Archive | January 19, 2014

‹‹ዶክመንተሪው የመንግስትን የንቃት ጉድለት ያሳያል››

ዘመኑ ተቀይሯል ፣ ማህበረሰቡ ከየትኛውም በላይ ነቅቷል ከመንቃትም አልፎም መጥቋል ፣ ውሸት እና ሐሰትን መለየት የሚችል ትውልድ ተፈጥሯል፣ ያልተማረ የለም ሁሉም ተምሯል፡፡ ተምሮም ተመራምሯል፡፡ ይህ የንቃት አውድማ አውሮፓ እና አሜሪካ አሊያም ህንድና አውትራሊያ ላይ አልተገደበም፡፡ ይሀው ሐበሻዊቷ ሐገራችን ላይ በገሐድ እያየነው ያለነው ተጨባጭ እውነታ ነው፡፡

ሰዉ በዚህ መልኩ በጣም ነጥቆና ተመንጥቆ ባለበት የስልጣኔ ዘመን ህውሀት/ኢህአዲግ ድራማዊ ዶክመንተሪ ሰርቶ ህዝቡን ለማስበርገግ መመከሩ እራሱ የንቃት ጉድለት እንደተጠናወተው በግልፅ ያሳብቅበታል፡፡ ይህ የንቃት ጉድለት ያለበት መንግስት የንቃት ጉድለቱን እንደጨቀየ እንድናውቅለት ስለፈለገ በተደጋጋሚ የተራቆቱ ዶክመንተሪ በመስራት እያሳየን ይገኛል፡፡ መንግስት በገሐድ ህግ አታክቡሩ ብሎ ቢነግረን እንኳ እኛ እንደ ህዝብ ህገመንግስቱን በማክበር እና በማስከበር ለዚ መንግስት መሐይም እንደሆነ እና የንቃት ጉድለት እንዳለበት በግልፅ እያሳየን እንደሆነ ይሀው ለሁለት አመት ያደረግነው ሰላማዊ ትግል ምስክር ነው፡፡

አስቡት እስኪ ህውሐት/ኢህአዲግ ጂሐዳዊ ሐረካት የሚበለውን ዶክመተሪ ሰርቶ እነ ያሲን ኑሩን ፣ እነ አቡኬን ፣ እነ ካሚል ሸምሱን እና እነ አህመዲን ጀበልን በሽብር መወንጀሉ ነገር በህዝብ ዘንድ እንደተነቃበት እያወቀ ህዝብ ነቃን ማለቱ እንዳልገባው ለመመሰል ሚሞክረው ሙከራና ድጋሚ የተባነነበትን ዶክመንተሪ መልሶ ለነቃ ህዝብ ማሳየቱ ሆን ብሎ ነገር ፍለጋን ከማሳየት ውጪ ምን ሚያስተላልፈው መልእክት አለ፡፡ ይህ ነው በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነት !
ዛሬ በታየው ዶክመንተሪ ህዝብ እና መንግስትን ያስተዛዘበው ነገር መንግስት በህዝብ ላይ ጭቆና ደርሷል ብለው እውነቱን ሲያጋልጡ የነበሩ አካላትን በተለይ የአሜሪካን መንግስትን በጓብታናሞቤ በግልፅ በኢቲቪ ሲያማ እንዳልነበር ዛሬ ደሞ ሐሳቡን ቀይሮ የአሜሪካን መንግስትን በ ዲሞክራሲ ማሞገሱ ከህዝብ ጋር በድጋሚ ያስተዛዝበዋል፡፡ ሌላው ሚጎረብጥ ነገር ደግሞ ዛሬ በዶክመንተሪው ላይ በዴሞክራሲ እድገት የኢህአዴግ መንግስት የአሜሪካን እና የኢንግሊዝ መንግስት መብለጡን መንገሩ ነው፡፡ ልብ ካልን በዛሬው ዶክመንተሪ የአሜሪካ እና የኢንግሊዝ መንግስታት የፀረ ሽብር ህጋቸው ህዝብን ያላማከለ እንደነበር በመግለፅ የኢህአዴግ ደግሞ ህዝብ እና ፓርላማ እንደተወያየበት በይፋ ገልጾልናል፡፡ ከዚህ በላይ እሺ በህዝብ ላይ መቀለድ አለ?

