት የነበረውን ጥድፊያ አጉልቶ ነው። ከሁሉ የሚገርመው በትንሽ ቀን ያንን ሁሉ ሕዝብ ማጓጓዝ እንዴት አስከፊ ነበር። በችኮላውና በሕዝብ ብዛቱ ምክንያት ከአንድ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ ቤተሰቦች በምደባ ይለያዩና አንዱ ጎሬ ሌላው ጋምቤላ ይደርሰው ነበር። ማንም ጥንቃቄ የሚያደርግ አልነበረም። ብዙ ቤተሰቦች ሳይገኛኑ ይቀሩ ነበር። ልጆች በረሃብም ይሆን በጉዞው አድካሚነት ይረግፉ ነበር። ይህንን ያልተጠና ሰፈራ የመንግሥቱ መመሪያ ነውና ማንም ባለሥልጣን፣ ማንም የእርሻ ኤክስፐርት ሊቃወም አልሞከረም።

ሰፋሪዎቹ መጥተው በሰራው ቤት ከተመደቡ በኋላ እየተመላለስኩ እጠይቃቸው ነበር። ይህንን ግዜ ነው አንድ ሽማግሌ ስለዚህ አባባል ያጫወቱኝ። አዎ ገበሬዎቹ  ነገሩ ገብቷቸው ኑሮ በ1978 ከ 1977 እንደሚብስ ገምተው ነበር።

የፈረንጆቹ ዓመት ከ2013 ወደ 2014 ሲቀየር የተመኘሁት ይህንን ግጥም ነበር። የሃገራችንን ጉዳይ በጥሞና ሳስበው፣ በየቀኑ እየባሰ የሄደውን የወያኔን ግፍ ስንገምተው፣ የደሃውና የሃብታሙ ልዩነት እየገፋ መምጣቱን ስመለከተው፣ ችግርን በመሸሽ በየበርሃው በየባሕሩ የሚያልቀው ወጣት ዜጎችቻን ቁጥር መጨመርን ሳሰላው፣ በእየእስር ቤቱ የሚማቁትን ዜጎቻችንን ሳስታውሳቸው፣ ለሃያ ዓመት  በነጃዋር፣ በነ ተሰፋዬ ግብረ አብ፣ በእነ ብርሃኑ ዳምጤ መሰሎቹ የተዘራው የዘር ፖለቲካ ስሞኑን የደረሰበትን ደረጃ በጣም ያሳስበኛል።

ሃገራችን አንድነቷን ጠብቃ የመኖሩዋ ሁኔታ ጥርጣሬ ውስጥ ሲገባ፣  ጠንካራ የሆነ ተቃዋሚ ለመፍጠር ያለውን ችግር ስንገመግመው፣  በትግሉ ውስጥ ተስፋ የሚሰጥ ሁኔታ ሳጣበት 2014 ከ 2013፣ የሚብስ መሆኑን ስንረዳው ያኔ እንደ ገበሬዎቹ፡ –

ይህን 13ትን እሰሩት በገመድ

ወደ 14ቱ እንዳይረማመድ ።

ለማለት ተገደድኩ።

የሃገራችንን ሁኔታ ልብ ብለን ስንመከተው ይህ ዘመን ከመቼውን ጊዜ ይበልጥ የሚያስፈራ ሆኖ ይታሰበኛል። በተለይ 2013 መጨረሻ ላይ የተመለከትነው ሁኔታ ስንገመግመው፣ በተለይ እነዚህ በዘር የተለከፉ አጋንቶችን እዚህ ማን አደረሳቸው የሚለውን ስንመለከተው፣ በወያኔ ቀጥሎ ራሳችንን እንድንገመግም ይጠይቀናል። ሞኝ ብቻ ነው ቤቱ ሲቃጠል የሚስቀው። ለሚቃጠለው ቤቱ ቤንዚል የሚያቀብለው። ሞኝ ብቻ ነው ፎቅንና ጥልፍልፍ መንገድን ተመልክቶ እየፈረሰ ያለውን የሃገሩን አንድነት የሚዘነጋው። ሞኝ ብቻ ነው ሃገርን ለሚፈርሱ መድረክ እየሰጠ ሃገሩን የሚያፈርሰው። የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚለው በሃገር አይሰራም።

የዘር ፖለቲካ የደረሰበትን ደረጃ ያልተረዱ ብዙ ናቸው። ክምር ፎቅ፣ ጥልፍፍ መንገድ፣ ዳንኪራ መደለቂያ ቡና ቤት ብቻ ለሃገር አንድነት የሚበቃ የሚመስላቸው የዋሆች እየበዙ ነው።  ዛሬ በድሎት የሚንደላቀቁ ዘመናዮች በየጥጉ በረሃብና በበሽታ የሚልቁት ዜጎቻችንን እንዳያዩ የየክለቡ አብለጭላጭ መብራት ዓይናቸውን ሽብቧቸዋል። በዓለም ታሪክ በቅርብ እንኳን ስንት የሚያምሩ ፎቆች በዘር ክፍፍል እንደፈረሱ የማይረዱ አሉ።ትንሽ ዘርን ተመርኩዛ የምትንሳ ሁኔታ የእርስ በእርስ መተላለቅን  እንደምታስከትል፣ የተከመሩ ፎቆችም ሆነ ፣ጥልፍለፍ መንገዶች በቀናት ሊፈርሱ እንደሚችሉ ያልተረዱ የዋሆች የአንድነት ኃይሎችን እየተዋጉ ጭንብል ላጠለቁ ዘረኞች መድረክ ፣ እውቅና እየሰጡ እንዳሉ ሊረዱት ይገባል።

ከወያኔ ተፋተናል ያሉን ሁሉ መለያየታቸው መልካም ነው። ለምን ከወያኔ እንደተፋቱ አሳማኝ ምክንያት ሳያቀርቡ ሰው እንደጠፋ በየቦታው የፖለቲካ ተንታኝ . . . የኮሚቴ አባል . . .  የመድረክ የክብር እንግዳ፣ . . .  ወዘተ. እያደረጉ መካብ በተሰፋዬ ገብረአብም ይሁን በጃዋር የከሸፈ ነው። ነገም በብርሃኑ ዳምጤ ቢደገም የሚያስደንቅ አይደለም። ከወያኔ ወጥተው ተቃዋሚ ሆንን ሲሉ ወያኔ ውስጥ ሆነው የሠሩትን ጥፋት ለሕዝብ እንኳን ይቅርታ እንዲጠይቁ አይደረግም። ብቻ የሰሞኑን ፖለቲካችንን ይደግፉልን እንጂ በሃገር ላይ የሚያመጡትን ጥፋት አይታየንም።

ለሃገራቸው የሠሩ፣ የሞቱ እየተወገዙ፣ ሃገራቸውን የገደሉ ወደፊትም ሊገድሉ የተዘጋጁ ትላንት የወያኔ አሽከር የነበሩ፣ አሁን ተቃዋሚ ነን የሚሉ  እነ ጃዋር፣ እነ ብርሃኑ ዳምጤ (ደቡር) ጀግና ተብለው እየተዘፈነላቸው ነው። ሲሞቅ ኦ.ፒ. ዲ. ኦ.(OPDO) ሲቀዘቅዝ ተቃዋሚ፣ ትላንት የወያኔን  ቀንደኛ ደጋፊ ሥልጣን ሲከለከል ተቃዋሚ መሆን የዘመኑ የፖለቲካ ገጽታ ነው።

እንደነ ጃዋር አይነት የዘር ፖለቲከኞች አቋም በቀየሩ ቁጥር አብረን ዳንኪራ የምንረግጠው ምን እንባል? አንድ ሰሞን ፓልቶኩም ፣ ራዲዮኑም ጃዋር ፣ ጃዋርና ሲልና የፖለቲካ ተንታኝ የሚል አዲስ ስም ተሰጥቶት በባልና ሚስት ጥል ላይ እንኳን ሳይቀር(እንደ ቀልድ ውሰዷት) ሃሳብ እንዲሰጥ ሲጠየቅ እንዴት ያላገባ ሰው የትዳር ሊቅ ሊባል ይቻላል የሚል ተቃውሞዬን አቅርቤ ነበር። ይኸው ዛሬ ጃዋርን ተቀምጠቀው የሰቀሉ  ካስቀመጡበት ቆመው ማውረድ አቃታቸው። ሕዝብን የሚከፋፍለውን ጥያቄ ይዞ ለኢትዮጵያ የሚመኝላትን የእርስ በእርስ ጦርነቱን ይቀሰቅስ ጀመር። ጃዋር ትንሽ ሲፍቁት ኦፒዲኦ(OPDO)፣ በጣም ከፋቁት ወያኔ(TPLF) መሆኑን አጥተነው ነው። አይመስለኝም ለሰሞነኛ ፖለቲካ ከጠቀመን ስለሃገራቸን ግድ ስለማይኖረን ይመስለኛል።

