Archive | June 2014

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?

መስፍን ወልደ-ማርያም
ሰኔ 2006 ዓ.ም

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

teddy

በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣ ስሙ እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤

ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣» (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤ በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦

ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣

ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።

ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣ አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ እንኳን የሌላቸው ናቸው።

ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤ እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?

አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤ የጨለማዎቹም ሰዎች እንደገና ተነሡ፤ ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤ አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።

የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።

በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤ የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።

ዳያስፖራው በሁለት ቢሊዮን ብር ሆስፒታል ሊገነባ ነው

የኢትዮ-አሜሪካን ሐኪሞች ቡድን አዲስ አበባ ውስጥ በሁለት ቢሊዮን ብር  ለሚያሠራው ሆስፒታል ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ አኖረ፡፡

ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው 30 ሺሕ ሜትር ካሬ ቦታ ላይ በሚገነባውና በዓይነቱ ለኢትዮጵያ ልዩ በሆነው ሆስፒታል የአጥንት፣ የጅማት፣ የልብ፣ የደም ሥር፣ የጭንቅላትና ሌሎችም ቀዶ ሕክምናዎች የሚካሄዱበት ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለዘላቂ የጤና አጠባበቅ ፕሮግራም የሚረዱ ተቋማትና ማዕከላት ይኖሩታል፡፡

ቡድኑ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙት የውስጥ ደዌ ሐኪምና የፕሮጀክቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ደምሴ  እንደገለጹት ከማዕከላቱም መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ስምንት የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል አገሮች የሚገለገሉበት የካንሰር ማዕከል ይገኝበታል፡፡ ለዚህም እውን መሆን ቡድኑ ከአባል አገሮቹ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ሆስፒታሉ ዘመናዊ መመርመሪያ ቴክኖሎጂዎችና 300 አልጋዎች የሚኖሩት ሲሆን፣ የኢትዮጵያንና አካባቢውን አገሮች ብሎም የአፍሪካን የጤና አገልግሎት ደረጃ ትርጉም ባለው መልኩ የሚቀይር የልቀት ማዕከል እንዲሆን የሚደረግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሆቴል፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ቢሮዎች፣ የመድኃኒት መደብሮች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂምና ወጌሻ እንደሚይዝ፣ አገልግሎት መስጠት በሚጀምርበትም ወቅት ለሕክምና ወደ ውጭ የሚሄዱትን ሕሙማን ቁጥር እንደሚቀንስ፣ ሜዲካል ቱሪዝምን ለመጀመር የሚረዱ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች፣ ለሕክምና ባለሙያዎችና ለሌላው የኅብረተሰብ ክፍል የሥራ መስክ እንደሚፈጥርና ለመንግሥት ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ በሚገኙ 12 ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በ2003 ዓ.ም. የተመሠረተው ኢትዮ-አሜሪካን የሐኪሞች ቡድን በአሜሪካ እውቅና ያለው ሲሆን፣ ዓላማውም ኢትዮጵያ ውስጥ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ሆስፒታል ማቋቋምና በጤናው ዘርፍ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

ሆስፒታሉ እውን ሲሆን፣ በውጭ አገር ያሉ ከፍተኛ ትምህርትና ዕውቀት ያላቸው ሐኪሞች በዚህ ፕሮጀክት አማካይነት ወደ አገር ውስጥ በመምጣት ያላቸውን ልምድና ዕውቀት የሚያካፍሉና የአገሪቱን የሕክምና አገልግሎት ዘርፍ ለማጠናከር የሚሠሩ ይሆናል፡፡

በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮፓ በሚገኙ አባል ሐኪሞች ላይ በተካሄደው የዳሰሳ ጥናት የሆስፒታሉ ግንባታ በሚያልቅበት ጊዜ ከአባሎቻቸው 37 ከመቶ ያህሉ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ለማገልገል እንደሚፈልጉ መረጋገጡን ዶ/ር ተስፋዬ ጠቅሰው፣ የሆስፒታሉ ግንባታ ከሦስት ዓመታት በኋላ ተጠናቅቆ አገልግሎት እንደሚሰጥም አስታውቀዋል፡፡

ዶክተር ሔኖክ ገብረፃድቅ ገብረእግዚአብሔር የልብ ሐኪምና የቡድኑ ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ‹‹በአሁኑ ጊዜ የአባል ሐኪሞቹ ቁጥር ከ200 በላይ ከፍ ማለቱንና ከሐኪሞቹም መካከል ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት በሰሜን አሜሪካ  የቀሩት በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪካ እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡

ሆስፒታሉ ሥራ ሲጀምር በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያክም ይሆናል ወይ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ ሆስፒታሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አኳያ ዋጋው ከፍ ሊል እንደሚችል፣ በዚህም መሠረት አቅም ለሌላቸው መደገፊያ የሚሆን የኢትዮ-አሜሪካ ሐኪሞች ቡድን ፈንድ መቋቋሙን ዶ/ር ግርማ ተፈራ የቡድኑ የቦርድ ሰብሳቢ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በዚህ ፈንድ አማካይነት አቅም የሌላቸውን ለመርዳት ታስቧል፡፡ የሐኪም አባሎቻችን ዋነኛ ፍላጎት ግልጋሎት መስጠት ላይ ያተኮረ ቢሆንም እንደዚህ ያለ ተቋም በበጎ አድራጎት ብቻ ይሥራ ከተባለ ራሱን ሊያኖር አይችልም›› ብለዋል፡፡

አቶ መላኩ ንጉሤ የቡድኑ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰርና ጀነራል ካውንስል የሆስፒታሉ ግንባታ የሚካሄደው በሁለት ምዕራፎች ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ምዕራፍ  አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚመደብ፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ ለሚያስፈልገው ገንዘብ  ከአባላት ብቻ 20 ከመቶ ያህል መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

የተሰበሰበው ገንዘብ የሕንፃው ዲዛይንና ግንባታውን ለማስጀመር እንደሚያስችልና በተጨማሪም በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር በትብብር ለመሥራት መታሰቡን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ መወያየታቸውን ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከሌሎችም ዓለም አቀፍ ባንኮች ገንዘብ ለማግኘት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

80 የሚደርሱ የኢትዮ አሜሪካን ሐኪሞች ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሁለት ቀናት ሥልጠና የሚሰጡ መሆኑም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ልጅ በእንግሊዝ መነጋገሪያ ሆኗል

ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ 19 የእንግሊዝ ጠ/ ሚኒስትሮች የተማሩበት ታዋቂ ኮሌጅ ይገባል “ፖለቲከኛ ለመሆን የግድ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የለብኝም!…” – ልጁ

“ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን አንጸባራቂ ኮከብ እንደሚሆን አምናለሁ!” – መምህሩ

Ishak Ayiris Eton Scholar

በአገረ እንግሊዝ ያጡ የነጡ ድሆች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች አንዷ ናት – ኒውሃም፡፡
እዚህ ግባ የሚባል ገቢ የሌላቸውና ከመንግስት በሚያገኙት ድጎማ ከእጅ ወደአፍ ኑሮን የሚገፉ ድሃ ዜጎችና ስደተኞች የከተሙባት የምስራቅ ለንደኗ ኒውሃም፣ ከሰሞኑ የበርካታ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን የዜና ርዕስ ሆናለች፡፡
የድሆች መንደር ኒውሃም፣ በአንድ ልጇ ስሟ ተደጋግሞ ተጠራ። ነገ ከነገ ወዲያ የኒውሃምና የድሃ ነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን፣ የመላ እንግሊዝ ተስፋ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት የተሰጠው ይህ ልጅ፣ ይስሃቅ አይሪስ ይባላል፡፡ ይስሃቅ አሁን፣ የመንግስት ተረጂ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወላጆቹ የአቶ አባተ እና የወ/ሮ በቀለች ብቻ ሳይሆን የኒውሃም ብሎም የእንግሊዝ ልጅ ነው፡፡ ከሰሞኑ ስለይስሃቅ የተሰማው ወሬ፣ ለወላጆቹ ብቻ አይደለም የምስራችነቱ – ለመላ ኒውሃም ነዋሪዎች ጭምር እንጂ፡፡
“የኒውሃሙ ይስሃቅ፣ የኤተን ኮሌጅ ተማሪ ሊሆን ነው!” ሲሉ ዘገቡ፣ እነ ቢቢሲና ዘ ጋርዲያን፡፡
ከኒውሃም ድሆች መካከል የሚኖረው ይስሃቅ፣ የሞላላቸው የእንግሊዝ ባለጸጎችና ታላላቅ የአገሪቱ መሪዎች ተመርጠው ወደሚገቡበት ቅጽር ግቢ ይገባ ዘንድ ተጠራ፡፡ በመንግስት ድጎማ ከሚተዳደር እዚህ ግባ የማባይል ተራ ትምህርት ቤት ወጥቶ፣ በአገረ እንግሊዝ ዝናቸው ከናኘ ኮሌጆች አንዱ ወደሆነው ታዋቂው ኤተን ኮሌጅ ሊገባ ነው፡፡
“ታዲያ ኮሌጅ መግባት አዲስ ነገር ነው እንዴ!?… የልጁ ኮሌጅ መግባት ዜናነቱ ምን ላይ ነው!?” የሚል ጥያቄ የሚሰነዝር አንባቢ፣ እሱ ልጁንም ኤተንንም በቅጡ የማያውቅ ሊሆን ይችላልና አይፈረድበትም።
ልጁ ይስሃቅ ነው፡፡ ከኒውሃም ድሆች መካከል በመንግስት ድጎማ ኑሯቸውን የሚገፉ የስደተኛ ኢትዮጵያውያን ወላጆች የአብራክ ክፋይ። በመንግስት ድጎማ በሚተዳደር እዚህ ግባ የማባይል የማህበረሰብ ትምህርት ቤት የሚማር ያልተመቸው ብላቴና፡፡ ግማሽ ያህሉ ተማሪዎች፣ ከመንግስት የሚሰፈርላቸውን የእለት ቀለብ እየተመገቡ የሚማሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ ቀለም ሲቆጥር የሚውል ያልደላው ተማሪ፡፡

