Archive | March 1, 2014

ሰሞነኛ ትዝብቶች …..

ግርማ ሠይፉ ማሩ

girmaseifu32@yahoo.com

ኢህአዴግ የሚባል ገዢ በሄድንበት ሁሉ ለትዝብት የሚሆኑ ነገሮችን ማስቀመጥ አይተውም እኛም አንጀታችን ማረሩ ይቀጥላል፡፡ አንዳንዶቻችን ለአንጀታችን ማረር መፍትሔ ብለን በፅሁፍ አስፍረን እንገላገላለን ያለበለዚያ ለስንቱ አውርተን እንዘልቃለን፡፡ የሚያነብ ካለ ደግሞ ማስተካከያ ይወስዳል፡፡ ለሚስተካከሉት ማለት ነው፡፡ ተጠያቂ ካለ ደግሞ እንዲጠየቅ ማድረግ የእርምጃው አንድ አካል ይሆናል፡፡ ኢህአዴግ ግን አፍ እንጂ ጆሮ የለውም ሰለሚባል ተጠያቂነት ያሰፍናል ብሎ ማመን አስቸጋሪ ነው፡፡ አባላቶቹ ሲያጠፉ ለአሽከርነት ቀብድ እንደከፈሉ ተቆጥሮ ይመዘገብና ሲፈለግ ይመዘዛል እንጂ በወቅቱ እርምጃ አይወስድም፡፡
አንድ ሰሞን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ የነበረ አስቻለው የሚባል ጓደኛዬ በከተማው ውስጥ መንገድ ዘግተው አጥር የሚያጥሩ ባለስልጣናትን ማሾር ጀምሮ ነበር፡፡ በዚያ መነሻ ብዙ የከተማ መንገዶች ተከፍተው መተንፈሻ አግኝተን ነበር፡፡ ባላስልጣናቱ በመንግሰት ገንዘብ ህገወጥ ግንባታ ማካሄዳቸው ከተጠያቂነት እንደማያድናቸው አስረግጦ ሲነገራቸው ማፍረስ ጀመሩ፡፡ እኛም ጉድ ተሰኝተን በቀጣይ መከላከያም ሆነ ቤተ መንግሰት የእግረኛ መንገድ እየዘጉ ማለፍ ክልክል ነው ማለት አይቻሉም ጥበቃቸውን ውስጥ ግቢያቸው ያደርጋሉ ብሎን በቴሌቪዥን መስኮት ተመለከትነው፤ ይህም ሳይተገበር እርሱም ተገፍቶ ከሀገር ወጥቶ ይኖራል፡፡ ይህን ጉድ ያስታወሰኝ በቅርቡ ቂሊንጡ እስር ቤት ሄጄ ያየሁት ጉድ ነው፡፡ አቶ አስራት ጣሴን በገደብ ከተጣለበት እስር የሚታሰብ ይሁን አይሁን ባይታወቅም በጣቢያ ለሶሰት ቀን እና በቂሊንጡ ለሰባት ቀን ቆይቶዋል፡፡ እንዳሰቡት አስራት ጣሴን አንገት ያስደፉት አልመሰለኝም ይልቁንም ውስጥ ገብቶ ተምሮ የወጣ ይመስለኛል፡፡ ብዙ ወዳጆች እንዳፈራ ነው የነገረኝ፡፡ አቶ አስራትን ለማውጣት እንደ ማስገባት ቀላል አልነበረም፡፡ የማውጣት ሂደቱም ግምገማ/ቢ.ፒ.አር ሊሰራለት እንደሚገባ የሚያሳብቅ ነው፡፡ ውስጥ ገብቼ ምን ያህል ደቂቃ እንጠብቅ ብዬ ሰሟገት ከ20 -30 ደቂቃ ቢሆን ነው ውጪ ጠብቁ ተብለን ወጥተን አላፊ አግዳሚ መታዘብ ጀመርን የተባለው ደቂቃ አለፈ ከሁለት ሰዓት በላይም ሆነ፡፡ ከቅጥር ጊቢ ውጭ ያለስራ መቀመጣችን አንድ ነገር ይዞ ብቅ አለ፤ ወዲህ ወዲያ ማየት እና መንቀሳቀስ፡፡ እየተንቀሳቀስን እያለ የጊቢው አጥር በግምት ርዝመቱ ከሁለት መቶ ሜትር እና ቁመቱ ከሁለት ሜትር በላይ የሚሆን ነው፡፡ ይህ አጥር ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ወደ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚሄደውን አዲስ መንገድ ዘግቶ ተገትሮዋል፡፡ የመንገድ ሰራውን አስቁሞታል፡፡ ይህ አጥር የተሰራው በቅርብ ሲሆን ለምን 12 ሜትር ከፕላን ወጥቶ እንደ ተሰራ ግርምት ፈጠረብኝ፡፡ ይሄኔ ነው አሰቻለው ትዝ ያለኝ መፍትሔውን ሳሰብ አጥሩ መፍረስ አለበት ግን ይህ የሚፈርስ አጥር የተገነባው በህዝብ ሀብት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ መፍትሔው መፍረስ ብቻ ነው፡፡ ይህ አጥር በዚህ ሁኔታ ከፕላን ወጥቶ እንዲሰራ ያደረገ መጠየቅ አለበት፡፡ ከፕላን አልወጣንም የሚል