Archive | August 2014

እውን የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ይሄ ነው?

3

ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ የመጣው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ሃገሪትዋን  መውጣት ወደ አልቻለችበት ድህነት እና ሰቆቃ ከቶዋት ህዝቡ ከዘመናት ዘመናት በረሃብ ፣ በድህነት ፣ በጦርነት እና በዘር በጎሳ በመከፋፈል ያለ ማቁዋረጥ እየማቀቀ ይገኛል::

ይህንንም ተረድተው ደሞ ሃገሪትዋን ካለችበት ችግር ለማላቀቅ የሚጥሩትንም ሰዎች የማይሆን ስም በመስጠት ከህዝብ ጋር እንዲቃቃሩና ትግላቸው ከግብ ሳይደርስ መና እንዲቀሩ የተደረጉ ሰዎች ብዙ አሉ::

ህዝባችንን አንድነትን ፈጥሮ በጋራ ከማቆም ይልቅ ጥቃቅን ስብእናን የሚያጎድፉ ነጠላ ሃሳቦችን ይዞ እርስ በእርስ ከማጠላለፍ ይልቅ ለህዝብ የሚጠቅመውን ከምንም በላይ በዚህ ሰአትና ወቅት ብዙ የሚያስጨንቀንና እንቅልፍ የሚነሳን ከአንድነት ይልቅ መከፋፈልን ፣ ከመተባበር ይልቅ መጠላለፍን በማናፈስ ለወያኔ የፖለቲካና ስልጣን ማራዘሚያ የሚውል ፕሮፖጋንዳ እራሳችን እየፈጠርን የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር ለማባባስ በወቅቱ ጥቂት ግለሰቦች የፈጠሩት ውዥምብር አንዱ ማሳያ ነው::

እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ማሰብና ማተኮር ያልቻለው ትልቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆነውን የወያኔን መንግስት ከስር መሰረቱ ከመንቀል ይልቅ እርስ በእርስ በመከፋፈል እና በመካሰስ አባላትንና ደጋፊዎቻቸውን አላስፈላጊ እና ወቅታዊ ባልሆነ ውዥምብር  ውስጥ መክተት እንደስራ በያዙ ግለሰቦች እንዲሁም የማተራመስ ተልኮዎቻቸውን በወያኔ ቀቢጸ ተስፋ በመመራት ወይም ሃገር ቤት በመመላለስ የሚያገኙትን ጥቂት ፍርፋሪ ላለማጣት ህሊናቸውን ሸጠው የወገኖቻቸውን ቸግር በጊዜያዊ ጥቅም ለመቀየር እየተንቀሳቀሱ ያሉትን አሉባልተኞች ለዚህ አፍራሽ ተልኮዋቸው ተገቢውን ቅጣት ማግኘት እንዳለባቸው ሊገነዘቡት ይገባል::

ከውዥምብሮቹም አንዱ በቅርቡ በአውሮፓ የሚገኙ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ላይ እየተዛመተ ያለው አሉባልታና ስም ማጥፋት አንዱና ዋነኛው የውዥምብሩ ገጽታ ነው::

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ አመራር እና አባላቶቹ ጋር አንድ ላይ በመሆን ቀን ከለሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅረፍ በመንቀሳቀስላይና በሃገሪትዋ ላይ የሚደረጉትን ግፍ እና በደሎች ለአለም በማሳወቅ የበኩሉን አስተዋጽዎ በማድረግ ላይ እያለ ይህንን የመሰለ አሳዛኝ የመከፋፈል እና ለማፍረስ መሩዋሩዋጡ የሚያስተዛዝብ ሆኖ  አግኝተነዋል::

የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር የዲሞክራሲ እጦት እና የፍትህ ጥማት ሆኖ እያለ በቀላሉ የሚገኙ እና በሚፈበረኩ ሶሻል ሚድያዎች እንደ ፌስ ቡክ ባሉ ገጾች የሚያወጡትን የስም ማጥፋት ህግ በሚከበርበት ሃገር ላይ ተቀምጠን በዝምታ የምናልፈው ነገር እንደማይሆን ሊያውቁት ይገባል!!