David-Cameron
ኮሌጁ ደግሞ ኤተን ነው፡፡ ኤተን ዝም ብሎ ኮሌጅ አይደለም። እንኳን በመንግስት ድጎማ ለሚተዳደሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን፣ ለሞላላቸው እንግሊዛውያን ወላጆችም ልጅን ከፍሎ ለማስተማር የሚያዳግት ውድ ኮሌጅ፡፡ የተመረጡ ተማሪዎች የሚገቡበት፣ የላቁ ተመራቂዎች የሚወጡበት ዝነኛ ግቢ ነው – ኤተን፡፡ እንግሊዝ የወቅቱን ጠቅላይ ሚኒስትሯን ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ፣ 19 ጠቅላይ ሚኒስትሮቿን ያገኘችው ከዚህ የተከበረ የልሂቃን አጸድ ውስጥ ነው፡፡
የድሃው ልጅ ይስሃቅ፣ በመንግስት ድጎማ ከሚተዳደር እዚህ ግባ የማባይል ተራ ትምህርት ቤት ወጥቶ፣ በአገረ እንግሊዝ ዝናቸው ከናኘ ኮሌጆች አንዱ ወደሆነው ታዋቂው ኤተን ኮሌጅ የመግባት ዕድል ማግኘቱ ነው፣ ነገርዬውን የእነ ዘጋርዲያን ትልቅ ወሬ ያደረገው፡፡
አንድ ዕለት…
ተማሪው ይስሃቅና የፎሬስት ጌት ትምህርት ቤት መምህሩ ሲሞን ኢሊየት፣ ያችን የለመዷትን የምሳ ሰዓት ወግ ጀመሩ፡፡ ይስሃቅና መምህር ሲሞን በኢራቅ ስላለው ጦርነት ማውራት ከጀመሩ አንድ ወር ያህል ሆኗቸዋል፡፡ መምህሩ የተማሪያቸውን ዝንባሌ ተረድተዋል፡፡ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንደሚመስጡት ልብ ብለዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በአለማቀፋዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያነሳላቸው ጥያቄዎች፣ በውስጡ ያለውን እምቅ ስሜት ፍንትው አድርጎ አሳይቷቸዋል፡፡ ከፎሬስት ጌት የተሻለ ትምህርት ቢያገኝ፣ ጥሩ ፖለቲከኛ እንደሚወጣው ተሰምቷቸዋል፡፡ ለዚህ ነው መምህሩ ለተማሪያቸው አንዲት ሃሳብ የሰነዘሩለት፡፡
“እኔ እምልህ ይስሃቅ፣ ለምን ግን ለኤተን ኮሌጅ አመልክተህ ነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት አትሞክርም?” ነበር ያሉት መምህሩ። እውነቱን ለመናገር ይስሃቅ፣ እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ኤተን ስለሚባለው ኮሌጅ እምብዛም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ይስሃቅ መምህሩ ያቀረቡለትን ሃሳብ እንደዋዛ ችላ ብሎ አላለፈውም፡፡ ስለ ጉዳዩ ያማከራቸው አባቱ አቶ አባተ “በርታ” ሲሉ አበረታቱት፡፡
ይስሃቅ እንደተባለው በረታ፡፡ የነጻ የትምህርት እድል ማመልከቻውን ወደ ኤተን ሰደደ፡፡ ይህ እድለኛ ብላቴና፣ ለታዋቂው ኤተን ኮሌጅ ያስገባው ማመልከቻ ተቀባይነት አግኝቶ ለቃለ መጠይቅ ተጠራ፡፡ ከትምህርት ቤቱ መልማይ ባለሙያዎች ጋር ተገናኘ፡፡ በተደረጉለት ተደጋጋሚ ቃለ መጠይቆች የመዛኞቹን ቀልብ መግዛት የቻለው ይህ ተማሪ፣ በስተመጨረሻም ያንን የተከበረ ግቢ አልፎ ይገባ ዘንድ ተመረጠ፡፡ በኮሌጁ የሁለት አመታት ነጻ የትምህርት እድል ተሰጠው፡፡
አሁን የዚህ ታላቅ ግቢ በር ከባለጸጋ ላልተወለደው ብላቴናም ወለል ብሎ ተከፍቷል፡፡ የስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ወላጆች የአቶ አባተ እና የወ/ሮ በቀለች የአብራክ ክፋይ የሆነው ይስሃቅ፣ ከሰሞኑ 76ሺህ የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ነጻ የትምህርት ዕድል አግኝቶ ወደ ኤተን ለማምራት ጓዙን እየሸከፈ ነው፡፡
መስከረም ላይ ይስሃቅ ከዚያች የድሆች መኖሪያ መንደር ከኒውሃም ወጥቶ የቴምስን ወንዝ ተሻግሮ ተጓዥ ነው – ወደ ኤተን ኮሌጅ ቅጽር ግቢ፡፡ ኤ ሌቭል በተባለው ደረጃ የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የሂሳብ፣ የፍልስፍናና የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን መከታተል ወደሚጀምርበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም፡፡
ለይስሃቅ ነገ እንደ ትናንት አይሆንም፡፡
የአገሪቱ መንግስት ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት እድል ተጠቃሚነት በሚሰጠው የገንዘብ ድጎማ በሚተዳደረው የፎሬስት ጌት የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ነበር፣ ትምህርቱን ሲከታተል የኖረው፡፡ እንደማንኛውም የኒውሃም ነዋሪ ልጆች፣ እዚህ ግባ የማይባል ትምህርት ነበር የሚማረው – ከክፍል ጓደኞቹ ከእነ ኢርፋንና አሌክሲስ ጋር፡፡
ይስሃቅ አይሪስ አሁን አርቆ ማየት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊቱ አንድ ሰፊ መንገድ ይታየዋል – ወደ ኤተን ኮሌጅ የሚያመራ፣ ከዚያም ወደ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሚያቀና፡፡ የነገ ህልሙ ይሄን መንገድ ተከትሎ መጓዝና ተገቢውን ትምህርት ተከታትሎ ሲጨርስ በፖለቲካው መስክ መሰማራት ነው፡፡
“በኤተን ኮሌጅ ለሁለት አመታት የሚሰጠኝን ትምህርት ካጠናቀቅኩ በኋላ፣ ወደ ኒውሃም ከመመለሴና በፖለቲካው መስክ ከመሰማራቴና ምናልባትም በገለልተኛ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩነት ከመወዳደሬ በፊት፣ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ፖለቲካ ወይም ታሪክ ማጥናት እፈልጋለሁ፡፡ ለእኔ የሌበር ፓርቲ ፖለቲከኞችና ወግ አጥባቂዎች ላይ ላዩን ሲታዩ ለየቅል ይምሰሉ እንጂ፣ ጀርባቸው ሲፈተሸ አንድ ናቸው፡፡ ኦክስፎርድ የምገባው ፖለቲካ ተምሬ ለመውጣትና እንደማንኛውም ፖለቲከኛ የተለመደውን ስራ ለመስራት አይደለም፡፡ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው የምፈልገው፡፡” ብሏል ይስሃቅ፡፡
የይስሃቅ የትምህርት ዕድል፣ ህይወቱን ወደተሻለ አቅጣጫ እንደሚያመራትና የሆነ ጊዜ ላይ ስማቸው ከሚጠራ ታላላቅ እንግሊዛውያን አንዱ እንደሚያደርገው ብዙዎች ግምታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ትልቅ ተስፋ እንደሚጠብቀውም ይተነብያሉ፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ደግሞ፣ በ1440 ከተመሰረተው ከዚህ ታዋቂ ኮሌጅ ተመርቀው የሚወጡ ብዙዎች በተሰማሩበት የሙያ መስክ እውቅና ማግኘታቸው ነው፡፡
“በምኖርበት የኒውሃም ማህበረሰብ ውስጥ፣ አደንዛዥ እጾችና የወንጀል ድርጊቶች ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደሩ ነው የሚገኙት፡፡ ወላጆቼ ከመንግስት በሚደረግላቸው ድጋፍና ጥቅማጥቅሞች ነው የሚኖሩት። ይሄም ሆኖ ግን፣ ድህነቱ እንዳለ ሆኖ ኒውሃምን እንደቤቴ ነው የማያት። ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ተከታትዬ ከጨረስኩ በኋላ፣ ተመልሼ ወደ ኒውሃም እመጣለሁ፡፡ ከዚያም ቀሪ ህይወቴን የኒውሃምን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ስራ ላይ ተሰማርቼ እገፋለሁ፡፡” ይላል ይስሃቅ ስለወደፊት እቅዱ ሲናገር፡፡
