ይህን አንብባችሁ ዝም አትበሉ ይህን መልዕክት ለሌላው በማስተላለፍ ተባበሩ:: !


 Image

3ኛ ወንጀል ችሎት በእኔ ላይ ፍርድ ሲሰጥ የተሰማኝን ሃዘንና ባዶነት የትኛውም ኢትዮጵያዊ ድጋሚ እንዲሰማው አልሻም ::በፈጣሪ እርዳታ ከእድሜም ልክ በላይ ምት ቢፈርዱብኝም ለምቀበል ተዘጋጅቼ ነበር :: ይሁንና ይኼን ያህል የሚያስፈርድ ወንጅል ቀርቶ አንድ ምሽት ወህኒ የሚያሳድር ወንጀል ባለመስራቴ ህሊናዬ ፍፁም እረፍት ይስማዋል ::እንዲህ አይነት ” የፍትህ ስርዓት ” ያለባት ሃገር ልጅ መሆኔ ግን የሃፍረት ማቅ አከናንቦኛል:: ዳኞቹ አሳዘኑኝም ፤ አሳፈርኝም::

ያም ሆነ ይህ እኔና እኔን መሰል ስዎች ያልሆነውን ሆናችሁ ተብለን የምንገፍው የመከራ ህይወት በኢትዮጵያችን የነፃነት ቀን እንዲጠባ የሚረዳ ክሆነ ፤ የሚከፈለው መስዋዕትነት ቢያንስ እንጂ ፈጽሞ አይበዛም:: በትውልድና በታሪክ ፊት ለከበረ ነፃነት ሲባል ዋጋ መክፈል ተመርቆ መፈጠር እንጂ ከቶም አለመታደል አይሆንም:: የልጆቻችንና የሚስቶቻችንም ስብራት ሁላችንም የምንኮራባት ሀገር ስትኖረን ያን ግዜ ይጠግን ይሆናል ::

ዛሬ ግን በዚች ሀገር የፍትህ ስርዓት አለን ብለን መናገር ፈጽሞ የማንችልበት ደረጃ ላይ እንገኛለን :: እንደዚህ ዘመን ፍትህ መሬት ላይ ተጥሎ የተዘበተበት ዘመን ይኖር ይሆን ? ፍርድ ቤቶቻችን የፍትህ መባ የሚፈታባቸው ምኩራቦች እስኪሆኑ ድረስ አበክረን ልንታገል ይገባል:: ይኽንን የነፃነት ብርሃን የሚናፍቅ ህዝብ በልበ ሙሉነትም የሚታገል ትውልድ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል:: ለመታግል ገዠዎችን መፍራት አያስፈልግም:: በተላይ ወጣቱ ለነገዋ ሀገሩ ዛሬ በእውነትና በልበ ሙሉነት ይቁምላት :: የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ከልብ የማይሰራ የኢህአዴግ አመራር ከፕለቲካ ሜዳው በአስቸኳይ ሊወጣ ይገባዋል፤ በተቃዋሚ ጎራውም ይኽን መሰል አስተሳሰብ ያለው ወገን ካለ መንገዱን ይልቀቅ:: ከዚህ በላይ ኢ-ፍትሐዊነትንና ኢ-ሰብአዊነትን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያሰፈኑ ሊቀጥሉ አይችሉም፤ ለፍትህ ለወንድማማችነትና ለነፃነት መንገዱን መልቀቅ አለባቸው:: በእኔ እይታ ሁሉንም የድርድር በሮች ዘግቶ የምላችሁን ብቻ ተቀበሉ ለሚል ጠቅላይ አገዛዝ መታዘዝ በሽታው እንዲብስበት ማድረግ ብቻ ነው :: ዘላቂ መፍትሄው ደግሞ በየግዜው የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈሉ ከእውነትና ነፃነት ጋር መቆም ብቻ ነው::

በቃልቲ እስር ቤት የሚገኘው አቶ አንዱዓለም አራጌ ዋለ ” ያልተሄደበት መንገድ ” መጽሐፍ የተወሰደ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s