እነ ጃዋር  እኛን የሞቀው ላይ የምንጣደውን ሲፈለጉ  ደጋፊያቸው አድርገው ያጫጩናል፣ ሲደብራቸው ደግሞ የዘር ፖለቲካቸውን አምጥተው ያምሱናል። ዛሬ ወያኔ ፣ ነገ ተቃዋሚ ፣ ተነገ ወዲያ ደግሞ ተመልሰው ወያኔ እንደፈለጉ መሆን ይችላሉ። በተቃዋሚው መድረክ ላይ ከወያኔ ለተመለሱት ሁሉ እግራቸው ሥር እንድንነጠፍ የሚፈልጉ ብዙ ናቸው።

እድሜ “ለነጻ ሜዲያ ጋዜጠኞች“፣ እድሜ ለኛ በሞቀበት ለምንጣደው፣ ሃገራችንን ሊበትኗት ሲራወጡ አብረን  ልንበትናት እየሮጥን ነው። እንግዲህ ፍላጎታችን ይህ ከሆነ አሁን የምናየው ደስ ሊለን ይገባል።  ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ስንት አንጋፋ አሮሞዎች እያሉ ይህ ስንዝሮ ፖለቲከኛ ጃዋር  ይጋበዛል። ስለ እስልምና ስንት የተማሩ የበሰሉ ሊቀ ሊቃውንቶች እያሉ ጃዋር ሁሉም ቦታ የሃይማኖት ተንታኝ ሆኖ ይቀርባል። ጥፋቱ ጃዋር ጋር አይደለም ጥፋቱ ለሃገራቸን አንድነት እንዋጋለን ብለን ግን ለክፍፍል በምንሰራው ላይ ነው። እነ ጃዋር በኛው መድረክ፣ በኛው ገንዘብ አላማቸውን ሲስፈጽሙ እንደሞኝ የሚቃጠለውን ቤታችንን እያየን እንስቃለን። በነጻ ፕረስ ስም እውቅና እንሰጣለን።

ትላንት የወያኔ ደጋፊ ሆኖ ዛሬ ከወያኔ ተጣላሁ ካለን ምራን ብለን እግሩ ሥር እንነጠፋለን። ይህ ደግሞ ለምዶብናል። 1997 ምርጫ ዋና የወያኔ አቀንቃኝ የነበረውና የነ ሽብሬን መገደል ትክክል ነው ብሎ ሲያቀነቅን የነበረው፣ አሁን  በግል ጥቅም ምክንያት ከወያኔ የተጣላው ብርሃኑ ዳምጤ (ደቡር፣ አባ መላ) ዛሬ በየሃገሩ የክብር እንግዳ፣ በመገናኛ ዘዴው ተንታኝ ከሆነ ሰነበተ። ለአንዲት የሰሙኑ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል ብርሃኑ ደቡርን እላይ የሰቀላችሁት በኋላ እንደለመደው ሲክዳችሁ ስትንጫጩ መስማታችን አይቀርም። ትንቢት እንዳይመስላችሁ ደቡርን በደንብ አድርገን እናቀውቀዋለን። ቆዳችሁን ገፎ ይሸጠዋል፣ ደቡር ሃገሩን አይደለም እናቱንም ቢሆን ይደልላል። አታውቁት እንደሆን መርካቶ ላይ ሄዳችሁ የተሰራውን ግፍ ጠይቁ። እንኳን የቀይ ሽብሩን ፣ እነ ሽብሬን ረስተን የለም እንዴ !!  ምን ይደንቃል።

እድሜ ለኛ ብጻይ ብርሃኑ ዳምጤ ከወያኔ ጋር የምናደርገውን ትግል ይምሩልን ብለን  . . .  ሁሉንም እናስረክበው  . . .  እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ ብርሃኑ ዳምጤ ደቡር ይክደናል። ከዛም አሁን ከሰማይ ሰማየት  የሰቀልነው እንደ ድመት እግሩ ስር እናለቅሳለን። ብርሃኑ ደቡር ቆዳችንን ገፎ ሥጋችንን ለአሞራ ይበትነዋል። በጨረታው አይገደድም ለበለጠው ይሸጠናል። ኢሕአፓ ነው ፣ ግንቦት 7 ነው ፣ መኢአድ ነው . . . እያለ እንደፈለገ ይከፍለናል። ምን እንሆናል ለመሸጥ የተዘጋጀን በጎች አይደለንም እንዴ? በሉ የዘመኑ ፖለቲከኞች ከጃዋር ፣ ከብርሃኑ ዳምጤ ጥፋት መፈለግ ትታችሁ ከነቴዲ አፍሮ ጥፈት ፈልጉ። መቼም፣ የምታሸንፉት አይደለም የምታጠቁ ወያኔን ከመቃወም ቴዲን መስደብ ይሻላል። ጃዋርን ከመቃወም ቴዲን መስደብ ለዝሙት ቱሪስቶች ፣ ለዘመኑ ኢንቨስተሮች ፣ የደደቦች ሸንጎ አባሎች የሚሻል ነው ።

2013 ተቀይሮ 2014 ሲገባ ተስፋ የሚሰጥ ራዕይ ያለው ፖለቲካ እያከተመ እንጂ እያበበ መሆኑ  አይታይም። ጠብ አጫሪ፣ እኔ እኔ በሚል የተቃኘ የግለሰቦች ፍላጎት የሕዝብን ራዕይ ሸፍኖ ጎልቶ ወጥቶ ስንመለከት የዴሞክራሲ ትግል የመጨረሻው ቀን ርቆ ይታየናል። ከነገ ደህና የሚጠብቅ ትንሽ ነው።

ዓመትን ማሰር ቢቻል የምናስራቸው ዓመታት ብዙ ይሆኑ ነበር። ከዛ በፊት ግን ሕዝብ ለክፍፍል የሚጠሩ ምክንያቶችና እነዚህ አጀንዳዎች ለግል ጥቅማቸው ከፍ የሚደርጉ ፖለቲከኞች ከፖለቲካው መድረክ ሊሸበቡ ይገባል። እነ ተስፋዬ ግብረ እባብ፣  እነ ጃዋር ፣  እነ ብርሃኑ ዳምጤ . . .  ነገም ብዙዎች ይመጣሉ። ተቃዋሚ መሆናቸውን መከልከል አይገባም ምሩን ማለት ግን ደደብነት ነው።

ወያኔዎች ሃገራችንን ለማፍረስ የማይጠቀሙበት መንገድ የለም። በማካከላችን አንቀላፊዎች(Sleepers) ያስቀምጡብናል። ቀኑ ሲደርስ ያነቋቸዋል። ሰሞኑን በእነ ጃዋር ያየነው ይህንን ነው።  እነ ጀዋር ሲነቃባቸው ሌሎች ይላካሉ። እኛም ምሩን ብለን እንቀበላቸዋለን። ለወራት ካመሱን በኋላ ያደረሱትን ጉዳት አድርሰው ተልዕኳቸው ተፈጽሟልና  ይሸሸጋሉ። ሌሎች በምትካቸው ይመደቡልናል . . .  እንዲህ እንዲህ እያልን ዓመት እንቆጥራለን . . .። መቼ ይሆን እያየን አለማየታችንን የምንገነዘበው? መቼ ይሆን ከተኛንበት የቁም እንቅልፍ የምንነቃው? መቼ ነው ሰው ነኝ ወይስ በሰው ምስል የቆምኩ “ሰው“ ብለን ራሳችንን የምንመረመረው። ብልህን አንዴ ያሞኙታል፤ ሞኝን ግን ዘንተለት እንዲሉ ነውና ከእንቅልፋችን እንንቃ።

በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት ስለ ሃገራችን አንድነት የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ!