ይስሃቅ ያገኘው የትምህርት ዕድል ለወላጆቹ ትልቅ ደስታን ፈጥሯል፡፡
“አባቴ በህይወት ዘመኑ ተሳክተው ማየት የሚፈልጋቸው ሁለት ህልሞች እንዳሉት ይናገር ነበር፡፡ የመጀመሪያው ወደ እንግሊዝ መምጣት ነበር፡፡ ሁለተኛው ህልሙ ደግሞ፣ ልጁ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በተማሩበት ኮሌጅ ሲማር ማየት ነበር፡፡ አሁን ሁለቱም ህልሞቹ እውን ሆነውለታል” ብሏል- ይስሃቅ፡፡
እርግጥም አቶ አባተ ሁለት ህልሞች ነበሯቸው፡፡ የ17 አመት ወጣት ሆነው ነው ከአገራቸው ኢትዮጵያ በመነሳት ውጣ ውረድ የበዛበትን የስደት ጎዳና ተከትለው ጉዞ የጀመሩት፡፡ ካይሮ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት ደጋግመው ሞክረው፣ በሶስተኛው ተሳክቶላቸው ግብጽ የገቡት አባቱ፣ ህልማቸው የእንግሊዝን ምድር መርገጥ ነበር፡፡ ይህ ህልማቸው እውን ከሆነ ከሃያ አመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ የጤናቸው ጉዳይ አላሰራ ብሏቸው እስካቋረጡበት ጊዜ ድረስ፣ በእንክብካቤ ሰጪነት ተቀጥረው ሲሰሩ ነው የኖሩት፡፡ ሁለተኛው ህልማቸው ደግሞ፣ እዚያው እንግሊዝ ከገቡ በኋላ ካገኟት የትዳር አጋራቸው ከወ/ሮ በቀለች የወለዱት ልጃቸው ይስሃቅ፣ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሲማር ማየት ነበር – ከሰሞኑም ይሄው ህልማቸው እውን ሆነ፡፡
“ለኤተን ኮሌጅ የነጻ የትምህርት ዕድል ማመልከቻ ሊያስገባ ማሰቡን ሲያማክረኝ በደስታ ነበር የተቀበልኩት፡፡ ይሄም ሆኖ ግን፣ እንዳሰበው ኮሌጁ ማመልከቻውን ተቀብሎ የትምህርት ዕድል ባይሰጠው፣ ልጄ ይከፋብኝ ይሆን ብዬ መስጋቴ አልቀረም” ብለዋል አባትዬው በወቅቱ ስለነበረው ነገር ለዘጋርዲያን ሲናገሩ፡፡ እናቱ ወ/ሮ በቀለች በበኩላቸው፣ ይስሃቅ ልዩ ተሰጥኦ የታደለ ብስል ልጅ ነው ሲሉ ይመሰክሩለታል፡፡
ይስሃቅ ግን እናቱ እንዳሉት እርግጥም የተለየ ብቃት የታደለና ተጋንኖ የሚነገርለት ልጅ አለመሆኑን ነው የሚናገረው፡፡ “እውነቱን ለመናገር፣ የላቀ አእምሮ አለው ተብሎ ያን ያህል ተጋንኖ የሚወራልኝ ሰው አይደለሁም፡፡ በትምህርቴም መካከለኛ ውጤት ነበር የማመጣው። ያም ሆኖ ግን ለንባብ የተለየ ፍቅር አለኝ፡፡ በተለይ መምህሬ ስለ ኤተን ኮሌጅ ከነገሩኝ በኋላ ደግሞ፣ ልቦለድ ያልሆኑና በታሪክ፣ በወቅታዊ ጉዳዮችና በፖለቲካ ላይ ያተኮሩ በርካታ መጽሃፍትን ማንበብ ጀምሬያለሁ” በማለት፡፡
“አንዳንድ ጋዜጦች፣ ‘በመንግስት ድጎማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ልጅ፣ ወደ ኤተን ሊገባ ነው’ የሚል ዘገባ አሰራጭተዋል፡፡ እኔ እንደማስበው ግን፣ ወደዚህ ኮሌጅ የመግባት ዕድል ያገኘሁት በድጎማ የሚኖሩ ስደተኛ ወላጆች ልጅ ከመሆኔ ጋር ተያይዞ በተደረገልኝ ልዩ ድጋፍ ወይም ቅድሚያ በማግኘት አይደለም፡፡ ኮሌጁ ባደረገልኝ ቃለ መጠይቆችና በተሰጡኝ ፈተናዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሌ እንጂ!” ብሏል ይስሃቅ ስኬቱ በጥረት እንጂ በችሮታ የተገኘ አለመሆኑን ሲናገር፡፡
ከዚህ ቀደም የተከታተለው ትምህርት እምብዛም ጥራት ያለው አለመሆኑ፣ በኤተን ኮሌጅ ከሚገጥሙት የላቁ ተማሪዎች ጋር ተወዳድሮ ውጤታማ እንዳይሆን እክል ይፈጥርበት እንደሆን የተጠየቀው ይስሃቅ፣ በፍጹም ሲል ነበር ምላሹን የሰጠው፡፡
“በእነሱና በእኔ መካከል ያለው ብቸኛ ልዩነት ያደግንበት ማህበረሰብ በውስጣችን የራስ መተማመን ስሜት በማስረጽ ረገድ የሚከተለው አካሄድ ነው፡፡ እነሱ ገና ከልጅነታቸው ጀምረው የፈለጉትን ነገር የማሳካት ብቃት እንዳላቸው እየተነገራቸው ነው ያደጉት፡፡ ወደኤተን ሲገቡም ስኬታማ ሆነው እንደሚወጡ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የላቸውም፡፡ እኔ ባደግሁባት ኒውሃም ግን እንዲህ አይነት አስተዳደግ የለም፡፡ ስኬታማ የመሆን ብቃት እንዳለህ ሳይነገርህና በራስ የመተማመን ስሜት ሳታጎለብት ነው የምታድገው፡፡ እኔን ለዚህ ደረጃ ያበቃኝ መምህሬ ሲሞን ኢሊየት ያደረጉልኝ ማበረታታትና ድጋፍ ነው” ብሏል ይስሃቅ፡፡
ጋዜጠኞቹ እንዳሉት፣ እርግጥም በኤተን ኮሌጅ ለመማር ከሌሎች የተሻሉ አካባቢዎች የሚመጡ ተማሪዎች ከእሱ የላቁና ለውድድር የሚያዳግቱ አለመሆናቸውን፣ ለማረጋገጥ ጊዜ እንዳልፈጀበት ነው ይስሃቅ የሚናገረው፡፡
“በኤተን ኮሌጅ ለቃለመጠይቅ በተገኘሁበት ወቅት ያጋጠሙኝ ተማሪዎች፣ ከእኔ የተለዩና የላቀ አእምሮ ያላቸው እንዳልሆኑ ተረድቻለሁ፡፡ ስንገኛኝ ያቀረቡልኝ የመጀመሪያው ጥያቄ፣ የየትኛው እግር ኳስ ክለብ ደጋፊ ነህ የሚል ነበር፡፡ እኔ የማስበው የነበረው ስለፖለቲካ ወይም ስለሌላ አለማቀፋዊ ጉዳይ ይጠይቁኛል ብዬ ነበር” ብሏል ይስሃቅ፡፡
የኒውሃሙ ተማሪ በመጪው መስከረም ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ዊንድሶር ውስጥ ወደሚገኘው ኤተን ኮሌጅ ያመራል፡፡ ከማህበረሰብ ትምህርት ቤት ወጥቶ፣ ከአዲሱ የኤተን ኮሌጅ ማህበረሰብ ጋር ይቀላቀላል፡፡ ይስሃቅ ከቤተሰቡ የሚነጥለው ቀጣዩ ጉዞ ይከብደው እንደሆን ተጠይቆ ነበር፡፡
“ከቤተሰቦቼ ተነጥዬ ወደ ኤተን መግባቴ ከእኔ ይልቅ ለቤተሰቦቼ ነው አስቸጋሪ የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም ከእነሱ ተነጥዬ የምሄደው ወደ ዊንድሶር ነው፡፡ ዊንድሶር ደግሞ አሁን ከምኖርባት ኒውሃም ያነሰ ግርግርና ጩኸት ያለባት አካባቢ ናት፡፡ ትልቅ እድል ነው ያጋጠመኝ፡፡ እርግጥ ነው፣ የምሄደው ከቀድሞው ፍጹም የተለየ ነገር ወዳለበት አካባቢ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ካደግሁበት ኒውሃምም ሆነ ከተማርኩበት ፎሬስት ጌት ትምህርት ቤት ማህበረሰብ የተለየ ከሆነው የኤተን ማህበረሰብ ጋር ነው የምቀላቀለው፡፡ ቢሆንም አይከብደኝም ብዬ አስባለሁ” በማለት መልሷል ይስሃቅ፡፡
መምህሩ ሲሞን ኢሊየትም ቢሆኑ ተማሪያቸው በኤተን ኮሌጅ የሚገጥመውን አዲስ አኗኗር ተላምዶ አላማውን በማሳካት ውጤታማ እንደሚሆን ጥርጥር የላቸውም፡፡
“ይስሃቅ አሁንም ቢሆን፣ ወጣት ተማሪዎች የእሱን ፈለግ ተከትለው እንዲጓዙ ያነሳሳ ተማሪ ነው፡፡ ነገ ከነገ ወዲያም ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን አንጸባራቂ ኮከብ እንደሚሆን አምናለሁ!” ብለዋል የቀለም አባቱ ኢሊየት፡፡
“ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን ህልም አለህ?” የሚል ጥያቄ ሰንዝሮለት ነበር የዘጋርዲያኑ ዘጋቢ ለይስሃቅ፡፡
“ፖለቲከኛ ለመሆን የግድ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የለብኝም… ከታች ወዳለው ህዝብ ወርዶ ማህበረሰቡን የሚለውጡ ስራዎችን የሚሰራ ፖለቲከኛ ልሆን እችላለሁ!” ሲል መልሷል፡፡
ጋዜጠኛው ሌላ ጥያቄ ይዞ ወደ አባትዬው ፊቱን አዞረ፡፡
“በርካታ ጠቅላይ ሚንስትሮችን ወዳፈራው ኤተን የሚጓዘው ልጅዎ፣ አንድ ቀን የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ብቅ ይላል ብለው ያስባሉ?” ሲልም ጠየቀ፡፡
“ማን ያውቃል!?…” አባትዬው ፈገግ ብለው መለሱ፡፡

