Archive | May 1, 2014

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን! (Abraha Desta)

በአዲሱ የአዲስ ማስተር ፕላን በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልል ገጠር መሬቶች የአዲስ አበባ ከተማ አካል ያደርጋቸዋል። ይሄን ጉዳይ በኦሮሞ ህዝብ ባጠቃላይ በኦሮሞ ተማሪዎች ደግሞ በተለይ ዓመፅ አስነስቷል።

ማስተር ፕላኑ የገጠር ቦታዎች ማካተቱ በራሱ ችግር አይደለም። እንዳዉም ፕላኑ ኦሮምያ አልፎ መቐለም ቢያጠቃልል ደስ ባለኝ ነበር። ከተማ ቢያድግ መልካም ነው። ከተማ ሲያድግም በዙርያው ይሰፋል። ይህ ባህርያዊ ነው። ግን ችግር አለ። በኢህአዴግ ዘመን እየተስተዋለ ያለው የከተሞች ማስፋፋት ስትራተጂ አፈፃፀም ኗሪዎችን እጅግ ይጎዳል።

የገጠር መሬት ወደ ከተማ ሲገባ በዛ የሚኖሩ አርሶአደሮች ያለ ፍቃዳቸው ከቀያቸው ይፈናቀላሉ። በቂ ካሳ (ክፍያ) አይሰጣቸውም። በዚህ መሰረት አርሶአደሮቹ ተቃውሞ ያሰማሉ። ይህ ጉዳይ በኦሮምያ ብቻ አይደለም የተከሰተው። በመቐለ ከተማም ተመሳስይ ችግር አለ። በመቐለ ዙርያ የሚኖሩ የእንደርታ ኗሪዎች ሁሌ ያለ ፍቃዳቸው እንደተፈናቀሉ ነው። በመቐለ ዙርያ ሁሌ ተቃውሞ አለ። ዓመፅ አለ። በመቐለ ዙርያ በዓይናለም፣ እግሪሓሪባ፣ ሰራዋት ወዘተ ያለ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ አሁን በኦሮምያ እየተካሄደ ካለው ተመሳሳይ ነው። የመንግስት አካላት ተቃውሞ ለሚያሰሙ ሰዎች የኃይል እርምጃ እየወሰዱ ይደበድቧቸዋል፣ ይገድሏቸዋል፣ ያስሩዋቸዋል፣ ያሰቃያቸዋል።

ይሄ ነገር በኦሮምያም መከሰቱ አይቀርም። ምክንያቱም በትግራይ የሚከናወን የህወሓት ተግባር በኦሮምያም በኦህዴድ መተግበሩ አይቀርም። ምክንያቱም ህወሓትና ኦህዴድ ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉና ነው። ይህን ነገር ተቃውሞ መቀስቀሱ ታድያ አይገርምም። አርሶአደሮች ኮ ከቀያቸው ሊፈናቀሉ ነው። “ገበሬዎች መሬታቸው ሽጠው ከቀያቸው እንዳይፈናቀሉ መሬት የመንግስት አድርገዋለሁ” ብሎ የሚዘፍን ስርዓት አርሶአደሮቹን ያለፍቃዳቸው ያፈናቅላል።

eskinder-ethiopia

ሌላው ምክንያት ደግሞ የብሄር ፖለቲካችን ነው። ኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ እያራመደ እርስበርሳችን እንዳንተማመን በብሄር ለያይቶናል። ይሄ የናንተ መሬት ነው፣ ይህ ደግሞ የነሱ ነው ወዘተ እያለ በቡድን ከፋፍሎናል። በብሄሮች መግባባት እንዳይኖር እነእገሌ እንዲህ አደረጓቹ ታሪካችሁ እንዲህ ነው። መጀመርያ መምጣት ያለበት ብሄር ነው ወዘተ እያለ የብሄር ጥላቻ እንዲሰፍን ሐውልት ሰርቶልናል። ባጠቃላይ የዓመፁ ምክንያት የኢህአዴግ የጥላቻ ፖለቲካ ሰበካ ነው።