መከራከሪያ ካላ ይህን ፕላን አዘጋጅቶ የሰጠ መሃንዲስ መንገድ መኖሩን አላውቅም ነበር ሊለን ስለማይችል ተጠያቂ መሆን ይኖርበታል፡፡ በማነኛውም ሁኔታ ግን የተጠያቂ ያለ ብለን እንድንጮህ ይህን ሀሳብ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ከአጥሩ ጋር ተያይዘው የሚፈርሱ ብዙ የመብራትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መኖራቸውን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም፡፡ ለማነኛውም ይህን ፅሁፍ ያነበበ ጋዜጠኛ የእስር ቤቱንም ሆነ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሰዎቹን አነጋግሮ ለህዝብ ይፋ ያድርግልን፡፡ አንገታችን ታንቆ በምንከፍለው ግብር የሚሰራ መንገድም ሆነ አጥር እንደፈለገ የሚፈርስ መሆን የለበትም፡፡
ሌላው ሰሞነኛ ጉዳይ ደግሞ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወንበራቸውን በቅጡ ሳያደላድሉ ፈተና የበዛባቸው መሆኑ ነው፡፡ አንዱ የፈተናቸው ምንጭ ደግሞ አቶ አለምነው መኮንን የተባለ ካድሬ ነው፡፡ አቶ አለምነውን አንተ ያልኩት ከተመስገን ደሳለኝ ተውሼ ነው፡፡ አምባገነን ሰርዓትን የሚመሩ ሰዎች አንተም ሲበዛባቸው ነው ሰለሚል ማለቴ ነው፡፡ ለነገሩ እኛም ሰፈር ቢሆን አንቱ ብሎ ስድብ የለም፡፡ አቶ አለምነው ደግሞ ሰድበውናል ስለዚህ መሰዳደብ ሊጀመር ከሆነ አንቱታው አይገባቸውም፡፡ ብአዴን ለአማራ ህዝብ ክብር ሲል ይህን ካድሬ ይቅርታ እንዲጠይቅ በማድረግ ከኃላፊነቱ ማንሳት ሲገባው በየቦታው እየዞረ ማስተባበሉን ቢያቆም ጥሩ ነው፡፡ ለነገሩ የዚህ ዓይነት አካሄድ በኢህአዴግ መንደር የተለመደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናው በምክር ቤት ቀርበው ይሁን በጋዜጣው መግለጫ አንድ ፋውል መስራታቸው የተለመደ ነበር፡፡ ታዋቂዎቹ ፋውሎች ባንዲራ ጨርቅ ነው፣ የአክስሙ ሐውልት ለወላይታ ምኑ ነው? የመሳሰሉት አሁንም ትዝ ይሉናል፡፡ በዚህ ጊዜ በህዝቡ ዘንድ ጫጫታ ሲነሳ እርሳቸው ማለት የፈለጉት የግል ሚዲያ፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች፣ ኒዎሊብራሎች እንደሚሉት ሳይሆን ይህን ለማለት ነው በማለት እንደምታ ትርጉም ይስጠው ነበር፡፡ አለቆቻቸው ውሃ እየተጎነጩ የፈለጉትን ይናገራሉ፤ ካድሬዎች ምራቃቸው እስኪደርቅ በውሃ ጥም እየተሰቃዩ ለማስተባበል ይሞክራሉ፡፡ ይህ የማስተባበል ዘመቻ በፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው መታወቅ ይኖርበታል፡፡
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ቢሆን በማስተባበል ጫወታው የገቡ ይመስላል፡፡ አቶ አለምነው መኮንን ፀያፍ ስድብ ተሳድቦዋል፡፡ ድምፁ የእኔ ነው ሰድቡ ግን የእኔ አይደለም የሚለውን ቀልድ ትቶ ማሰተባበል ካልቻለ ይቅርታ ይጠይቅ፣ ብሎም ከሃላፊነቱ ይነሳ፡፡ የአቶ ገዱ “አቶ አለምነው ለአማራ ሕዝብ ዕድገትና ብልፅግና ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሰሩ ናቸው” የሚለው ምስክርነት እውነት ከሆነ ጥፋት ማቅለያ እንጂ ከጥፋተኝነት መዳኛ አይደለም፡፡ በፍርድ ቤት ጥፋት አጥፈተሃል አላጠፋህም ተብሎ ሲጠየቅ የቤተሰብ ሃላፊ ነኝ ብሎ እንደ መመለስ ነው፡፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አሁን የያዙት ተግባር ደረጃቸውን አይመጥንም የሚጠበቅባቸው ለተሰደበው ህዝብ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ነው፡፡ እኔ አቶ አለምነው ይሰቀል አላልኩም፤ ይውረድ ነው፡፡
