Archive | June 20, 2014

A typical Ethiopian family dream come true; the sky is the limit.

hagere

(Ashebir) To me, there is so much more to this picture than meets the eye. I see a snapshot of life’s journey and realization of long-held ambition. The parents represent typical Ethiopian parents and stayed true to their everyday self. I particularly love the necklaces, “meqenet”, “niqsat” and the Ethiopian flag-styled head cover, the rose the mum held and her hair cut… The father with bottled up emotions and his face telling volumes about his life. Also the new graduate “standing taller” and inches closer to his aspirations. I see the stories of many fellow Ethiopians in the picture. Man, spread your wings and fly. Congrats to you and your family! –  thanks for sharing.

የሁለት ፈረሶች ጥያቄ – በዳንኤል ክብረት

horses

ሁለት ፈረሶች እንደነበሩ ተነገረ፡፡ አንደኛው እጅግ ለምለም በሆነ ሰፊ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ፣ ሲያሻው ደግሞ በግራ በቀኝ ገብስ ፈስሶለት፣ ሲጠማው የሚጠጣው ውኃ በሜዳው መካከል ኩልል ብሎ እየወረደለት፣ አውሬ እንዳይተናኮለው ዙሪያውን በውሻ እየተጠበቀ ይኖር ነበር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሣር ዘር ለአመል ያህል ብቻ እዚህም እዚያም በበቀለበት፣ ጭው ባለ ደረቅ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ ያገኛትን እየነጨ፣ ከዕለታት በአንድ ቀን ከደጋ የዘነበ ዝናብ በአካባቢው ሲያልፍ የሚያገኘውን ጥፍጣፊ ውኃ እየተጎነጨ፣ ሌትና ቀን ምን ዓይነት አውሬ መጥቶ ይዘነጥለኝ ይሆን? እያለ በሥጋት ይኖር ነበር፡፡

ምንም እንኳን ሁለቱም ፈረሶች በኑሮ በማይቀራረብ ሜዳ ላይ በመከራና በቅንጦት ተለያይተው ቢኖሩም የኑሮ ጥያቄ ግን አገናኝቷቸው ኖሯል፡፡ ያ እንዲያ በለመለመ መስክ ተሠማርቶ እምብርቱ እስኪነፋ ሆዱ እስኪቆዘር እየበላ ሲተኛ ሲነሣ የሚውለው ፈረስ ‹‹ይኼ ሣር ያለቀ ዕለት፣ ይኼም ውኃ የነጠፈ ጊዜ፣ እነዚህም ውሾች እኔን መጠበቅ ትተው የሄዱ ጊዜ፣ ይኼስ ገብስ የጠፋ ቀን ምን ይውጠኝ ይሆን? ያስ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡ ይኼ ጥያቄ ምንጊዜም ይረብሸው ነበር፡፡

 

ያ በደረቅ ሜዳ ላይ እዚህም እዚያም የበቀለች ሣር እየነጨ ከርሱን ሲደልል የሚውለው ፈረስ ደግሞ ‹‹መቼ ይሆን አልፎልኝ ለምለም መስክ ላይ ውዬ፣ ከፈሰሰ ውኃ እንደ ልቤ ተጎንጭቼ፣ ያለ ሥጋት አድሬ የሚነጋልኝ? ያ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡

እዚህ ሀገር ያለን ሰዎች በሁለቱ ፈረሶች ጥያቄ ውስጥ ወድቀናል፡፡ አንደኛው መስኩ ለምልሞለት፣ ውኃው መንጭቶለት፣ ሥጋቱ ጠፍቶለት፣ ሕይወቱ ቀንቶለት የሚኖረው ሰው ጥያቄ ነው፡፡ እንዴት ሜዳው ላይ እንደደረሰ አያውቀውም፤ ብቻ አንድ ቀን ተቀለጣጥፎም፣ ተጣጥፎም፣ ተለጣጥፎም፣ ራሱን ሜዳ ላይ አግኝቶታል፡፡ ለስንትና ስንት ፈረስ የሚበቃውን መስክ ብቻውን ተሠማርቶበታል፡፡ አገር የሚያጠጣውን ወንዝ ብቻውን ይንቦራችበታል፡፡ ጥጋብን ከልኩ በላይ፣ ምቾትንም ከመጠን አልፎ ቀምሶታል፡፡ ድህነትን ረስቶ የት መጣውን ዘንግቶታል፡፡ ግን ሥጋት አልለቀቀውም፡፡