ኢህአዴግ ብሄር መሰረት ባደረገው ፌደራሊዝሙ “ይሄ መሬት የኦሮምያ ነው፣ ነፍጠኞች እንዳይወስዱባቹ ተጠንቀቁ!” እያለ ጥላቻ ሲሰብክ ከርሞ አሁን የኦሮሞ ተወላጆች “የኦሮምያ መሬት የኛ ነው። ለማንም አሳልፈን አንሰጥም!” ሲሉት ግዜ ለምን የኃይል እርምጃ መውሰድ መረጠ? ኢህአዴግ ራሱ የዘራውን ነው እያጨደ ያለው።

ለማንኛውም አሁን ሁኔታው ማረጋጋት አለብን። ኢህአዴግም በጉዳዩ ራሱን መፈተሽ ይኖርበታል። የኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ ከባድ ፈተና ደቅኖብናል።

It is so!!!

ኦህዴድ የተከፋፈለ አቋም ይዟል፤ ኢህአዴግ ጉልበት መርጧል

ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት በአቀራረቡ ቢለያይም ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ዜናዎች ሊስተባበሉ የሚችሉ አይደሉም። በታችኛው እርከን የሚገኙትን ጨምሮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጥቅሉ፣ ገሃድ አይውጣ እንጂ በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ካድሬዎች የተቃውሞው ተሳታፊና ደጋፊ መሆናቸውን ክልሉም ሆነ ኢህአዴግ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን በዙሪያዋ ያሉትን ስድስት የኦሮሚያን ከተሞችና ስድስት የገጠር ቀበሌዎች የተካተቱበት መሆኑ ያስነሳው ተቃውሞ ቀደም ሲል በክልሉ በምክር ቤት ደረጀ በካድሬዎች ተቃውሞ አጋጠመው። ይህንኑ ተከትሎ ከሳምንት በፊት በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት ብልጭ ድርግም ሲል የነበረው ተቃውሞ እየጠነከረ መጣ። የክልሉ የጎልጉል ምንጭ “ተቃውሞው እንደሚጨምር፣ ካድሬውም የተቃውሞው ስውር አጋር እንደሆነ፣ በመረጃ ትንተና አስቀድሞ ይታወቅ ነበር። በዚሁ መሰረት አስቀድሞ አመጹን ማምከን ካልተቻለ የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ ለፌዴራልና ለመከላከያ አባላት መመሪያ ተሰጥቷል”።

የሰላማዊ ሰልፍ በሚጀመርበት አካባቢ ሌላውን “ሊያስተምር” የሚችል ከበድ ያለ የሃይል ርምጃ እንዲወሰድ በተላለፈው መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ቢደረግም ረብሻውና የተቃውሞ እንቅስቃሴው እየሰፋ መሄዱን የጎልጉል መረጃ አቀባይ ይናገራሉ። ከከተማ ወደ ከተማ እየሰፋ የሄደው ተቃውሞ፣ የተቃውሞው አካል በሚመስሉ የስለላ ሰራተኞች በሚያቀብሉት መረጃ መሰረት ለማስታገስ ቢሞከርም አለመቻሉ ኢህአዴግ ውስጥ ጭንቀት ፈጥሯል።

የኦህዴድ አባላት በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉትን ጨምሮ ተመሳሳይ አቋም ያልያዙበት አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ በኦሮሚያ የተላዘበውን የፖለቲካ ችግር ሊያባብሰው ይችላል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢህአዴግ የፖሊስ የመከላከያ ሃይላት ከልዩ መመሪያ ጋር በተጠንቀቅ እንደቆሙ ምንጩ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በኦህዴድ የታችኛው የቀበሌ መዋቅር ጭምር ተቃውሞው ስለሚደገፍ የአቋም መንሸራተት ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት ከፍተኛ መሆኑንንም አልሸሸጉም።