By : Girum Teklehaimanot

Ethiopia reportedly fires 18 journalists from a state-run outlet

 By Mohammed Ademo

cjr.org

The quiet dismissal of some 10 percent of the station’s journalists underscores the country’s further descent into total media blackout – See more at: http://www.cjr.org/behind_the_news/ethiopia_cans_18_journalists.php#sthash.kNMFSHD3.dpuf

On June 25, when 18 journalists from Ethiopia’s state-run Oromia Radio and Television Organization (ORTO) arrived to start their scheduled shifts, they learned their employment had been terminated “with orders from the higher ups.”

press
The quiet dismissal of some 10 percent of the station’s journalists underscores the country’s further descent into total media blackout. The firing of dissenting journalists is hardly surprising; the ruling party controls almost all television and radio stations in the country. Most diaspora-based critical blogs and websites are blocked. Dubbed one of the enemies of the press, Ethiopia currently imprisons at least 17 journalists and bloggers. On April 26, only days before US Secretary of State John Kerry’s visit to the capital, Addis Ababa, authorities arrested six bloggers and three journalists on charges of working with foreign rights groups and plotting to incite violence using social media.

Reports on the immediate cause of the latest purge itself are mixed. But several activist blogs noted that a handful of the dismissed journalists have been irate over the government’s decision not to cover the recent Oromo student protests. An Ethiopia-based journalist, who asked not to be named due to fear of repercussions, said the 18 reporters were let go after weeks of an indoctrination campaign in the name of “gimgama” (reevaluation) failed to quiet the journalists. The campaign began earlier this month when a meeting was called in Adama, where ORTO is headquartered, to “reindoctrinate” the journalists there into what is sometimes mockingly called “developmental journalism,” which tows government lines on politics and human rights. The journalists reportedly voiced grievances about decisions to ignore widespread civic upheavals while devoting much of the network’s coverage to stories about lackluster state development.