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አመራር እና አባላቶቹ ድርጅቱን አሁን ላለበት ደረጃ ለማድረስ በፊት ያለፉበት ከባባድ ፈተናና ችግሮች አሁን የተነሳንባቸውን ከእውነት የራቀ ውንጀላና አሉባልታ እንዲያውም ወደፊት የበለጠ ሊያጠናክራቸውና የበለጠ ትግላቸውን ከግብ የሚያደርስ ጥንካሬያዊ መልእክት እንደሆነ የነዚህ ለሆዳቸው ያደሩ ህሊናቢሶች ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት ይገባል በሚል የግል አስተያየቴን እቌጫለሁ::

ከአውግቸው ከበደ

ነሃሴ 24/12/2006 አውስትራልያ

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

 

 

 

Ethiopia: Where is the ‘double-digit growth’ and rapid development?

 

Where is the ‘double-digit growth and rapid development the ethnic apartheid regime of the TPLF/EPRDF vouching about? Addis Ababa has more than 3 million people, but there are just 63 public toilets. The truth must be admitted and openly discussed, for tensions related to it have become a source of potential backlash that could evolve into violence and instability.

Community toilets in Addis Ababa typically consist of a hole in the floor.

Ethiopians’ plight: ‘The toilets are unhealthy, but we don’t have a choice’

The Guardian

Officials plan to build extra public conveniences in Addis Ababa, which has just 63 loos for its 3 million inhabitants

Addis Ababa has more than 3 million people, but there are just 63 public toilets. At one, in the oldest part of the city, there is constant activity and bustle as people queue to pay varying prices for a urinal, full cubicle or shower in the white-tiled facility inside a circular yellow building. For many, this is the only option because of the lack of provision in their own homes.

Nine in 10 households use “non-improved” toilet facilities, according to the Wash Ethiopia Movement. The most common type of non-improved toilet is an open pit latrine or pit latrine without slabs, used by 57% of households in rural areas and 43% in urban. Only one in 25 households has access to improved toilet facilities which are not shared with other households.

Mesay Berhanu, a spokesman for the movement, said: “Many people have shared toilet facilities which they would not find very comfortable. They might have to line up for some time to make use of the facilities. As a result, you may find people doing it here or there along the street.”

Government figures show that diarrhoeal diseases are among the 10 most prolific in the country. “These are one way or another linked to an unhygienic environment,” Berhanu added.

Waste can accumulate because service providers are stretched. “There is a huge problem in liquid waste management. The number of vehicles they have to collect it is limited. People might have to wait two or three months. We have a very small number of private operators in liquid waste collection.” Progress has stalled, Berhanu said, because of bureaucracy. “A year ago there was a plan to create more than 1,000 public toilets, but there is a lack of co-ordination between different departments of government.One of the main challenges is the coordination of the various actors.”

But officials in this fast-developing city say they have a 100m birr (£3m) plan to build an extra 25 public toilets within the next year along with 103 community and 289 mobile toilets, the latter equipped for pregnant women and people with disabilities. About 150 areas have been identified, including markets and bus and train stations.

Mulugeta Kemise, of the Addis Ababa Water and Sewerage Authority, said: “We are trying to improve the lot of the downtrodden masses. After five, six or seven years you’ll see the difference. We are doing our best to transform the lives of our people.”

At a community toilet shared by 35 households in an impoverished neighbourhood of Addis Ababa the scene is typical: behind a corrugated iron door, beside dirty scraps of paper and tissue, is a small, dark hole in the floor. Above, a cable runs to a naked lightbulb. The stench is rank. These four toilets are used by more than 200 people a day. Those who live here describe them as undignified, unhygienic and inhuman.

