Archive | February 8, 2014

የአንዷለም አራጌ የውሳኔ አሁንም ቀጠሮ ተራዘመ፤ ኢሕአዴግ 4 የአንድነት አመራሮችን ሊያስር መሆኑ ተሰማ

በኢትዮጵያውያን ዘንድ የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል የተሰየመው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ በካንጋሮው ፍርድ ቤት ዕድሜ ልክ ዕስራት እየተፈርደበት መሆኑ ይታወሳል። ወጣቱ ፖለቲከኛ ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ለውሳኔ ከተቀጠረ በኋላ አሁንም እንደዚህ ቀደሙ ቀጠሮው መራዘሙን የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል።

አቶ አንዷለም አራጌ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ እየተሰቃየ ቢሆንም “የእኔን መታሰር ተቃዋሚዎች ሊጠቀሙበት አልቻሉም” ሲል መናገሩ አይዘነጋም። ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረበት አንዷለም በዳኞች የተለመደ ምክንያት ቀጠሮው ለመጋቢት 8 ቀን 2006 እንዲተላለፍ ተወስኗል። ዛሬ አንዷለም ላይ ምን ይወሰን ይሆን የሚለውን ለማየት በርካታ ሰዎች ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታድመው እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመልከታል።

የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ ነብዩ ሃይሉ እንደዘገበው ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ። በዘገባው መሠረት ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ 4 አመራሮችና አባላት እንዲታሰሩ ኢህአዴግ ወስኗል፤ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ታውቋል፡፡
የፍትህ ሚ/ር ምንጮች እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው ይላል የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገባ።

ሞት ለሌቦች፣ በዝባዦች፣ በግዚያዊ ጥቅም የታወሩ የሀገርና ህዝብ አውዳሚዎች

Alemayehu Tibebu

handout3

ሙስና እንደአስተሳስብ በሀገራችን የቆየ ቢሆንም ባለፉት ዐስር ዐመታት ግን በብርሀን ፍጥነት አድጎ ባለስልጣኖቻችን፣ ነጋዴዎቻችን፣ ባለሀብቶች ሙስና መስራት ሳይሆን አለመስራቱ እንደነውር እየቆጠሩት ነው፡፡ ባሁኑ ሰዐት ስሙ ራሱ ተቀይሮ “ቢዝነስ” ተብሎ የየዕለት ገጠመኝ፣ የተለመደ የቢሮክራሲው አካል ሆኗል፡፡

ለዛሬ በባለስልጣኖች(የታችም የላይም) ያለውን ሙስና ብናይ፤ ባሁን ሰዐት ሶስት ዐይነት ሙሰኞች አሉ፡፡

1. ትንሽ እየሰሩ የሚሰርቁ፡፡ በተሰማሩበት ስራ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተፍ ተፍ ይላሉ፡፡ ከዘረፉትና ካስዘረፉት በተቀረው ብር የተወሰነ ስራ ሊሰሩ ይሞክራሉ፡፡ እነዚህ ሌቦች፣ ወንጀለኞች ናቸው፡

2. እኒዚህ እየሰረቁ እየመዘበሩ የተቀረውም ብር/ንብረት መረጃ ለማጠፋፋት ይሁን ህዝብ እንዳይጠቀም በማሰብ እንዲወድም የሚያደርጉ ነቸው፡፡ እነዚህ ሌቦች ብቻ ሳይሆኑ ህሊና-ቢስ የጥፋት ሰይጣን ያደረባቸው ናቸው፡፡

3. ትንሽ በልተው ሌላ በተለይም ባዕድ የውጭ ሰው ቢልዮኖች እንዲመዘብር፣ ሚልዮኖችን እንዲጎዳ ለመተባበር ምንም የማይገዳቸው ህሊናቸው የጨቀየ ሀገራቸው የሚሸጡ ሌቦች፣ ባንዳዎች፣ ህሊና-ቢሶች

