Archive | July 14, 2014

ሰበር ዜና – የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዜና  የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ  ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ  መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ ያሳለፈውን ውሳኔ  ”ጠቃሚ እርምጃ” በማለት አሞካሽቶታል።
ውሳኔው በተለይ በቅርቡ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገት በኃላ የእንግሊዝ መንግስት  ”የባህር ማዶ የልማት ትብብር ድርጅት” (UK Department for International Development (DFID) ) ለኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግ የነበረ ከመሆኑ አንፃር የዛሬው ውሳኔ ከፍተኛ መልዕክት ማስተላለፉ አይቀርም።በሌላ በኩል የዛሬው የፍርድቤቱ ውሳኔ ይሄው የልማት ድርጅት (DFID) በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ ይዞታ ጉዳይ አለመመርመሩን ጠቁሞ በእዚሁ አዲሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግበት ማዘዙን ያብራራል።
የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእርምጃውን ፋይዳ ሲያስረዳ  የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ የተናገሩትን በመጥቀስ ነው።እንዲህ ይነበባል –

የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድቤት ውሳኔ ለሌሎች መንግሥታት እና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የማንቅያ ጥሪ ነው።ምክንያቱም ሀገራትም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡትን የልማት ፕሮግራም ሁሉ ቅድምያ ከሰብዓዊ ይዞታ አንፃር እንዲመለከቱ ያደርጋል”ይላል።

የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ስለ እንግሊዙ ከፍተኛ ፍርድቤት የዛሬ ውሳኔ አስመልክቶ ያወጣውን ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

Ethiopia: UK Aid Should Respect Rights
Ruling Permits Review of Development Agency’s Compliance
JULY 14, 2014

(London) – A UK High Court ruling allowing judicial review of the UK aid agency’s compliance with its own human rights policies in Ethiopia is an important step toward greater accountability in development assistance.

In its decision of July 14, 2014, the High Court ruled that allegations that the UK Department for International Development (DFID) did not adequately assess evidence of human rights violations in Ethiopia deserve a full judicial review.

“The UK high court ruling is just a first step, but it should be a wake-up call for the government and other donors that they need rigorous monitoring to make sure their development programs are upholding their commitments to human rights,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “UK development aid to Ethiopia can help reduce poverty, but serious rights abuses should never be ignored.”

The case involves Mr. O (not his real name), a farmer from Gambella in western Ethiopia, who alleges that DFID violated its own human rights policy by failing to properly investigate and respond to human rights violations linked to an Ethiopian government resettlement program known as “villagization.” Mr. O is now a refugee in a neighboring country.

Human Rights Watch has documented serious human rights violations in connection with the first year of the villagization program in Gambella in 2011 and in other regions of Ethiopia in recent years.

A January 2012 Human Rights Watch report based on more than 100 interviews with Gambella residents, including site visits to 16 villages, concluded that villagization had been marked by forced displacement, arbitrary detentions, mistreatment, and inadequate consultation, and that villagers had not been compensated for their losses in the relocation process.

People resettled in new villages often found the land infertile and frequently had to clear the land and build their own huts under military supervision. Services they had been promised, such as schools, clinics, and water pumps, were not in place when they arrived. In many cases villagers had to abandon their crops, and pledges of food aid in the new villages never materialized.

The UK, along with the World Bank and other donors, fund a nationwide development program in Ethiopia called the Promotion of Basic Services program (PBS). The program started after the UK and other donors cut direct budget support to Ethiopia after the country’s controversial 2005 elections.

The PBS program is intended to improve access to education, health care, and other services by providing block grants to regional governments. Donors do not directly fund the villagization program, but through PBS, donors pay a portion of the salaries of government officials who are carrying out the villagization policy.

The UK development agency’s monitoring systems and its response to these serious allegations of abuse have been inadequate and complacent, Human Rights Watch said. While the agency and other donors to the Promotion of Basic Services program have visited Gambella and conducted assessments, villagers told Human Rights Watch that government officials sometimes visited communities in Gambella in advance of donor visits to warn them not to voice complaints over villagization, or threatened them after the visits. The result has been that local people were reluctant to speak out for fear of reprisals.

