Archive | March 2014

አምባገነናዊውን ስርዓት አቅፈውና ደግፈው የያዙት ምዕራባዊ አገራት

(እዮብ ከበደ ኖርዌይ)

IMPERIALISM-620x310

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆና፣ ስቃይ እና መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካደረጉት ምክንያቶች መካክል አንዱ፣ የወያኔ መንግስት ከምዕራባዊያን የሚያገኘው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ሙገሳ ትልቅ ቦታ ይይዛል። ከነዚህ መንግስታት የሚያገኘው ድጋፍ እና ሙገሳ ምክንያት የማን አለብኝነት ስሜት ስርዓቱ እንዲሰማውና የኢዴሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝቡ ላይ እንዲንያሰራፉ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ስርዓቱም ከነችግሩ ለረዥም ጊዜ በስልጣን እንዲቆይ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የምዕራባዊያን ድጋፍ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። እነዚህ ሀገራት የራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም ብቻ ትኩረት በመስጠታቸው ላለፉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በጭቆና ውስጥ እንዲያሳልፍ አድረገውታል። የሀገሪቱ መልካምድር\ጅኦግራፍያዊ አቀማመጥ፣ የመንግስት ለምዕራባዊያን ፍላጎት አጎብዳጅነት እና ሃገሪቱ በአካባቢው ብሎም በአፍሪካ ፖለቲካ ያላት ማእከላዊ ስፍራ የለጋሽ ሀገራትን ትኩረት ሊስብ ችሏል። በዚህ ምክንያት ምዕራባዊያን የወያኔ ስርዓትን አቅፈውና ደግፈው በመያያዛቸው ህዝቡ ከዚህ አስከፊ ስርዓት ነጻ ለመውጣት የሚያደርገውን ትግል አስቸጋሪ አድርጎታል።

 

የወያኔ መንግስት በህዝብ ላይ እያደረሰ ካለው ዘርፈ ብዙ ወንጀሎች እና የስርዓቱ ልዩ መለያ ባህርያት መካከል በዋናነት፣ በሀይል ህዝቦችን ለዘመናት ከሚኖሩበት መሬት ማፈናቀል እና መሬታቸውንም በርካሽ በኢንቨስትመንት ስም መቸብቸብ፤ የጸረ-ሽብር ህግ በማውጣት የፖለቲካ አመራሮችን እና ጋዜጠኞችን ማፈን፤ ከፍተኛ ሙስና እነዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማስገባት የስልክ እና የኢንተርኔት ክትትል እና ጠለፋ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው። የምዕራባዊያን በወያኔ ላይ ያላቸው ቸልተኝነትና ለዘብተኛ አቋም መንግስት የማናለብኝነት ስሜት እንዲሰማውና በህዝብ ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃና ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑና ስፋቱን እየጨመረ በመሄድ የሀገሪቱን ብሎም የአካባቢውን መጻይ ዕድል አሳሳቢ አድርጎታል።

ከምዕራባዊያን የሚገኝ እረዳታ በመጠቀም ብዙ የአፍሪካ መንግስታት አምባገነናዊ ስርዓትን በሰፊዊ የማጠናከራቸው ሁኔታ አዲስ ነገር አይደለም። ከሰሞኑም የወጣው የHuman Rights Watch ሪፖርት እንዳመለከተው መንግስት ህዝቡን እንዴት ጠፍንጎ እና ጨቁኖ እንደያዘው ምናልባት ለውጭ ማህበረሰብ አዲስ ነገር ሊመስል ቢችልም ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን አዲስ አይደለም። በተለያዩ ወቅቶች የተቃዋሚ ሓይሎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሲገልጹት የቆዩት ጉዳይ ነው። ነገር ግን እዚህ ላይ መጠቆም የሚገባን፤ ወቅታዊ ሪፖርቶችን በተከታታይ በማቅረብ፣ ሰፋ ያለ ማብራሪያና መረጃወችን የሚያቀርበውን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት( Human Right Watch) ማመስገን ይገባናል።