በትግራይ የሆነውን አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡

ከ10 ዐመት በፊት አንድ የቻይና የመንገድ ስራ ተቋራጭ ብዙ መኪናዎችን፣ የተለያዩ ዐይነት ማሽነሪዎችን ገዝቶ ስራ ይጀመራል፡፡ ከቤትመራ እስከ መቐለ ያለውን መንገድ ነበር ሊሰራ የተዋዋለው፡፡ ስራው እየተጓተተ በፍጥነት መሄድ የቻለም አልነበረም፡፡ የድርጅቱ መኪናዎችና ማሽነሪዎች ከስራ ሰዐት ውጪ የሚቆዩበት ግዚያዊ ካምፕ ድርጅቱ መሬት-ሚእቲ በተባለ ቦታ አካባቢ ሰርቶ አዘጋጅቷል፡፡ እዛም እያደሩ ነበር፡፡

የስራ ተቋራጩ በጣም በአስቀያሚ ጥራት ከተሰራው የመንግድ ስራው ኩንትራት በከፍተኛ ሁኔታ ብዙ ትርፍ ያጋበሰ ስለነበር ስራውን ጨርሶ አገሩ ሲገባ የነበሩትን መኪናዎችና ማሽነሪዎች ለክልሉ የመንገድ ስራዎች ድርጅት በስጦታ መልክ ነበር አስረክቦ የሄደው፡፡

አሰርቶት በሄደው ካምፕ የቆሙት መኪኖችና ማሽነሪዎች በየቀኑ ወሳኝ ብልቶቻቸው እያስወለቁ መሸጥ ተፋፋመ፡፡ ከፍተኛ ሀላፊዎች፣ የጥበቃ ክፍሉና ሌሎች ሰራተኞች እየተመሳጠሩ ሚልዮኖች የወጣባቸውና አሁን የሀገሪቱ ንብረት የሆኑትን መኪኖችና ማሽነሪዎች ብልቶቻቸውን እያወጡ መቸርቸር፣ መቸርቸር፡፡ አንዲህ እያሉ ከ40 በላይ ከባድ መኪናዎችና ማሽኖች ከጥቅም ውጪ ሆኑ፡፡ ይሀንን ለማጋለጥ የሞከሩም ከስራ ተፈናቀሉ፡፡

ታድያ የበለጠ የሚያሳዝነው ነገር፤ መኪና ሲያረጅ ወይም ሲበላሽ በግልፅ ጨረታ የሚወጣበት አሰራር አለ፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን ብልቶቻቸው የወላለቁ መኪኖች ለጨረታ ቢያወጡ ተጫራቾች ጉዳዩ ይደርሱበትና ሚስጢሩ ይወጣል ብለው በማሰብ ለጨረታ እንዳይወጡ አደረጉ፡፡ እነዛ መኪኖችና ማሽነሪዎች ላለፉት 10 ዐመታት ገደማ እዛው ግቢ በፀሓይ፣ በዝናብ፣ በቁር ሲመቱ ከርመው አሁን ሙሉ ለሙሉ በስብሰዋል፡፡
ከመቀሌ ወጥታችሁ የአዲስ-አበባ መንገድ በምትይዙበት ጊዜ ዐዲ-ጉደም ሳትደርሱ(መሬት- ሚእቲ በተባለ ስፍራ አካባቢ) መንገዳችሁ ላይ የሚገጥማችሁ የተበሉ የወላለቁ በርካታ መኪኖች፣ ብረታ-ብረቶችና የወላለቁ ማሽኖች የተከማቹበት ቦታ ብዙዎቻችሁ እንዳያችሁት አስባለሁ፡፡
ኮረም አለፍ እንዳላችሁ የምታዩት ትልቅ የብረታብረቶችና፣ የፈረሱ መኪኖች ክምርም ተመሳሳይ ታሪክ አለው፡፡
ተከዘ አካባቢም ይህ ነገር በገፍ እንዳለ ይነገራል፡፡ በሌሎች ብዙ ቦታዎችም እንዲሁ ነው፡፡

እንግዲህ ሙስና ክፋቱን እዩት፡፡ ሚልዮኖች የወጣባቸው መኪኖች ትንሽ አካሎቻቸውን በማውለቅና በመሸጥ የቀረውን ከ90 በመቶ በላይ የሆነ አካላቸው እንዲህ በስብሶ ባክኖ እንዲቀር ወሰኑበት፡፡ በእውነት በጣም ያማል፡፡

ሞት በሙስና፣ የጥቅም፣ የዝምድና ሌላ ትስስር የተገነባ ጨካኝ ቢሮክራሲ!