ሌላኛው አስገራሚ ዜና ደግሞ ፖሊሶች ማን ፍርድ ቤት እንደደፈረ አላወቅንም አሉ፡፡ ኮምሽነር ጄነራሉም ማወቅ አልቻልምን አሉ፡፡ አሰቂኝ ዜና ነው፡፡ እኔ የገባኝ ግን ፍርድ ቤት በመድፈር ከተጠረጠሩት ውስጥ ባለ ከፍተኛ ማዕረጎች ፍርድ ቤቱን እንደደፈሩ የሚያሳይ ነው ፍንጭ ነው፡፡ ተራው ወታደር ቢሆን ኖሮ ታንቆ ይስጥ ነበር፡፡ ተራ ወታደሩ አለቆቹ እንዳጠፉ አውቆ ቢናገር ደግሞ የሚከተለውን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ዝም ማለት መርጠዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ በእለቱ ተረኛ የነበሩት አስራ አምስቱም በጋራ ተባብረው ነው ያጠፉት ማለት ነው፡፡ ለጥፋታቸው የሚመጥን ቅጣት ይገባቸዋል፡፡ በነገራችን ላይ ፍርድ ቤት ባይደፍሩም ጥፋተኛ እንዲታወቅ ትብብር ባለማድረጋቸው ሁሉም ጥፋተኞች ናቸው፡፡ ዳሬክተር ጄነራሉ እንደሚሉት ጉዳዩን ወደ እኛ መልሱትና እኛ በተቋም ደረጃ እርምጃ እንውሰድ የምትለውም ፌዝ ቢጤ ነች፡፡ ለማነኛውም ግን ፍርድ ቤቱ አስተማሪ የሆነ ነገር ያደርጋል ብለን እንጠብቃለን፡፡ ይህ ጉዳይ በህዝብ ዓይን እና ጆሮ ሰር ገብቶዋል፡፡ ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ለሚደርስ ጥፋት መርምሮ እንዲይዝ የተቀመጠ አካል ከአስራ አምስት ሰዎች ውስጥ ጥፋተኛ መለየት አልቻልኩም ሲል ግን ትዝብት ውስጥ እንደሚገባ ያለማወቁ ያስተዛዝባል፡፡
በመጨረሻም ለመሰናበቻ የሚሆን ሰለ የካቲት 11 ክብረ በዓል እናንሳ፡፡ ይህ በዓል በየአምሰት ዓመት በሰፊው ይከበር የነበረ ሲሆን አሁን ግን በተለየ ሁኔታ እንደተከበረ አብርሃ ደስታ ነግሮናል፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ምን አልባት በቀጣይ ዓመት በምርጫ ውጥረት ምክንያት ሊሆን ቢችል ብሎ መጠርጠር የአባት ነው፡፡ ግን ምን ችግር አለው በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ከዚህ በበለጠ ቢያከብሩት ገንዘቡ እንደሆነ የፓርቲ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እኔ ግን ግርምት የፈጠረብኝ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ከፍተኛ አመራሮችን(እነ ተፈራ ዋልዋን ጨምሮ) ይዞ ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ሲል ችግር ገጥሞት የነበረው የሱዳን አውሮፕላን ለምን ለህውሓት ብቻ መታሰቢያ እንዲሆነ ተፈለገ የሚለው ነው፡፡ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ይህን አሮጌ አውሮፕላን አይደለም አዲስ ጀት ገዝተው ቢሰጡን የሚበዛብን አይደለም፡፡ ምክንያቱም በነብሰ ገዳይነት ለእስር የሚፈለጉ ሰውዬ እንደፈለጉ የሚወጡበትና የሚገቡበት ሀገር ከዚያም አልፎ ክሳቸው ይነሳላቸው ብሎ የሚከራር መንግሰት ይህ ስጦታ ቢያንስ እንጂ አይበዛም፡፡ የእነ ተፈራም ነብስ የህውሓት ነብስ ነች እንዴ እረ እየተስተዋለ፡፡