ድርጅቱ ከጥቂት ድርጅቶች መካከል አምባገነናዊ ስርዓቶችን በማጋለጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ስለ ወያኔ ፍጹም አምባገነናዊ ስርዓት ሲነገር ቢቆይም ሰሞኑን የወጣው የ Human Rights Watch ሪፖርትም የዚህን ስርዓት አስከፊነትና ከምእራባዊያን ከሚያገኘው ዳጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ ዘመናዊ የስለላና የክትትል ቴክኖሎጂዎችን በማስገባት ስርዓቱ ፍጹም አምባገነናዊ እንደሆን አመላክቷል። በረቀቀ እና ጊዜውን በጠበቁ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት መንግስት በህዝቡ ላይ እያደረጋ ባለው ጭቆና የምዕራባዊያን ሀገራት እና ድርጅቶች በተዘዋዋሪ ተሳታፊና ተባባሪ አድርጓቸዋል። በመሆኑም የ Human Rights Watch ሪፖርት እንደሚያመልክተው የምዕራባዊያን የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ለጨቋኝ ስርዓት ተባባሪ በመሆናቸው ሊጠየቁ እንደሚገባ በማሳሰብ ቴክኖሎጂውን የሚያቀርቡ፣ የሚሸጡ፣ እና አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች የቴክኖሎጂ ውጤታቸው ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ተግባር በተደጋጋሚ ክስ የሚቀርብባቸው እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ላሉ መንግስታት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መቆጣጠር እንዳለባቸው ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ ለጋሽ አገራት በአመት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በውጭ እርዳታ መልክ ድጋፍ ያገኛል። ይህ ከፍተኛ ድጋፍ በአግባቡ ለልማት ቢውል በደሃው ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ቀላል አይደለም። ነገር ግን አምባገነናዊው መንግስት ለፖለቲካ ፍጆታ ከመጠቀም አልፎ ህዝቡን ለማፈን፣ ለመጨቆን እና ለመሰለል እንዲረዳው ዘመናዊ እና የረቀቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማስገባት ይህን ድጋፍ ያውለዋል። ድጋፉን ለሚሰጡት ምዕራባዊያን ግን ይህ ድርጊት ከእይታቸው የተሰወረ አይደለም።የ Human Right Watch እና የተላያዩ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ጋዜጠኞች፣ ዳኞች፣ ምሁራን፣ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተሰደዋል። እነዚህንም መረጃዎች ለጋሽ አገራት አንብበዋል፤ የጉዳዩንም ክብደት ከማንም በተሻለ ሁኔታ ያውቃሉ። ነገር ግን ምዕራባዊያን በጉዳዮ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ወይም ተጽዕኖ ለማሳደር ለዘብተኛ መሆናቸው ሳያንስ በአሳፋሪ ሁኔታ ጉዳዩን አይተው እንዳላዩ በመሆንና የመንግስትን ፕሮፖጋንዳ ተቀብለው በማቀንቀን የበሰበሰው ስርዓት በህዝቡ ላይ እንዲንሰራፋ አድረጎታል።

በተጨማሪም ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በህይወት እያሉ የምዕራባዊያንን ፍላጎት በማስቀደም በሰላ ምላሳቸው የምዕራባዊያንን ቀልብ መሳብና ማማለል ችለው ነበር። የለጋሽ ድርጅቶች ቡድን (The Donors Assistance Group) እንደሚያመለክተው የወያኔ መንግስትን በተመለከተ በተከታታይ የሚወጡትን ሪፖርቶች መርምሮ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ጉዳዩን ወደጎን በመተው ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር የለት ተለት ተግባራቸውን መቀጠል እንደሚመርጡ አመልክቷል። ከዚህ በፊት ካለን ልምድ እንደምንረዳው ለጋሽ ድርጅቶች ወይም ሀገራት ከወያኔ መንግስት ጋር ፊት ለፉት ከመላተም ይልቅ ከገለልተኛ ወገኖች እንደ ከ Human Right Watch የሚወጡ ሪፖረቶችን ውድቅ ማድረግን ይመረጣሉ። ከተቻለም የራሳቸውን ሪፖርት በማዘጋጀት በመንግስት ላይ የሚቀርበውን ውንጀላ የሚያጠናክር መረጃ እንዳላገኙ በመግለጽ ጉዳዩን ያለዝባሉ ወይም ከገለልተኝ ወገኖች የሚወጡ ሪፖረቶች የተፋለስ ድምዳሜ እንዳላቸው በመጥቀስ መሬት ያልያዙና እውነታውን እንደማያሳይ ማመልከት ይመርጣሉ። ይህ ሁኔታ እነዚህ የውጭ ሀገራትና ድርጅቶች ምን ያህል ለሰፊው ህዝብ መብት እና ጥቅም ደንታ እንደሌላቸው ያመላክታል።

የምዕራባዊያን ከአምባገነናዊ ስርዓት ጋር ያላቸው አጋርነት እና ቁርኝት በኢትዮጵያ ወይም በአፍሪካ ብቻ የተወሰነ ክስተት ሳይሆን በተለያዩ አገሮችም የሚስተዋል ነው። ምዕራባዊያን ለምን ይህን ድጋፍ እንደሚያደረጉ ሲገልጹ፤ እረዳታ መስጠት ብናቆም ዞሮ ዞሮ ተጎጂው ድሃው ህብረተሰብ ስለሆነ ያለው ብቸኛ አማራጭ ባለው ስርዓት አማካኝነት እርዳታ መስጠቱን መቀጠል እንደሚመረጡ ይናገራሉ። ይህ አስተሳሰብ ለጋሽ ሀገራት ለሰብአዊ መብት ክብር እና ለዴሞክራሲያዊ እሴቶች ባይተዋር እንደሆኑ ያሳያል። ለሚሰጡት እርዳታ ቁጥጥርና ክትትል ተአማኒነትና ግልጽ ያሰራር ስርዓት በመዘርጋት የሚሰጡትን ገንዘብ ላልተፈለገ አላማና ፍጆታ ሲውል  እርዳታውን ማቆም የሚቻልበትን መንገድ የሚጠፋቸው አይመስለንም።

መንግስትም ማንኛውንም አማራጮች የሚዘጋ ከሆነም ከነጭራሹ እረዳታውን በማቆም ጠንከር ያለ ተጽዕኖ መፍጠር ይችሉ ነበር። እረዳታ ብናቆም ደሃዉ ህብረተሰብ ይጎዳል የሚባለው ምክንያት አጥጋቢ መነሻ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ህብረተሰቡ ከእርዳታው ተጠቃሚ እየሆነ አይደለምና። ስለሆነም ማነኛውም ምዕራባዊ አገር ለአምባገነናዊ መንግስት የሚሰጡትን እርዳታ ለማቆም ዝግጁ ባለመሆናቸው የሚሰጡት የገንዘብ ድጋፍ አላማውን ስቶ በተቃራኒው ንጹሃንን ህዝቦች ለማፈን እና ለመጨቆን ትልቅ መሳሪ እንደሆነ ሊረዱ ይገባል።