The UK development agency has apparently made little or no effort to interview villagers from Gambella who have fled the abuses and are now refugees in neighboring countries, where they can speak about their experiences in a more secure environment. The Ethiopian government’s increasing repression of independent media and human rights reporting, and denials of any serious human rights violations, have had a profoundly chilling effect on freedom of speech among rural villagers.

“The UK is providing more than £300 million a year in aid to Ethiopia while the country’s human rights record is steadily deteriorating,” Lefkow said. “If DFID is serious about supporting rights-respecting development, it needs to overhaul its monitoring processes and use its influence and the UK’s to press for an end to serious rights abuses in the villagization program – and elsewhere.”

ምንጭ – http://www.hrw.org/news/2014/07/14/ethiopia-uk-aid-should-respect-rights

እየነጋ ነው! (እስከመቼ)

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew

አሁን ደግሞ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንዔል ሺበሽ፣ አብረሃ ደስታን አሰሩ። አንዳርጋቸው ፅጌን የማሠራቸው ዜና ገና አቦሉ ሳይጠጣ እኒህን ደገሙ። ለምን? አጭሩ መልስ እየነጋ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ የእኒህን ታጋዮች ማንነትና ተግባር የማያውቅ የለም፤ ቢያንስ በትግሉ ዙሪያ ያለነው ኢትዮጵያዊያን። ታዲያ መንጋቱ እኮ፤ የአውራ ደሮውን ጩኸት፣ የጎኅን መፈንጠቅ፣ የጨለማውን መገፈፍ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ በገዛ ፈቃዱና ቁጭ ብለው ስለጠበቁት የሚሆን አይደለም። የመሬትን በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከር ተፈጥሯዊ ግዴታ ተከታይ ነው። በጭቆና የሚማቅቅ ሕዝብ፤ ለነፃነቱ መነሳቱና ከመካከሉ ቆራጦቹ ጧፍ ሆነው ከፊት መቅለጣቸው ግዴታ ነው። ይህ ነው የኒህ ቆራጥ ታጋዮች ሕይወት ትርጉሙ። እንደኛው ቤተሰብ፣ ንብረትና ምቾት አልጠሉም። ለወገንና ለሀገር ሠጡት። የሕይወታቸውን ትርጉም፤ በጣሊያን ጊዜ ከፋሽስቶች ለመጋፈጥ ከየመንደሩ በባዶ እግራቸው፤ ከመላ ኢትዮጵያ ጫፍ እስከጫፍ ወጥተው እንደቀሩት አርበኞቻችን፤ የኔ ሕይወት ለነገዋ ኢትዮጵያ ሕልውና ይሁን ብለው ያለማመንታት፤ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነውን ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራውን መንግሥት በመቃወማቸው እስር ቤት ገቡ። ከኛ የተለዩ ልዩ ፍጡር ሆነው አይደለም። እንደኛ አባትና እናት፣ እህትና ወንድም፣ አክስትና አጎት፣ ባለቤትና ልጆች ያሏቸው ናቸው። ሰው ናቸው። አርበኛ ያደረጋቸው ተፈጥሯዊ ልዩነታቸው ሳይሆን፤ ለሕይወታቸው የሠጡት ትርጉም ነው። የብዙኀኑን የኢትዮጵያዊያን ሕይወት የኔ ብለው፣ ስቃያቸውን እነሱ ተሸክመው፣ ለሕዝቡ ጭዳ ሆነው ተሰለፉ። እንደነ አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንደር ነጋ፣ ርዕዩት ዓለሙ፤ ሰግዶ ማደርን አልፈልግም ብለው፤ አረዓያችን ሆኑ። እንዲነጋ ምን ማድረግ አለብን።