ለንደን  ታህሳስ 2006

ዲታ መንግሰትና ምስኪን ህዝብ

images (1)
(ግርማ ሠይፉ ማሩ)
የ“አባት ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” የሚባል አባባል አለ፡፡ ይህን አባባል ሰረዳው ዘራፊዎችን ማስቆም ካልቻልክ በዘረፋወ በመሳተፍ የድርሻህን ማንሳት ችግር የለውም የሚል እንደምታ እንዳለው ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ይመስለኛል በአብዛኛው የመንግሰት በሚባለው ንብረት ላይ በዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ድርሻቸውን እንደወሰዱ እየተሰማቻው ይህን በማድረጋቸው አንድም ቅሬታ አይታይባቸውም፡፡ ይልቁንም የጀግንነት ሰሜታቸው ሀይሎ ይህን ዘረፋ የሚጠየፉትን እንደ ጅል መቁጠር እየተለመደ መጥቶዋል፡፡ በዘረፋው ላይ ያልተሳተፉም ቢሆኑ ይህ የመንግሰት የሚባለው ንብረት ሲዘረፍ ከመመልከት ዘለው ለምን አይሉም፡፡ አንድ አንዶች ደግሞ በመዝረፍ ባይሳተፉም በማዘረፍ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለመዝረፍም ለማዘረፍም ጥሩ ማሳያ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡
የአዲሰ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሰርቶት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የነበረው ከመሰቀል አደባባይ ቃሊት ያለው መስመር አሰፋልቱ እየፈረሰ ሰፊ ጉድጓድ እየተማሰ አደሲ ቁፋሮ እየተካሄደ ሰመለከት ከባከነው ገንዘብ ይልቅ ያብከነከነኝ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፣ ካልቻሉም እራሳቸው የሚጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሰጡት ማብራሪያ ትውስ ብሎኝ ለምን መዋሸት ያስፈልጋል ብዬ ጉዳዩን ማንሳት ወደድኩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዝረፍ ተሳትፈዋል ለማለት መረጃም ማስረጃም የሌለኝ ቢሆንም ሲዘimages (2)ረፍ ዝም ብሎ በመመልከት እና ሲከፋም ለማዘረፍ ከለላ እየሰጡ መሆናቸው ግን የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ ድረስ ያለው መንገድ አንድ ዓመት እንኳን ሳያገለግል በመንገዱ አሰፋልት መሆን ምክንያት የተማሪዎችን ህይወት መቅጠፍ ሳይበቃው ይህን ሊከላከል ይችላል የተባለ የብረት አጥር ግንባትን ጨምሮ ከፍተኛ ገንዘብ ከንቱ ቀርቶዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዋነኛ ተጠያቂ መሆን ያለበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሲሆን፤ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጉዳዩን፤ የባቡር መስመሩ ድንገት በመምጣቱ ነው የሚል አስተያየት መስጠት ዕቅድ አልባ መንግስት መሆኑን ማሳያ ነው፡፡ ይህ በሚመለከት ሃሳቡን ያጋራኝ በመንገድ ዘርፉ ኃላፊ የሆነ ሰው የነገረኝ ደግሞ፤ በባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ ውስጥ የአዲስ አበባ መንገዶች መስሪያ ቤት ኃላፊ ያሉበት መሆኑን አስተያየታቸውን አሰገራሚ ያደርገዋል ነው ያለኝ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ኃላፊው ባቡር መስመሩ መንገዱን ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ግምት ነበር ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችንም የዚህ ሰበብ አውቀው ይሁን ሳያውቁ ሰለባ የሆኑ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማስተባበያ በሰጡበት ወቅት ባለ ሞያ መሐንዲስ መሆናቸውን ጠቅሰው ከላይ ያለው አሰፋልት ብቻ ስለሚነሳ ከሰር ያለው ሙሊት ስራ ላይ ይውላል በዚህ የተነሳ ብክነቱ ዝቅተኛ ነው ብለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ገልፀው ነበር፡፡ የነበራቸው መረጃ ይህ ከሆነ አሁን እያየን ያለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ሳይሆን እንደ አዲስ ተቆፍሮ ሌላ እየተሞላ ነው፡፡ አሁንም ጉዳዩ ቀላል ነው ሊሉን አይችልም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዋሽተውናል፤ አልዋሸውም የሚሉ ከሆነ ደግሞ በሹሞቻቸው ተታለዋል፡፡ ሰለዚህ የተሳሳተ መረጃ የሰጧቸውን ይጠይቁልን ወይም እራሳቸው ኃላፊነቱን ይውሰዱ፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አሰተያየት የህዝብ ሀብት ብክነት ሲነገራቸው እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ከለላ መስጠታቸው ተባባሪነታቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ አሁንም አሰቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱልን እንጠይቃለን፡፡
በቅርቡ ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት ግንባታ ከተከናወነ በኋላ መፍረሱን አስመልክቶ መስሪያ ቤቱ ኃፊዎች የሰጡት አሰተያየት አሁንም ያስገርማል፡፡ ዲዛይን ለውጥ በመደረጉ የተነሳ ግንባታው መፍረሱን አረጋግጠው፤ እንደዚያም ቢሆን ወጪው የሚመለከተው ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና ድርጅት ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ኮንትራቱ ሰሰጥ ዲዛይንም ግንባታንም የሚጨምር የኮንትራት ዓይነት ስለሆነ ነው ብለውናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ይህ ኮንትራት የተሰጠበት ዋጋ እንደፈለጉ አባክነውም ቢሆን አትራፊ ያደርጋቸዋል የሚል እንደምታ በጆሮዋችን ያቃጭላል፡፡ ድሮም ቢሆን ገንዘብ ይዞ መጥቶ ዲዛይንም ግንባታም ለመስራት የሚገባበት ውል ሰላማዊ እንደማይሆን ልባችን ያውቀዋል፡፡ ለማነኛውም ይህ የባቡር ፕሮጀክት ተጠናቆ ሰራ ሲጀምር ወጪውን በግራም በቀኝ አሰበን በወቅቱ ካለው ዋጋ አንፃር ማየታችን የግድ የሚል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ዋነኛ ዘራፊው የቻይና መንግሰት ሲሆን አዘራፊው ደግሞ የብድር ስምምነት የገባው የፌዴራል መንግሰትና የባቡር ኮርፖሬሽን ነው፡፡ የእነዚህ አካላት ሀለቃ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው፡፡
ከመንገድ ጋር በተያያዘ የማንረሳቸው በባቡር ግንባታ ስም የህዝብን ሃብት ያባከኑት ከሾላ ገበያ፣ በለም ሆቴል ወደ ቀለበት መንገድ ማቋረጫ መንገድ፤ በደሳለኝ ሆቴል ሳርቤት የሚወስዱት መንገዶች አገልግሎት ሳይሰጡ መፍረሳቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሃላፊዎችን እንቅልፍ ይሰጣቸው እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ምን ችግር አለው ለዘመናዊ ባቡር ሲባል ነው ብለው በሚዲያ የሚሰጡት መልስ ውሃ የሚቋጥር አይሆንም፡፡ አሁንም በድፍረት ሚዲያ እየወጡ ይህን መልስ የሚሰጡ ሰዎች ትዝብት ላይ ከመውደቅ ባለፈ ይህ ሰበብ ግብር ከፋዩን ዜጋ እንደማያሳምነው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የሚዲያ ዘማቻ አሁንም አላቆሙም፤ ልብ ማለት ግን የተሳናቸው ይመስለኛል፡፡
በከተማችን በከፍተኛ ወጪ እየተገነቡ ያሉት የትራፊክ መብራቶች ለመፍረስ አንድ ወር ሲቀረው የሚሰሩ መሆናቸው የዚህ መብራት ባለቤት ማን ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል:: የመንገድ ማካፈያዎች፣ አደባባዮች የሚሰሩት በጥቃቅን በተደራጁ ይሁን በኮንትራክተር መፍረሳቸው እየታወቀ የሚገነቡበት ምክንያት ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ የጥላሁን ገሠሠ አደባባይ የሚባለው የተጠናቀቀው እንደሚፈርስ
ግርማ ሠይፉ ማሩ
ታውቆ ሌሎች መንገዶች መፍረስ ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡ ይህን ተግባር ለማከናወን ውል ተገብቶ እንኳን ቢሆን ገንብቶ ከማፍረስ ተደራድሮ
ሀብት እንዳይባክን ማድረጊያ “አስገዳጅ ሆኔታዎች” የሚል የውል አንቀፅ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይህ የኮንትራት አስተዳደር ሀሁ ነው፡፡
በግርግር የሚባክነው ግን ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሀብት መሆኑ ተዘንግቷል፡፡ ህዝብና መንግሰት የተለያዩበት ሀገር የመንግሰት ሀብት
የሚባለውን መዝረፍ ለፅድቅ እንደሚደረግ ተግባር ይወሰዳል፡፡
በነገራችን ላይ በመርዕ ደረጃ የመንግሰት የሚባል ነገር የለም፡፡ መንግሰት ህዝብ በመወከል ለህዝብ የጋራ ጥቅም የሚውል የጋራ የሚባሉ ንብረቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተሰማሚ የሆነው የህገ መንግሰት አንቀፅ 89፡3 “መንግሰት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በህዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሕዝብ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡” ይላል፡፡ በተቃራኒ ደግሞ የሚቆመው አንቀፅ 40፡3 “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው” በማለት መንግሰት እራሱን ከህዝብ የተለየ ሌላ አካል አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ አሁን በተግባር ያለውም የመንግሰት ባለቤትነት እንጂ የህዝብ ባለቤትነት አይደለም፡፡ ለመንግሰት ንብረት ዜጎች የማይቆረቆሩት የመንግሰት የሆነ የእነርሱ ባለመሆኑ ነው፡፡ የእኛ መንግሰት ከህዝብ ይበልጣል፤ ለዜጎች የሚያስፈልገውን እየነፈገ ለራሱ ጡንቻ ማደበሪያ የሚሆነውን ሀብት፣ ንብረት ያፈራል፡፡ በዚህም ህዝብን ይጨቁናል፡፡ ይህም ሆኖ የመንግሰት የሆነ የማንም ስለአልሆነ ቀዳዳ ያገኘ ሁሉ ይዘርፋል ያዘርፋል፡፡
አሁን እዚህም እዚያም የሚባክነው ገንዘብ በእኔ እምነት የህዝብ ንብረት ነው፡፡ መንግሰትም በህዝብ ስም የማስተዳደር ስራ እንዲሰራ የተቀመጠ እንጂ ንብረት እንዲያፈራ የተቀመጠ አካል አይደልም፡፡ የህዝብን ንብረት ሲያስተዳድር የሚያባክን ደግሞ ሃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ ምንም ዓይነት ሰብብ ሳያቀርብ ቦታውን መልቀቅ ይኖርበታል፡፡ እንቢ ካለም ባለቤት የሆነው ህዝብ ማስለቀቅ ይኖርበታል፡፡ ምን ያደርጋል ህዝቡ ይህ የሚሰራው ስራ በገንዘቡ ወይም በስሙ ልጆቹና የልጅ ልጆች በሚከፍሉት ዕዳ መሆኑን እንዲዘነጋ እና መንግሰት በቸርነት የሚሰራው እስኪመስል ድረስ የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ እየሆነ ነው፡፡ የዚህ ፕሮፓጋንዳ ዓላማ አንድና አንድ ነው፡፡ መንግስትን ከተጠያቂነት ማሽሽ፤ ንብረት ሲያባክንም የራሱን ንብረት እንዳባከነ እንዲቆጠር ማድረግ፡፡ ከተቻለም የመንግሰት ንብረት መዝረፍ ነውር እንዳልሆነ ማስጨበጥ ናቸው፡፡
ልብ በሉ የባቡር መስመር፣ የመንገድ. የቴሌ፣ የመብራት መሰረተ ልማቶች የሚገነባልን ዲታ መንግሰት ነው ያለን፡፡ መንግሰት ቸርነቱ የበዛ፣ እንዲሁም ደግ ሲሆን መንግሰት ለህዝቦቹ የሚያስብ አንድ አካል ነው፡፡ ህዝብ ደግሞ እነዚህ ሁሉ የመሰረተ ልማቶች የሚያስፈልጉት ምሰኪን ከመንግሰት እጅ የሚጠብቅ፡፡ የሚገርም ነው!! የገዛ ንዘቡን እና ንብረቱን እንዲያስተዳድር የተቀመጠ አካል አዛዥ ናዛዥ ሲሆን፤ ባለ ገንዘቡ ደግሞ ምስኪን ተመፅዋች የሚኮንበት ጥቂት ሀገሮች ካሉ አንዷ ምስኪኗ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ናቸው፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
January 6, 2014