“They’re dirty and it’s not good for our health,” said Berhane Keraga, 45, a housewife who gave birth eight times here. “They make a lot of men, women and children ill with typhoid and diarrhoea. A couple of months ago I got sick and had to go to hospital because of these toilets. I felt cold and shivering and had a headache and stomach ache.”

The lavatories, housed in concrete blocks under a corrugated roof, encourage flies and rodents. “There are really black scary rats that come and run on our feet. It’s disgusting, and when my children use these toilets I feel really bad.” Nor is there separation between men and women, Keraga added: “It’s undignified for women. It’s difficult for me to use sanitary products. Some women urinate in bowls at home then dispose of them.”

Since the toilets were built by a non-government organisation more than a decade ago they have been neglected, despite appeals to the government. The community pays 1,200 birr for waste removal once or twice a month and has recently started charging outsiders 1 birr to use them. Girma Taddese, a furniture maker, said: “These toilets are not safe, healthy or hygienic for children. A lot of people fall sick because the toilets get filled quickly. The smell is very disgusting. It fills the air and our kids play on the ground. We can’t take it.” Holding his two-year-old daughter, Blen Girma, he adds: “I don’t like her using these toilets. I feel so sad about our lives, but we don’t have a choice.”

የአንዲት እናት ደብዳቤ፤ (በአቤ ቶኪቻው)