Ethionetsanet

የአፍሪካ ቀንድ፤ ዙሪያው እሳት መሀሉ ብሶት

  መስፍን ወልደ ማርያም

ታኅሣሥ 2006

Download

የአፍሪካን ቀንድ ሰሞኑን ትኩሳት ይዞታል፤ ሁኔታውን ለማብራራትና ለመተንተን ሰፊ ቦታን ስለሚፈልግ አንባቢው ራሱ እንዲያስብበት በመተው ሁነቶችን ብቻ ማቅረቡ የተሻለ ነው፤ የኢትዮጵያን የውስጥ ሁኔታ ትተን በአፍሪካ ቀንድ የሚከተሉትን የተለያዩ ግጭቶችን እንመለከታለን፤

  1. በጦርነት ሁኔታ ሁኔታ ላይ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች፤–
  • ኤርትራና አትዮጵያ
  • ሰ.ሱዳንና ደቡብ ሱዳን
  1. በውስጥ ብጥብጥ ላይ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች
  • ሰ.ሱዳን በውስጥ
  • ደ.ሱዳን በውስጥ
  • ሶማልያ

በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለጊዜው ግጭት የማይታይባቸው አገሮች ኬንያና ጂቡቲ ብቻ ናቸው፤ ኬንያ ከብሪታንያ ጋር ባለው የቆየ ትስስርና በኬንያ በሚኖሩ የብሪታንያ ሰዎች ምክንያት ጋሻ አለው፤ ጂቡቲም የቆየ የፈረንሳይ ጋሻ ቢኖረውም በአሁኑ ጊዜ አሜሪካም ተጨማሪ ጋሻ ስለሆነ የውጭ ኃይል አይደፍርም፤ ጂቡቲና ኬንያ በእውነትም እንደጌታዋን የተማመነች በግ ናቸው!

የአፍሪካ ቀንድን ውስብስብ የፖሊቲካ ሁኔታ ለመገንዘብ አገሮቹን የሚያካትቱ ማኅበሮች ብዛት መመልከት ነው፤– የአረብ ማኅበር፤ የአሜሪካ ማኅበር፤ የፈረንሳይ ማኅበር፤ የአፍሪካ ማኅበር፤ የትኛው አገር የየትኛው ማኅበር አባል መሆኑን ብቻ ሳይሆን የየትኛው ማኅበር ተቃዋሚ መሆኑንም መረዳት አካባቢው ያለበትን ውስብስብ ሁኔታ ያሳያል፤ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማልያና ጂቡቲ የአሜሪካ ማኅበር አባሎች ናቸው ለማለት ይቻል ይሆናል፤ ጂቡቲና ሶማልያ የአረብ ማኅበር አባሎችም ናቸው፤ በዚያ ላይ አራቱም የአፍሪካ ማኅበር አባሎች ናቸው፤ የማኅበር ትርጉም ትንሽ ያሳስባል።

