Archive | June 11, 2014

የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድርና ግብ ወሳኝ ቴክኖሎጂ

ብራዚል የምታስተናግደው ፤ የዘንድሮው የዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ነገ የሚጀመር ሲሆን፣ የ 5ቱም- ክፍላተ-ዓለም እግር ኳስ አፍቃሪዎች፤ ይህን ልብ አንጠልጥል የአስፖርት ውድድር አንድ ወር ሙሉ ለመከታተል ተዘጋጅተዋል። በዘንድሮው የዓለም

world

የእግር ኳስ ዋንጫ አንዱ አዲስ ነገር፤ አምና በዚህ ወር በኮንፈደሬሽን የዋንጫ ውድድር ወቅት የተሞከረው የኳስን ግብመሆን-አለመሆን፣ የሚቆጣጠረው የአጫዋች ዳኛ አስተማማኝ ረዳት የሆነው ሥነ ቴክኒክ፣ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይእንዲውል የሚደረግ መሆኑ ነው።

2,44 ሜትር ከፍታና 7,32 ሜትር ሳፋት ባለው ግብ ፣ ኳስ በአየርም ሆነ መሬት የግቡን መሥመር ካለፈች፣ ዳኛውእንደ እጅ ሰዓት በሚያሥረው መሳሪያ Goal የሚል ማረጋገጫም ሆነ መረጃ ያገኛል። Goal Line Technologyወይም Goal Decision System የተሰኘው ከ 3 አቅጣጫ ምስል የሚያሳየው ካሜራ ፣ ግብ አካባቢ ፣ የኳሷንአካሄድ—አቅጣጫና ማረፊያ በጥሞና የሚከታተል ሲሆን፤ «ኳስ መሥመር አልፋ ግብ ሆናለች –አልሆነችም!»እየተባለ ሲያነታርክ የኖረን አስቸጋሪ ጉዳይ የሚያስወግድ መሆኑ ይታመንበታል።

በአንድ የእግር ኳስ ሜዳ የሚተከል ይህ ዓይነቱ መሣሪያወደፊት ዋጋው ካልቀነሰ 240,000 ዩውሮ የሚያስወጣመሆኑ ነበር ከዚህ ቀደም የተገለጠው። «ፊፋ»አወዳድሮና ይበልጥ አስተማማኝ ነው ብሎ የመረጠው፤Goal Control የተባለውን አንድ የጀርመን ኩባንያያቀረበውን ነው። ኳስ ግብ መሆን –አለመሆኗንትክክለኛ መረጃ ሰጪ ነው የተባለውን ቴክኖሎጂአጠቃቀም የአስፖርት ባለሙያዎች እንዴት ያዩታል?ቀደም ባለው ጊዜ በኢትዮጵያ የክለቦች ቀጥሎም የብሔራዊው ቡድን አS።ልጣኝ የነበረውን ፤ በአውሮፓ የአግር ኳስማሕበር (UEFA) ፕሮፌሽናል የማሠልጠን ፈቃድ አግኝቶ አሁን በቼክ ሪፓብሊክ ፤ የተለያዩ ክለቦችን የሚያሠለጥነውንዶ/ር ተስፋዬ ጥላሁንን አነጋግሬው ነበር።

«የዚህ ቴክኖሎጂ———-»»

በሐምሌ ወር 1958 ማለት እ ጎ አ ሐምሌ 30 ቀን 1966 በኢንግላንድና ምዕራብ ጀርመን የፍጻሜ ግጥሚያ፤ መሥመርላይ የነጠረ ኳስ ግብ ተብሎ አድልዎ ተፈጽሞብናል በማለት ጀርመናውያን በየጊዜው ሲያነሱት የኖረው ጉዳይም አለ፦ጊዜው ራቅ ቢልም! FIFA የግብን ውጤት ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ለውሳኔው ሌሎች የገፋፉት ምክንያቶችም ይኖራሉ—