ይኼ መሥመር የተበጠሰ ዕለት፣ ይኼ ሥርዓት ያለፈ ቀን፣ ከእገሌ ጋር የተጣላሁ ጊዜ፣ ቀን የዞረችበኝ ሰዓት፣ የተነቃ ለታ፣ ዕቁቡ የተበላ ጊዜ፣ ካርታው ያለቀ ቀን፣ መንገዱ የታወቀ እንደሆን፣ ሕግ የተቀየረ ቀን፣ ምን ይውጠኝ ይሆን? ያችስ ቀን መቼ ትሆን? እያለ ይጠይቃል፡፡ እየበላ ይሠጋል፣ እየጠጣም ይጨነቃል፤ አይቷል፣ ሰምቷል፡፡ ድንገት ለምለሙ  ሜዳ ላይ ተገኝተው ድንገት ከሜዳው የጠፉ አሉና፡፡

አሁን ሆዱ ተቀይሯል፤ አንገቱ ተቀይሯል፤ እጁ ተቀይሯል፤ መቀመጫው ተቀይሯል፤ ማረፊያና መዋያው ተቀይሯል፡፡ ይህንን ያጣ ዕለት ምን ይውጠዋል?

ያኛውም ፈረስ አለ፡፡ እንደ ዐርባ ቀን ዕድል ሆኖ የደረቀ መስክ ላይ ውሎ እንዲያደር የተፈረደበት፤ ቢሄድ ቢመጣ፣ ቢወርድ ቢወጣ ከዚያ መስክ መላቀቅ ያቃተው፡፡ መቼ ይሆን የእኔስ ሜዳ በሣር ተሞልቶ እንደነዚያ ሣር የምጠግበው እያለ ምኞት የገደለው፡፡ የእኔስ ወንዝ መቼ ይሆን ውኃ ሞልቶት ሳልጨነቅ የምጠጣው? እያለ ሃሳብ ያናወዘው፡፡ የእርሱ ቤት እየፈረሰች ከጎረቤቱ ዘጠኝ ፎቅ ሲበቅል አይቷል፡፡ ስትተከል፣ ውኃ ስትጠጣ፣ አላያትም፡፡ እንዲሁ ብቻ ፎቋ በቀለች፡፡ ስትገዛ ያላያት፣ ፍንጥር ያልጠጣባት መኪና እንዲሁ ሽው እልም ስትል አያት፤ እናም ምን ዓይነት ፈረሶች ይሆኑ ለዚህ የሚበቁት እያለ ይጠይቃል፡፡ ዝርያቸው ምን ቢሆን ነው? መልካቸውስ ምን ቢሆን ነው? የፈረስ ጉልበታቸውስ ምን ያህል ቢሆነ ነው? ፍጥነታቸውና ቅልጥፍናቸውስ እንዴት ያለ ቢሆን ነው?ጌቶቻቸውንስ እንዴት አድርገው ቢያገለግሏቸው ነው? እንዲህ ለምለም መስክ ላይ የለቀቋቸው?እኛም ስናገለግል ኖረናል፤ ጋሪ ስንጎትት፣ እህል ስንሸከም፣ ዕቃ ስናጓጉዝ ኖረናል፤ ጌቶቻችን ሲጋልቡን ኖረናል፤ ግን እነርሱ ምን ያህል ቢያስደስቷቸው ነው ይህንን ዕድል የሰጧቸው? እያለ ይጠይቃል፡፡

ለመሆኑ እነርሱ ናቸው ወደ እኛ የሚመጡት ወይስ እኛ ነን ወደ እነርሱ የምንሄደው? ለመሆኑ የኛን ድህነት ነው ወይስ የእነርሱን ሀብት ነው የምንካፈለው? በርግጥ ከኛም የሄዱ አሉ፤ ከእነርሱም የሚመጡ አሉ? ይላል፡፡ አንዱ ሜዳ ላይ ተሠማርተን እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን መጋጥ ሲገባን ለምን ሁለት ዓይነት ሜዳ ሆነ፡፡ አሁን እኛና እነርሱ እኩል ‹‹ፈረስ›› ተብለን እንጠራለን? እኛ ‹‹ሌጣ ፈረስ›› ነን፣ እነርሱ ደግሞ ‹‹ባለ ወግ ፈረስ›› ናቸው፡፡

ግን ይሁን፤ እሺ መቼ ይሆን እኛስ እንደነርሱ የምንሆነው? መቼ ይሆን ያለ ሥጋት ውለን የምናድረው?ለምለሙን መስክ ማን ይነካዋል፤ ላለው ነው ድሮም የሚጨመርለት፤ የኛ የድኾቹን መስክ ነው ለሀብታሞቹ የሚሰጡት፤ የድኾቹን ደረቅ መስክ ሀብታሞቹ የሚቀኑበትን ያህል እኛ በእነርሱ ለምለም መስክ አንቀናም፡፡ ደግሞ አንድ ቀን ይመጣሉ፡፡ ‹‹ይህንን መስክ ለምለም ማድረግ እንፈልጋለን›› ይላሉ፡፡ እኛም ደስ ይለናል፡፡ የዘመናት ምኞታችን አይደል? መንገዱ ጠፍቶን እንጂ እኛም ለምለም ማድረግ እንፈልግ ነበርኮ? መንገዱን ያወቀው ሰው ሲመጣ ለምን እንቃወመዋለን፡፡