የአረብ ማኅበር በሰሜን ሱዳን በኩል ሌሎች የማኅበሩን አባላት ግብጽንና ሊብያን ኤርትራን (ተመልካች አባል) ይነካል፤ በሁለቱ ሱዳኖች በኩል የማእከላዊ አፍሪካና የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነበልባል ይታያል፤ በተጠቀሱት የምዕራብ አፍሪካ አገሮች የሚነደው እሳት በሁለቱ ሱዳኖች በኩል አድርጎ ወደሶማልያና ወደኦጋዴን ሲዘልቅ ከግብጽና ከሊብያ የሚወጣው ነበልባልም ወደሰሜን ሱዳን ይደርሳል፤ በዚህ በእሳት በታጠረው የአፍሪካ ቀንድ ሰፈር አንድ የአሜሪካን አውሮጵላን ተመትቶ ጉዳት ሲደርስበት ሁለት ያህል ሰዎችም ቆስለዋል፤ ይህ ሁሉ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን የተከፈተውን የአሜሪካንን ‹‹በሽብር ላይ ጦርነት›› ወደአፍሪካ መሻገሩን የሚያመለክት ይመስላል።

ዛሬ በሁለቱ ሱዳኖች፣ በሶማልያና በኦጋዴን ሰላማዊ ሰዎች ምኑንም በማያውቁት ምክንያት ቤታቸው እየተቃጠለና እየፈረሰ፣ ንብረታቸው እየወደመ፣ በደሀነታቸው ላይ መፈናቀልና  ስደት ተጨምሮ እየተሰቃዩ ናቸው፤ ነገ አንዳንዶቹ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች እንደኢራቅ፣ እንደአፍጋኒስታንና እንደፓኪስታን ሉዓላዊነታቸውን ያጡ አይሆኑም ለማለት ይቻላል? ከአፍሪካ ቀንድ አገሮች ውስጥ እስካሁን ለአሜሪካ ያልገበረው ኤርትራ ብቻ ነው፤ ይህንንም ሁኔታ ለመለወጥ ኤርትራን ማባበል የተጀመረ ይመስላል።

የአፍሪካን ቀንድ ከከበበው ነበልባል ኢትዮጵያ እንዴት መውጣትና ማምለጥ ትችላለች? የውስጥ ጉዳይ አመራሩ ሳይለወጥ የውጭ ጉዳይ አመራሩ አንዴት ይለወጣል? የውጭ ጉዳይ አመራር አብዛኛውን ጊዜ የውስጥ ጉዳይ አመራር ነጸብራቅ ነው ይባላል፤ እስቲ በዚህ አስተሳሰብ እነዚህን በእሳት የተከበቡ አገሮች እንመልከታቸው፤ ከአዲሱ አገር ከደቡብ ሱዳን እንጀምር፤ ገና በሕጻንነት እሳት ነደደበት፤ እሳቱን የፈጠረው ብሶት ነው፤ አዲሱ ፕሬዚደንት እንደኢትዮጵያ የአገዛዙ ሎሌዎች በቤተ ክርስቲያንም የማይወልቅ ሰፊ ባርሜጣ አድርጎ በሱፍ ልብስ እየተንሳፈፈ በጎሣ አድላዊነት መሥራት ሲጀምር ምክትሉ ተቃውሞውን በመግለጽ ሸፈተ፤ ከሠላሳ ዓመታት በላይ ከሰሜን ሱዳን ጋር በጦርነት ሲደማ የኖረው ሕዝብ አሁን ወደሌላ የጎሣ የእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ገባ።

ለየጎሣው ራሳቸውን  በመወከል ሥልጣንን መጋራት የሚፈልጉ ሁሉ ለራሳቸው እንጂ ለሕዝብ የሚያስቡ አይደሉም፤ በመሀከላችንም ብዙ ሰዎች፣ የፖሊቲካ መሪዎች ነን ባዮችም የፖሊቲካ መብትን ጉዳይ በሚገባ ያላሰቡበት ናቸው፤ ለምሳሌ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአመራር ላይ የነበሩት ሰዎች በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የነበረውን የግለሰብ የፖሊቲካ መብት የግለሰብና የቡድን መብት በእኩልነት ደረጃ እንዲታይ በሚል የለወጡት ይመስለኛል፤ ይህም የሆነው አቶ ግዛቸው፣ አቶ ዓሥራትና ዶር. ኀይሉ አቶ ስዬንና ዶር. ነጋሶን ለመያዝ ሲሉ ነው፤ ግለሰብ የሚያዝ፣ የሚጨበጥ ፣ግዙፍ አካል ያለው ነው፤ ቡድን የፈቃደኛች ግለሰቦች ስብስብ ነው፤ ግለሰቦች ሲገቡና ሲወጡ ይለዋወጣል፤ ግለሰቦች ሳይስማሙ ሲቀሩ ይፈርሳል፤ ግለሰቦች ተስማምተው ዓላማቸውን ሲለውጡ ይለወጣል።