Still, although unprecedented, the biggest tragedy is not the termination of these journalists’ positions. Ethiopia already jails more journalists than any other African nation except neighboring Eritrea. The real tragedy is that the Oromo, Ethiopia’s single largest constituency (nearly half of Ethiopia’s 92 million people) lack a single independent media outlet on any platform.

The reports of the firings come on the heels of months of anti-government protests by students around the country’s largest state, Oromia. Starting in mid-April, students at various colleges around the country took to the streets to protest what they saw as unconstitutional encroachment by federal authorities on the sovereignty of the state of Oromia, which according to a proposed plan would annex a large chunk of its territory to the federal capital—which is also supposed to double as Oromia’s capital. Authorities fear that an increasingly assertive Oromo nationalism is threatening to spin out of state control, and see journalists as the spear of a generation coming of age since the current Ethiopian regime came to power in 1991.

To the surprise of many, the first reports of opposition to the city’s plan came from ORTO’s flagship television network, the TV Oromiyaa (TVO).

A week before the protests began, in a rare sign of dissent, journalist Bira Legesse, one of those fired this week, ran a short segment where party members criticized the so-called Addis Ababa master plan. Authorities saw the coverage as a tacit approval for public displeasure with the plan and, therefore, an indirect rebuke of the hastily put-together campaign to sell the merits of the master plan to an already skeptical audience. But once the protests began, culminating in the killings of more than a dozen students in clashes with the police and the detentions and maimings of hundreds of protesters, TVO went mute, aside from reading out approved police bulletins. This did not sit well with the journalists, leading to the indoctrination campaign which, according to one participant, ended without any resolution.

In the last decade, the country’s economic improvements have become something of a cliche in the West. In March, Time Beijing correspondent Michael Schuman included Ethiopia in his new development acronym, PINEs—the NextGen emerging markets, namely the Philippines, Indonesia, Nigeria, and Ethiopia. Schuman called Ethiopia “one of Africa’s lion economies,” along with Nigeria.

Ethiopia’s state-controlled media touts the country’s “radical” economic transformation ad nauseum. In analysis after analysis, Western journalists and donors such as the World Bank Group and the International Monetary Fund refer to the country as “one of the fastest growing non-oil economies” in Africa.

Mohammed Ademo is a journalist at Al Jazeera America. He’s also the founder and editor of OPride.com, an independent news website about Ethiopia. He can be reached on Twitter @OPride.

በሸቀጦች ላይ የዋጋ ንረት እየታየ ነው

sheket

  •  Written by  አለማየሁ አንበሴ

በኪሎ 35 ብር የነበረው በርበሬ 55 ብር እየተሸጠ ነው
በ115 ብር እንዲሸጥ የተተመነው ባለ 5 ሊትሩ ዘይት 150 ብር ገብቷል

በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የስኳር፣ የዘይትና የዳቦ እጥረት ተከስቷል
የፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን የፈጠረው ነው ተብሏል