ጸሃፊውን ለማግኘት ከፈለጉ eyobekebede1@gmail.com ይጠቀሙ።

Is this the most farcical use of taxpayers’ money ever: Ethiopian gets legal aid from UK – to sue us for giving aid to… Ethiopia

by Ian Birrell
Mail Online
  • The farmer claims aid is funding a despotic one-party state in his country

  • Alleges regime is forcing thousands from their land using murder and rape

  • Prime Minister David Cameron says donations are a mark of compassion

  • If farmer is successful, Ministers might have to review overseas donations

Gift: Prime Minister David Cameron claims the donations are a mark of Britain's compassion

An Ethiopian farmer has been given legal aid in the UK to sue Britain – because he claims millions of pounds sent by the UK to his country is supporting a brutal regime that has ruined his life.
He says UK taxpayers’ money – £1.3 billion over the five years of the coalition Government – is funding a despotic one-party state in his country that is forcing thousands of villagers such as him from their land using murder, torture and rape.
The landmark case is highly embarrassing for the Government, which has poured vast amounts of extra cash into foreign aid despite belt-tightening austerity measures at home.
Prime Minister David Cameron claims the donations are a mark of Britain’s compassion.
But the farmer – whose case is set to cost tens of thousands of pounds – argues that huge sums handed to Ethiopia are breaching the Department for International Development’s (DFID) own human rights rules.
He accuses the Government of devastating the lives of some of the world’s poorest people rather than fulfilling promises to help them. The case comes amid growing global concern over Western aid propping up corrupt and repressive regimes.
If the farmer is successful, Ministers might have to review major donations to other nations accused of atrocities, such as Pakistan and Rwanda – and it could open up Britain to compensation claims from around the world.
Ethiopia, a key ally in the West’s war on terror, is the biggest recipient of British aid, despite repeated claims from human rights groups that the cash is used to crush opposition.
DFID was served papers last month by lawyers acting on behalf of ‘Mr O’, a 33-year-old forced to abandon his family and flee to a refugee camp in Kenya after being beaten and tortured for trying to protect his farm.
He is not seeking compensation but to challenge the Government’s approach to aid. His name is being withheld to protect his wife and six children who remain in Ethiopia.
‘My client’s life has been shattered by what has happened,’ said Rosa Curling, the lawyer handling the case. ‘It goes entirely against what our aid purports to stand for.’
Mr O’s family was caught in controversial ‘villagisation’ programmes. Under the schemes, four million people living in areas opposed to an autocratic government dominated by men from the north of the country are being forced from lucrative land into new villages.
Their land has been sold to foreign investors or given to Ethiopians with government connections.
People resisting the soldiers driving them from their farms and homes at gunpoint have been routinely beaten, raped, jailed, tortured or killed.

Exodus: The farmer claims villagers are being attacked by troops driving them from their land

‘Why is the West, especially the UK, giving so much money to the Ethiopian government when it is committing atrocities on my people?’ asked Mr O when we met last year.
His London-based lawyers argue that DFID is meant to ensure recipients of British aid do not violate human rights, and they have failed to properly investigate the complaints.
Human Rights Watch has issued several scathing reports highlighting the impact of villagisation and showing how Ethiopia misuses aid for political purposes, such as diverting food and seeds to supporters.
Concern focuses on a massive scheme called Protection of Basic Services, which is designed to upgrade public services and is part-funded by DFID.

Ethiopian-federal-police-on-action

 

Force: Ethiopian federal riot police point their weapons at protesting

students inside Addis Ababa university in the country’s capital, Addis Ababa

Critics say this cash pays the salaries of officials implementing resettlements and for infrastructure at new villages.
DFID officials have not interviewed Mr O, reportedly saying it is too risky to visit the United Nations-run camp in Kenya where he is staying, and refuse to make their assessments public.
A spokesman said they could not comment specifically on the legal action but added: ‘It is wrong to suggest that British development money is used to force people from their homes. Our support to the Protection of Basic Services programme is only used to provide healthcare, schooling, clean water and other services.’
As he showed me pictures on his mobile phone of his homeland, the tall, bearded farmer smiled fondly. ‘We were very happy growing up there and living there,’ he said. This was hardly surprising: the lush Gambela region of Ethiopia is a fertile place of fruit trees, rivers and fissures of gold, writes Ian Birrell
That was the only smile when I met Mr O in the Dadaab refugee camp in Kenya last year. He told me how his simple family life had been destroyed in seconds – and how he blames British aid for his misery. ‘I miss my family so much,’ he said. ‘I don’t want to be relying on handouts – I want to be productive.’
His nightmare began in November 2011 when Ethiopian troops accompanied by officials arrived in his village and ordered everyone to leave for a new location.
Men who refused were beaten and women were raped, leaving some infected with HIV.
I met a blind man who was hit in the face and a middle-aged mother whose husband was shot dead beside her – she still bore obvious the scars from her own beating and rape by three soldiers.
Unlike their previous home, their new village had no food, water, school or health facilities. They were not given farmland and there were just a few menial jobs.
‘The government was pretending it was about development,’ said Mr O, 33. ‘But they just want to push the indigenous people off so they can take our land and gold.’
After speaking out against forced relocations and returning to his village, Mr O was taken to a military camp where for three days he was gagged with a sock in his mouth, severely kicked and beaten with rifle butts and sticks.
‘I thought it would be better to die than to suffer like this,’ he told me.
Afterwards, like thousands of others, he fled the country; now he lives amid the dust and squalor of the world’s largest refugee camp. He says their land was then given to relatives of senior regime figures and foreign investors from Asia and the Middle East.
‘I am very angry about this aid,’ he said. ‘Britain needs to check what is happening to its money.
‘I hope the court will act to stop the killing, stop the land-grabbing and stop your Government supporting the Ethiopian government behind this.’
As the dignified Mr O said so sagely, what is happening in his country is the precise opposite of development.