ግን ይቀጥሉና ሌላ ነገር ይሉናል፡፡ ‹‹መስኩን ግን ለምለም የምናደርገው ለእኛ እንጂ ለእናንተ አይደለም›› ይሉናል፡፡ ለምን? ለምን? እኛ ለምለም ሣር አይወድልንም? እኛ ለምለም የምናደርግበትን መንገድ ለምን አያሳዩንም? ባያሳዩንስ ለምን አይፈቅዱልንም? ባይፈቅዱልንስ ለምን አይተውንም?እንላለን፡፡ ይህ ግን ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የለውም፡፡ እኛም ጥያቄውን የምናውቀውን ያህል መልሱን አናውቀውም፡፡ ስንጠይቅም ‹‹ምላሽ›› እንጂ ‹‹መልስ›› የሚሰጥ አናገኝም፡፡

እኛም ከዚያ መስክ እንወጣለን፣ ወደሌላ መስክም እንዛወራለን፤ አሁንም ቅንጥብጣቢ ሣር እንፈልጋለን፤ ጥፍጣፊ ውኃ እናስሳለን፡፡ ያ እኛ የነበርንበት መስክ ግን በአንድ ጊዜ ይለመልማል፡፡ ውኅው ጅረት ሆኖ ይፈስበታል፡፡ ይገርመናል፡፡ እኛ እዚያ ሳለን፡፡ ውኃ አልነበረም፡፡ እንደ ወር በዓል ቀን ቆጥረን ነበር የምናገኘው፡፡ አሁን ግን ይንፎለፎላል? ለመሆኑ እኛ ምን ብለን መጠየቅ ነበረብን?ይኼ ራሱ ሌላ ጥያቄ ይሆንብናል፡፡ መቼ ይሆን እኛስ እንዲህ ባለው መስክ ላይ የምንሠማረው?እንላለን፡፡ የማይሳካ ምኞት እንመኛለን፤ የማይመለስ ጥያቄ እንጠይቃለን፡፡

እዚያም ቤት ሌላ ጥያቄ አለ፡፡ ፀሐይዋ እንደወጣች ትቀጥል ይሆን? ወንዙ እንደፈሰሰ ይቀጥል ይሆን?ነፋሱ እንደነፈሰ ይቀጥል ይሆን? ሣሩ እንደለመለመ ይዘልቅ ይሆን? እኔስ እንደተወደድኩና ሞገስ እንዳገኘሁ እኖር ይሆን?

ሰውየው ስለ አውሮፕላን አነዳድ የሚገልጥ ማኑዋል አገኘና አውሮፕላኑን አስነሥቶ አበረረ፡፡ ገጹን ይገልጣል፤ የተጻፈውን ይፈጽማል፤ አውሮፕላኑም ይበራል፡፡ በቀጣዩ ገጽ ላይ ምን እንዳለ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ገጹ ተገንጥሎ ቢገኝ ምን ማድረግ እንዳለበትም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ብቻ ይገልጣል፣ ያነባል፣ ይነካካል፣ ይበራል፡፡ አውሮፕላኑ ተነሥቶ በሃያ አምስት ሺ ጫማ ከፍታ ላይ ሲደርስ የመጨረሻው ገጽ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹ክፍል ሁለትን በክፍል ሁለት መጽሐፍ ይመልከቱ›› ይላል፡፡ ክፍል ሁለት መጽሐፍ ግን የለውም፤ የት እንዳለም አያውቅም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበትም አልተዘጋጀም፡፡ ስለዚህም እንደወጣ መውረድ ጀመረ፡፡ ያውም በዝግታ ሳይሆን እየተምዘገዘገ፡፡

እናም እኛ በለምለም መስክ ላይ ያለን ፈረሶች፣ አንድ ክፉ ቀን መጥቶ ‹‹ክፍል ሁለትን በሌላ መጽሐፍ›› ቢለንስ? ምን ይውጠናል? ለመሆኑ ክፍል ሁለት የት ነው ያለው? እስካሁን ያሳየን የለም፡፡ እኛ የምናውቀው የየዕለቱን ምዕራፍ ብቻ ነው፡፡ ያንን እናነባለን፣ በእርሱ እንኖራለን፣ ቀጣዩን ምዕራፍ አናውቀውም? ስለዚህም እኛም እንጠይቃለን? እንዲሁ እንዘልቅ ይሆን? ብለን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

