Archive | March 11, 2014

Breaking News: Ethiopians in Harar are protesting; clashes with police reported

 

Breaking News: Ethiopians in Harar are protesting; clashes with police reported

የሃረር ከተማ በህዝባዊ ተቃውሞ እና በቶክስ እየተናወጠች ነው።

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ ትላንትና ምሽት በሃረር ከተማ በተለምዶ መብራት ሃይል በሚባል የገበያ ቦታ ላይ የወያነ ተላላኪዎች በለኮሱት እሳት ለሁለተኛ ጊዘ የነጋደውን ንብረት ማውደሙን ተከትሎ ብሶት ያረገዝው ህዝቡ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን አሰምቷል።

ከሁለት አመት በፊት በዚሁ የገበያ ቦታ የወያን ተላላኪዎች በለኮሱት እሳት ከፍተኛ ንብረት መውደሙ የሚታወስ ሲሆን ትላንትና ምሽቱን በድጋሚ የእነዚሁ ተጎጂ ነጋደዎች የበፊት ቁስል ሳያገግም እና ንብረታቸውን ሰርተው ሳይተኩ በድጋሚ ቃጠሎው ተከስቷል።

Image

የወያነው ተላላኪዎች እሳቱን እንዲለኩሱት ተደርጓል ሊባል የቻለበት ምክንያት ባለፉት ሶስት አመታት ነጋደዎቹ ከቦታው እንዲለቁ የተነገራቸው ሲሆን ከክልሉ ባላስልታናት ጋር በተነሳ አለመግባባት ባለስልጣናቱ እሳቱ እንዲለኮስ እና ንብረት እንዲወድም ያደረጉ መሆኑ ምንጮቹ ተናግረዋል።

በዛረው እለት በብሶት የተወጠረው የሃረር ህዝብ አደባባይ በመውጣት የወያነን መንግስት ያወገዘ ዚሆን ፖሊሶች ለተቃውሞ የወጣውን ህዝብ በማፈስ ወደ እስር በት የወሰዱ እና አከባቢውን በቶክስ በማናወጥ ከፍተኛ ሽብር ፈጥረዋል። እስካሁን የተጎዳ ሰው ይኑር አይኑር የወጡ መረጃዎች የሉም ።

ትናትና በጥይት የተመቱት የሃረር ወጣቶች ሁለቱ ኮማ ውስጥ ናቸው:: ፖሊስ መረጃ ከሆስፒታሉ እንዳይወጣ በጥበቃ ላይ ነው ::

ትናትና በጥይት የተመቱት የሃረር ወጣቶች ሁለቱ ኮማ ውስጥ ናቸው:: ፖሊስ መረጃ ከሆስፒታሉ እንዳይወጣ በጥበቃ ላይ ነው ::

Image

Re: Breaking News: Ethiopians in Harar are protesting; clashes with police reported

በሀረር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ታሰሩ

በሀረር ባለፈው እሁድ ምሽት የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጣው ህዝብ በፖሊስ ከተበተነ በሁዋላ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከትናናት ጀምሮ ፖሊሶች መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ወጣቶች እያፈሱ እንዲሁም ከቤታቸው እያወጡ ወደ እስር ቤት ወስደዋቸዋል።

በዛሬው እለት በቃጠሎው የደረሰውን ጉዳት አቤት ለማለት የተሰባሰቡ 15 ወጣቶች በፖሊሶች ተይዘው መታሰራቸውን አንድ ወጣት ተናግሯል። ከትናንት ጀምሮ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ፖሊሶች መታሰራቸውንም ወጣቱ አክሎአል።
የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ አቡደላሂ የተወሰኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አምነዋል።

የክልሉ ፖሊሶች የእሳት ቃጠለው በደረሰበት አካባቢ በስፋት ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ዘገባውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶችም ተዘግተዋል።አብዛኛው የከተማው ነዋሪ የእሳት አደጋው መንስኤ የክልሉ መስተዳድር ነው የሚል እምነት ሲኖረው መስተዳድሩ በበኩሉ በህዝቡ የሚቀርበውን ክስ አይቀበልም።
በከተማው ባለፈው እሁድ የተነሳው የእሳት ቃጠሉ ከፍተኛ የንብረት መውደም ማስከተሉ ይታወቃል። ሀረር ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር እና መሰረታዊ የሆኑ ፍላጎቶች እጥረት እንዳለባት ነዋሪዎች በተደጋጋሚ በምሬት ሲገልጹ ቆይተዋል።
ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና

ባለፈው ቅዳሜ march 8/2014 በጀርመን ሃገር ኑረንበርግ ከተማ /EPCOU/ ስብሰባ አካሂዷል::

By Alemayehu Tibebu

ባለፈው ቅዳሜ የካቲት 27/2006 (march 8/2014) በጀርመን ሃገር ኑረንበርግ ከተማ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበር አባላት /EPCOU/ ስብሰባ አካሂዷል::

በእለቱም በወቅታዊ የሃገራችን የፖለቲካ ሁኔታ የተወያየ ሲሆን በተለይ ከኢትዮጵያ ለሱዳን ተላልፎ ሊሰጥ የታሰበውን መሬታችንን አግባብ እንዳልሆነ በመወያየት በአፋጣኝ ይሄ እርምጃ ከመሆኑ በፊት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አጽንዎት ሰቶ ተወያይተዋል::

f8393258a411a5b415ef1eebace5fe8c81b322e9a983281807ad6051daa7f140

የወያኔ መንግስት የሃገርን ጥቅም ለሌላ አሳልፎ መስጠት ይህ የመጀመርያው እንዳልሆነ ላለፉት 23 አመታት የታየ በመሆኑ ከዚህ በሁዋላ ግን የእጅ መዳፍም የምታህል መሬትም ቢሆን ለሌላ ሲሸጥ ዝም ብለን ማየት የለብንም የሚል በተደጋጋሚ ከተሰብሳቢው የተነሳ ሃሳብ ነበር::

በተጨማሪም በታዳሚዎች የተለያዩ ዝግጅቶችና በወጣት ሳሚ ሰለሞን አድዋ በሚል ርእስ በወቅታዊ የሃገራችንን የፖለቲካ ጉዳይ ላይ የተጻፈ ግጥምም ተነቧል::

እንዲሁም የአድዋ ድልንና የማርች 8 የሴቶች ቀንም በእለቱ ታስቦ ውልዋል በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለመድረኩ የቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቶበት የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆንዋል::

b588dc375f9f8c1f453fb97763d22000ed0729135e63b91ff952339e38ded07f3ef8835129bdc5b9bbf2ea58b96ecb9be5458ebd0808c1d44baec1987a325804