የስቃይ ቤት ስለመሆኑ እየተነገረለት የሚገኘው ማዕከላዊ


የማዕከላዊ ሃላፊዎች ግን ለምን ዝም ይላሉ
በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጸም በየጊዜው የሚወጡ ሪፖርቶች ከማጋለጣቸውም በላይ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ዜጎች በምርመራ ላይ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው በመጥቀስ አንዳንዶቹ ልብሳቸውን እያወለቁ ጭምር ሲያሳዩ ማስተዋላችን አልቀረም፡፡ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መካከል በተለይ የቀድሞው የሸሪዓ ፍርድቤት ፕሬዝደንት ሼኽ መከተ ሙሄ በማዕከላዊ ፊደል የማይገልጸውን የመብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
እኔ የምለው
ፍርድ ቤቱ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል በምርመራ ስም ዜጎች ሲናገሩ እያደመጠ‹‹ሁለተኛ እንዳይደገም››በሚል ቃል የሚያልፈው እስከመቼ ነው?ተሰቃየን ቶርቸር ተፈጸመብን ያሉ ተጠርጣሪዎችን የዋስ መብት ነፍጎ በወህኒ እንዲቆዩ ማድረግስ መልሶ ለገራፊዎቻቸው አሳልፎ መስጠት አይሆንምን?
የማዕከላዊ ዝምታ
የስቃይ ቤት ስለመሆኑ እየተነገረለት የሚገኘው ማዕከላዊ ስለሚቀርቡበት ሪፖርቶችና ማስረጃዎች ስለ ምን ዝምታን መረጠ?እንዲህ ያደረጉ ፖሊሶች እንደሌሉት ወይም ጨለማ ክፍል ፣ቀዝቃዛ ቤት መግረፊያ ክፍል እንደሌለው ለምን ህዝብ እንዲጎበኘው አያደርግም፡፡እግረ መንገዴንም ማዕከላዊ ለህዝብ ክፍት ይሁን የሚል ጥያቄዬን ላቅርብ፡፡

posted by Alemayehu Tibebu

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s