የፌደራል ፖሊስ በቦዴዎች ላይ በሰነዘረው ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አስታወቀ


ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በቦዴዎችና በኮንሶች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ ወደ 29 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለድርጅታቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

federal_police_ethiopia

የሟቾችን ስም ዝርዝር በማጠናቀር ላይ ሲሆኑ  ሰሞኑን ይፋ እንደሚያደርጉም ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል ሆስፒታል ሄደው የቆሰሉትን ሰዎች መጎብኘታቸውና ማነጋገራቸውን የሚናገሩት አቶ አለማየሁ ፣ ከሁለቱ በስተቀር ሌሎች ወደ 6 የሚጠጉ ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ጥይት መቁሰላቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ምንም እንኳ የግጭቱ መነሻ መንግስት ካሰፈራቸው የኮንሶ ተወላጆች ጋር የተያያዘ ቢመስልም፣ ቦዴዎች ለሸንኮራ ገዳ ተክል በሚል ከአካባቢያቸውን እንዲነሱ መደረጉ የፈጠረባቸው ስሜት የችግሩ ዋነኛ መነሻ መሆኑን ገልጸዋል። ቦዴዎች ዘላኖች በመሆናቸው ለዛፎች ልዩ እንክብካቤ እንደሚያደርጉ የገለጹት ባለስልጣኑ፣ በእርሻ ስራ የሚተዳደሩት ሰፋሪ ኮንሶዎች ወደ አካባቢያቸው በመግባት ዛፎችን እየቆረጡ የእርሻ ማሳ ሲያስፋፉ ሲመለከቱና ለሸንኮራ ልማት በሚል ቀያቸውን እንዲለቁ ሲገደዱ የፈጠረባቸው ቁጭት ደም አፋሳሽ ወደ ሆነ ግችት ተቀይሯል።

ምንም እንኳ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል የተነሳው ግጭት በፌደራል ፖሊስ የሃይል እርምጃ ቢቆምም፣ ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን አቶ አለማየሁ ገልጸዋል። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ አሁንም ድረስ በአካባቢው ይገኛል።

በጉዳዩ ዙሪያ የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ በኔትወርክ ችግር ምክንያት ሊሳካልን አልቻለም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s