ይድረስ በውጪ ሃገር ለምትኖሪው ውድ ልጄ፤ ባለፈው ሰሞንልሽ… ያቺ ከበታቻችን ያለችው ቀጭኗ ሴትዮ… ምነው እንኳ ቀበሌ ገባ ወጣ የምትለው… እ… እርሷ ወደቤታችን ብቅ ብላ ነበር። እና ታድያ፤ ዲያስፖራዋ ልጅዎ እንዴት ነች… ብላ ብትጠይቀኝ ጊዜ ኧረ እኔ እንዲህ የምትባል ልጅ የለችኝም ፍቅርዬ አበራ… ማለትሽ ነው… ብዬ ጠይኳት፤ እርሷቴ ”በውጪ ሀገር የሚገኝ ማንኛውም ሰው ዲያስፖራ ነው የሚባለው” ብላ ነገረችኝ። አከል አድርጋም፤ ”በልማቱ ተሳታፊ ከሆነች ልማታዊ ዲያስፖራ ልማቱን አደናቃፊ ከሆነች ደግሞ የቀድሞ ስር አት ናፋቂ ነው የምትባለው!” ስትል ጨመረችልኝ፤ እኔም እንዳላወቀ እንዳልገባው ሆኜ፤ የወደፊቱ ስርዓት ናፋቂዎች የሚባሉስ የሉም…. ብዬ ብላት፤ ”ምን አሉኝ….” ብላ ስተደናበር፤ የለ…. እንደው ለቤተሰብ ሳታሳውቁ ስም መለዋወጥ ምን ይሉት ፈሊጥ ነው… ብዬ ገርሞኝ ነው…. እያልኩ፤ ሳዳርቃት ዋልኩልሽ… እንዲህ በሆነ ባለሆነ ያዝ ካላደረግናቸው የነርሱ ፓለቲካ ማለቂያም የለው ልጄ….
የሆነው ሁኖ… አንቺ እንዴት አለሽልኝ፤ እኔ እናትሽ ካንቺ ሃስብ እና ናፍቆት በቀረ እጅጉን ደህና ነኝ።Enat
እንዳልኩሽ፤ ሰሞኑን የቀበሌ ሰዎች ወደቤት መጣ መጣ ማለት አብዝተውብናል… ምክኝያቱ ምን እንደሁ እስቲ ከእኛ እናንተ ታውቁታላችሁና ምን ፈልገው እንደሆነ አጣርተሽ ነግሪኝ፤ እውነቴን ነው ልጄ እንደውም አሁን ይቺን ኢሳቴን ከተከልኩ ኋላ ትንሽ ሻል አለኝ እንጂ ድሮማ ኢቶጵያ ቴሌቪዥን የሚለንን ብቻ እየሰማን የመረጃ ድርቅ ገብቶን ነበር። እርግጥ አንዳንድ ወቅት ዜናውን ገልብጦ በመስማት እውነቱን እንረዳዋለን ለምሳሌ፤ ”አንዳንድ አሸባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ” የሚል ዜና የተነገረ እንደሆነ አንድንድ ጀግኖች እና ለሀገር ያገባኛል የሚሉ ወገኖች፤ ታግተዋል ማለት ነው… ብለን እየተረጎምን ሃቋን እናገኛታለነ!
በነገሬ ላይ ልጄ፤ እንዴት ነው አንቺ እስካሁን ድረስ አሸባሪ ያልተባልሽው… ስንት ጊዜሽ ሀገር ሀገር እያልሽ ስትለፊ እና ስትለፈለፊ አይደል እንዴ የምተውይው… እና ታድያ መንግስት እንዴት ነው እስከዛሬ አሸባሪ ያላለሽ… ልጄ… የጎረቤት ልጆች ሁሉ አሸባሪ ተብለው አንቺ ብቻ ይህንን ማዕረግ ሳታገኚ ቀርተሽ፤ ከሰው በታች አደረግሽኝ እኮ ልጄ… በይ ጠንከር በይ እና ስለ ሀገርሽ ስሪ… እና አሸባሪ ተብለሽ ከሰው እኩል አድርጊን እንጂ ልጄ….
እናልሽ ቀበሌዎቻችን ሰሞኑን ምን እንደሰሙ እንጃ ቤታችን እግር አብዝተዋል። ምርጫ እየደረሰ ስለሆነ እንድንመርጣቸው ሊሰብኩን ይሆን … ብቻ፤ ሰላምታቸው ፈገግታቸው ሁሉ ሌላ ሆኖልሻል። እንግዲህ እስከ ምርጫው ድረስ ኮብልስቶኑ እንዳያደናቅፋችሁ እንነጠፍላችሁ ማለት ነው የሚቀራቸው። ምርጫዋ ካለፈች በኋላ ለቀጣዩ አምስት አመት ሊያነጥፉን እኮ ነው…! ዘንድሮስ ልጄ እንጃ ሰይጣንም እንኳ ቢወዳደር ያሸንፋቸዋል…
ውይ ጋሽ ወንድሙ የነገረኝን ቀልድ ሳልነግርሽ፤ ሰይጣን እና አንድ የኢህ አዴግ ካድሬ መንገድ ሲሄዱ ይመሽባቸውና ማድሪያ ይቸገራሉ… ታድያልሽ፤ ከአቅራቢያቸው ካለ መንደር ለማድር ያስቡ እና ሰይጣን ሆዬ ኢህአዴግን ምን አለው መሰለሽ፤ ከእኔጋ ከሄድክ እኔን ሰዎች ስለምፈሩኝ እሺ ብለው አያሳድሩንም ስለዚህ በኔ የተነሳ አንተ ብርድ ከምተጎዳ ሂድና አሳድሩኝ በል እኔ እንደ ልማዴ አንዱ ዛፍ ጥግ አድሬ ጉዟችንን ጠዋት እንቀጥላለን… ይለዋል አሉ… (አንቺዬ ለካስ ሰይጣን ለኢህአዴግ ሲሆን ሩሩህ ነውና…. አትይልኝም…)
