Archive | May 24, 2014

በፒያሳ ወርቅ ቤቶች ኮርኒስ ውስጥ ለ3 ቀን ያሸመቀው ወጣት ተያዘዘ

በረሃብ ደካክሞ ለ5ቀን ራስ ደስታ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎለታል

lalibela

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፒያሳ እምብርት ላይ በሚገኘው ዝነኛው ላሊበላ ወርቅ ቤት ውስጥ ለብዙዎች ትንግርት የሆነ ነገር ተከስቷል፡፡ ያውም በጠራራ ፀሃይ፡፡ ላሊበላ ወርቅ ቤት፤ በአካባቢው ከሚገኙ ሌሎች ወርቅ ቤቶች ለየት የሚያደርገው ለምሳ ከ7-9 ሰዓት መዘጋቱ ነው የሚሉት የወርቅ ቤቱ ባለቤት አቶ ኢዛና ካሣዬ፤ የዚያን ዕለት ግን ገበያ በመብዛቱ ለምሳ ሳይዘጋ እንደቀረ ይናገራሉ፡፡
የላሊበላ ወርቅ ቤት ትንግርት የተጀመረው ከጎኑ በሚገኘው ኢየሩሳሌም ወርቅ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ኮርኒስ ውስጥ የመንደፋደፍ ድምፅ እንደሰሙ የሚናገሩት የኢየሩሳሌም ወርቅ ቤት ሰራተኞች፤ ለጊዜው ቢደናገሩም “እርግብ ነው” በሚል ተስማምተው ወደ ስራቸው መግባታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ሆኖም ድምፁ እየጨመረ በመምጣቱ ጥርጣሬ ይገባቸውና አንደኛው ሰራተኛ ክፍት በሆነው ኮርኒስ በኩል ባትሪ አብርቶ ተጠግቶ ይመለከታል፡፡
ኮርኒስ ውስጥ የሚንደፋደፈው እርግብ ሳይሆን ሰው መሆኑን ያረጋገጠው የወርቅ ቤቱ ሰራተኛ፤ “ሌባ… ሌባ” እያለ ሲጮህ ያልደነገጠ የለም፡፡ ኮርኒሱ ውስጥ ያሸመቀውን ወጣት ጨምሮ ሁሉም ድንብርብሩ ወጣ፡፡ ለማምለጥ የሞከረውም ወጣት ሲንደፋደፍ ከጎኑ ያለው የላሊበላ ወርቅ ቤት ኮርኒሱ ተቀዶ መሬት ሊፈጠፈጥ ሲል አንዱ የእንጨት ምሰሶ ደግፎት ይተርፋል፡፡  በዚህ ዱብዕዳ ወርቅ በመግዛት ላይ የነበሩ ደንበኞችና የወርቅ ቤቱ ሠራተኞች መደናገጣቸው አልቀረም፡፡ በዚህ ግርግር ወጣቱ ተመልሶ ወደ ኮርኒሱ  ውስጥ ይሸሻል፡፡ ይሄኔ ሁሉም ባለወርቅ ቤት በየራሱ ኮርኒስ ውስጥ ባትሪና ሻማ ይዞ በመግባት ወጣቱን ተጠርጣሪውን ማደን ጀመረ ይላል፤ የቅዱስ የብር ጌጣጌጥ መሸጫ ቤት ሠራተኛ ብርሃኑ አበበ፡፡ ተርታውን ያሉት የወርቅ መሸጫ መደብሮች የጥንት ቤቶች ስለሆኑ በኮርኒሳቸው ውስጥ ለውስጥ እንደሚገናኙ የነገሩን ሠራተኞቹ፤ ማታ ማታ ቤቱን ከመዝጋታቸው በፊት ወርቅና ብሮቹን ካዝና ውስጥ ከተው እንደሚቆልፉባቸው ገልፀዋል፡፡
በየግል ተጀምሮ የነበረው ወጣቱን የማደን ዘመቻ ከደቂቃዎች በኋላ በፖሊስ ሃይል ተጠናክሮ ቢቀጥልም ወጣቱ እምጥ ይግባ ስምጥ ሊታወቅ አልቻለም – ይላሉ አቶ ኢዛና፡፡ ከዚያም ጣራው አናት ላይ ወጥተው አሰሳውን ቀጠሉ፡፡ ወጣቱን ባያገኙትም ስለእሱ ድርጊቶች የሚጠቁሙ ፍንጮችን ለማግኘት እንደቻሉ የሚናገሩት አቶ ኢዛና፤ አንድ ቦታ ላይ ጣራው መቀደዱን ማየታቸውን፤ እዚያው አካባቢም ጣራው የተቀደደበት መቀስ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡ወዲያው የተቀደደውን ቆርቆሮ በባለሙያ እንዳስደፈኑ ጠቁመው፤ አሰሳው ግን ያለውጤት መቋጨቱን ተናግረዋል፡፡
በነጋታው አርብ ጠዋት ደግሞ ቅዱስ የብር ጌጣጌጥ መሸጫ መደብር ውስጥ ሌላ ፍንጭ ተገኘ፡፡ በሩን ለመክፈት ሲሞክር የበሩ ቁልፍ (ጋን) እንዳስቸገረው የሚያስታውሰው ብርሃኑ፤ የቤቱን ባለቤት ጠርቶ አብረው ከፍተው መግባታቸውን ይገልፃል፡፡ ውስጡን ሲቃኙም አንዳንድ ነገሮች ተመሰቃቅለው ያገኛሉ፡፡ ወዲያው ፖሊስ ይጠሩና ሌላ የፍለጋ ዘመቻ ይጀመራል፡፡ ሆኖም ተፈላጊው አልተገኘም፡፡
ቅዳሜ ጠዋትም ብርሃኑ ከሱቁ ባለቤት ጋር ነበር በሩን የከፈትነው፡፡ የብር ጌጦቹን የሚደረድርበትን የመዝጊያ ብረት ሸርተት ሲያደርግ ነው ፈፅሞ ካልጠበቀው ነገር ጋር የተፋጠጠው፡፡ ሁለት ቀን መከራቸውን ያበላቸው ወጣት፤ ትልቅ የብር መስቀል በእጁ ይዞ መስተዋቱ ጋ ተለጥፎ ቆሟል፡፡ “ፊት ለፊት ቢያገኘኝ ግንባሬን ብሎኝ ወደ ውጭ ለመፈትለክ አስቦ እንደነበር ያስታውቅበታል” ያለው ብርሃኑ፤ በመስተዋት ውስጥና ውጭ ሆነን እንፋጠጣለን ብሎ የጠበቀ አይመስልም ብሏል፡፡ በሩን ከፍተው ሲገቡ ወደ ውስጥ ሊያመልጥ ቢሞክርም ወዴትም ሳይደርስ እንደያዙት የሚናገረው ብርሃኑ፤ ወዲያው  ተዝለፍልፎ መውደቁንም ገልጿል፡፡ ሰውነቱ ደካክሞና አቅም ክዶት እንደነበር በመግለፅም የምግብ እጥረት ሳያጋጥመው እንዳልቀረ ግምቱን ገልጿል፡፡
ወጣቱ ኪሱ ሲፈተሽ የብር ጌጦችና ጥቂት የወርቅ ቀለበቶች የተገኙበት ሲሆን ጀርባው ላይ ባዘለው ቦርሳ ውስጥ ደግሞ ውሃ፣ ቆሎ፣ መቀስ፣ ባትሪ እና የስለት መሳሪያዎች እንደተገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተጠርጣሪው ወጣት ሰውነቱ በመጎዳቱና አቅም በማጣቱ፣ ራስ ደስታ ሆስፒታል ገብቶ ለአምስት ቀናት የህክምና እርዳታ የተደረገለት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ ፖሊስ ጣቢያ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ ጠቁሟል፡፡ ፒያሳ የሚገኙ አብዛኞቹ ወርቅ ቤቶች በመደብራቸው ውስጥ እያንዳንዳቸው ከ2 ሚ.ብር ያላነሰ የወርቅና ብር ጌጣጌጦች እንዳላቸው ምንጮች ሲገልፁ፤ በዚህ ዓመት ብቻ በእነዚህ ወርቅ ቤቶች ከአራት ጊዜ በላይ የዝርፊያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው ፖሊስ ገልጿል፡፡