ሳጠቃለው መንግስት በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ሹፈት ደደብነቱን እና የህሊና ንቃት ጉድለቱን ሲያንፀባርቅበት ህዝብ ግን እያሳየ ባለው ሰላማዊ ትግል ምን ያህል እንደነቃና እንደመጠቀ እያረጋገጠት ይገኛል ፡፡ ህዝብ እያሳየ ያለው ንቃትም አጠናክሮ ሊቀጥልበት ገባዋል፡፡
ፍትህ ለኢትዮጵያ ሙስሊም፡፡
‹‹ዶክመንተሪው የመንግስትን የንቃት ጉድለት ያሳያል›› ========================== ዘመኑ ተቀይሯል ፣ ማህበረሰቡ ከየትኛውም በላይ ነቅቷል ከመንቃትም አልፎም መጥቋል ፣ ውሸት እና ሐሰትን መለየት የሚችል ትውልድ ተፈጥሯል፣ ያልተማረ የለም ሁሉም ተምሯል፡፡ ተምሮም ተመራምሯል፡፡ ይህ የንቃት አውድማ አውሮፓ እና አሜሪካ አሊያም ህንድና አውትራሊያ ላይ አልተገደበም፡፡ ይሀው ሐበሻዊቷ ሐገራችን ላይ በገሐድ እያየነው ያለነው ተጨባጭ እውነታ ነው፡፡ ሰዉ በዚህ መልኩ በጣም ነጥቆና ተመንጥቆ ባለበት የስልጣኔ ዘመን ህውሀት/ኢህአዲግ ድራማዊ ዶክመንተሪ ሰርቶ ህዝቡን ለማስበርገግ መመከሩ እራሱ የንቃት ጉድለት እንደተጠናወተው በግልፅ ያሳብቅበታል፡፡ ይህ የንቃት ጉድለት ያለበት መንግስት የንቃት ጉድለቱን እንደጨቀየ እንድናውቅለት ስለፈለገ በተደጋጋሚ የተራቆቱ ዶክመንተሪ በመስራት እያሳየን ይገኛል፡፡ መንግስት በገሐድ ህግ አታክቡሩ ብሎ ቢነግረን እንኳ እኛ እንደ ህዝብ ህገመንግስቱን በማክበር እና በማስከበር ለዚ መንግስት መሐይም እንደሆነ እና የንቃት ጉድለት እንዳለበት በግልፅ እያሳየን እንደሆነ ይሀው ለሁለት አመት ያደረግነው ሰላማዊ ትግል ምስክር ነው፡፡ አስቡት እስኪ ህውሐት/ኢህአዲግ ጂሐዳዊ ሐረካት የሚበለውን ዶክመተሪ ሰርቶ እነ ያሲን ኑሩን ፣ እነ አቡኬን ፣ እነ ካሚል ሸምሱን እና እነ አህመዲን ጀበልን በሽብር መወንጀሉ ነገር በህዝብ ዘንድ እንደተነቃበት እያወቀ ህዝብ ነቃን ማለቱ እንዳልገባው ለመመሰል ሚሞክረው ሙከራና ድጋሚ የተባነነበትን ዶክመንተሪ መልሶ ለነቃ ህዝብ ማሳየቱ ሆን ብሎ ነገር ፍለጋን ከማሳየት ውጪ ምን ሚያስተላልፈው መልእክት አለ፡፡ ይህ ነው በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነት ! ዛሬ በታየው ዶክመንተሪ ህዝብ እና መንግስትን ያስተዛዘበው ነገር መንግስት በህዝብ ላይ ጭቆና ደርሷል ብለው እውነቱን ሲያጋልጡ የነበሩ አካላትን በተለይ የአሜሪካን መንግስትን በጓብታናሞቤ በግልፅ በኢቲቪ ሲያማ እንዳልነበር ዛሬ ደሞ ሐሳቡን ቀይሮ የአሜሪካን መንግስትን በ ዲሞክራሲ ማሞገሱ ከህዝብ ጋር በድጋሚ ያስተዛዝበዋል፡፡ ሌላው ሚጎረብጥ ነገር ደግሞ ዛሬ በዶክመንተሪው ላይ በዴሞክራሲ እድገት የኢህአዴግ መንግስት የአሜሪካን እና የኢንግሊዝ መንግስት መብለጡን መንገሩ ነው፡፡ ልብ ካልን በዛሬው ዶክመንተሪ የአሜሪካ እና የኢንግሊዝ መንግስታት የፀረ ሽብር ህጋቸው ህዝብን ያላማከለ እንደነበር በመግለፅ የኢህአዴግ ደግሞ ህዝብ እና ፓርላማ እንደተወያየበት በይፋ ገልጾልናል፡፡ ከዚህ በላይ እሺ በህዝብ ላይ መቀለድ አለ? ሳጠቃለው መንግስት በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ሹፈት ደደብነቱን እና የህሊና ንቃት ጉድለቱን ሲያንፀባርቅበት ህዝብ ግን እያሳየ ባለው ሰላማዊ ትግል ምን ያህል እንደነቃና እንደመጠቀ እያረጋገጠት ይገኛል
፡፡ ህዝብ እያሳየ ያለው ንቃትም አጠናክሮ ሊቀጥልበት ገባዋል፡፡ ፍትህ ለኢትዮጵያ ፡፡
Abu Bayen

posted by Alemayehu Tibebu

መሬታቸው ለህንድ ሻይ ልማት ኩባንያ መሰጠቱን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ከመንግስት ዱላ ገጠማቸው

tea

ሰንደቅ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው፦

በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታር መሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችን ጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስት ብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎ መታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉ አስረድተዋል።

በጋምቤላ ክልል የመጀንግ ዞን አመራር የሆኑት አቶ ይማም ቃሪስ በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ የሚያሰሙት ጥቂት ግለሰቦች የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውና ተጨፈጨፈ የሚሉትም ጥብቅ ደን ሳይሆን ቁጥቋጦ ነው ብለዋል። አክለውም እንደጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ደንብና አሰራር መሰረት የህንዱ ኩባንያ መሬቱን እንዲያለማ መፍቀዳችን ትክክል ነው ይላሉ።

የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብ ባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ም መጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።

በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብ አይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉ ይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎች ወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብም ስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታ አቅራቢዎቹ።
የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።