የአንበጣ ምድር


(ሄኖክ የሺጥላ)

sillouhette-of-girl-praying
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው “ወደ ፈርዖዎን ግባ ፣ እኔ የ ፈርዖዎንን ና የሹሞቹን ልብ አጽንቼአለሁና፣ ተአምራቴ በነሱ ላይ በትክክል ይመጣ ዘንድ፣ በግብጻውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፣ ያደረጉሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና እና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮዎች ትነግሩ ዘንድ፣ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። ሙሴና አሮንም ወደ ፈርኦን ገቡ ፣ አሉትም ፣ ” የእብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እምቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፣ ህዝቤን ለመልቀቅ እምቢ ብትል ግን፣ እንሆ ነገ በዚህ ጊዜ በተራራዎችህ ላይ አምበጣ አመጣለሁ ፣ የምድሩንም ፊት ይሸፍናል፣ ምድሩንም ለማየት አይቻልም፣ ከበረዶውም ተርፎ በምድሩ ላይ የቀረላችሁን ትርፍ ሁሉ ይበላል; ያደገላቹን የእርሻ ዛፍ ሁሉ ይበላል; ቤቶችም፣ የሹሞችህም ሁሉ ቤቶች፣ የግብጻውያን ሁሉ ቤቶች በእርሱ ይሞላሉ፣ አባቶችህ ፣ የዓባቶችህም አባቶች በምድር ላይ ከተቀመጡበት ቀን ጀምሮ እስቀዝ ቀን ድረስ እንደ ርሱ ያለ ያላዩት ነው። ሙሴም ተመልሶ ከፈርዖን ዘንድ መጣ። እናም እግዚአብሔር አምላክ ቃሉን ጠብቆ መጣ። እኔም ይሄንን አየሁ ያየሁትንም እናገራለሁ።
አንደበቴ ያንተን ትልቅነት ያወራል፣ በቃልህ ትገኛለህ፣ ከቀጠሮህ አትዛንፍም፣ ሃጣን ከጥፋት ውሃው አይተርፍም የተረፉ ምስክሮች ያንተን ትልቅነት ተናጋሪዎች ይሆናሉ። ኖህ መርከቡን ሳያንጽ ሃጣን ንስሐ ሳይገባ ያፈሰሱትን ደም ሳይደርቅ ያንተ ፍርድ ደረሰ
እንሆ ይሄ የመጨረሻ ሰዓት ነው። ውንድማምቾች ተለያይተዋልና፣ የአባቶች ደም በከንቱ ፈሶዋልና፣ ብላቴናው ያለ እናት፣ አውድማው ያለ ዘር ቀርቶዋል ፣ አንተም ይህንን ባደረጉት ላይ ለመፍረድ መጣህ ።
የመጨረሻው ሰዓት ደረሰ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመከራው እና ከግፉ አርነት የሚወጣበት ቀን፣ የነጻነቱ ቀን ደረሰ፣ የዚያን ጊዜ ወየው ለባንዳ፣ ወየው ሀገር ለገነጠሉ ፣ ወየው ኢትዮጵያዊነታቸውን ለጣሉና ለጠሉ፣ ወየው በምድሪቷ ላይ ግፍን ለፈጸሙ፣ ወየው በባዕድ መሪነት ወገንን ለገደሉ፣ ላቆሰሉና ላደሙ፣ ወየው ምክርን ሳይሰሙ የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ በእንቢታ ለደረሱ፣ ወየው ለልበ ዝጎቹ፣ ወየው ለ ክፍዎቹ፣ ወየው ። ግፋቸው ከነሱ አለፈ ፣ የጃቸውንም ያገኙ ዘንድ ቀኑ ተቆረጠ፣ የሚያስተርፉላቸውም ሰው አይኖርም፣ አውድማቸው በቀበሮ ፣ መልካው በጭንጫና በግቻ ይሞላል፣ በመንደራቸው ጥንብ አንሳና ጅብ ይሰማራሉ፣ ያላደኑትንም ይበላሉ፣ የሰማዩ አሞራ ቤቱን ምድር ላይ ይሰራል፣ በንዥብቦ ሰማዩን ይሸፍነዋል : ጥፍሩም ሬሳቸውም ላይ ይበረታል ፣ አይጥ ሬሳ ወደ ጉድጉዋዱ ይስባል፣ የሚቀብራቸውም አያገኙም፣ አጥንታቸው እንደ ጠጠር ይለቀማል፣ልብሳቸውም ለ 7 ዓመት ማቅ ይሆናል። በዚያ በመጨረሻ ሰዓት አንበጣ ሰማዩን ይወራል፣ እህሉንም ያወድማል፣ ከምሥራቅ የበረታ ጉልበት ይነሳል፣ ፈጥኖም ይገሰግሳል፣ ከደቡብ ሌላ ኃይል ይነሳል፣ ከምዕራብ ሶስተኛ ኃይል ይነሳል ። የበረታ እልቂት ይሆናል፣ እናት ማህጸኑዋ ይደፈን ዘንድ አምላኩዋን ትለምናለች፣ የኔ ማንም ማንንም አያድንም፣ ማንም ለማንም ጉልበት አይሆንም፣ ያኔ ኢትዮጵያ እጆቹዋን ወደ እግዚያብሄር ትዘረጋለች። ያፈሩትን አይበሉም፣ የገነቡት ውስጥ አይኖሩበትም፣ ምህረት ከነሱ እንደራቀች ፣ እንሱም ምሕረትን ይነፈጋሉ፣ እስኪጠፉ ድረስ።
ከዚያ መዝሙረ ዳዊቴን ማንበብ ቀጠልኩ
ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ
በዋዘኞች መንገድ ያልቆመ
በሃጥ ያተኞች መንበር ያልተቀመጠ
ነገር ግን እሱ በእግዚያብሔር ሕግ ደስ ይለዋል
ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል
ክፉዎች ግን እንዲህ አይደለሁም
ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው ።
መዝሙረ ዳዊቴን ዘጋሁ ፣ ግራና ቀኝ ተመለከትኩ፣ ከዚያም ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። በአህያ ላይ መሰንቆዋቸውን ሰቅለው እንዳለቀሱት የእስራኤል ልጆች። በ በሽታ እንደተመታው እዮብ አይነት ለቅሶ፣ እንደ ” አንቺ ሴት ሃጥያትሽ ተሰርዞልሻል ” ስትባል እግሩን በንባ እንዳጠብችው መቅደላዊቱ ማርያም አይነት ለቅሶ። ኢትዮጵያ እውነትም እጆቹዋን ወደ እግዚያብሄር ትዘረጋለች።
እግዚያብሄር አምላክ እንዲህ ይላል – ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s