«ጎል ኮንትሮል» ጎል ላይን ቴክኖሎጂ አስተማማኝነቱ ተሞክሮ ቢረጋገጥለትም አሁንም የሚቃወሙ የእግር ኳስአፍቃሪዎች አልታጡም—

world 2

በዓለም ዙሪያ እጅግ ተወዳጅ የሆነው የእግር ኳስ ጨዋታየሚካሄድበት ፤ የሜዳው ስፋትና ርዝመት ፣ በ 120 እና90 ሜትር መካከል ሲሆን ፣ የአንዳንድ ኳስ ሜዳዎች ስፋትበጥቂት ሜትሮች ወይም ሴንቲሜትሮች ከመደበኛ የእግርኳስ ሜዳ ልዩነት አለው። የሆነው ሆኖ ፤ በዓለም አቀፉየእግር ኳስ ፌደሬሽን(FIFA) ደንብ መሠረት፣ የሜዳውርዝማኔ 105 ሜትር ወርዱ ደግሞ 68 ሜትር ነው። ለውጥእስኪደረግ ድረስ እስካሁን በዚሁ እንደጸና ነው። የተጋጣሚቡድኖችን ግብ ጠባቂዎች ሁለቱን ብንቀንስ 20 ተጫዎቾች ናቸው በተጠቀሰው ሜዳ ውስጥ የሚራኮቱት ። ይህምናልባት ለውጥ የሚያስፈልግበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?!

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

በሃረር በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ግጭት ተነሳ

harere

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀበሌ 19 ልዩ ስሙ ሃመሬሳ ወይም መድፈኛ ጀርባ በሚባለው አካባቢ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓም በቁፋሮ ላይ የነበረ አንድ የግሪደር ሹፌር የተከማቹ አስከሬኖችን አግኝቷል።

የ2ቱ አስከሬን ምንም አይነት የመበስበስ ምልክት አለማሳየቱን የገለጸው ወኪላችን፣ ግለሰቦቹ በቅርቡ የተገደሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሎአል። አንደኛው ሟች እጆጁን ወደ ሁዋላ ለፊጥኝ ታስሮ የተገኘ ሲሆን ሌላው ደግሞ አይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነዋል።

የአራት አስከሬኖች አጽምም እንዲሁ አብሮ መገኘቱን የገለጸው ወኪላችን ፣ ቀደም ብለው የተገደሉ መሆናቸውን መረዳት እንደሚቻል ገልጿል።

ህዝቡ አስከሬኖቹ እንዳይነሱ እና ምርመራ እንዲካሄድባቸው ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ፖሊስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ አስከሬኖቹን በማንሳት ከዋናው ቦታ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ቦታ ላይ እንዲቀበሩ አድርጓል። በቅርቡ የተገደሉትን የሁለቱን አስከሬኖች ማንነት ለማወቅ አልተቻለም።

የግሪደሩ ሾፌር አስከሬኖቹን እንዳየ ራሱን በመሳቱ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

ኢሳት  በሃረር ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ሁለት ወጣቶች አድራሻቸው መጥፋቱን መዘገቡ ይታወሳል።

ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ደግሞ የአወዳይ ህዝብ ዛሬ  ሰኔ 3 ወደ አካባቢው በመኪና ተጉዞ ከደረሰ በሁዋላ ተቃውሞ አሰምቷል። የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በአስለቃሽ ጭስ እና በተኩስ ተቃውሞውን የተቆጣጠሩት ሲሆን፣ ህዝቡ በወሰደው እርምጃ በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ሳላሃዲን ግራ አይኑ አካባቢ በድንጋይ ተመትቶ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

አካባቢው በክልሉ የኢንዱስትሪ መንደር የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስም ለተደራጁ የባለስልጣናት ዘመዶች መሰጠቱን የዘገበው ወኪላችን፣ ለግንባታ የሚውሉ እቃዎች የተጠራቀሙበት መጋዘን በህዝቡ እንዲቃጠል ተደርጓል።

የህዝቡ ጥያቄ “አስከሬን እንዴት የትም ይጣላል፣ ትክክለኛ ቦታ ተፈልጎ በክብር ሊያርፍ ይገባል” የሚል መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።

የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ወደ አካባቢው ተጉዘው ለማረጋጋት ሙከራ አድርገው ባለመሳካቱ ፖሊሶች ህዝቡን በሃይል ለመበተን መገደዳቸውን ወኪላችን አክሎ ገልጿል።

ሀመሪሳ ከአወዳይ ወደ ሃረር መግቢያ ሲሆን አካባቢው ጫካ እና ሜዳ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።