“አንድነት” የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምፅ ማግኘቱን ገለፀ

JANUARY 7, 2014 

የህዝብ ፊርማ ይዘን በፍ/ቤት ክስ እንመሰርታለን ብሏል
የፀረ-ሽብር አዋጁን በመቃወም “የሚሊዮኖች ድምፅ” በሚል መርሃግብር የህዝብ ፊርማ ሲያሠባስብ የቆየው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል በቂ ድምፅ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ከ1ሚ. በላይ ፊርማ አሰባስቤአለሁ ያለው ፓርቲው፤ የህዝቡን ፊርማ በመያዝ ክስ እንደሚመሰርት ገልጿል፡፡
ፓርቲው ለ3 ወራት ባካሄደው ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ የፀረ ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የሚያስችል ድምጽ ማግኘቱን የገለፁት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ አሁንም ድረስ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኦንላይን እየፈረሙ በመሆኑ አጠቃላይ የፈራሚዎቹን ቁጥር መግለጽ ቢያዳግትም፣ እስካሁን ከ1 ሚሊዮን በላይ ፊርማ መሰባሰቡን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ የተሰባሰበው የፊርማ ብዛት ፓርቲው ከገመተው በላይ ስኬት መቀዳጀቱን ይጠቁማል ያሉት ሃላፊው፤ በአጠቃላይ የተሰበሰበውን የፊርማ ብዛት ፓርቲያቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
“አንድነት” ፓርቲ በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ያለው አቋም ሙሉ ለሙሉ ይሰረዝ የሚል እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዳንኤል፤ የተሰበሰበውን የህዝብ ፊርማ ለፍ/ቤት በማቅረብ፣ ህጉ ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጋጭና የዜጐችን መሠረታዊ መብት እንደሚጥስ በመጥቀስ ክስ እንመሠርታለን ብለዋል። ከፍ/ቤት ቀጥሎም ጉዳዩን ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ የገለፁት ሃላፊው፤ ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም በህዝብ ድምፅ ህግ የማሠረዝ እንቅስቃሴ ተሞክሮ ባያውቅም ፍ/ቤቶች እና  ምክር ቤቱ የፓርቲውንና የፈራሚውን ህዝብ ጥያቄ ተቀብለው ውሳኔ እንደሚሰጡ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጐችን ድምፅ ዝም ብለን ሜዳ ላይ አንጥልም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ የፍ/ቤቶች ገለልተኝነት አጠያያቂ ከመሆኑ አንፃር ጥያቄው ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን ህዝቡ የተሣተፈበት የፓርቲው የትግል አካል ተደርጐ ለታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጣል ብለዋል፡፡
ህጉ ይሠረዝ የሚል አቋማቸው በመንግስት በኩል “ለሽብርተኝነት ድጋፍ ከመስጠት አይለይም” የሚል ትችት ማስከተሉን ያነሳንባቸው አቶ ዳንኤል በሰጡት ምላሽ፤ “የወንጀለኛ ህጉ አልበቃ ብሎ የፀረ-ሽብር ህግ ራሱን ችሎ የሚያስፈልግ ከሆነም ከውጭ የተቀዳ ሣይሆን ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎች የተሣተፉበት እንዲሁም ህብረተሠቡ በየደረጃው ውይይት ያደረገበትና የመላውን ህዝብ ይሁንታ ያገኘ ህግ ማውጣት ይቻላል” ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንፀባርቀዋል፡፡  ፓርቲያቸው በስራ ላይ ያለው የፀረ – ሽብር አዋጅ እንዲሠረዝ ጥብቅ አቋም የያዘበትን ምክንያት ሲያስረዱም፤ “ህጉ ከወጣ በኋላ በቀጥታ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ለማስፈራሪያና ለማጥቂያ በመዋሉ ነው” ብለዋል – ሃላፊው፡፡
የፀረ – ሽብር ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምጽ ማሠባሠብ መቻላችን አገሪቱ አቤቱታ ለማቅረብ ምቹ የዲሞክራሲ ቁመና ላይ መገኘቷን ፈፅሞ አያመለክትም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ፓርቲያቸው የፀረ-ሽብር አዋጁን በተመለከተ ህጋዊ መነሻ ይዞ ለመላ ኢትዮጵያውያን በይፋ የተቃውሞ ጥሪ ያቀረበ ቢሆንም ሠሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው ዘጋቢ ፊልም ላይ “አንድነት ፀረ-ሠላም ለማድረግ መሞከሩ ተገቢ አይደለም” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ በ97 ምርጫ ትልቁ የኢህአዴግ አጀንዳ “ኢንተርሃሞይ” እንደነበር ያስታወሱት ሃላፊው፤ በ2002 ምርጫ “ተቃዋሚዎች አጀንዳ የላቸውም” ወደሚል ቅስቀሣ መቀየሩን ጠቁመው፤ ለቀጣዩ ዓመት ምርጫ ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን “ፀረ-ሠላም ናቸው” የማለት እንቅስቃሴ  ከወዲሁ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ፓርቲው፤ ከዚህ ቀደም ሠላማዊ ሠልፍ እንዳላደርግ እንቅፋት ሆነውብኛል ባላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ፖሊስ ላይ ክሡን ለመመስረት በዝግጅት ላይ እንደሆነ አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለት አዲስ በተመረጡት የፓርቲው ሊቀመንበር በኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ይፋ የሚደረገው የፓርቲው ካቢኔ የመጀመሪያ ስራ፣ የፀረ – ሽብር አዋጁን ማሠረዝ እና ክስ የሚቀርብባቸው አካላት ላይ ክስ መመስረት እንደሚሆን ሃላፊው አክለው ገልፀዋል፡፡

ሕዝባዊ ብሶት – የከተማ አብዮት? – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ሕዝባዊ ብሶት – የከተማ አብዮት? – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ባለፈው ሳምንት ኢህአዴግ በከተሞች ላይ የቋጠረውን ስር የሰደደ ጥላቻ ከነመግፍኤው ጨርፈን ከተመለክተን በኋላ፤ ለዛሬ፣ ታላላቅ ግድፈቶቹ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅኦና በአደባባዩ የሚነሱትን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመዘርዘር፤ እንዲሁም ‹‹ማኦኢዝም›› የሚበይነውን ከገጠር የሚነሳ ብረታዊ ትግል፣ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት አንፃር ለመፈተሽ ቀጠሮ መያዛችን ይታወሳል፡፡ እናም እንዲህ እንቀጥላለን… 