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት… የህወሃት ሰዎች ጉድ!

 በዝርፊያ ወንጀል ተጠርጥረው በተከሰሱ የደኅንነት ሠራተኞች ላይ ምስክሮች ተደመጡ

በውጭ ዜጋ ላይ ዝርፊያ በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው በተከሰሱ የደኅንነት ሠራተኞች ላይ ምስክሮች መደመጥ ጀመሩ፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአገር ውስጥ ደኅንነት ሠራተኛ በሆኑት አቶ ዮሐንስ ኪሮስ አብዩና በአቶ በኩረ ጽዮን አብረሃ ዜና፣ እንዲሁም ሾፌር መሆኑ በተገለጸውና ተባባሪ ነው በተባለው የኑስ አብዱልቃድር መሐመድ ላይ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን ምስክሮች መስማት የጀመረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ነው፡፡

tplf
ክሱ እንደሚለው፣ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከአሥር ወራት በፊት ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 19 ልዩ ቦታው ደንበል ሲቲ ሴንተር ሕንፃ አካባቢ፣ ሚስተር ካሊድ አዋድ የተባሉ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸውን ግለሰብ ያገኟቸዋል፡፡
ግለሰቡን ሲፈትሿቸው 1,200 ዶላርና 1,600 የሳዑዲ ሪያል አግኝተው ከወሰዱ በኋላ፣ ወደ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው እንዳሳደሯቸው ክሱ ያስረዳል፡፡ በማግሥቱ ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. የግል ተበዳይን ቤታቸው በመውሰድ ቤታቸውን በመበርበርና የተቆለፈ ሳምሶናይት በመስበር 8,000 የሳዑዲ ሪያልና 2,000 ዶላር፣ በድምሩ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር 106,880 ብር ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውንም በክሱ ተጠቁሟል፡፡
ሾፌር መሆኑ የተገለጸው የኑስ አብዱልቃድር የተባለው ተርጣሪ ደግሞ ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር፣ የግል ተበዳይ የሆኑትን የሚስተር ካሊድ አዋድን ቦታና እንቅስቃሴ በመጠቆም፣ እንዲሁም የተሽከርካሪ አገልግሎት በመስጠትና በወንጀሉ ተሳትፎ በማድረግ 13,000 ብር ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ክሱ ያብራራል፡፡

የደኅንነት ሠራተኞቹ የግል ተበዳይን በቁጥጥር ሥር ባዋሉበት ዕለት በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን፣ የተበዳዩ ሠራተኛ መሆናቸው ለተገለጸ ግለሰብ ስልክ ደውለው 100 ሺሕ ብር ካልሰጧቸው ተበዳዩ እንደማይፈቱ መግለጻቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ፈጸሙት በተባለው ገንዘብ ወስዶ መሰወርና ጉቦ መጠየቅ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው፣ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ የሚያስረዱለትን ሦስት ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
የዓቃቤ ሕግ የመጀመሪያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ሾፌሩ ስልክ ደውሎላቸው 100 ሺሕ ብር ካልሰጧቸው ተበዳዩን እንደማይለቋቸው እንደገለጹላቸውና በድጋሚ ከደኅንነት ሠራተኛው በኩረ ጽዮን ጋር በመሆን የተጠየቀውን 100 ሺሕ ብር ወደ 80 ሺሕ እና 50 ሺሕ ብር ዝቅ በማድረግ እንደተደራደሯቸው መስክረዋል፡፡
ሁለተኛው ምስክር የግል ተበዳዩ ሲሆኑ፣ በክሱ ላይ የሰፈረውን ቃል በቃል አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቀሪ ምስክር ለመስማት ለሚያዝያ 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

EMF

የስልክና የኢንተርኔት ስለላ እሰጥ አገባ

‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቃወሙትን ዜጎች ለማፈን የስልክና የኢንተርኔት ስለላ ያካሂዳል›› ሒዩማን ራይትስ ዎች

‹‹ቅርፁን ቀየረ እንጂ የተለመደ ውንጀላ ነው›› የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት

Redwan

የኢትዮጵያ መንግሥት የቴሌኮሙዩኒኬሽንና የኢንተርኔት አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም

ዜጎቹን እየሰለለ ነው በማለት፣ መቀመጫውን በኒውዮርክ አሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች ወቀሳ አቀረበ፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገር አዘጋጀሁት ባለውና በተጠናቀቀው ሳምንት ይፋ ባደረገው ባለ 100 ገጽ ሪፖርት ነው የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ነው በማለት የኮነነው፡፡ ‹‹የምናደርገውን በሙሉ ያውቁታል›› በሚል ርዕስ ይፋ የሆነው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለስለላ ተግባሩ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘ፣ የስለላ ተግባሩን የሚፈጽመውም በአብዛኛው በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ላይ ነው ሲል ወንጅሏል፡፡

ከ100 በላይ በመንግሥት የቴሌኮምና ኢንተርኔት ስለላ የተያዙና ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንን፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት የደኅንነት ሠራተኞችንና የሌሎች አሥር አገሮች የደኅንነት ባለሙያዎችን አነጋግሮ ሪፖርቱን ማውጣቱን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

በተለይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም አገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማንኛውም መንገድ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ይሰለላሉ፣ የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በተለይ ደግሞ ከውጭ አገር የተደወለ ከሆነ ያለ ግለሰቦቹ ፈቃድ ወይም ዕውቅና ተጠልፎ እንደሚቀዳ የሒዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያስረዳል፡፡

ሰላማዊ ሠልፎች በሚኖሩበት ጊዜ በተለይ ሠልፍ በሚደረግበት አካባቢ የሞባይል ስልክ ኔትወርክ የሚቋረጥ መሆኑን፣ አንዳንዴ ደግሞ ዋነኛ የሠልፉ አዘጋጆች ባሉበት ቦታ የስልክ ልውውጣቸውን መሠረት በማድረግ እንዲያዙ የሚደረግ መሆኑን ሪፖርቱ ያብራራል፡፡

‹‹አንድ ቀን የደኅንነት ሰዎች መጡና አሠሩኝ፡፡ ከዚያም እኔን የሚመለከቱ ነገሮች አሳዩኝ፡፡ የተደዋወልኳቸውን ስልኮች ዝርዝር በሙሉ አሳዩኝ፡፡ ከዚያም አልፈው በስልክ ከወንድሜ ጋር የተለዋወጥኩትን መልዕክት አስደመጡኝ፡፡ ይዘው ያሠሩኝ ከወንድሜ ጋር ስለፖለቲካ በስልክ ስላወራን ነው፡፡ ይህ የሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ የሞባይል ስልክ ባለቤት በሆንኩበት ወቅት ነው፡፡ አሁን ግን በነፃነት ማውራት እችላለሁ፤›› ሲል አንድ ስሙ ያልተገለጸ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆነ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ደረሰብኝ ያለው እንግልት በሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ተካቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ስለላውን በስኬታማ መንገድ እንዲያካሄድ የሚያስችሉ መሣሪያዎችን በማቅረብ ረገድ ዜድቲኢ የተባለው የቻይና የቴሌኮም ኩባንያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡

ዜድቲኢ ከተባለው የቻይና ኩባንያ በተጨማሪ በርካታ የአውሮፓ ኩባንያዎች የተለያዩ የስለላ ቴክኖሎጂዎችን ለኢትዮጵያ መንግሥት አቅርበዋል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ከእነዚህም መካከል መቀመጫውን በእንግሊዝና በጀመርመን ያደረገው ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለ ኩባንያ የሚያመርተው “Finfisher” (ፊንፊሸር) የተባለ ዘመናዊ የስለላ ሶፍተዌር፣ እንዲሁም ሃኪንግ ቲም የተባለ በጣሊያን የሚገኝ ኩባንያ የሚያመርታቸው ‹‹ሪሞት ኮንትሮል ሲስተም›› የተባሉ የስለላ ቴክኖሎጂዎችን የኢትዮጵያ መንግሥት በእጁ አስገብቶ እየተጠቀመበት ነው ሲል ሪፖርቱ ያብራራል፡፡

እነዚህ ከላይ የተገለጹት ሶፍትዌሮች ለደኅንነት ተቋማትና ለስለላ ሠራተኞች የሚፈለጉ ሰዎችን መረጃዎች ለማግኘት የሚያስችሉ እንደሆነ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

የተጠቀሱት ሶፍትዌሮችን በመልቀቅ የሚፈለጉ ሰዎች ኮምፒዩተሮችንና ስልኮችን እንዲያጠቁ፣ በተጨማሪም ያለ ኮምፒዩተሮቹ ወይም ስልኮቹ ባለቤቶች ዕውቅና መረጃውን ማየት፣ የኮምፒዩተሮቹን ካሜራ በመጠቀም ምን እየተከናወነ መሆኑን ከርቀት መመልከት የሚያስችሉ ናቸው ሲል የሒዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያስረዳል፡፡

በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሱት ዜድቲኢ እና ጋማ ኢንተርናሽናል የቴክኖሎጂ ምርቶቻቸውን ለኢትዮጵያ መንግሥት ከማቅረባቸው በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይፈጸምባቸው የሚያስችሉ ገደቦችን አካተው እንደሆነ ለማነጋገር ቢሞክርም፣ ምላሽ ሊሰጡት እንዳልቻለ የሒዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ይገልጻል፡፡