ከዛልሽ፤ እሺ ብሎ የዋሁ ካድሬ ወደ አንዱ ጎጆ ሄዶ አሳድሩኝ…ማለት፤ ሰዎቹም ማንነቱን ሲያውቁ ጊዜ ቦታ የለንም፤ ብለው ይመልሱታል… አንዱ ቤት ብቻ መሰለሽ የመንደሩ ሰዉ ሁሉ ቦታ የለንም እያለ ፊት ነሳው። ከዛ አንገቱን አቀርቅቅሮ ከወዳጁ ሰይጣን ዘንድ ሄደና፤ ”እኔ አላሳድር አሉኝ ባክህ… ምን አይነት ልማት አደናቃፊ ሰዎች እንደሆኑ እንጃ…” አለው። ለጠቅ አድርጎም፤ ”እስቲ አንተ ደግሞ ሞክራቸውና ጉዳቸውን እንይ”፤ ቢለው ጊዜ ሰይጣንም ”እስቲ እንዳልክ ይሁን” ብሎ ገና የመጀመሪያው ቤት አሳድሩኝ ብሎ ሲጠይቅ እሺ ይሉት እና ያስገቡታል… (ጋሽ ወንድሙ ይሄን ሲነግረኝ፤ ”ሰይጣን መሆኑንን ባያውቁ ነው በጄ ያሉት…” ብዬው ነበር… ለካስ እንደርሱ አይደለም ሰይጣን እንደሆነ አውቀዋል… ኢህአዴጉን ሰው አናሳድር ብለው እርኩሱን ሰይጣን ያሳደርሩት ምን ብለው መሰለሽ፤ ”ሰይጣን አለወጣ ቢል በጸበል ይወጣል ኢህአዴግ ግን አንዴ ከገባ መውጫም የለው….” ብለው ሰግተው ነው…. ብሎ በሳቅ ሊገድልኝ…
እናልሽ ዘንድሮ ሰይጣንም እንኳ ቢወዳደር እርሱን እንመርጥ እና ኋላ አልወጣ ወይ አላዋጣ ካለ በጸበል እንሞክረዋልን እንጂ ዳግም ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ይቆይ ብሎ መምረጥ፤ በራስ ላይ ሌላ ጦስ ማምጣት ነው…
”ይሄኔ አንቺ በሆድድሽ እስከዛሬስ መርጣችሁት ነው እንዴ ስልጣን ላይ ተጣብቆ የቀረው…” ብለሽ ልትሞግቺኝ ወገብሽን ይዘሻል… መች አጣነው፤ ኢህአዴግ ዋና ዘመዱ፣ ዋና መመኪያው ጠብመንጃው ነች። ያ በደሉ ሞቅ ሲለው ምን እንደሚል ሰምተሻል፤ ”የሚመካ በክላሽ ይመካ ብሏል ኢህአዴግ” እያለ አንዴም ሲያስቀን አንዴም ሲያሳቅቀን ባየሽ…
እርግጥ ነው ነው ልጄ ኢህአዴግ ምርጫን የሚጠቀመው ለመተዛዘቢያ ያክል እንጂ እንደ ዘጠና ሰባቱ ጊዜ ሆ… ብለን ወግድ ብንለው እንኳ ”አንዳንድ ጸረ ልማት ሃይሎች” የሚል ነጠላ ዜማ ይለቅ ይሆናል እንጂ ስልጣኑንስ በምርጫ እንደማይለቅ እናውቀዋለን። ቢሆንም ግን ልጄ እንደ ሁለት ሺህ ሁለቱ ምርጫ ምን አለፋን ብለን ካርድ ሳንወስድ እቤት ቁጭ ብሎ ዜና ከማየት፤ ካርዳችንን አውጥተን ለሆነው ተቃዋሚ ድምጻአችንን ሰጥተን ጉዱን ማየት ይሻለናል። ቢያንስ ቢያንስ የሚገዙን በግድ መሆኑን ብናሳያቸው ራሱ ቀላል አይደለም፤ ብለን እኔም የሰፈሩ ሰው ሁሉም በየ ቡናው በየ ሀዘን እና ደስታ ቦታው ሁሉ እየመከረን ነው….! በነርሱ ቤት ቦለቲካውን የሚያውቀው ቀበሌ ገባ ወጣ ያለ ብቻ ነው… እኛ እነርሱ ፊት ምንም የማናውቅ መስለን ውስጥ ውስጡን ያሰብንላቸው ብዙ ነው… እስቲ ብቻ ግዜው ይደርስ…
እና ልጄ እንዴት አለሽልኝ…
እናንተማ ምን አለባችሁ ልጄ፤ ባለፈው፤ ሚሚ ከፌስ ቡክ አየሁ ብላ እንደነገረችኝ፤ ሰሞኑን ውሃ በባልዲ እየሞላችሁ አናታችሁ ላይ እየደፋችሁ እየተራጫችሁት ነው አሉ። እኛ በጀሪካን አናታችን ላይ ጭነን ከየትና የት ወደቤታችን ለማምጣት አበሳ ስናይ እናንተ ተራጩት እንጂ… ደግሞ ሌላውም ሰው እንደናንተው ውሃ በበረዶ አድርጎ አናቱ ላይ እንዲያፈስ አልያ ግን በህምም ላሉ ወገኖⶭ ገንዘብ እንዲከፍል እያላችሁ ትፎካከሩልን ይዛችኋል፤ አይ ልጄ እናንተ እዛው ርስ በርሳችሁ እንዳሻችሁ ነገር ግን ይሄንን ጥቆማ ወደኛ ታደርጉትና ኋላ እንቀያየማልን ልጄ… እንደምታውቂው የእኛ ሰው በረዶ ይሰራበት ኤሌክትሪክ እንዲሁም አናቱ ላይ ያፈሰው ውሃ የለውም። አንቺ አናትሽ ላይ ውሃ በበረዶ ደፍተሽ እኔ እናትሽን የጠቆምሽ እንደሆነ የግድ ያልሽውን ለማድረግ ጅቡቲ መሄድ ነው ያለብኝ፤ ውሃውም መብራቱም ለጅቡቲ ተሸጦ እኛ ዘንድ በስንት አንድ ቀን ነው…ልጄ። ስለዚህ ”ትጠጣው የላት ትደፋው አማራት” እንዳታሰኚኝ…አደራ እንዳትጠቁሚብኝ ልጄ!
እና እንዴት አለሽ ልጄ…
በመጨረሻም እኔ፤
(ይቀጥላል… ) ብለን እናክብደው እንዴ…!