addis admas

በፒያሳ ወርቅ ቤቶች ኮርኒስ ውስጥ ለ3 ቀን ያሸመቀው ወጣት ተያዘዘ

  • አበባየሁ ገበያው /addisadmassnews/

በረሃብ ደካክሞ ለ5ቀን ራስ ደስታ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎለታል

news

በአዲስ አበባ ከሚፈርሱ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየተከሰተ ነው

ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ በቀጠለው የቤት ፈረሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በድንገት ቤቶቻቸው እየፈረሱባቸው ንብረቶቻቸውን እየተዘረፉ ሜዳ ላይ እየወደቁ ሲሆን፣ ትናንት ሌሊት በድንኳን ተጠልለው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል የ4 ልጆች አባት የሆኑ ግለሰብ በጅብ ተበልተው ዛሬ ከፊል አካላቸው በፖሊሶች መነሳቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

ፖሊሶች መረጃው እንዳይወጣ አካባቢውን ተቆጣጥረው ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲያደርጉ የዋሉ ሲሆን፣ ቀሪው አስከሬን ከተነሳ በሁዋላ ደግሞ በማይክራፎን እየዞሩ በላስቲክ ድንኳን የተጠጉትን ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያዘዙዋቸው ነው። ብዙዎቹ ልጆቻቸውን የት እንደሚያስጠጉዋቸው ጨንቋቸው ለኢሳት በመደውል የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል

የሟቹን ግልሰብ ስም ለማግኘት ጥረት ብናደርግም እስካሁን አልተሰካላንም።ፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናድርግም አልተሰካላንም።

ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት በጻፉት የጋራ ደብዳቤ ደግሞ ፣ እንደ አዲስ ሰሞኑን የሚፈርሱ ቤቶች በዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተስፋ በተደረገ ፈንድ ለሚገነባው የኦሎምፒክ መንደር ፕሮጀክት ቦታ ለማዘጋጀት ሲባል በመሆኑ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የህዝቡን ስቃይ አይቶ፣ ድጋፉን እንዲያዘገይ ጠይቀዋል።

ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው “የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 2 ሚሊዩን የኢትዮጵያ ብር እንደሚሰጣቸው” ገልጸዋል።

“በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሦስት ቀናት ውስጥ መኖሪያቸውን ነቅለው ከአካባቢው እንዲወጡ ጥብቅ ትዕዛዝ የተላለፈው ከዚህ ፕሮጅክት ጋር በተያያዘ መሆኑን ነዋሪዎች በደብዳቤያቸው ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ” የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ከዚህ በፊት ቤታቸውን ነቅለው አካባቢውን እንዲለቁ በተደጋጋሚ እንደ ተገለጸላቸው የሚጠቁም  ቢሆንም ፣  ከዚህ በፊት ቤት ግን አንድም ቀን ነዋሪዎቹ ነቅለው እንዲነሡ እንዳልተነገራቸውና ደብዳቤም ተጽፎላቸው እንደማያውቅ” ጠቅሰዋል፡፡

በሦስት ቀናት ውስጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የታዘዘበት ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ሁሌም እንደ ሚያደርጉት የኗሪዎችን ቤት ነቅለው በመወሰድ እንጨቶችን፣ ቆርቆሮዎችን፣ በሮችንና መስኮቶችን በወረዳ አሰተዳደር ቅጥር ግቢ እያጫረቱ በመሸጥ ቤት አፍራሾቹና አመራሩ እንዲካፈሉት ለማድረግ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

“የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ከክፈለከተማው አስተዳደር የመጣ ትእዛዝ ነው ምንም ማድረግ አልችልም የሚል መልስ ለአቤቱታ አቅራቢዎች ሲሰጡ፣ የክፍለ ከተማው አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ደግሞ አቤቱታ አቅራቢዎች ከቢሯቸው እንዲባረሩ ማስደረጋቸውን ነዋሪዎች በጽፋቸው አስፍረዋል።

ኗሪዎች በንብረታቸው ላይ ሊካሄድ የታቀደውን ዝርፍያ በመፍራት የቤቶቻቸውን ጣራና በር አንስተው ዘመድ ያለው ከዘመድ የሌላቸው ደግሞ ላስትክ ዘርግተው በተጠለሉበት ቅዳሜና እሁድ ባለማቋረጥ የዘነበውን ዝናብ በላያቸው ማሳለፋቸውን፣ አራስ እናቶች እና አዲስ የተወለዱ ሕጻናት፣  ነፍሰጡር ሴቶች  በበሽታ ላይ መውደቃቸውንም አመልከተዋል።

የኢህአደግ መንግስት በሕይወት እያለን ገድሎን በድኖቻችንን በሜዳ ላይ በትኗል የሚሉት ነዋሪዎቹ፣  በካሬ እስከ ሠላሳ ሺ ብር ድረስ የሚያጫርቱትን የአዲስ አበባ መሬት 18 ብር ብቻ ተቀብለው እንዲለቁ የታዘዙ በዙሪያችን ያሉ የኦሮሚያ አርሶ አደሮች እያለቀሱ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው መጨረሻ ” የኦለምፒክ ፌዴሬሽን በዓላማውና ባለው እሴት ሰብዓዊ መብትን ከሚጋፋ ተግባር ጋር የማይተባበር ተቋም ቢሆንም በጭካኔ ከሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት መተባባሩን ኮንነዋል።

” በኢትዮጵያውያን ላይ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ስም እያረፈ ያለውን ሊረሳ የማይችል ጠባሳ በተመለከተ  በማስገንዘብ በእኛ ላይ ለሚፈጸመው ግፍ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚያገኘውን ፈንድ እንዲቆምላቸው” ጠይቀዋል።

ከአለማቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችም ጉዳዩን እንዲያደርሱላቸው ተማጽነዋል።

ደብዳቤውን የጻፉትን ሰዎች በስልክ አነጋግረን እንደተረዳነው፣ ደብዳቤያቸውን ከጻፉ 2 ሳምንታት ያለፈው ሲሆን፣ መንግስት የሚወሰድውን እርምጃ በመፍራት እስካሁን ይፋ ለማድረግ ሳይፈልጉ ቀርተዋል።

news