“የአቶ አስራት ጣሴ እስር ፖለቲካዊ እንደምታ ያለው ይመስላል” – አቶ ተክሌ በቀለ

(ፍኖተ ነፃነት) አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት “አኬልዳማ” በሚል ርዕስ ያቀረበው ዶክመንተሪ ፊልም የፓርቲያችንን ስም ያጎደፈ ነው በሚል የከፈተው ክስ በሂደት ላይ እያለ ዶክመንተሪ ፊልሙ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን በማውገዝ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የፃፉትን የግል አስተያየት ተከትሎ “በፍርድ ቤቱ ላይ ዘለፋ” ሰንዝረዋል በሚል ለእስር መዳረጋቸው ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ተጠቆመ፡፡

አስራት ጣሴ

Asrat-Tassie
የአቶ አስራት የህግ ጠበቃ አቶ ተማም አባ ቡልጉ በትላንትናው ዕለት ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት በቅድሚያ የስነ -ስርአት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲፈቀድላቸዉ በመጠየቅ የሚከተለዉን የስነ-ስርአት ጥያቄ አቅርበዋል “ደንበኛዬ የተጠሩበት መንገድ ላይ የስነ-ስርአት ጥያቄ አለኝ ፡፡ በችሎት ያልነበሩ ሰውን በሌላ ቦታና መጽሔት በሰጡት አስተያየት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 480 ሊጠየቁ አይገባም” ብለዋል ፡፡ አስከትለውም የተጠቀሰውን አንቀፅ ቃል በቃል በማንበብ በአንቀፁ ሊጠየቁ የሚገባቸው በችሎት ተገኝተው የፍርድ ቤቱን ሂደት ያወኩ እንደሆነ ብቻ መሆኑን በማስመር “የኔን ደንበኛ ከውጪ ተጠርተው መጠየቅ አይችሉም፤ ደንበኛዬ ብዚህ ችሎት ተማጋች አይደሉም በስፍራውም አልነበሩም፤ ጥፋት ሰርተዋል ቢባል እንኳን በዚህ አንቀፅ ሊጠየቁ አይገባም ፡፡” በማለት ተከራክረዋል፡፡ሆኖም የጠበቃውን መከራከሪያ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ባለመቀበሉ አቶ አስራት ስለተጠሩበት ጉዳይ ጠበቃ ተማም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በምላሻቸውም “ደንበኛዬ ይህን ችሎት በተለየ በሚመለከት አልፃፉም፤ አቶ አስራት የገለፁት አጠቃላይ እውነታን ነው፡፡ ኢህአዴግ ስላቋቋማቸው ፍርድ ቤቶች ነው በአጠቃላይ የጻፉት፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 29 መሰረት ስለፍርድ ቤትም ሆነ በማንኛውም ጉዳይ ላይ መጻፍም ሆነ አመለካከት የማበጀት መብት አላቸው፡፡” በማለት ምላሻቸውን አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ውሳኔውን በ8፡30 እንደሚያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ፡፡

ከሰአት በኋላ በችሎቱ ቀጠሮ መሰረት የቀረቡት አቶ አስራት ጣሴ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጥፋተኛ ተብለው ለቅጣት ውሳኔ ከሰባት ቀናት በኋላ እንዲቀርቡ እስከዛውም በእስር እንዲቆዩ ተወስኖባቸዋል፡፡

ከውሳኔው በኋላ ለፍኖተ ነፃነት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ እስሩ ፖለቲካዊ እንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ተናግረው፣ “አቶ አስራት ጣሴ ፓርቲዎችን በማቀራረብ ረገድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኢህአዴግን አስደንግጦታል እስሩም የአስራትን አስተዋፅኦ ለመገደብ የተደረገ ይሆናል፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም በቅርቡ በአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ና ስራአስፈፃሚ የፓርቲዎችን የውህደት ድርድር እንዲመሩና የፓርቲውን አማካሪ ምክር ቤት እንዲያቋቁሙ ኃላፊነት እንደተሰጣቸውም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

Weyane used aid money to buy planes

 

Beggars have nothing to brag about. Chigaram weyanes who rely on Canadian wheat handouts for survival are claiming to have achieved a double digit economy growth :lol: :lol: :lol: :lol: They chose to buy buy dreamliners with the money that was supposed to feed hungry Ethiopians. As a result today there is a double digit famine in Ethiopia :cry:

British aid money flows into offshore fund

More than £160 million of British foreign aid is being channelled through an offshore investment fund used to buy Boeing jets for an African airline and other big business deals.