ከተለያዩ የማህበረሰብ አምዶች ሲደመጥ እንደሰነበተውና ሚያዚያ 22፤2006 (ኤፕሪል 30/2014) ቀን የአሜሪካ ሬዲዮ ከስፍራው ሰዎችን በማነጋገር እንደገለጸው ጅማ፣ አዳማ፣ ነቀምት፣ አምቦ፣ ሃሮማያ፣ ድሬዳዋ፣ በመሳሰሉት ከተሞችና የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ ላሰሙት የተቃውሞ ድምጽ የተሰጣቸው ምላሽ ዱላና እስር ነው። ከአምቦ በስልክ ስለሁኔታው የተናገሩ እንዳሉት አላፊ አግዳሚው ሳይቀር “ተጨፍጭፏል”።

በተጠቀሰው ቀን ረፋዱ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ከሰዓት በኋላ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተቃውሞ ሲወጡ የመከላከያ አንጋቾችና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት የሃይል ርምጃ በርካቶች መቁሰላቸውን፣ በነፍስ አውጪኝ አጥር ዘለው የሸሹትን በማሳደድ ጨፍጭፈዋቸዋል። እኚሁ ሰው በስልክ እንደተናገሩት “ሸሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡትን ተማሪዎች ለምን ቤትህ አስገባህ ተብዬ ተጨፈጨፍኩ፣ ነፍሴን ለማትረፍ መሬት እየተንከባለልኩ ጮህኩ። ሁለት ልጆቼን ወሰዱ” በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የአምቦ ቤተመንግሥትም እስረኛ እንደሞላው አመልክተዋል።

ለማቅረብ ከያዟቸው ሶስት ጥያቄዎች መካከል አንዱ “ፊንፊኔ ያለው የአጼ ሚኒሊክ ሃውልት ይነሳ የሚል ነው” በማለት ፈርቶ እንደተሸሸገ የተናገረ ተማሪ ከአዳማ ለቪኦኤ ተናግሯል። የቪኦኤው ዘጋቢ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት፣ በመጨረሻም ከኦሮሚያ ምክር ቤት ያገናቸው ሰው መልስ ሳይመልሱ እንደመሳቅ እያሉ ስልኩን እንደዘጉት በግብር አሳይቷል።

ከምርጫ 97 በፊት አዳማን የኦሮሚያ ዋና ከተማ መደረጓን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ችግር ከምርጫ 97 በኋላ ቀውሱ እልባት እንደተበጀለት ይታወሳል። በወቅቱ በሜጫና ቱለማ ማህበር አስተባባሪነት አዲስ አበባ ላይ የተካረረ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበርም አይዘነጋም። በዚያን ወቅትም የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ድሪቢን ጨምሮ በርካቶች ታስረው ነበር። ኢህአዴግ አቋሙን ለምርጫ ቀውስ ማርገቢያ በሚል ሲቀይር፣ ድርጊቱን አስቀድመው በመቃወማቸው የተገረፉ፣ የታሰሩና ከስራ እንዲሰናበቱ የተደረጉ ካሳ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

አገሪቱ ላይ ከተንሰራፋው የተለያየ ችግር ጋር ተዳምሮ በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ እንዳይካረር ስጋት የገባቸው ክፍሎች “ኢህአዴግ ጉልበት እየተጠቀመ የሚዘራውን ቂምና ቁርሾ ካላቆመ፣ ጠብመንጃ እጄ ላይ ነው በማለት የሚፈጽመውን ግፍ በማቆም ለእርቅ ካልሰራ አሁን ባለው ሁኔታ ነገሮች ከቁጥጥር ሊወጡ” እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ፤ ጂኒው አንዴ ከሳጥኑ ከወጣ በኋላ ልዩነት ሳያደርግ የሚያመጣው መዘዝ ለህወሃት/ኢህአዴግና በቅድሚያ ከዚያም ለሥርዓቱ ባለሟሎች በተዋረድ የሚባላ እሣት እንደሚሆን ታስቦ ካሁኑ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Breaking News:- Ethiopian Security Forces opened fired and killed 30 people.

(ireport.cnn) Ethiopian security Forces opened fire during the oromo students nonviolent protest rally at western oromia Ambo town.
Eye witnesses said more than 30 people including 8 students killed and several wounded by security forces. the peaceful protestors opposing the alleged “integrated Master Plan of Addis Ababa”.The peaceful protest continued in different oromia region.