የኢህአዴግ ግድፈቶች

ፈረንጅኛው ‘Achilles Heels’ በሚል ስያሜ የሚገልፃቸው እና አማርኛው ደካማ ጎኖች ብሎ የሚሰይማቸው የስርዓቱ ታላላቅ ግድፈቶች ከዕለት ዕለት ራሳቸውን ማብዛታቸው ፍፃሜው የሚተነበይ አድርገውታል፤ ይኸውም ብሔር ተኮር ጥያቄዎች አለመመለሳቸው፣ ውጤት አልባው የገጠር ፖሊሲ፣ የድህረ-ደርግ የዴሞክራሲ ሽግግሩ መክሸፍ (ከፖለቲካ፣ ከሰብዓዊ እና ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንፃር)፣ የኢኮኖሚ እድገት አለመኖር፣ ድህነት ከቀድሞውም በበረታ መልኩ መስፋፋቱ፣ የትምህርት ፖሊሲው ክስረት፣ የስራ-አጥ ቁጥር አለቅጥ ማሻቀብ፣ የራስ አስተዳደር (Self-adminstration) ሙሉ ለሙሉ አለመተግበር (ከስልጤ እስከ ቁጫ ያሉ የማንነት ጥያቄዎች መቆሚያ ማጣታቸው)፣ የመሬት ፖሊሲው የአርሶ አደሩን የነፍስ ወከፍ የይዘት መጠን ከአንድ ሄክታር ማሳነሱ፣ የከተሞች ስራ-አጥነት በወጣት ከተሜ የተማሩ ልጆች ላይ መብዛቱ፣ በልማታዊ መንግስት ትግበራ እና በብሄር ፌደራሊዝም መሀከል የማይታረቁ ቅራኔዎች መኖራቸው፣ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲመጣ በብሔር ፖለቲካ ሞት ላይ ግለሰባዊነት እንደሚነግስና ኢህአዴግም ይህንን ተቃርኖ ተከትሎ የርዕዮተ-ዓለም መሸጋሸግ ማድረግ የማይችል መሆኑ እና መሰል ተቋማዊ ክስረቶች በቀጣይ ሊያርማቸው የማይቻለው ታላላቅ ግድፈቶች በመሆናቸው እንደተለመደው ውጤቱ ቀድሞ የሚታወቀውን የይስሙላ ምርጫ ከመጠበቅ ይልቅ የአደባባይ ተቃውሞን ለማማተር ሥረ-ምክንያት ሊሆን መቻሉ አጠራጣሪ (አከራካሪ) አይደለም፡፡

ጉዳዩን በሚገባ ለማስረገጥ ከኢህአዴግ አጠቃላይ ህልውናዊ ባህሪ አኳያ ከላይ ከጠቀስኳቸው ነጥቦች ሊፈታቸው የማይቻላቸው ‹ብሎኖች› መሀከል ሶስቱን (ዋነኞቹ ናቸው ከሚል አረዳድ) በጨረፍታ በአዲስ መስመር እንያቸው፡፡

ያ ሁሉ ነጋሪት የተጎሰመለት የድህረ-ደርግ የዲሞክራሲ ሽግግር ‹ተስፋ› ሙሉ በሙሉ ሞት የታወጀበት አሁን በምንጠራው የ97ቱ ምርጫ ማግስት ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ አቶ መለስ ‹ልማታዊ መንግስት› የሚል ሀልዮት ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፤ በወቅቱ (1998 ዓ.ም ይመስለኛል) በማንችስተር ዩንቨርስቲ በመገኘት ቀጣዩ የስርዓቱ ማዋቀሪያ ምሶሶ አድርጎ ሃሳቡን ያብራራው የምርጫ ፖለቲካ፣ የሰብዓዊ መብቶችን እና መሰል ዲሞክራሲያዊ ዕሴቶችን ጨፍልቆ ‹በአብዮታዊ› መንገድ ልማት ማምጣትን ቀዳሚ ግቡ እንደሚያደርገው በመፎከር ጭምር ነበር፤ ይሁንና ፅንሰ-ሃሳቡን በቅርበት ስንመለከተው፣ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አውድ፤ በተለይም ስርዓቱ ካነበረው ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም ጋር በማይታረቁ ቅራኔዎች መሞላቱን ለመረዳት አያዳግትም፡፡

ለዚህ ክርክር ማስረገጫ ይሆን ዘንድም ከተቃርኖዎቹ ውስጥ ሁለት ነጥቦችን ብቻ እናንሳ፤ የመጀመሪያው ልማታዊ መንግስት ‹የዜጎች የክሂል ልቀትን በመንተራስ ብቻ የተሳለጠ ቢሮክራሲን መገንባትና ተቋማዊነትን ማጎልበት ያስፈልጋል› ከሚለው መደምደሚያ አንፃር ነው፤ በርግጥ ይህ ሃሳብ ስኬታማነቱ የታየው በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት ውስጥ ቢሆንም፣ በሙያ ብቻ ስርዓቱ ሲዋቀር ግን የተለየ የቡድን ጥቅሞችን ለማስፈፀም እንደማይመች ተግባራዊ ተሞክሮዎቹ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አኳያም የገዥው ፓርቲ የፌደራሊዝም ቅርፅ በግልባጩ የብሔር ማንነቶችን ተቀዳሚና ብቸኛ ተቋማዊነትን መገንቢያ አማራጭ ማድረጉ ከተጠቀሰው የልማታዊ መንግስት ጭብጥ ጋር በቀጥታ ያላትመዋል፡፡ እናም ከላይ እስከታች ያለው የስልጣን አወቃቀሩ የላቀ ክሂልን ረግጦ የብሔር ተዋፅኦን ለመጠበቅ በማለም ብቻ የተወሰነ ስርዓታዊ መልክ መያዙን ስንመለከት፣ ገዥዎቻችን ሀልዮቱን ለመተግበር ሲንቀሳቀሱ በሁለት ምርጫዎች ቅርቃር ውስጥ እንዲወድቁ መገደዳቸው የማይቀር ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፤ እነርሱም የፌደራሊዝሙን ቅርፅ ወደ መልከአ-ምድራዊ (Geographical) መቀየር፣ አሊያም ‹‹ልማታዊ መንግስት ነን›› የሚለውን አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ አራግፎ መጣል የሚሉ ናቸው፡፡ ይህንን ደግሞ ኢህአዴግ
ከግትረኛነት ባህሪው አንፃር ይቀበለዋል ተብሎ አለመጠበቁ አንዱ ህልውናዊ ግድፈቱ ያደርገዋል፡፡

ሌላው ተጣራሽ ርዕሰ-ጉዳይ በስልጣን ኢ-ማዕከላዊነትና በማዕከላዊ መንግስት መጠናከር መካከል ያለው ነው፤ በሁለት አስርታቱ ስርዓታዊ ሙከራ፣ የበዛው ከወረቀት ላይ ባይዘልም፣ በጥቂቱም ቢሆን ኢ-ማዕከላዊ ለማድረግ ስለመጣሩ የምናውቀው እውነት ነው፡፡ ይሁንና የልማታዊ መንግስት ፅንሰ-ሀሳብ ማዕከላዊ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አጠቃላይ የስልጣን ገፆችን ጠቅልሎ እንዲይዝ ያስገድደዋል፡፡ ይህንንም ስልጣን በማከፋፈል ላይ የሚመሰረት ግጭት ህልውናዊ ድክመቱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡

ሁለተኛው አስረጂ ጭብጥ የብሔር ማንነትን ዘላለማዊ የስርዓት መልክ ማድረጉ፣ ከከተሜነትና የከተሞች መስፋፋት ጋር አብሮ እየገነገነ ከሚመጣው ግለሰብኝነት (የግለሰብ መብትን ማስቀደም) ጋር ሊኖረው የሚችለው ግጭት ነው፡፡ በስነ-ማህበረሰብና ፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተምህሮቶች መሰረት (በዋናነት በምዕራባዊ ሥልጣኔ)፣ የከተሜነት ዕድገት መገለጫ ኢህአዴግ ቀን-ከሌሊት እንደሚለፍፈው የፎቆች መደርደርና የመንገድ መስፋፋት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ከተሜነት ማለት ከጋርዮሽ ማንነት እየተላቀቁ በመምጣት የግል የሆኑ አለማዊ ዕይታዎችን በማጎልበት፣ በመረጡት ማንነትን መተርጎሚያ ፈር ከሚተሳሰሩ ዜጎች ጋር ህብረት መፍጠር የሚለው አንድምታ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም በፆታ፣ በሙያ፣ በኃይማኖት አሊያም በተመረጠ ርዕዮተ-ዓለም ስር ምክንያተኝነትን ብቻ በመንተራስ ‹መደራጀት› የከተሜነት ቀዳሚ መለዮ ነውና፡፡ ይህንን ድምዳሜ በተለይም በአዲስ አበቤዎች ዘንድ እየመጣ ካለው የከተሜነት ባህሪ እና ከብሔር ፖለቲካው ጋር ስናስተያየው ‹‹የማይታረቀው ቅራኔ›› (በካርል ማርክስ አባባል) እነበረከት ስምዖን ፊት ይቆማል፡፡ ኢህአዴግ ይህ ተፈጥሮአዊ የማህበረሰብ ዕድገት እንኳ እንደሚገታው አለማሰቡ ከህልውናዊ ግድፈቶቹ አንዱ አድርገን ልንቆጥረው እንገደዳለን፡፡