A recent deal, signed last year, helped finance the purchase of 10 Boeing 787 Dreamliners – the world’s most advanced passenger plane – by Ethiopian Airlines, owned by the Ethiopian government.

http://www.telegraph.co.uk/news/politic … -fund.html

ወቅታዊ የአገራችንን ሁኔታ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ(ኢህአግዘ) የተሰጠ መግለጫ

ethiopian-territory-protest1
በጀግኖች አባቶቻችን ና እናቶቻችን ደም ተከብራ የኖርች አገር በክሃዲዎች አትደፈርም። ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላላት ክብር እና ማንነት ጀግኖች አባቶቻችን በከሰከሱት አጥንት እና ባፈሰሱት ደም ነው።
ለጠላት የማይንበረከከው እና ማንንም የማይፈራው የኢትዮጵያ ጀግና ከፋሺስት ኢጣልያ ጋርም ቢሆን አንገት ለአንገት ተናንቀው በጦር በጎራዴ ይችን ሃገር ባላት ቅርጽና ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ አቆይተዋታል። አሁን ግን የደም መስዋእትነት የተከፈለበትን ይህንን መሬት ሃገር እናስተዳድራለን ባሉ ወረበሎች ስትበጣጠስ እና ስትቆራረስ ማየት ያማል።
ይቺ ሀገር ባንዲራዋ በየ ዳር ድንበሩ የተውለበለበላት ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ባንዲራዋን ጨርቅ ሳይሉ በደማቸውና ባጥንታቸው አጥር አጥረው ያኖርዋት ፣ ጀግኖች አትሌቶች ድል አድርገው ላባቸውን እና እንባቸውን እያወረዱ ባንዲራውን ከፍ አርገው የሚያስከብርዋት ፣ ሃገር ማለት ባልታወቀ ሰንሰለት ከልብ ጋር የታሰረ የማትተው፣ የማትሰለች ፣ ካንቺ በፊት እኔን ያርገኝ የተባለላት ፣ በፍቅርዋ ተነደፈው ስንቱ በብእራቸው የተቀኙላት፣ በድምጻቸውም የፎከሩላት ፣ ሰአሊው በቡርሹ ቀባበቶ ያሳመራትን ሃገር የወያኔ ወረበላ ቡድን ኤርትራን አስገንጥሎ ለሻብያ መስጠቱ ሳያንሰው ዛሬ ደሞ ሌላ ጉድ ስንሰማ እውነት ሃገር እንዲህ በሽፍታ መንግስት እንዲህ መበጣጠስዋ ቢያቆስለን ድምጻችንን ለማሰማት ተነሳን።
በ 1881 ዓ/ም ሚኒሊክ ድንበሬ ይሄ ነው ብለው ለአለም መንግስታት ከበተኑ በሁዋላ ሌላ ምንም አይነት ህጋዊ ውል ያልተፈረም ሲሆን ባሁኑ ሰአት ግን ለሱዳን የወያኔ ወረበላ ቡድን ከመተማ እስከ ጋምቤላ ጠረፍ ድረስ ከ1 ሺ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ቁመትና ከ40-50 ኪሎ ሜትር ጎን በላይ ያለዉን ሰፊ ታሪካዊ ለም መሬት አሳልፎ በመስጠት ላይ እንዳለ ይታወቃል። ሥለዚህ ወገኔ ወያኔ ዳር ደንበር የማካለልም ሆነ የየመሸጥ ሞራልም ብቃትም የለውም» እኛ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ዘብ ከምንታገለበት ጉዳይ ዋናው የሃገራችንን ዳር ድንበር አንዲት ክንድ እንኩዋን ለሌላ ቆርሶ እና አሳልፎ ላለመስጠት ነው። ይህ ለሱዳን ሊሰጥ የታሰበው መሬት ማለትም ከ 1901 እስከ 1904 የተሰመረው /Gjuhen/ የሻለቃ ጉሄን መስመር ሲሆን ይህንን መስመር በኢትዮጵያ በኩል ማንም ያልተስማማበት እና እውቅና ያላገኘ ነው። ነገር ግን መሰሪው የወያኔ መንግስት ህዝቡ ሳያውቅ ውስጥ ውስጡን ስራውን እየሰራ ደሃው ገበሬ በሃገሩ መሬት ሲያርስ ሰው ድንበር ገብተህ ተብሎ በሱዳን ወታደር መከራውን እያየ ነው። የደሃው