Archive | February 27, 2014

ብራቮ አንድነት! ብራቮ መኢአድ!

1900714_597588846985107_1052161865_o

(Abraha Destaአንድነትና መኢአድ የጠሩት የእሁዱ ሰለማዊ ሰልፍ የህዝብ ፖለቲካዊ መነቃቃት እንደገና ማነሳሳት እንደሚቻል ማሳያ ነው። ብራቮ አንድነት! ብራቮ መኢአድ! ህዝብ መነቃቃት መልሳችኋልና። በሌሎች አከባቢዎችም ተመሳሳይ ተግባር ቢከናወን መልካም ነው።

1796607_572235646205141_706337022_n

ህዝብን በሰለማዊ መንገድ ለለውጥ የሚያነሳሳ ማንኛውም ፓርቲ እደግፋለሁ። ምክንያቱም የኔ ዓላማ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ነው። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባ የህዝብን ፖለቲካዊ ንቃተ ህሊና ከፍ እንዲል በማድረግ ነው። ምክንያቱም ዴሞክራሲ የህዝብ መንግስት መመስረት ነው። የህዝብ መንግስት መመስረት ደግሞ ህዝብን የስልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ህዝብ የስልጣን ባለቤት ለማድረግ ህዝብ ስልጣን ለመረከብ መጀመርያ የፖለቲካ ዓቅም ሊኖረው ይገባል። የፖለቲካ ዓቅም እንዲኖረው ነፃነት ሊያገኝ ይገባል። ነፃነት እንዲኖረው መብቱ መጠቀም መቻል አለበት። መብቱ ለመጠቀም ቅስቀሳ ያስፈልገዋል። ስለዚህ ህዝብን ለለውጥ ለማነሳሳት ቅስቀሳ የሚያደርጉ ፓርቲዎችን እደግፋለሁ: ቅስቀሳ በማድረግ የህዝቦችን ዓቅም መገንባት በመቻላቸው።

የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ላልደግፍ እችላለሁ። ግን የትኛው የፖለቲካ አቅጣጫ እንደሚበጅ መወሰን ያለበት ህዝቡ ነው። ስለዚህ ስልጣን የህዝብ ይሁን። ፓርቲዎችም ስልጣን ከህዝቡ ይዋሱ። በራሳቸው ጠመንጃ የህዝብን ስልጣን የሚነጥቁ ፓርቲዎችን ብቻ ነው የምቃወመው።

It is so!!!

የኩዬት መንግስት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ወደ ሃገሩ ገብተው እንዳይሰሩ እገዳ ጣለ፡፡

የኩዬት መንግስት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ወደ ሃገሩ ገብተው እንዳይሰሩ እገዳ ጣለ፡፡
የኩዬት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ኢትዮጵያውያን ወንድ እና ሴት የቤት እና የጉልበት ሰራተኞች ወደሃገሩ ገብተው እንዳይሰሩ ማገዱን አስታውቋል፡፡
የፓስፖርት እና የብሄራዊ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ፈይሰል አል ናዋፍ እንዳሉት ለኢትዮጵያውያኑ ቪዛ መስጠት
የታገደው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች እየተፈጸመ ያለው የግድያ ፣
የስርቆት ፣ የድብደባ እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች በማስፈራራት ገንዘብ የመጠየቅ ወንጀሎች በመበራከታቸው ነው፡፡እገዳው ተግባራዊ የሚሆነው ከየካቲት 12 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

አለጀዚራ ‪JOURNALISM IS NOT A CRIME! እኛም ትክክል አልነው!!!

1656019_271308126362871_341357600_n

አለጀዚራ ‪#‎FreeAJStaff‬ JOURNALISM IS NOT A CRIME (ጋዜጠኝነት ወንጅል አይደለም) በሚል በግብፅ የታሰሩ ጋዜጠኞችን ዛሬ እንድናንሰላስላቸው፣ እንድናስባቸው እና አጋርነታችንን እንድናሳያቸው አለም አቀፍ ጥሪ አደረጓል።

እኛም የመታሰርን ነገር ዋጋ እየከፈሉ ባሉ ጓድኞቻችን አሳምረን እናውቅዋልን እና አዎ ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም ስንል የአልጀዚራም ጋዜጠኞች የእኛም አንበሶች ከተቆለፈባቸው እስር ቤት እንዲፈቱ ጩኸቱን እንቀላቀላለን።

ትላንት ወሰድ መለስ የሚያደርገው ጓደኛችን ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን (ራስ በራሳችንም መገማገምማ አለብን…) በፌስ ቡክ ገፁ እንደነገረን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ገንዘቡን ከፍሎ ሊማር የጀመረውን የርቀት ትምህርት እንዳይማር ደብተሮቹ ተቀምተዋል መጸሃፉንም ጥበቃዎቹ ተረክበውታል።

ከትላንት በፊት ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ የታሰረችው አንሶ ከእናቷ ውጪ ጠያቂ እንዳያያት እገዳ ተደርጎባታል። እንድውም በቅርቡ ከቤተሰቦቿ አንዷ ሌላ እስረኛ ለመጠየቅ ቃሊቲ አምርታ ያጋጠማት ነገር አስቂኝ ነበር።

አንዱ ዋርዲያ ”እዚህ ምን ልታደርጊ መጣሽ…” አላት

እርሷም “እስረኛ ለጠይቅ” አለቸው…

ተከልክለሽ አይድለም እንዴ አላት…

የከለከላችሁኝ ርዮት አለሙን እንዳልጠይቅ ነው… ብትለው ጊዜ

ርዮት አለም የለ ሰማያዊ ፓርቲ የለ አንድነት የለ ማንንም መጠየቅ አትችይም ብሏት ቁጭ። ይሄን ጊዜ አብሯት የነበረ አንድ ወዳጇ ነገሩ ግር ብሎት ዋርዲያውን ሌላ ጥያቄ ጠየቀው “የኔ ጌታ ሌላ ቀንም ተሳስታ ደግሞ እንዳትሄድ… ሆስፒታል የታመመስ መጠየቅ ትችላልች ?” ብሎ ጠየቀው።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መታስሩ ሳያንስ የልጁ እና የቤተስቡ መተዳድሪያ የሆነውን ከእናቱ ውርስ ያገኘው ቤት መንግስት ለእናቱ ምንም ሳይሆን ይገባኛል ብሎ ወሰደበት።

ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው መታሰር ብቻ ይበቃሃል አልተባለም፤ መንግስታችን ኢህአዴግ እኔን እንጂ ሌላ አታምልክ ብሎ ነው መሰል ለፈጣሪው የሚያደርገውን ሶላት እንዳያደርግ እንኳ ከልክሎት አበሳውን ሲያበላው ነበር።

እናም አልጀዚራ የሚለውን ጮክ በለን እንደግመዋለን፤

ጋዜጠኝነትኮ ወንጀል አይደለም!

JOURNALISM IS NOT A CRIME!