ሞት ለሌቦች፣ በዝባዦች፣ በግዚያዊ ጥቅም የታወሩ የሀገርና ህዝብ አውዳሚዎች


Alemayehu Tibebu

handout3

ሙስና እንደአስተሳስብ በሀገራችን የቆየ ቢሆንም ባለፉት ዐስር ዐመታት ግን በብርሀን ፍጥነት አድጎ ባለስልጣኖቻችን፣ ነጋዴዎቻችን፣ ባለሀብቶች ሙስና መስራት ሳይሆን አለመስራቱ እንደነውር እየቆጠሩት ነው፡፡ ባሁኑ ሰዐት ስሙ ራሱ ተቀይሮ “ቢዝነስ” ተብሎ የየዕለት ገጠመኝ፣ የተለመደ የቢሮክራሲው አካል ሆኗል፡፡

ለዛሬ በባለስልጣኖች(የታችም የላይም) ያለውን ሙስና ብናይ፤ ባሁን ሰዐት ሶስት ዐይነት ሙሰኞች አሉ፡፡

1. ትንሽ እየሰሩ የሚሰርቁ፡፡ በተሰማሩበት ስራ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተፍ ተፍ ይላሉ፡፡ ከዘረፉትና ካስዘረፉት በተቀረው ብር የተወሰነ ስራ ሊሰሩ ይሞክራሉ፡፡ እነዚህ ሌቦች፣ ወንጀለኞች ናቸው፡

2. እኒዚህ እየሰረቁ እየመዘበሩ የተቀረውም ብር/ንብረት መረጃ ለማጠፋፋት ይሁን ህዝብ እንዳይጠቀም በማሰብ እንዲወድም የሚያደርጉ ነቸው፡፡ እነዚህ ሌቦች ብቻ ሳይሆኑ ህሊና-ቢስ የጥፋት ሰይጣን ያደረባቸው ናቸው፡፡

3. ትንሽ በልተው ሌላ በተለይም ባዕድ የውጭ ሰው ቢልዮኖች እንዲመዘብር፣ ሚልዮኖችን እንዲጎዳ ለመተባበር ምንም የማይገዳቸው ህሊናቸው የጨቀየ ሀገራቸው የሚሸጡ ሌቦች፣ ባንዳዎች፣ ህሊና-ቢሶች

በትግራይ የሆነውን አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡

ከ10 ዐመት በፊት አንድ የቻይና የመንገድ ስራ ተቋራጭ ብዙ መኪናዎችን፣ የተለያዩ ዐይነት ማሽነሪዎችን ገዝቶ ስራ ይጀመራል፡፡ ከቤትመራ እስከ መቐለ ያለውን መንገድ ነበር ሊሰራ የተዋዋለው፡፡ ስራው እየተጓተተ በፍጥነት መሄድ የቻለም አልነበረም፡፡ የድርጅቱ መኪናዎችና ማሽነሪዎች ከስራ ሰዐት ውጪ የሚቆዩበት ግዚያዊ ካምፕ ድርጅቱ መሬት-ሚእቲ በተባለ ቦታ አካባቢ ሰርቶ አዘጋጅቷል፡፡ እዛም እያደሩ ነበር፡፡

የስራ ተቋራጩ በጣም በአስቀያሚ ጥራት ከተሰራው የመንግድ ስራው ኩንትራት በከፍተኛ ሁኔታ ብዙ ትርፍ ያጋበሰ ስለነበር ስራውን ጨርሶ አገሩ ሲገባ የነበሩትን መኪናዎችና ማሽነሪዎች ለክልሉ የመንገድ ስራዎች ድርጅት በስጦታ መልክ ነበር አስረክቦ የሄደው፡፡

አሰርቶት በሄደው ካምፕ የቆሙት መኪኖችና ማሽነሪዎች በየቀኑ ወሳኝ ብልቶቻቸው እያስወለቁ መሸጥ ተፋፋመ፡፡ ከፍተኛ ሀላፊዎች፣ የጥበቃ ክፍሉና ሌሎች ሰራተኞች እየተመሳጠሩ ሚልዮኖች የወጣባቸውና አሁን የሀገሪቱ ንብረት የሆኑትን መኪኖችና ማሽነሪዎች ብልቶቻቸውን እያወጡ መቸርቸር፣ መቸርቸር፡፡ አንዲህ እያሉ ከ40 በላይ ከባድ መኪናዎችና ማሽኖች ከጥቅም ውጪ ሆኑ፡፡ ይሀንን ለማጋለጥ የሞከሩም ከስራ ተፈናቀሉ፡፡

ታድያ የበለጠ የሚያሳዝነው ነገር፤ መኪና ሲያረጅ ወይም ሲበላሽ በግልፅ ጨረታ የሚወጣበት አሰራር አለ፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን ብልቶቻቸው የወላለቁ መኪኖች ለጨረታ ቢያወጡ ተጫራቾች ጉዳዩ ይደርሱበትና ሚስጢሩ ይወጣል ብለው በማሰብ ለጨረታ እንዳይወጡ አደረጉ፡፡ እነዛ መኪኖችና ማሽነሪዎች ላለፉት 10 ዐመታት ገደማ እዛው ግቢ በፀሓይ፣ በዝናብ፣ በቁር ሲመቱ ከርመው አሁን ሙሉ ለሙሉ በስብሰዋል፡፡
ከመቀሌ ወጥታችሁ የአዲስ-አበባ መንገድ በምትይዙበት ጊዜ ዐዲ-ጉደም ሳትደርሱ(መሬት- ሚእቲ በተባለ ስፍራ አካባቢ) መንገዳችሁ ላይ የሚገጥማችሁ የተበሉ የወላለቁ በርካታ መኪኖች፣ ብረታ-ብረቶችና የወላለቁ ማሽኖች የተከማቹበት ቦታ ብዙዎቻችሁ እንዳያችሁት አስባለሁ፡፡
ኮረም አለፍ እንዳላችሁ የምታዩት ትልቅ የብረታብረቶችና፣ የፈረሱ መኪኖች ክምርም ተመሳሳይ ታሪክ አለው፡፡
ተከዘ አካባቢም ይህ ነገር በገፍ እንዳለ ይነገራል፡፡ በሌሎች ብዙ ቦታዎችም እንዲሁ ነው፡፡

እንግዲህ ሙስና ክፋቱን እዩት፡፡ ሚልዮኖች የወጣባቸው መኪኖች ትንሽ አካሎቻቸውን በማውለቅና በመሸጥ የቀረውን ከ90 በመቶ በላይ የሆነ አካላቸው እንዲህ በስብሶ ባክኖ እንዲቀር ወሰኑበት፡፡ በእውነት በጣም ያማል፡፡

ሞት በሙስና፣ የጥቅም፣ የዝምድና ሌላ ትስስር የተገነባ ጨካኝ ቢሮክራሲ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s