Archive | March 4, 2014

ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል

eskinder-ethiopia

በሀገራችን ውስጥ ያለው የ አፓርታይድ አገዛዝ አጋዛዙን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሮ ቀጥሏል ሕዝቡም ከጭቆናውብዛት

የተነሳ ቀና ብሎ ማየትና መሄድ ወደማይችልበት ደረጃ አድርሰውታል ይህ ለምን ሆነ ሲባል ወያኔ በመቻቻል የኖረውን

ሕዝብ የመከፋፈሉን ስራ ለሆዳቸው በ አደሩ ካድሬወች ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል

እንዲሁም ሆኖ የ ኢትዩጵያ ሕዝብ አምባገነኑንና ወያኔን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እናንተ በሙስና የተጠቅለቀለቃችሁ፤የሀገር

ጠላቶች ፤ድንበር ቆራሾች በመሆናችሁ ልትመሩን ልታስተዳድሩን አይገባም አተችሉም በማለትበሚገባቸው ቋንቋ በተጋገመ

ጊዜ በምርጫም ውድቅ እየነገራቸው ቢሆንም ሊገባቸው አልቻለም

በዘመነ ወያኔ ከውድ ሀገራቸው ሳይወዱ በግዳቸው እትብታቸው እያለቀሱ የተሰደዱትን መተኪያ የሌላቸውን ምሁራን ቤት

ይቁጠራቸው በ እነሱ ምትክ ካድሬወችን ቦታውን እዲሸፍኑ ቢያደርግም ፍየል ወዲያ ቅምዝምዝ ወዲህ እንደተባለው

ስራውና ሰራተኛው ሳይገናኙ ዘመናት ተቆጠሩ በኃላፊነት የሚመደቡት የካድሬነት ዲግሪ እንጂ በቂ ትምህርት ችሎታ

የሌላቸው ናቸው በዚህ ምክንያት ሀገሩን እየተወ የሚሰደደው ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ነው በሀገሩ ሰርቶ መኖር

ያቃተው ዜጋ ከወያኔ የከፋ አገዛዝ ለመሸሽ ኢትዩጵያውያን ያልሄዱበት መንገድ ያልተበተኑበት ሀገር የለም በሱዳን፤በግብጽ’፤

በሊቢያና በየመን በረሀ ቀልጠው የቀሩ ወገኖቻችን ደም እንደ አቤል ደም የ አምላክን በር እያንኳኳ ይገኛል በዚህም የተነሳ

የወገኖቻችን ጩኸት ለቅሶ ዋይታ አላስቀምጥ አላስተኛ ያላቸው የቁርጥ ቀን ልጆች የወያኔን ስርአት በመቃውም

የነጻማውጣቱን ትግል እየተቀላቀሉት ይገኛሉ አሁን በቅርቡ ከ አየር ሀይል አንድ የጦር ጀት አብራሪ የ አርበኞች ግንባርን

የተቀላቀሉ ሲሆን የ አለም መገናኛ አውታሮች የሳበው ደግሞ የቁርጥ ቀን ልጅ ረዳት ፓይለቱ ስርአቱ አንገፍግፏቸው

በሀገራቸው የሚከናወነው ጭቆና እንግልት እስራት ለ አለም ለማሳወቅ ሲሉ የወሰዱት እርምጃ ወያኔን ከስሩ ያነጋነገ ሲሆን

ለጭቁኑ ሕዝብ ደግሞ የተስፋ ደወል ያበሰሩና የሚቀጥል ትእይንት መሆኑን አመላካች ነው በዚህ ወቅት አይደለም ጭቁኑ

ሕዝብ መናገር፤መጻፍ፤መሰብሰብ፤መደራጀት፤በሀገሩ በፈለገው ቦታ መኖር የተነፈገው የህገመንግስት መብት ከለላ የሌለው

ቀርቶ በጦር ሰራዊቱ በደህንነቱ ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትም ቢሆኑ ደስተኞች አይደሉም ጊዜና ወቅት ነው የሚጠብቁት

ለዚህም ማሳያወች ለተቃዋሚ ድርጅቶች ጠቃሚ ማስረጃ አሳልፈው እሰጡ ነው የተጀመረውና የተቀጣጠለ ትግል ባለበት

ተጠናክሮ እዲቀጥል ለማደረግ በሀገር ቤት ሆነ በውጪ ለሚገኙ ለንጹሀን ወገኖች ይሁን ለስርአቱ አቀንቃኞች የወያኔን

አስከፊነት በተገኘው አጋጣሚ ማሳወቅ የሁላችንም የዜግነት ግዴታችን ሊሆን ይገባል አሁን ያለውን ችግር ገልጾ መናገርና

ማሳወቅ ጤናማ ሕብረተስብን ሊፈጥር እደሚችል ጭቆናን ፈርቶ መሸሽ /አለመናገር /አፈናን አፍኖ መያዝ ግን የበለጠ

ውድቀትን ሊፈጥር እንደሚችል ማወቅ አለብን

የጫካን እሳት ከማጥፋትህ በፊት ትንንሽ የወዳደቁ የዛፉን ቅጠሎችና የቅርንጫፎችን እሳት ቅድሚያ አጥፋ ማለት

ወያኔን አናቱ ላይ ወጥተን እናጠፋለን ከማለት በፊት የ እሱን ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑትን ቅርጫፎችን በተለያየ መንገድ

እሱበማይገባውን በማይጠረጥርበት ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ የተጫነባቸውን ሸክም ማራገፍ ለምን ቢባል ለጥፋቱም ሆነ

ለልማቱ ከፍተኛውን ተልእኮ ወይም ድርሻ የሚወጡት ቅርጫፎች በመሆናቸው ነው ለዚህ ነው ቅድሚያ ትግሉ ከግነዱ

ሳይሆን ከቅርንጫፉ ቢሆን ውጤቱ አጥጋቢና አስተማማኚ የሚሆነው ትግሉን በዚህ መልክ መቀጠል ስላለበት አንተም

አንቺም እኔም ሀላፊነት ጭቁኑ ሕዝብ ከ አደራ ጋር ተሰጥቶናል

ድል ውድ ህይወታቸው ለተከበረችው ኢትዩጵያ ለሰውት እየሰው ላሉት ለ አርበኞች ግንባር ጀግቻችን

Tedela Getenet

DEUTSCHLAND