አይቀሬው ንጋት እየመጣ ነው። የኛ ኃላፊነት ብዙና የተቆላለፈ አይደለም። እኒህ ቆራጦች የነገሩን ምንድን ነው? ፍርሃትን፤ ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ቀምቶናል። ከኛ በኩል ፍርሃት ቦታ የለውም። የኢትዮጵያዊያን ጠላት የሆነው ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት በፍርሃት ተውጧል። ምስክርነቱ፤ ማንንም የሚፈራውንና በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አለው የሚለውን ግለሰብ ሁሉ እያሠረ ነው። እኒህ ጀግኖች የታሠሩት የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባል ስለሆኑ አይደለም። ከሕዝቡ ጋር ስለወገኑ ብቻ ነው። ለዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት፤ ማንኛውም ከሱ ቁጥጥር ውጪ የተደራጀ ክፍል ጠላቱ ነው። እናም የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባል መሆን አይደለም የመታሰሪያ ወንጀሉ፤ ከሕዝቡ ጋር የቆመ መሆኑ ብቻ ነው። የሚያስበረግገውና የሚያንቀጠቅጠው የሕዝብ ወገን የሆነ ማንኛውም ድርጅት ነው። ታዲያ ድርጅቶች በሙሉ አንድ ዓላማ እስከያዙ ድረስ፤ ሕዝቡ አሁን ነው ትግሉ ወደፊት መሄድ ያለበት እስካለ ድረስ፣ ንጋቱ በር አያንኳኳ እስከሆነ ድረስ፤ ተልዕኳችንን አንድ አድርገን ሌቱን እናንጋው።

ምንድን ነው የአሁን ጥያቄ? ይፈቱልን ብሎ ልመና አይደለም። ይህ በታሠሩት ቆራጦች ዓይን ጥቃት ነው። ይህን ብናደርግ ለገዥው ቡድን ኩራት ነው። እንኳን ያሠራቸውን ሊፈታ፤ የሚቀጥሉትን ታሳሪዎች እያዘጋጀ ነው። እነሱም ሆኑ መታሠራቸው፤ ጧፍ ሆኖ መንገዱን መሪያችን እንጂ፤ የመንገዱ ማብቂያ አይደለም። ገና የራሱን ጥላ ለማሠር የሚሯሯጥ ጠላት ነው ያለን። አጥንት ቆጠራውን ለገዥው ክፍል እንተውለት። እሱም እንኳ ለአጥንት ቆጠራው ቦታ እንደማይሠጠው አብርሃ ደስታን በማሠር አሳይቶናል። አብርሃ ደስታ በትግራይነቱ፣ ትግሬዎች እየተጠቁ ነው ብሎ የተደራጀ ነበር። አልሆነም። ኢትዮጵያዊነታችንን እንጎናጸፈው። በኢትዮጵያዊነታችን ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት እንታገለው። ሁላችንን ሊያስተባብሩን የሚችሉ አራት የትግል ዕሴቶች አሉን።

፩ኛ፤     የኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት                                    ፪ኛ፤     የኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት
፫ኛ፤     የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች        ፬ኛ፤     በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት

እኒህ ናቸው የታጋዮችን አንድነት የሚጠይቁ የትግል ዕሴቶቻችን። በነዚህ ዙሪያ ሁላችን መጠማጠም አለብን። የየድርጅቶች ታሣሪዎች መሆናችንን ለነፃነቱ ጊዜ እንተወውና፤ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ፣ ለሀገራችን አንድነት፣ በየእስር ቤቱ ለሚማቅቁ ጀግኖቻችንና አሁን በየዕለቱ ለሚታገቱት ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን አርበኞቻችን አንድነታችንን እናጠንክር። ይህ ወደ ድል ይወስደናል። እነዚህን ሁሉን አቀፍ የሆኑ አራት ነጥቦች በሚያኩ ዙሪያ ሀገራዊ አጣዳፊ ጥሪዎች ሰሞኑን ድረገፆቻችንን አሙቀውታል። ጥሪዎቻችሁ ወደ መሰባሰቡ እንዲያመራ ፈልጋችኋል በማለት፤ ጥሪዎችን በተደጋጋሚ ያደረጋችሁ ግለሰቦች፤ እኛው ጀማሪዎች እንሁን የሚል ጥሪ በማስቀደም እንድንገናኝ ይኼው በ ( eske.meche@yahoo.com ) እገኛለሁ።