በአሁኑ ወቅት በ800 ሚሊዮን ዶላር የቴሌኮም ማስፋፊያ ፕሮጀክት እያከናወነ የሚገኘው የቻይናው ዜድቲኢ የአዲስ አበባ ቢሮ ሪፖርቱን አስመልክቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጥያቄ የቀረበለት ቢሆንም፣ ጉዳዩ ‹‹መንግሥትን የሚመለከት ነው›› በማለት ማብራርያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የመንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አመራሮች በጽሑፍና በስልክ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡

ይሁን እንጂ የመንግሥትን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጡት ምላሽ፣ የሒዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት የተለመደ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ሒውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያን ገጽታ የማበላሽት የተለመደ ዘመቻው በመሆኑ የተለየ የምለው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የቴሌኮም አገልግሎትን ከከተሞች አልፎ በገጠር አካባቢዎች እያስፋፋ የሚገኘው አንዱ የልማቱ አካል በመሆኑ እንጂ ስለላን ለማስፋፋት አይደለም፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ይህ የሒዩማን ራይትስ ዎች የተለመደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ አሁን በቴሌኮም ኢንዱስትሪው አማካይነት የሰብዓዊ ጥሰት ይፈጸማል በማለት ያወጣው ሪፖርት የሄደበት መንገድ መቀየሩን ያሳይ እንጂ ግቡ አንድ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፈኑ “ወያኔ እጅ ገብተዋል”

የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።

በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል።

ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል። “ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት በማንሳት ወያኔን ለመታገል ከተነሱ ጋር ተቀላቅለዋል በሚል ስማቸው መመዝገቡንና ወደ ደቡብ ሱዳን ማቅናታቸው በመታወቁ ህወሃቶች እጅ ሊወድቁ ችለዋል” ብለዋል። ምንጩ ይህንን ይበሉ እንጂ አቶ ኦኬሎ አክዋይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትን ምክንያት በርግጠኛነት ሃላፊነት ወስዶ የገለጸ ወገን አልተደመጠም። ኢህአዴግም ቢሆን የቀድሞውን ሹመኛ ስለመያዙ ይፋ ያደረገው ነገር የለም።

ከደቡብ ሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የኑዌር ተወላጅ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጦር ጋር በመሰለፍ የሳልቫ ኪርን ሃይል ሲወጉ ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የኢህአዴግን ሰራዊት መለያ የለበሱ ኑዌሮች መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ያመለከቱት ምንጭ “ደቡብ ሱዳን እየወጋት ካለው ኢህአዴግ ጋር አብራ የቀድሞውን የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳደር ከምድሯ ላይ እንዲታፈኑ መፍቀዷ ቅሬታ ያስነሳል” ብለዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዛ ማቅናታቸውን ባሥልጣኑ “ታላቅ ጥፋት” ብለውታል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በቅርቡ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

አስማተኛው የኢኮኖሚ እድገት! (በ ገብርኤሉ ተስፋዬ)

Yeweyane-firewoch

ከየት ጀምሬ ወደየት እንደምሄድ አላውቀውም፣ አሁን አሁን የእድገት መለኪያው ምን እንደሆነ እንኩዋን ግራ ገብቷችዋል:: ወይስ የኢኮኖሚ እድገቱ ለኢትዮጲያውያን ሳይሆን ኢትዮጲያን ለሚያስተዳድሯት ብቻ ነው ወይ? እውነቱ በገሀድ ግልፅ ብሎ እያለ ካለፉት አስር አመታት ጀምሮ ጆሮዋችንን በሁለት ዲጅት ሀገሪቱ አድጋለች እያሉ ሲያደነቁሩን ከረሙ:: ለኔ እድገት የሚለው ቃል በአሁን ሰሀት ስድብ መስሎ እየታየኝ ነው:: የተወሰኑ ሰዎች ብር በብር ላይ አካበቱ፣ሀፍታም ሆኑ፣ ህንፃ ገነቡ፣ከመኪና መኪና ቀያየሩ ወዘተ እየተባለ  በኢትዮጲያ ስም መነገዱ አግባብ አይደለም:: ለመሆኑ የኢትዮጲያ ህዝብ ጠግቦ የሚበላው ሀሁን ነው ወይስ የዛሬ 10 እና 20 አመት በፊት ነው? መልሱን የሁላችንም ልቦና ያውቀዋል! ህዝቡ አንገቱን ደፍቶ ሁሉን ነገር ሰምቶ እንዳልሰማ  አይቶ እንዳላየ ዝም ሲል ጅል የሆነ መሰላችው:: እስቲ የኢትዮጲያ እድገት ተብየው ያመጣውን ለውጥ ለመመልከት ልሞክር::