ዳንኤል ክብረት

Äthiopien : ein Journalist im Gefängnis

  Pays : Äthiopien

Tags : JournalistPressefreiheit

 

(arte.tv) Ende April wurde der Journalist Tesfalem Waldyes in der äthiopischen Hauptstadt Addis Abeba verhaftet. Ihm wird, zusammen mit zwei anderen Journalisten und sechs Internet-Bloggern, wegen regierungskritischer Äusserungen der Prozess gemacht. Tesfalem Waldyes hatte erst vergangenen November als Producer für die ARTE Serie “Afrikas Löwen” gearbeitet.

Was hätten wir nur ohne Tesfalem gemacht? Drehs vorbereiten, offizielle Genehmigungen besorgen, Interviews übersetzen und uns dann auch noch Äthiopiens Geschichte, Politik und Gesellschaft näher bringen. Es sind Menschen wie Tesfalem, die uns und den Zuschauern helfen neue Horizonte zu entdecken.

 

Verhaftung und Gefängnis

 

Die äthiopische Regierung scheint sich allerdings vor neuen Horizonten zu fürchten. Laut Augenzeugen wurde Tesfalem Ende April vor seiner Wohnung in Addis Abeba von sieben Polizisten in Zivil und zwei Uniformierten in ein Auto gezerrt. Danach wurde der Journalist ins Maekelawi-Gefängnis gebracht. Bisher wurde unserem Kollegen jeder Kontakt zu seinen Angehörigen oder seinem Anwalt verweigert. Tesfalems Twitter Account und seine Facebookseite sind gesperrt. Es sieht nach einer konzertierten Aktion aus.  Neben Tesfalem wurden zwei weitere Journalisten und sechs Internet-Blogger festgenommen.

 

Tesfalem Waldyes (2.v.r.) wird in Handschellen zur Gerichtsverhandlung geführt.

 

Bei einer ersten richterlichen Anhörung wurde ihnen vorgeworfen, mit ausländischen Organisationen zusammengearbeitet zu haben, die in terroristische Aktivitäten verwickelt seien. Ausserdem sollen sie soziale Netzwerke im Internet genutzt haben, um in Äthiopien Instabilität zu erzeugen.

 

Autoritäres Regime

 

Seit dem Ende des Bürgerkriegs 1991 ist die Parteienkoalition “Revolutionäre Demokratische Front der Äthiopischen Völker » an der Macht. Nach dem plötzlichen Tod von Premierminster Meles Zenawi im Jahr 2012, übernahm Hailemariam Desalegn die Nachfolge. Im kommenden Jahr wird in Äthiopien gewählt. Bis dahin will das autoritäre Regime offensichtlich regierungskritische Stimmen und die Opposition mundtot machen.

 

Die äthiopische Regierung hat in den letzten Jahren enorme Summen in Bildung, Gesundheit und die Sicherung der Nahrungsmittelversorgung investiert. Doch von Pressefreiheit will sie nichts wissen.  “Reporter ohne Grenzen” führt Äthiopien in seinem “Press Freedom Index” auf Platz 143 von 180 Ländern. “Journalisten sind Terroristen” Vor wenigen Tagen brachte US-Aussenminister John Kerry bei einem Besuch in Addis Abeba die jüngsten Verhaftungen zur Sprache. Ministerpräsident Hailemariam Desalegn reagierte pikiert. Es handele sich nicht um Journalisten, sondern um Terroristen. Ein Freifahrtschein für die Staatsanwaltschaft, um die Anklage auf die Anti-Terrorismus-Gesetze von 2009 stellen zu können. Tesfalem und den anderen Journalisten würden dann jahrelange Haftstrafen drohen.

 

Freiheit für Tesfalem und seine Kollegen

 

Wir haben Tesfalem Waldyes als einen absolut professionellen Journalisten und liebenswürdigen Vertreter eines phantastischen Landes kennengelernt. Auch das ZDF und die BBC haben in der Vergangenheit mehrfach mit ihm zusammen gearbeitet. Tesfalem Waldyes ist einer dieser mutigen Löwen, die wir in unserer Serie über Afrika  getroffen haben. Wir hoffen, dass er und seine Kollegen so schnell wie möglich wieder in Freiheit kommen .

http://info.arte.tv/de/athiopien-ein-journalist-im-gefangnis

– See more at: http://info.arte.tv/de/athiopien-ein-journalist-im-gefangnis#sthash.omgO7LEy.dpuf