Archive | June 4, 2014

የመኪና አስመጪዎች ቅሬታ

መኪና ከውጭ ሲያስገቡ እቃ እየጠፋባቸው የተቸገሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የመኪና አስመጪዎች ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።

Mekina

መኪናቸውን በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት በኩል ከጅቡቲ ወደ ደረቅ ወደብ በሚያስገቡት ሰዓት እንደ ወንበር እና ጎማ የመሳሰሉ ነገሮች እየተሰረቁባቸው እና ለከፍተኛ ወጪ እንደተዳረጉ ይናገራሉ። የመኪና አስጫኞቹን ወቀሳ እና የድርጅቱን ምላሽ አግኝተናል።

ያነጋገርናቸው ከአውሮፓ መኪና ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ ነጋዴ እና ያስመጪ ንግድ ፍቃድ ስለሌላቸው፤ ፍቃድ ካለው ጓደኛቸው ጋር ተዋውለው መኪና ያስገቡ ግለሰብን ነው። ለግለሰቦቹ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት የኢንሹራንስ እና የካሳ ክፍል ዳሬክተር የሆኑት አቶ ያሬድ ሽፈራው ለወቀሳዎቹ የሰጡት ምላሽ አለ።

ሁሉንም ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

http://www.dw.de