ሰሞኑን በአንዳንድ መሰረታዊ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ሲሆን ነጋዴዎችና  የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ውጤት ነው ብለዋል፡፡
በተለይ የበርበሬ፣ የስንዴ ዱቄትና የምስር ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የስኳር፣ ዘይትና ዳቦ እጥረትም መከሰቱን ሪፖርተሮቻችን በአዲስ አበባ የተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ተዘዋውረው ባደረጉት ቅኝት አረጋግጠዋል፡፡ ሸማቾች የዋጋ ጭማሪው እንዳማረራቸው ሲገልፁ፣ ነጋዴዎች፤ የሸቀጦች አቅርቦት ከፍላጎት ጋር  አልተጣጣመም ብለዋል፡፡
ከሳምንት በፊት በኪሎ 35 ብር ይሸጥ የነበረው ዛላ በርበሬ፣ እስከ 20 ብር ጭማሪ አሳይቶ ኪሎው በ55 ብር እየተሸጠ ሲሆን በንግድ ሚኒስቴር የመሸጫ ዋጋ ተመን ከወጣላቸው ሸቀጦች አንዱ የሆነው የስንዴ ዱቄት ከ12 ብር ወደ 14 ብር ከፍ ብሏል፡፡ የምስር ዋጋም በኪሎ 21 ብር የነበረው 25 ብር እየተሸጠ መሆኑን ከተለያዩ የገበያ ስፍራዎች የተሰበሰቡ የዋጋ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በሌላ በኩል ስኳር፣ ዘይትና ዳቦ የመሳሰሉትን እንደልብ ማግኘት እንደተሳናቸው ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በሳሪስ አካባቢ በአንድ ዳቦ ቤት ዳቦ ለመግዛት ተሰልፈው ያገኘናቸው አቶ ወንድይፍራው ደምሴ፤ ለቤተሰቦቻቸው በየእለቱ ዳቦ እንደሚገዙ ገልፀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደታክሲ ትራንስፖርት ሁሉ ዳቦ ለመግዛትም ሰልፍ መያዝ የግድ ሆኗል ይላሉ፡፡ ከዚህም የባሰው ግን ለረጅም ደቂቃዎች ከተሰለፉ በኋላም ዳቦ አልቋል እየተባሉ በተደጋጋሚ ባዶ እጃቸውን ወደ ቤታቸው መግባታቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በሳሪስ አብዛኞቹ የችርቻሮ ሱቆች ስኳር የጠፋ ሲሆን ያላቸውም ቢሆኑ ከበፊት ዋጋው  እስከ 4.50 ብር እየጨመሩ እንደሚሸጡ ሸማቾች ተናግረዋል፡፡ መሰረታዊ ሸቀጦችን በማቅረብ የህብረተሰቡን ፍላጎት ያሟላሉ በተባሉ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት ሱቆችም የአቅርቦት እጥረት እንዳለ የጠቆሙት ሸማቾች፤ ዘይት ባለ 5 ሊትሩ 115 ብር እንዲሸጥ የዋጋ ተመን ቢወጣለትም አሁን እስከ 150 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በጥቂት ቀናት ውስጥ የበርበሬ ዋጋ የ20 ብር ጭማሪ ለምን እንዳሳየ የጠየቅናቸው የበርበሬ አከፋፋይ  አቶ ምሳሌ ወ/አምላክ፣ የበርበሬ ምርት በአብዛኛው የሃገራችን አካባቢዎች በስፋት የሚሰበሰበው ከመስከረም እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ እንደሆነ ጠቅሰው ወደ ክረምት መግቢያ ላይ ምርት በስፋት ስለማይገኝ ዋጋው እንደሚጨምር አስረድተዋል፡፡ በአሁን ወቅት ከባሌ አካባቢ የሚመጣ በርበሬ ለገበያ እንደሚቀርብ የጠቆሙት ነጋዴው፤ አምራቾች ዋጋው ላይ ጭማሪ በማድረግ ለአከፋፋዮች እየሸጡ እንደሆነ ጠቅሰው የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም መኖሩን አብራርተዋል፡፡
ክረምት ላይ የበርበሬ ብቻ ሳይሆን የብዙ መሰረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ እንደሚጨምርም ነጋዴው ይናገራሉ፡፡ ምርቱ በሚገኝባቸው የገጠር አካባቢዎች መንገዱ ጭቃ ስለሚሆን ነጋዴው ወደ አምራቾች ሄዶ ምርቱን ለማምጣት አይሞክርም ያሉት አቶ ምሳሌ፤ ወቅቱ የእርሻ በመሆኑም ገበሬው ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለመግዛት ሲል የምርቱን ዋጋ ያዝ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡
“የአብዛኛው ሸማች ገቢ ባላደገበት ሁኔታ የሸቀጦች ዋጋ በየጊዜው መጨመሩ ጤናማ አይደለም” ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡን በአለማቀፍ ድርጅት ውስጥ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ባለሙያ፤ ወቅት እየጠበቀ በሸቀጦች ላይ የሚስተዋለው የዋጋ ጭማሪ አቅርቦትን ከፍላጎት ጋር በማጣጣም ረገድ እያደገ ነው የሚባለው ኢኮኖሚ ክፍተት እንዳለበት ያመለክታል ብለዋል፡፡ መንግስት ገበያውን ለመቆጣጠር መሞከሩም የችግሩ መንስኤ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ ገበያው በምርት አቅርቦቱ መጠን እንዲመራ መንግስት መፍቀድ አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ በበኩላቸው፤ የሸቀጦች ዋጋ መጨመርና መቀነስ የአቅርቦቱና ፍላጎቱ መጠን የሚወስነው መሆኑን ጠቅሰው፣ መንግስት ገበያ መር ኢኮኖሚ ነው የምከተለው እያለ በሌላ በኩል ዋጋ ትመና ውስጥ መግባቱ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ፡፡ መንግስት ዋጋ ከመተመን አልፎ የራሱን ጅምላ ሽያጭ እያቋቋመ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ አሰራሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ይጠቅማል ተብሎ ቢታሰብም ውጤታማ ይሆናል ለማለት አያስደፍርም ብለዋል፡፡
“በየጊዜው የጤፍ ዋጋ ቀንሷል ቢባልም ሰው መግዛት ስለተወ እንጂ በእርግጥ በሚፈለገው መጠን ዋጋው ስለቀነሰ አይደለም” የሚሉት ባለሙያው፤ የብር የመግዛት አቅሙ እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር ተደማምሮ ከውጭ የሚገቡ ነዳጅ፣ የምግብ ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳርና የመሳሰሉት ዋጋቸው በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር ይችላል ብለዋል፡፡
የሸቀጦችን ዋጋ በተመለከተ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ የሚያወጣቸው መረጃዎች ምን ያህል ትክክለኛ ናቸው የሚለው አጠያያቂ ነው የሚሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ 90 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት ሰፊ ሀገር አቅርቦትንና ፍላጎትን ማጣጣም ከባድ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ያለው የኑሮ ሁኔታ ከሌላው ለየት ይላል ያሉት አስተያየት ሰጪው፤ከተማዋ  የዲፕሎማቲክስ መዲና መሆኗ፣ የውጭ ኢንቨስተሮችና አቅም ያላቸው ሰዎች በመዲናይቱ መበራከትና ቀደም ሲል በከተማዋ ዙሪያ የነበረው ገበሬ አሁን ወደ ቀን ሰራተኝነት ተቀይሮ ሸማች መሆኑ ተፅዕኖ አሳርፏል በማለት  ያስረዳሉ፡፡ እስከ 2 ሚሊዮን የሚደርስ ገበሬ ከተማዋን ተቀላቅሎ ሸማች ሆኗል የሚል ግምት እንዳለም  ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
መንግስት በትላልቅ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ላይ ብቻ በማተኮር መሰረታዊ ፍላጎቶችን ችላ ማለቱ ጥቂቶች ብቻ በስግብግብነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በር ከፍቷል የሚሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ የተለያዩ የጅምላ ሽያጮች በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፡፡
እንዲህ ያለ የዋጋ ንረት ሲፈጠር መንግስት የተለያዩ የማረጋጊያ ስልቶችን መጠቀም እንዳለበት የጠቆሙት ምሁሩ፤ አንዳንድ መሰረታዊ ሸቀጦች በሃገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ መንግስት አቅሙ ላላቸው ባለሃብቶች ከ500 እስከ 800 ሄክታር መሬት በመስጠት እንዲያለሙ ድጋፍ ማድረግና የምርት አቅርቦቱን መጨመር አለበት ሲሉም ይመክራሉ፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ 6.5 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱን የጠቀሱት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ “ሃገሪቱ የ70 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ባለቤት ሆና ለግብርና አገልግሎት የዋለው 14 በመቶው ብቻ ነው፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውሃ ማማ ብትባልም ዛሬም ከምግብ እርዳታ ፈላጊነት መላቀቅ አልቻለችም” ይላሉ፡፡
መንግስት መሬት አልሚዎች ከባንክ ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ እያመቻቸና ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ የምርት መጠኑን በማሳደግ፣ አቅርቦቱን ከፍላጎቱ ጋር ማመጣጠን አለፍ ሲልም ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢ ማስገኘት አለበት ሲሉ የመፍትሄ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ መንግስት እስካሁን ትኩረት የሰጠው ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ መሆኑን በመግለፅም “የሃገሪቱን ሃብት ተጠቅሞ የዜጎቹን የምግብ ዋስትና ወደ ማረጋገጥ ፊቱን ማዞር አለበት” ብለዋል ምሁሩ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ተወካይ ሆነው በዚምባቡዌ ሲሰሩ፣ሮበርት ሙጋቤ ከእርሻ መሬታቸው ያፈናቀሏቸውን ነጭ ገበሬዎች አግኝተው ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ በግል ጠይቀው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ገበሬዎቹ አማራጫቸውን ሞዛምቢክ አድርገው በዘጠኝ ወር ውስጥ የሃገሪቱን ምርት በ3 እጥፍ መጨመራቸውን በመጥቀስ፣መንግስትም እንደነዚህ አይነት ባለሙያዎችን መጋበዝ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ እቅድ ያስፈልጋል የሚሉት ምሁሩ፤ በተለይ አምራቾችንና ነጋዴዎችን መቆጣጠር የሚችሉ ጠንካራ የሸማቾች ማህበራትን ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማከለ ይማም “የስንዴ አቅርቦትን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በቂ ማብራሪያ ሰጥተናል፣ ደግመን አንሰጥም፤ የዱቄት ዋጋ ጨምሯል የሚባለውም ምናልባት ንግድ ሚኒስቴር ከዘረጋው የገበያ ትስስር ውጪ የሆኑ ነጋዴዎች የሚሸጡበት ዋጋን ተመርኩዞ ሊሆን ይችላል እንጂ በንግድ ትስስሩ ስር ባሉ የንግድ ተቋማት የዱቄት ዋጋ ጭማሪ አልተደረገም” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ

stressed-948x472

ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት  አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል።

የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣  እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።

በስልጠናው የብአዴን ታሪክ አብሮ መቅረቡንና ሰልጣኞችም የብአዴንን ታሪክ በማወቃቸው መርካታቸውን ሰነዱ አክሎ ይዘረዝራል።

“ግልጽነት ያልተያዘባቸውና በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተከታታይ ውይይትና ስራ የሚጠይቁ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ድረስ ብአዴንን የማይቀበሉ እና ከ97 ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ድምጾች አሉ፣ ነገር ግን የመንግስትን የሃይል እርምጃ ተከትሎ በፍራቻ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሎአል።” ሲል አስቀምጧል።

“በውይይቱ ወቅት የታዩ የአመለካከት ችግሮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በርካታ ችግሮች ተዘርዝረው ቀርበዋል። ” በ1989 ዓም የነበረው የመሬት ክፍፍል ለቢሮክራቶች ለምን 4 ቃዳ መሬት ተሰጠ? በአማራ ክልል ብቻ የአርሶ አደር መሳሪያ ለምን ተነጠቀ? ልማቱ ወደ ትግራይ ይሄዳል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አስመራንና አሰብን መያዝ ነበረብን” የሚሉት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰልጣኞች መቅረቡን ያወሳል።

ሰነዱ በስልጠናው የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችንም ይዘረዝራል። ሰልጣኙ እርስ በርስ በመተጋገዝ፣ በመማማር ተሞክሮውን በማካፈልና በመተራረም የነበረው ሁኔታ በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ለመንግስት ህዝቡ በአብዛኛው ጥላቻ ማሳየቱ” የሚል ሰፍሮአል።

የብአዴን አመራርና አባላት ” በአብዛኛው ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ የለም ” ብለው እንደሚያምኑ፣ “ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ደንታ እንደማይሰጣቸው”፣ እንዲሁም “መንግስትን በትክክል ዋጋ ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ” በሰነዱ ማብቂያ ላይ ተገልጿል።

ሰነዱን ለኢሳት የላኩትን የኢህአዴግን ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ በህዝብ ስም ለማመስገን እንወዳለን።

የስብሰባ ጥሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ /EPPFG/አባላት በሙሉ.-

ETHIOPIAN PEOPLE PATRIOTIFRONTGUARD

10372849_474460199356613_1697143056502894361_o
የስብሰባ ጥሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አባላት በሙሉ.-
በአሻፍንበርግ ና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አባላት ድርጅታችን ዘረኛውን የወያኔን መንግስት ለመጣል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከግብ ለማድረስ የአባላት ያላሰለሰ ጥረት ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በጁላይ 26/2014 በአሻፍንበርግ ከተማ ጠርቱዋል።
ስለሆነም በጀርመን የሚገኙ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት በሃገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲያደርጉ ልባዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በእለቱም አቶ ልዑል ቀስቅስ የኢ.ህ.አ.ግ.ዘብ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን ጉደታ የኢ.ህ.አ.ግ.ዘብ በጀርመን ጸሃፊ አቶ መራ አብረሃም በኢ.ህ.አ.ግ.ዘብ የባይርን ሊቀመንበር ወ/ሪት ዘውድነሽ ንጋቱ በኢ.ህ.አ.ግ.ዘብ የሄሰን ሊቀመንበር እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች የሚገኙ መሆኑን እናስታውቃለን።
ቀን – ጁላይ 26/2014 ከቀኑ 13.00 -16.00
ቦታ- Platanenalle Strasse, 1, ከሲቲ ጋለሪ ጎን-(Aschaffenberg)
ለበለጠ መረጃ
015215385478,
015213877998,
015211799119 ይደውሉ
ETHIOPIAN PEOPLES PATRIOTIC FRONT GAURD MEMBERS MEETING IN ASCHAFFENBUG. MEMBERS OF ETHIPIAN PEOPLES PATRIOTIC FRONT GUARD’S( EPPFG-GROUP)IN ASCHAFFENBURG HAVE ORGANIZED A MEETING ON JULY 26/2014 IN ASCHAFFENBURG.
WE INVITE ALL MEMBERS AND SUPPORTERS OF THE PARTY IN GERMANY TO PARTICIPTAE ON THE MEEETING AND MAKE THEIR CONTRIBUTION TO THE STRUGGLE AGAINST WOYANE REGIME.INVITED GEUSTS ARE ATO LUEL KESKIS CHAIRMAN OF EPPFGUARD,ATO TILAHUN GUDETA EPPFGUARD GERMANY SECRETARY ,ATO MERA ABRAHAM EPPFGUARD BAYERN CHAIRMAN, ZEWEDENESH NEGATU EPPFGUARD HESSEN CHAIRMAN AND OTHERS.
DATE-JULY 26-2014
TIME 13.00-16.00
PLACE –PLATANENALLE STASSE, 1 NEAR TO CITY GALLERIE(Aschaffenberg)
FOR MOR INFORMATION CALL –
015215385478,
015213877998,
015211799119