ርዕሰ-ጉዳያችንን ለመጠቅለል የምጠቅሰው የመጨረሻው ማሳያ፣ ስርዓቱ የተነሳበትን የራስ ዕድል በራስ በመወሰን መብት ላይ ትገበራው የሚያሳየውን ሀሳዊነት ነው፤ ወታደራዊው ደርግ ይከተለው የነበረው ‹አሀዳዊ አስተዳደር›፣ ቋንቋን መሰረት ባደረገው ፌዴራሊዝም ከተተካ በኋላ ስለ ጉዳዩ ያጠኑ ምሁራኖች ‹‹የስልጤ ሞዴል›› እያሉ የሚጠሩትን ይህንን ጭብጥ፣ ግንባሩ እየመረጠ መስጠቱን የሚዘክሩ በዜጎች ደም የተፃፉ የዳጎሱ ታሪኮች ያረጋግጡልናል፡፡ እንደ ምሳሌም የሲዳማንና ሰሞኑን እየታዘብን ያለውን የቁጫን የማንነት ጥያቄዎች ብቻ መጥቀስ በቂ ይመስለኛል፤ ሲዳማ በሀገሪቱ ሕገ-መንግስት መሰረት ክልል ለመሆን የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ሁሉ ቢያሟላም የተሰጠው ምላሽ ለዓመታት ሞትና እስርን በጥያቄው አራማጆች ላይ እንደ ሐምሌ ዝናብ መዘርገፍ ሲሆን፣ ከሲዳማ ቁጥር በታች ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ በክልል ደረጃ የመዋቀር መብታቸው ሲከበር ተመልክተናል፡፡ ይህንንም የተዛነፈ የመብት ትግበራን በመሰረታዊ የስርዓቱ ክሽፈትነት ልንቆጥረው እንደምንችል ይሰማኛል፡፡ የተቃውሞ መድረኩን ከውስጥም ከውጭም የሞሉት ኃይሎች ዋነኛ ጥያቄም፣ የብሔራችን መብት አልተከበረም የሚለው መሆኑ (በመጠኑ ላይ ባንስማማም፣ ቡድኖቹ ከየብሔራቸው ደጋፊ እንዳላቸው አይካድምና) ስርዓታዊ ሽንፈቱን ያበዛዋል፡፡ በአናቱም በስልጤው ሞዴል ግፊት ወደ አደባባይ የመጡት የወለኔና የቁጫ የማንነት ጥያቄዎች የሚጠቁሙት አንዳች ነገር ቢኖር፣ የስርዓቱ ቁንጮዎች የተጠቀሰውን ስታሊኒስታዊ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን ጉዳይ በሕገ-መንግስታቸው ውስጥ ሲከቱት፣ ኢትዮጵያን በመሰለ ባለብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች ሀገር ጥያቄው ማቆሚያ እንደማይኖረው አለማሰባቸውን ነው፡፡

በእነዚህ የኢህአዴግ ታላለቅ ግድፈቶች ህላዊነት ከተስማማን የለውጥ መንገዱንም አንስቶ መነጋገሩ የግድ አስፈላጊ ነውና ወደዚያው እንለፍ፡፡

የከተማ አብዮት ሲባል…

በዚህ ተጠይቅ የምናየው አማራጭ የለውጥ መንገድ ያለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የሚበይነውን ሰላማዊ የከተማ አብዮት ብቻ ሳይሆን፣ ረዥም ዓመታትን ወደ ኋላ ተጉዘን በአማራጭነት ይተገበሩ የነበሩትንም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያችን ዛሬም ከተቃውሞ ስብስቡ መካከል ሁለቱንም ስልት የሚያቀነቅኑ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸው እውነት ነውና፡፡

ምንም እንኳ ጥያቄያቸው፣ አመሰራረታቸው እና የሚከተሉት ርዕዮተ-ዓለም ፍፁም የተለያየ ቢሆንም፣ ከኦነግ እስከ ኦብነግ፤ ከአርበኞች ግንባር እስከ ግንቦት ሰባት (ሁሉን አቀፍ የሚሉት ስልት እንደተጠበቀ ሆኖ) ድረስ የሚጠቀሱ ድርጅቶች ከከተማ አብዮት የ‹ማኦኢዝም›ን (ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ጦርነት ላይ የሚያተኩር) የትግል ስልት እንደ ብቸኛ አማራጭ መውሰዳቸው የታወቀ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ተቃውሞ መነሾ የሆነው ራሱ ኢህአዴግም ወደ ስልጣን የመጣበት መንገድ ሳይቀነስ ሳይጨመር ይኸው እንደነበረም አይዘነጋም፡፡

በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ መቀንቀን ከተጀመረበት 1960ዎቹ አጋማሽ አንስቶ የተመሰረቱ ግራ ዘመም ድርጅቶች በሙሉ ‹‹መንፈሳዊ አባት›› አድርገው የሚወስዱት የማኦ ዚዱንግ (Mao Zedong) የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ (CCP) ለጥቂት ዓመታትም ቢሆን አራምዶት የነበረው የትግል ስልት ከከተማ ወደ ገጠር የሚነሳ እንደነበረ ይታወሳል፤ ይሁንና ሲሲፒ እ.ኤ.አ. በ1927 ዓ.ም. የፀደይ ወራት በሻንጋይ ሼክ (Chiang Kai-shek) ከሚመራው ‹‹Kuomintang›› (KMT)፣ የደረሰበትን ከባድ ወታደራዊ ጡጫ መቋቋም ተስኖት ከጠንካራ መሰረቶቹ ሻንጋይ እና ክንቶን (ዛሬ ስሟ ‹ጉዋንዡ› /Guangzhou/ በሚል ተቀይሯል) ከተሞች ወደ ገጠር ማፈግፈጉን ድርሳናቱ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በኋላም የእነ ማኦ ድርጅት ‹የሠራተኛ መደብ› የሚል አጀንዳውን አርቆ ሰቅሎ፣ እንደ አዲስ በገበሬ ሰራዊት በመዋቀር የትጥቅ ትግልን ከገጠር የመጀመር ጠቀሜታ ሰባኪ ብሎም የገበሬ አምባገንነት አቀንቃኝ ሆኖ ብቅ ማለቱን ከታሪክ ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ ሲሲፒ የስልት ለውጥ ከማድረጉ በፊት ከ11 ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍነውን ‹‹ረጅሙ-ጉዞ››ን (Long march) በፅናት መጨረሱ የዓላማ ፅናቱን ያሳያል፡፡

እነ ማኦ ለመስማት ከሚዘገንነው መስዋዕትነት በኋላ ለሥልጣን የበቁት ድርጅታቸው በተመሰረተ በሃያ ስምንተኛ አመት (እ.ኤ.አ. በ1949 ዓ.ም) ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የሚኖሩ ሕዝቦች ‹ጭቆናን ለማስወገድ› በሚል ‹ግራ ዘመም› ድርጅት መስርተው በእምቢተኝነት ሲያምፁ፣ ማኦኢዝም የትግል ስልት የሚበይነውን በገበሬዎች በተደራጀ ሰራዊት ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ሽምቅ ውጊያን እንደሁነኛ አማራጭ መከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በአናቱም የማኦ አስተምህሮ ‹በገበሬ አብዮት› የሚመሰረትን የ‹እርሻ መር ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian society) መፍጠርን እና የከተሞችን ፖለቲካል ኢኮኖሚ በማፈራረስ የገበሬውን ሁለንተናዊ ከፍታ ማረጋገጥ ላይ ማተኮሩ በዚህ መንገድ ወደ ሥልጣን የወጡ ገዥዎቻችንን ባህሪ ለመዳኘት ይረዳናል፡፡