በጎሣ ማኅበረሰብ ውስጥ ብጥብጥ የሚፈጠረው በብሶት ነው፤ ብዙውን ጊዜ የሥልጣን ጥሙን ያላሙዋላ ጎሠኛ በድንገት ጎሣው ከረጢት ውስጥ ይገባና የሙጥኝ ይላል፤ የግሉን ሥልጣን ማጣት ብሶት ወደጎሣው የሥልጣን ማጣት ብሶት ይለውጠውና የፖሊቲካ እንጀራውን መጋገር ይጀምራል፤ በእንደዚህ ያለ የግለሰብ ብሶት የጀመረ መሬት እነዚህን ጎሠኞች ብቻ ሳይሆን፣ ጎሣቸውንም፣ አገሩንም መከራ ውስጥ ይከታሉ፤ ቆስቁሰው እሳት ያነዳሉ፤ የሚቃጠልላቸው ሲጠፋም ራሳቸው እየነደዱ ያልቃሉ፤ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሣ እሳትን የሚቆሰቁሱትን ሰዎች ብንመለከት አብዛኛዎቹ ከሕዝቡ ጋር እየኖሩ ሲጠቃና ሲበደል ሲጮሁለት አይደሉም፤ በየፈረንጅ አገሩ ያገኙትን እየቃረሙ ራሳቸውን ያበለጸጉና በተደላደለ ጡረታ ሠላሳና ዓርባ ሺህ ብር በወር የሚያገኙ ናቸው፤ ለጎሣ መቆርቆር በስተርጅና ሥራ ሲጠፋ የተፈጠረ ፐሮጄክት ነው፤ በሥልጣን ላይ ላሉትም ቢሆን ጥልቅ ሕንጻ ሠርቶ በአምስት ሺህ ዶላር ማከራየት የራስን የሥልጣን ብሶት ወደጎሣ ብሶት በብልጠት በመለወጥ የተገኘ የፖሊቲካ ጥቅም ነው።

የአፍሪካ ቀንድ ሕዝብ እስካልነቃ ድረስ፣ ለራሳቸው ጥቅም የሻረ የጎሣ ቁስል የሚያሹትንና በእውነት ለአጠቃላይ የአገር ጥቅም የሚሠሩትን ለይቶ ካላወቃቸው የጀመረው እሳት እየተስፋፋ የእልቂት ዘመን እንደሚያመጣ መገንዘብ የሚያሻ ይመስለኛል።

Posted By Alemayehu Tibebu

Moyale: Police arrest 35 Ethiopians

By Liban Golicha

kenya-ethiopians

MOYALE, KENYA (Standard Media) : Police in Moyale have arrested 35 Ethiopians in Moyale town on Thursday morning.

The 35 Ethiopians were found in a bandoned house in Butiye village. Confirming the arrest, Moyale Officer Commanding Station Richard Ng’eno said the 35 aliens were locked up in a house which was left by the owner during the clashes.

He added the police were alerted by intelligence officers on the ground after realising movement of people in deserted Butiye village. According to the OCS, the aliens who neither speak English or Kiswahili were believed to be heading to South Africa.

They were, Zaude Mamo, Desta Ertaro, Getinat Demeke, Anamo Gichamo, Gilebo Erkalo, Matios Manore, Mulgeta Makebo, Takatal Wolebo, Miratu Bekele, Alamayo Hashenje, Garamo Ersiro, Wondimu Markos, Gitacho Adize, Abayan Gabube, And Nebizo Wolde,Chufano Kaltizo, Iyazu Kebeda, Gacan Kebeda, Ermiyan Jabara, Hartamu Bachore, Adana Tazama, Wondimu Abame, Takile Zanbat, Ashanalo Kashine, Abara Wanjalo, Malaza Mola, Masebo Daniel, Muze Jalatu, Alamayu Wondimu, Dababa Dama, Lire Arficho, Abayin Girma and Gudizo Mamo.

Mr Ng’eno said they will be arraigned in court to face illegal entry into the country charges. He called on locals to report suspicious characters to police.

Source: Standard Media