የሕክምና ስህተት የፈጸሙ ሐኪም ታሰሩ


የሕክምና ዕርዳታ በመፈለግ ወደ አንድ የሕክምና ተቋም የሄዱ የሁለት ወር ነፍሰ ጡር ወይዘሮን በቸልተኝነት በአካላቸው ላይ ጉዳት ያደረሱ የሕክምና ባለሙያ ታሰሩ፡፡

medical-laboratory

ክሱ የቀረበባቸው ተጠርጣሪው ዶ/ር በላቸው ቶሌራ ያደታ ሲባሉ፣ የግል ተበዳይ በሆኑት ወ/ሮ በላይነሽ ይመር ላይ ባደረሱት ጉዳት በዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው ነበር፡፡ ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት የመናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

ተከሳሽ የሌላ ሰውን አካል ወይም ጤንነት የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ እያለባቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ ኅዳር 1 2006 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 09/15 በሚገኝ የግል ክሊኒክ ውስጥ የሕክምና ስህተቱን በቸልተኝነት እንደፈጸሙ የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተበዳይ ወ/ሮ በላይነሽ ይመር የሁለት ወር ፅንስ ማህፀናቸው ውስጥ እንደነበርና የደም መፍሰስ ምልክት በማየታቸው ደሙ እንዲቆምላቸው የሕክምና ዕርዳታ ለማግኘት ወደ ክሊኒኩ መሄዳቸውን የመዝገቡ ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹በክሊኒኩም 987 ብር በመክፈል ፅንሱ ችግር ስላለበት መቋረጥ አለበት በማለት ያለጥንቃቄ በማህፀናቸው ብረት በማስገባት የማህፀናቸው ግድግዳ 3.2 ሴንቲ ሜትር እንዲሸነቆር፣ 70 ሴንቲ ሜትር ትንሹ አንጀት እንዲበላሽ ወይም እንዲሞትና ተቆርጦ እንዲወጣ የሕክምና ባለሙያው በማድረጋቸው፣ 300 ሲሲ ደም ወደ ሆዳቸው እንዲፈስ በማድረግ በፈጸሙት በቸልተኝነት አካል ላይ ከባድ ጉዳት የማድረስ ወንጀል ተከሰዋል፤›› ይላል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው የክስ መዝገብ፡፡

በጉዳዩ ላይ ላለፉት ወራት ሁለቱን ወገኖች ሲያከራክር የነበረው ፍርድ ቤቱ ባለፈው ግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም የሕክምና ባለሙያውን ጥፋተኛ በማለት በእስር እንዲቆዩ ወስኗል፡፡ በጉዳዩ ላይም ፍርድ ለመስጠት ለሰኔ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s