እነሆም በዚህ ትውልድ መቀመጫቸውን በሀገራችን የጠረፍ ከተሞች አሊያም በአውሮፓና አሜሪካ ያደረጉ ብረት ያነሱ ድርጅቶች ከላይ በተጠቀሰው የታሪክ ንባብ ከተመዘኑ፣ አንድም የመረጡት የትግል ስልት ዘመኑን የሚዋጅ ነው ብሎ ለመቀበል ያዳግታል፤ ሁለትም በለስ ቀንቷቸው ያሰቡት መሳካት ቢችል እንኳ፣ በእንዲህ አይነት መልኩ ባንክ ዘርፈው፣ መሰረተ ልማቶችን አውድመው፣ ንፁህን ዜጎችን ለህልፈት ዳርገው፣ የቅርብ ጓደኞቻቸውን ሰውተውና ጠብ-መንጃ ተሸክመው ወደ ቤተ-መንግስት የሚመጡበት መንገድ፣ ከዓመታት በፊት መለስና ጓዶቹ ‹ታግለናል፣ ሞተናል፣ ደምተናል… እናም ምርጥ ምርጡ ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ብቻ› በሚል ድምዳሜ ካዘጋጁት ‹መፅሀፍ› አንድ ገፅ ገንጥለው ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም እኛ…›› ወደሚል የአምባገነኖች ጠርዝ መገፋታቸው አይቀሬ ይመስለኛል፡፡

በተጨማሪም ‹‹ጨቋኝ ጨቋኝን ሊተካው ይችላል›› እንዲል አርስቶትል ኢህአዴግ ለአስራ ሰባት ዓመታት በዱር-በገደል ወጥቶና ወርዶ፣ አስከፊ መስዋዕትነትን ከፍሎ፣ አራት ኪሎ ከደረሰ በኋላ፣ ያነበረው ስርዓት ካመፀበት የመንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ጋር ያለው ልዩነት የስም ብቻ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህ ሁኔታም ነው በብረት የታጠረ፣ ደም አፋሳሽና የተናጥል አሸናፊነትን በሚያውጅ ስብከት ላይ ብቻ የተገነባው የትግል ትርጓሜ ዛሬም እንደአዲስ የመከለሱ ዜና በስጋት ያነጠበን፡፡ በርግጥም የጭቆናን ሸክም ከትከሻ ለማውረድ ሲባል የተካሄዱ መራራ ትግሎች ውጤታቸው ጨቋኞችን መቀያየር መሆኑና የትንቅንቁ ወራቶች መርዘም ያስከተሉት ኪሳራዎች ከዘመኔ ቀድሞ የነበረውን የማኦን መንገድ የታሪክ መዛግብት ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር በመገደብ ለአማራጭነት እንኳ እንዳይበቃ አድርገውታል፡፡ የዚያን ዘመን የጨቋኞች አገዛዝ ውርስን ለመከተል ወቅቱ አመቺ አለመሆኑንና የሥልጣን ወንበርን ለጊዜውም ለማሰንበት ዘመን-ወለዱን አመቻማች አምባገነንትን መጠመቅ ማስፈለጉም የትግሉ ስያሜ በድጋሚ ለብይን እንዲቀርብ ተጨማሪ ኃይል ሆኗል፡፡ ርዕዮተ-ዓለማዊ ልዩነቶች እስኪዘነጉ ድረስ መጥበባቸው፣ ክስተቶች ከአንድ ሀገር ድንበር መዝለላቸው እንዲሁም ወቅታዊዎቹ የለውጥ ስኬቶች በጋራ የቀድሞውን የአብዮት መስመር በጥርጣሬ እንድንመለከተው ፈርደውበታል፡፡ ዛሬ ላይ አብዮት ቃሉ ብቻ እስኪቀር ድረስ ተነቅሎ ነባር የመዳረሻ መንገዶቹ ፈራርሰዋል፤ በፍርስራሹ ላይም አዲስ ትርጓሜ ተቸክችኮበታል፡፡

እነዚህና መሰል ሁነቶች የለውጡን መንገድ ለመቃረም ፊታችንን ወደ አውሮፓውያኖቹ የ‹ብርቱካናማ› እና የ‹ፅጌረዳ› አሊያም ወደ አረቡ የ‹ፀደይ› አብዮት እንመልስ ዘንድ ያስገድዱናል፡፡ ይህ ግን እነ ሌኒን ያራምዱትና ይመክሩት ከነበረው በከተሞች ውስጥ ከሚደረገው የትጥቅ ትግል ፍፁም የተለይ ይመስለኛል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አማራጭ በ1966ቱ አብዮት ማግስት በራሳችን ሰዎች ተሞክሮ ከመክሸፉም በላይ ሀገሪቱን ወደ ቀለም ሽብር ከቷት መቼም ሊተካ የማይችል ዋጋ ማስከፈሉ ሁሌም በቁጭት የምናስበው ታሪካችን ነው፡፡ እናም ለእኔ ትውልድ የለውጥ ጥያቄ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት ውጪ ያሉ አማራጮች ከጠቀሜታቸው ይልቅ ጥፋታቸው አመዝኖ ነው የሚታየኝ፡፡ በተለይም ነባሩን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል (የ‹ጦር አርበኝነት›ን በ‹ሲቪል ጀግንነት›) ለመቀየርም ሆነ፣ ከእርስ በርስ እልቂት፣ ከደም መፋሰስ፣ ከደካማው ኢኮኖሚ መንኮታኮት፣ ካለመረጋጋት… ለመታደግ ብቸኛ መፍትሄ ይኸው ነው፡፡ በተጨማሪም ከከተማ መነሳቱ ለአገዛዙ ምሰሶ፤ ለሀገሪቱ ደግሞ ስጋት የሆኑትን የሃይማኖት እና ብሔር (ቋንቋ) ልዩነቶችን ተሻግሮ፣ በአንድ ሀገር በእኩል ማንነት ላይ የሚያሰባስብ ኃይል ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ፡፡

በነገራችን ላይ ለእንዲህ አይነቱ አደገኛ ስጋት መቃረባችንን የሚያሳየው በይበልጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተቃውሞ ስብስቡ አካባቢ የሚሰማው ከሀገር ይልቅ የትውልድ መንደርን የማስቀደም ድምፅ ነው፡፡ ይሁንና ይህ መንገድ የትም ሊያደርስ ካለመቻሉም በላይ ላለፉት ሃያ ዓመታት የጭቆና ቀንበርን ትከሻችን ላይ እንዲከርር አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ እናም ወደ ተናፋቂው የነፃነት ምኩራብ ሊያደርሰን የሚችለው ድምዳሜ ስርዓቱ ትግራይን ከኦሮሚያ፣ ወይም ከአማራ… የበላይ አድርጎ ያስተዳድራል ለሚሉ ከፋፋይ አሉባልታዎች ጆሮ መንፈግ ብቻ ነው፤ የአንዳንድ ብሔር ተኮር ድርጅት አፈ-ቀላጤዎችም ንጉሳዊውን ዘመን የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወኪል ለማስመሰል መሞከራቸውም ሆነ ህወሓት የተሰኘው የማፍያ ቡድን የሚፈፅመውን ግፋአዊ አገዛዝ በየትኛውም መስፈርት ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉትን ጥረት ማክሸፉ ከአብዮቱ ቅድመ ዝግጅቶች አንዱ ይመስለኛል፡፡

የሆነው ሆኖ ‹አብዮት የራት ግብዣ አይደለም› እንዲል ማኦ፣ አሁን እየተናገርንለት ያለው ሰላማዊው የከተማ ተቃውሞ የጠብ-መንጃውን ያህል ባይሆንም እንኳ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ በየትኛውም ሀገር ያሉ አምባገነን ገዥዎች በሕዝባዊ እምቢተኝነት አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎቻቸውን ወደ ቤተ-መንግስታቸው እንዲገቡ ሲፈቅዱ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡

እንዲያውም በግልባጩ በጦር ሠራዊትና በደህንነት ኃይል ለማስፈራራት ሲሞክሩ፣ ከተቃዋሚዎቻቸው የተወሰኑትን በመቀጣጫነት በጥይት ሲያስደበድቡ፣ አስተባባሪዎቹን ሲያስሩ፣ የአገዛዛቸውን የብረት መዳፍ ይበልጥ ሲያጠነክሩ… ይስተዋላሉ፡፡ ይሁንና ይህ አይነቱ የጭካኔ እርምጃ አምባገነኖችን ከአብዮቱ ወላፈን ሊታደጋቸው አለመቻሉን ማረጋገጥ ካስፈለገ ቱኒዝያ ጥሩ ማሳያ ትመስለኛለች፡፡ አደባባዩን ከማማተር አስቀድሞ ግን አብዮቱ መያዝ ስለሚገባው ባህርያት ጥቂት ነጥቦችን ማንሳት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡

የለውጡ መስመር አንዱ መለዮ መሆን የሚኖርበት የትኞቹንም ጨቋኝ ህጎችን በአደባባይ መጣስ ነው፤ እዚህ ቦታ ለመሰለፍ ጠይቀን ተከለከልን፤ ደጋፊዎቻችንን እንዳንሰበስብ አዳራሽ አጣን… እና መሰል ቀልዶችን በመተው አዋጆቹን (እንደ ፀረ-ሽብር እና የፕሬስ አዋጅ ውስጥ ያደፈጡ ቀፍዳጅ አንቀፆችን) በግላጭ በመጣስ በገፍ ወደዘብጥያ ለመውረድ መወሰን የአብዮቱ ዋና አካሄድ መሆን የሚኖርበት ይመስለኛል (በዚህ አውድ አንድ የቢሆን ምሳሌ እናንሳ፤ አሁን ካሉት ህጋዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ በአንድ ክፉ ቀን የፓርቲው የህጋዊነት ማረጋገጫ በሎሌው የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ቢሰረዝና እኛም አማራጭ አካሄዶችን ስለማሰላሰላቸው ብንጠይቅ፣ ‹‹ጨዋታው ፈረሰ…›› ብለው ወደየቤታቸው ገብተው ይቀመጡ ይሆናል ከሚለው ውጪ የምናገኘው ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል?)