በመጀመሪያ መመለከት የምፈልገው የምግብ ዋስትናን ነው::የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆሉን የማያምኑ ለሆዳችው የሞቱ እነሱ ብቻ ሲበሉ ሌላውም የበላ የሚመስላችው ብዙ አሉ:: ሆኖም ግን እውነት እውነት ነች እና ምንም ምንም ቢሉ እውነትነቷን  አትቀይርም:: ስለምግብ ዋስትና ለመናገር በአዲስ አበባ ስለሚኖረው ህዝብ መናገርን መረጥኩ ምክንያቴም አዲይስ አበባ የኢትዮጲያ ዋና ከተማ እንደ መሆኑዋ መጠን፣የኢህአዴግ አመራሮች ስለእድገት ሲያወሩ የሚጠቅሱዋት ከተማ ስለሆነች እና በጣም ብዙ ህዝብ(ከ 5 እስከ 6 ሚልየን) ስለሚኖርባት ነው:: እዝይጋ ሥራ አልባ የሆኑትን፣ሚበላ የሌላችውን ብዙዎቹን የማሀበረሰባች አካላትን ሳይሆን ማየት የምፈልገው ስራ አገኘው ብሎ በመንግስት መስሪያቤት ተቀጥሮ የሚሰራውን ነው:: አንድ የመንግስት ሰራተኛ የድግሪ ምሩቅ የሆነ በወር 1600 ብር የሚያገኝ ሲሆን ከዚያ ላይ 250 እስከ 300  ግብር ይከፍላል በእጁ ላይ 1300 ይቀረዋል እንበል ፣ የቤት ኪራይን በተመለከት በአሁን ሰሀት በአዲስ አበባ አንድ ክፍል ቤት በትንሹ ከ 700 እስከ 800 ብር የሚያወጣ ሲሆን ከ 1300 ላይ ይሄን ብር ስናነሳ  500 ብር አካባቢ ይቀረዋል፣ በየቀኑ ለትራንስፖርት በትንሹ 3 ብር አወጣ ቢባለ 400 ብር እጁ ላይ ቀረው ማለት ነው:: እስቲ ይሄ ሰውዬ ሙሉ ጤነኛ ነው የህክምና ወጪ አያስፈልገው ቤተሰብ (ልጆችም) የሉትም ብንል እንኳን 400 ብር አያምስት ኪሎ ጤፍ ወይም 4 ኪሎ ሥጋ በወር አይገዛለትም:: በአስማት መኖር ማለት ይሄ ነው!! በየቦታው እንደምንሰማው  ከ100,000 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ብቻ ይገኛሉ:: እነሱም ከእድገቱ ጋር  ነው አብረው የመጡት እያሉን ነው! ብሎ ብሎ ጉርሻ መሸጥ የተጀመረበት አገር እድገት አለ ከሚሉ አስማት አለ ቢሉ ይሻላል::እርግጥ ነው የተወሰኑ ሰዎች በአዲስ አበባ  የምግብ ዋስትናችው የተጠበቀ ነው  ከነርሱም ብዙወቹ የገዝው ፓርቲ አባላት ናችው:: እና ስለ እድገት ሲወራ የኢትዮጲያ ህዝብ በልቶ ጠግቦ አደረ  የሚለው ተረት ባይተረክ መልካም ነው እላለው::

ethiopia-Food

በመቀጠል ማየት የምፈልገው ማንኛው የምራባውያን ሀገር የኢኮኖሚ እድገት መጣ ብለው ሲያወሩ ለማሀበረሰባችው የተሻለ የስራ እድልን ፈጥረው ሲገኙ ነው:: በአሁን ሰሀት አብዛኛው የኢትዮጲያ ወጣት የት ነው የሚገኘው ጫት ቤት፣ መጠጥ ቤት፣ሺሻ ቤት፣ ወይስ ኑሮውን ለማሸነፍ ከሀገር ወቶ ተሰዶ በረሀ በልቶት ቀርቷል:: ማንም በአገሩ መኖርን የሚጠላ የለም! ወጣቱ ከሀገር ተሰዶ ሲወጣ ነጮቹ ናፍቀውት አይመስለኝም:: ከሀገር ተሰዶ በረሀ ላይ መሞት እንዳለ፣ በሀር ውስጥ የሻርክ እራት መሆን፣መደፈር፣ ከህንፃ ላይ ተወርውሮ መሞት አልፎ ተርፎም የሰውነት አካላችው እስከመሸጥ እንደሚደርስ እያወቁ ሀገራችውን ጥለው የሚሄዱት ቁጥር መጨመሩ ምንን ያሳያል? ምን ያህል ወጣቱ በኢህአዴግ አመራር እንደተማረረና  ተስፋ እንደቆረጠ ነው የሚያሳየን:: ሌላው የሴት እህቶቻችን ቁጥር በወሲብ ንግድ ላይ እየጨመረ መሄዱ በካንፓስ ደረጃ መርጠው  የተማሩት ፊልድ ነው ብዬ አላምንም ለኔ ይሄ የሚያሳየው ወጣቱ ከስራ ማጣት የተነሳ ኑሮን ለማሸነፍ የማይፈልገው አዝቀጥውስጥ እየገባ እንዳለ ነው:: ከሰሞኑ ደግሞ  ይባስ ብሎ እድሜያችው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጅ አገረዶችን በየድረ ገጹ ለወሲብ ሽያጫ አቅርበዋል፣ የሚገርም ነው እዚም ዘመን ላይ ደረስናል ያስብላል!

