ደሞ ኮካን


 

ሄኖክ የሺጥላ

Teddy Afro London-27

ሂደት ዝግመታችን የኤሊን፣ አስተሳሰባችን እንደወሃ ትል ከመንፈራገጥ ውጭ ምንም ሊያመነጭ እንደማይችል ግልጽ መሆኑን ገላጭ መፈለግ ልብ አልባነት ነው።
ትናንት በደሌን ቦይ ኮት ያደረጉትና ያስደረጉት ፣ ደሞ ዛሬ ኮካ ኮላን ጀመሩ አሉ። አባይን በጭልፋ ይሉሃል ይሄ ነው። እናንተዬ ምነው ጥላቻችን ቂጥ አወጣ ( ይቅርታ ማለቴ ቅጥ አጣ ? )።
በታላቁ መጽሐፍ ላይ በ ኦሪት ዘ ፍጥረት ” እግዚአብሔር ሰውን ባምሳሉ ፈጠረው ” ይላል። ከዛ ቀጥሎ ያላነበብነው ነገር አለ እንዴ ” ከዚያ ሰው መሆን የደበራቸውን በሰው አምሳል አህያ አድርጎ ፈጠራቸው የሚል ?” በጣም ይደብራል ፣ በእውነት አሁንስ እኝኝ አላችሁ። ሼም ምናምን አታውቁም እንዴ ? ለዚያውም አማሪካ እየተኖረ ፣ ቢያንስ ቢያንስ በቀን አንዴም ቢሆን እየታጠብን ፣ በቁን ሶስቴ እየበላን ፣ ምነው አእምሮዋችን ከዘር ኩዋሹዋከር እና ማራስመስ አልላቀቅም አለ።
ደባሪዎች !
እስቲ ወንድ ከሆናችሁ በለቼን ቦይ ኮት አድርጉ፣
ልብ ካላችሁ ገለምሶ ላይ በርቱ፣
ወንድ ከሆናችሁ አወዳይ ላይ አምጹ ።
በእውነት ሰው እንዲህ ታጥቦ በማየጠራ ገገማነት ስቆፈደድ እጅግ ይደብራል።
ቴዲ ለኮካ ብቻ ሳይሆን ገና ለኢትዮጵያ ነጻነት ፣ ትንሣዔም ይዘፈናል። ይሁንልህ አቦ !……

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s