ለም መሬት ከመነጠቅ አልፎ ሰፊው የደን እርሻችን እንዲሁም ብርቅየ የዱር አራዊቱ ሁሉ ሳይቀር ለሱዳን ቆርሰው እየሰጡ ይገኛሉ። ሟቹ የወያኔ ወረበላ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው መለስ ዜናዊ ኤርትራን ለሻዕብያ አሳልፎ ለመስጠት በአለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በ 1983 ዓም ሃገሬን ቆርሳችሁ ለሌላ ስጡልኝ በማለት ለተባበሩት መንግስታት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲሁም በሃሰት ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት በማለት ህዝቡ ሳይጠየቅ ሬፈረንደም እንዲደረግ በማድረግ ህዝብን ከህዝብ ወገንን ከወገን አለያይቶ እንዲሁም ሃገራችንን ያለ ባህር በር እንዲቀር አደረገ። ከዛም በሁዋላ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ተነካ ቢባል ከ 80 ሺህ ህዝብ በላይ በባድሜ ጦርነት አለቀ። በአሁኑ ሰአት ደሞ የባሰ ብለው ይህንን መሬት ማለትም ከመተማ እስከ ጋምቤላ ከ1 ሺ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ቁመትና ከ40-50 ኪሎ ሜትር ወደውስጥ ለሱዳን ለመስጠት መደራደር ይህ ወሮበላ ሃገር ሻጭ መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን። መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች :- ይህ የወረበሎች ጥርቅም በሳዓውዲ አርብያ ወገይኖቻችን ሲታርዱ አያገባኝም ያለ የጠላት ቅጥርኛ በመሆኑ ባለን አቅም እና ሃይል ተባብረን ከስሩ ነቅለን በፍጥነት ካልጣልን ህዝብን ከህዝብ አባልቶ ድንበርዋን ለጠላት ሸጦ እንዲሁም ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳትኖር በታትኖና ቆራርሶ የባሰ ችግር ወደ ማመጣት እንደሚሄድ የአደባባይ ሚስጥር ነው። የሀገር ፍቅር ፣ አንድነት ፣ ባንዲራ ፣ ጀግንነት እና የሀገር ታሪክ ለወያኔ ስርአት ከተረት ያላለፈ ነገር ቢሆንም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች ግን ህመምዋ የሚያመን ጩኧትዋ የሚሰማን የድሃው ህዝብ መፈናቀል መገፋት እና ከቅየው መባረር እንቅልፍ የሚነሳን በየበርሃውና በየስደት አለም ገብቶ ያለ ሃገር እና ያለ ወገን የቀረው ንጹሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶት እረፍት የሚነሳን ነገር በመሆኑ ይህንንም ነገር በጽኑ በመቃወም ለለውጥ የምናደርገውን ትግል በባሰ እልህ እና ቁጭት እንደሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ ይህንን ከፋፋይ መንግስት ለመጣል ባንድነት እንነሳ ስንል የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ዘብ ጥሪውን ያቀርባል ። ”ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብነውን አደራ በትግላችን እናስከብራለን!!!”

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ

ሁሉም ለናት አገሩ ዘብ ይቁም።

Contact: EPPFG – International <> Email: kirarayiso@googlemail.com <> http://www.eppfguard.com.
ETHIOPIAN PEOPLE PATRIOTIC FRONT GUARD