ሌላኛው ነጥብ ቡድናዊ መሰባሰቢያ መስፈርቶችን ይመለከታል፤ በአረቡ ፀደይ እንዳስተዋልነው (ስለአረቡ ዓለም አብዮት ባህሪያት ከፍትህ ጋዜጣ እስከ ፋክት መፅሄት ድረስ በተደጋጋሚ ሊብራራ ተሞክሯልና እዚህ መድገም አያስፈልግም) የፆታን፣ የኃይማኖትን፣ የመደብን፣ የአንድ ርዕዮተ-ዓለምን አሊያም የብሄር ልዩነቶችን በመሻገር ሁለንተናዊ የዜግነት ነፃነቶችን መሻትን ብቻ ማዕከል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁለንተናዊ የዜግነት ነፃነቶች ሲባል ደግሞ የኃይማኖት፣ የፖለቲካና የሲቪል መብቶች መከበር ማለት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የትኞቹንም የቡድንም ሆነ ግለሰብ ተኮር ጥያቄዎች ይህንን ነፃነት በማስከበር ትግል ውስጥ ማስመለስ እንደሚቻል መታወቁ የአብዮቱን መሪ ቡድኖች መልከዓ-ባህሪ በዜግነት ላይ ብቻ እንዲቆም ያደርገዋል፤ ይህ ክንውንም፣ በአንድ በኩል የስርዓቱን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሲያከሽፍ፣ በሌላ በኩል የተሻለች ሀገር ለማቆም የማይነቃነቅ ጠንካራ መሰረት ይጥላል (በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ፋክትን ጨምሮ በአራቱም የህትመት ውጤቶች ያነሳኋቸው የፈራ ይመለስ፣ ሞት የማይፈሩ ወጣቶች፣ ለምን ትፈራለህ? የታህሪር ናፍቆት፣ የዘገየው አብዮት፣ የግፉአን ዕድሜ ምን ያህል ይረዝማል? አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል? የመሳሰሉት ቀዳሚ ድምፆች በዚህ አይነቱ ሰላማዊ የከተማ
አብዮት የሚበየኑ መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል)

የአብዮቱ ግቦች…

በጥቅሉ እዚህ ድረስ ስንነጋገርበት የነበረው የከተማ አብዮት እንደ ሊቢያ ወይም ሶርያ ለእርስ በእርስ እልቂት የሚዳርግ ደም አፋሳሽ አለመሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በዚህ አውድ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው አንኳር ጉዳይ የአረቡን መነቃቃት ተከትሎ በሞሮኮ፣ የመን እና ኳታር እንደታየው አይነት፣ ከስር ነቀል ለውጥ ይልቅ የፖለቲካ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የአምባገነኑን አገዛዝ እጅ መጠምዘዙ ላይ ነው፤ ይህ ይሆን ዘንድም የሚከተሉት ጥያቄዎች ወደ አደባባይ መሰባሰብ የሚያስችሉን የጋራ አጀንዳ (የአብዮቱ ግቦች) ቢሆኑ ለስርዓቱ ‹‹የወንድ በር››፤ ለምንወዳት ሀገራችን ደግሞ የተስፋውን መንገድ ጠራጊ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡

ከፊታችን ያለው የ2007ቱ አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ከመደረጉ በፊት፣ ያን ጊዜ የ97ቱ ቅንጅት ፓርላማ ለመግባት በቅድመ ሁኔታነት አንስቷቸው የነበሩትን ከፊል ጥያቄዎች ጨምሮ ሌሎችም በዚህ ፅሁፍ የተካተቱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣቸው ዘንድ ከሥራ ማቆማ አድም አንስቶ ከአገዛዙ ጋር አለመተባበርን የሚያካትትና ለውጡ እስኪመጣ በተከታታይ (በብሔር አግላይ ያልሆነ) መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ራስን ማዘጋጀት ይጠይቃል፤ ጥያቄዎቹም የሚከተሉት ናቸው፡-

1/ ሁሉንም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር መፍታት፤
2/ እስከ ዛሬ ድረስ በሀገር ጥቅም ላይ ለተፈፀመው ጥፋትም ሆነ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስር፣ እንግልት፣ አካል መጉደል እና ስደት ኃላፊነት ወስዶ በአደባባይ ይቅርታ መጠየቅ (ካሳ የሚገባቸውን መካስ)፣ ለብሔራዊ ዕርቅ መደላድል መፍጠር፤
3/ አፋኝ የሆኑትን የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስ፣ የመያዶች እና የፖለቲካ ማሻሻያ አዋጆችን መሻር፤
4/ ዜጎች በሚያምኑበት የፖለቲካ አስተሳሰብ የመደራጀት መብታቸውን ያለአንዳች ገደብ መልቀቅ፤
5/ ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በእኩል ደረጃ መወያየትና መደራደር፤
6/ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ነፃና ገለልተኛ መሆኑን በሚያረጋግጥ ሁኔታ እንደገና ማቋቋምና የአቅም ብቃቱን መገንባት፤
7/ ፍትሐዊ የመንግስት ሚዲያ አጠቃቀም እንዲኖርና የግል የኤሌክትሮኒክስም ሆነ የህትመት ሚዲያዎች ያለ ከልካይ እንዲኖሩ መፍቀድ፤
8/ የፍ/ቤትን እና የሌሎች የፍትህ አካላትን ነፃነት ማረጋገጥ፤
9/ የፖሊስ፣ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ከፖለቲካ ገለልተኛ እንዲሆኑ ማድረግ፤
10/ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ተፈፃሚ የሚያደርግ ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት የማይወግን ነፃ የሆነ አካል ማቋቋም የሚሉት

ጥያቄዎች የመንደርደሪያ ነጥብ መሆን የሚችሉ ይመስለኛል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ኮካኮላ የቴዲ አፍሮ ውል እንዲሰርዝ ዘመቻ ተጀመረ (ከክንፉ አሰፋ) ጋዜጠኛ

images

 
በ 2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ ቴዲ አፍሮ የክብር እንግዳ እንዳይሆን አዲስ ዘመቻ በእነ ጃዋር መሃመድ መጀመሩ ተሰማ።

 በዓለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተረባረቡ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፤  ጃዋር እና ሜንጫዎቹ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ዘመቻቸውን በስፋት ተያይዘውታል።  በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ በደረሰን ዜና መሰረት ኮካኮላ የቴዲ አፍሮን የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ስፖንሰርነት እንዲያነሳ ጠይቀዋል።  አዲስ አድማ ለመጀመርም ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። በ 2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም እግር ኳስ ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ እንዲገኝ ኮካኮላ ቴዲን የመረጠው መሆኑ ይታወሳል። የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ወጣቱ ቴዲ አፍሮ አፍሪካን እንዲወክል መምረጡ ዘረኞቹን አስቆጥቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ቴዲ አፍሮ በአለም መድረክ ላይ የሚያቀርበው ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ቃና ሀገራችንን እና መላው አፍሪካን የሚያስጠራ ነው።   የሄነከኑ አድማ በኦህዴድ ብርቱ ጥረት የተሳካላቸው እነኚህ ባለ አድማዎች፣ ሰሞኑን የደስታ መግለጫቸውን በየድረ-ገጾቻቸው ላይ  እየተለዋወጡ እንደሆነ ተገልጿል። ሄኒከን ኮንሰርቱን የሰረዘው ከኦህዴድበተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ስለመሆኑ ማስረጃው አሉ።

እነ ጃዋር በዚህ አላበቁም። በዲሴምበር 8፤ 2013 በተላለፈ የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ እና ሌሎች ምሁራን ቃለ-ምልልስ ምክንያት የጀርመኑ (ዶቸ ቨለ) የአማርኛ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ከስራ እንዲነሳም ከአቤቱታ ጋር ቀጭን ትእዛዝ ለቦርዱ አስተላልፎ ነበር።  የዶቸ ቨለ ቦርድ ላይ ኦህዴድ ተጽእኖ ስለሌለው ይህ ዘማቻ ሊሳካ አልቻለም።

የኮካኮላው ዘመቻ የተነጣጠረው በቴዲ አፍሮ ላይ ሳይሆን በአኢትዮጵያዊነት ላይ ስለሆነ በአለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዝምታውን በመስበር በነዚህ ሰዎች ላይ የሶሻል ሚድያ ዘመቻ መክፈት ይገባቸዋል።