በሶስተኛ ደረጃ ማየት የምፈልገው ከምግብ ውጪ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ነገሮች ብዬ የምላችውን የውሀና የመብራት አቅርቦትን ነው:: በአዲስ አበባ ከተማ የመብራትና የውሀ ነገር አነጋገሪ ከሆነ ሰንብቷል:: አብዛኛው የከተማው ክፍሎች ውሀና  መብራት በፈረቃ ነው የሚያገኙት:: ጥቁር አንበሳን የሚያህል ሆስፒታል በየህለቱ በጣም ብዙ በሽተኞችን የሚያስተናግድ ሆኖ ሳለ ለዚህ አይነቱ ችግር መጋለጡ በጣም አሳዛኝ ነው:: የእድገት አንዱ መሰረቱ የህዝብን የ መጠጥ ውሀ እና የመብራት አቅርቦት ማሟላት ወይም ስርጭቱን መጨመር ሲሆን በአዲስ አበባ የምናየው ነገር ግን የተገላቢጦሽ ነው::

የህዝቡን የምግብ ዋስትና ካልጠበቁ ወይም ካላሻሉ፣ ለወጣቱ የስራ እድል ማመቻችት ካልቻሉ፣ በቂ ወይም ተመጣጣኝ የውሀ እና የመብራት አቅርቦት መስጠት ካልቻሉ ታዲያ  የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከህዝቡ ህየዘረፉ በሚወስዱት  ብር የሚገነቡት እንፃን በማየት ነው እድገት መጣ የሚባለው:: ኢትዮጲያ በየአመቱ በቢልየን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ታገኛለች ከዚህ ውስጥ ብዙው ገንዘብ የሚጠፋው በ ጥቁር ፕሮጀክት(Black project) ነው:: የ ጥቁር ፕሮጀክት ማለት መንግስት በህዝብ ስላልተመረጠ ስልጣኑን ለማቆየት ሲል  ለማሀበረሰቡ ብልፅግና የሚውለውን ገንዘብ ቀይሶ ለካድሬወችና  ለሰላዮች(ለሆድ አደሮች) እድሜውን ለማራዘም እንዲሁ የሚበትነው ብር ነው:: ከሰሞኑም እንደሰማነው መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲን እና አባላታችውን ለመሰለል በሚልዮን ዶላር የሚቆጠር  የህዝቡን  ንብረት እንደሚጠቀም(እንደሚበትን) ተገልጿል::ሌላው በሀገሪቷ ውስጥ መጣ እየተባለ የሚያወሩለት የኢኮኖሚ እድገት መሰረት አልባ ስለሆነ መሰረታዊ ለውጦችን ሊያመጣ አልቻለም ይህን ልል   የቻልኩበት ምክንያት

1.  ስለኢኮኖሚ እድገት ሲወራ ብዙም ጊዜ ትኩረት  የማይሰጠው ግን ለኢህአዴግ ዋንኛው የገንዘብ ምንጭ የሆነው የስራአጥ እህትና ወንድሞቻችን በየሀገሩ የሚሰደድ ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሄዱ ነው::ይሄን ስል በአሁን ሰአት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያን በየአገሩ ተበትነው የሚገኙ ሲሆን በየ ወሩ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለቤተሰቦቻችው ይልካሉ:: በተዘዎዎሪ ይሄን ብር ኢህአዴግ የኢኮኖሚ እድገት ነው ይላለ:: ዕህት እና ወንድሞቻችንን በተለያዩ ሀገሮች በትኖ በነሱ ጀርባ ላይ ቁጭ ብሎ መሰረታዊ እድገት ሊመጣ አይችልም::

2. በመቶ ሺዎች  የሚቆጠሩ ህዝቦችን ለብዙ ሺ አመታት ከኖሩበት ቦታ አፈናቅሎ ለተለያዩ የእንድ እና የውጭ ሀገር ባለሀፍቶች መሬታችውን በመሸጥ የኢኮኖሚ እድገት አመጣን ማለት አይቻልም::እነዚ ሰዎች መሬታችው ሲወሰድ በመንግስት ብዙ ነገር ቃል የተገባላችው ቢሆንም አንዳችውም ግን እውን አልሆኑም:: በአሁን ሰሀት ከተወሰኑት በስተቀር በሙሉ በኬንያና በተለያዩ ቦታወች ተሰደው ሲገኙ በተቃራኒው ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች የከበሩበትን መንገድ እናያለን:: ማንኛውም አይነት እድገት በመጀመሪያ ደረጃ አላማ ሊያደርግ የሚገባው የመሀበረሰቡን ጥቅም ማስከበር ነው::

3. ምህራባዊያን(mainly US,UK and ISREAL) ኢትዮጲያ ያላት የጆክራፊ አቀማመጥ ቴሬሪስትን ለመዋጋት ያመቻል ብለው ስለሚያምኑና የኢትዮጲያ መንግስትም ጥቅሙን ለማስከበር አሽከር እንደሆነ ስላዩ  በየአመቱ የሚሰጡት እርዳታ እየጨመረ መሄዱ ይህን እና የመሳሰሉትን አጋጣሚወች በመጠቀም በኢትዮጲያ  እድገት አመጣው እያሉ ያወራሉ:: መሰረታዊ ችግሮች እየተባባሱ ህዝቡም ኑሮ እያሰቃየው፣ ወጣቱም ሥራ አልባ ሆኖ በየአረብ አገሩ እየተንከራተተ እድገት መጣ ማለት አይቻልም!! በሀገሪቷ ውስጥ የሚገባውን ገንዘብ በሙሉ ኢህአዴግ እና ካድሬዎቻችው አፍኖ በመብላት መሰረታዊ ለውጦች ሊመጡ አይችልም::  ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጲያዊ የተሻለ አመራር  ያለው መንግስት ለማምጣት የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ አለብን!!!!!!!!!

ፍቅር ለኢትዮጲያ ህዝብ!!!