ዘጠኝ እስረኞች በሦስት መዝገብ


(Abe Tokichaw) የማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ ፖሊስ በትናንትናው (እሁድ) ዕለት ጠዋት አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ በሦስት መዝገብ የተከሰሱት ዘጠኝ ጸሐፊዎች አገሪቷን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሐሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማተው በአገሪቷ ላይ የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ውለዋል ይህንንም በሚመለከት መረጃ እስክናሰባስብ ጊዜ ይሰጠን በሚል የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡

fbbanner

በዚህም መሠረት በመዝገብ ቁጥር 118722 ተስፋለም፣አስማማው ዘላለም ለ29/08/2006 ተቀጥረዋል፡፡በመዝገብ ቁጥር 118720 በፍቃዱ፣ማሕሌትና አቤል ለ30/08/2006 ተቀጥረዋል፡፡በመዝገብ ቁጥር 118721 አጥናፉ፣ናትናኤልና ኤዶም ለ29/08/2006 ተቀጥረዋል፡፡ ጉዳዩን ያየችው ዳኛ ሊያ ዘነበ ስትሆን እስረኞቹ በዕለት ቀጠሮው ጠዋት አራት ሰዓት እንዲቀርቡ አዛለች፡፤ ነገር ግን ችሎቱ ሁል ጊዜ የሚሰየመው ከሰዓት ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ነው፡፡

(ሰትል የዘገበች ጺዮን ግርማ ናት ከአዲስ አበባ)

BmUqqD3CAAEyVmE

ጽዮን ግርማን እያመሰገንን፤ ወዳጆቻችን በእሁድ ቀን እንዴት ያለ ችሎት ላይ እንደቀረቡ ግራ ግብ…ት ብሎናል። በበኩሌ ዳኛዋ ሊያ ዘነበ ተባላለች፤ የሚለወን እስካነብ ድረስ እሁድ ቀን ኑ የሚል ፍርድ ቤት፤ ቤተስኪያን ዳኛውም መሪጌታ ናቸው በዬ አራዳ ጊዝዮርጊስ ቤትስኪያን ያቀረቧቸው ነበር የመሰለኝ!

እንግዲህ የክሱ ጭብጥ ይሄንን የሚመስል ከሆነ የኢቲቪ ዶክመንተሪ ”የቀለም አብዮት ሲጨናገፍ” በሚል ርዕስ በቅርቡ እንደሚቀርብ እንጠረጥራልን።

ባለፈው ጊዜ ስለ ቀለም አብዮት በኢቲቪ ዘጋቢ ፊልም ላይ፤ አንዱ ተንታኝ ”የቀለም አብዮት በአንድ ሃገር ላይ ውጤት እንዳያመጣ ከተፈለገ መንግስት የህዝቡን ቅሬታዎች ቶሎ ቶሎ እና በአገባቡ መቅረፍ አለበት” ሲል ተናግሮ ነበር። በእውነት ያንን ልጅ መንፍስ ቅዱስ ነው ያናገረው። መንፈስ ቅዱስ የራቀው መንግስታችን ግን ቅሬታዎችን ”የሚቀርፍው” ቅር ያላቸውን ሰዎች በማሰር ነው። ኧር ጎብዝ ቅር ያለውን ሁሉ አስራችሁ አትዘልቁትም… ወይ ዝም በላችሁ መላ ኢትዮጵያን ቆልፉ እና ርዮት እነዳለችው ዞን ዘጠኝ በሏት፤ በአጭሩ የታሰበው ሼራዊ ፖስት፤ እየረዘመ ሲመጣ…

ዞን ዘጠኝ የሚባለው ስያሜ እንዴት እንደመጣ ሰማችሁልኝ… በአንድ ወቅት ዛሬ ዞን ዘጠኝ ብሎግ ላይ ሲጽፉ ተገኝተው የታሰሩ ልጆች እና ሌሎችም ሆነው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙን ለመጠየቅ ቃሊቲ ዞን ስምንት ይሄዳሉ። ቃሊቲ ውስጥ እንግዲህ በዞን በዞን የተከፈለ ሲሆን ዞን ስምንት የመጨረሻው እና ሴቶች የሚገኙብት ዞን ነው። ታድያ ሰላም ተባበለው ሲያበቁ “በርቺ እንገዲ” በለው ሲሰናበቷት እናንተም በረቱ ሁላችንም እስረኞች ነን፤ ስምንቱ ዞን ቃሊቲ ውስጥ ቢኖረም ዘጠነኛው ዞን መላው ኢትዮጵያ ናት አለቻቸው።

እና እባካችሁ ስለጉልበታችሁ አምላክ ፍቱን እና እኛም ስለ ”ልማቱ” እናውራ…

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s