የቴዲ አፍሮ በሰባ ደረጃ ነጠላ ዜማና የበእውቀቱ ስዩም ዕይታ

Tedooo

ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ወይም ‹‹ቴዲ አፍሮ ›› በሰባ ደረጃ የተባለ(ች) ነጠላ ዘፈን ለቆልናል፡፡

‹‹በሰባ ደረጃ››ን እኔ ስሰማው እልም ያለ የፍቅር ዘፈን ነው፡፡ፍቅርን ልዩ በሆነ ቦታና ልዩ በሆነ ሥፍራ የሚያሳይ ዘፈን፡፡ በአማርኛ ዘፈን ባህል ውስጥ ቦታን ማስጎብኘት የተለመደ ነው፡፡ ‹‹የሐረር ልጅ ነች ወጣቷ/ጀጎል ነው ቤቷ››አይነት ዘፈን ሞልቶናል፡፡ አብዛኛው ያገራችን ዘፋኝ፣ ያስጎብኝነት ሚናም ደርቦ ሲጫወት ኖሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተፈቃሪዋ ሴት ሁሌም ከታሪካዊ ቦታ አጠገብ ለመወለድ ትገደዳለች፡፡
ቴዲ በዚህ ዜማው ባልተሄደበት መንገድ ሄዷል፡፡ ሲጀምር፣እዚህ ግባ የማይባል ፣ለዓይን የማይሞላ ቦታ መረጠ፡፡ብዙ ጊዜ፣ታሪካዊ ቦታ ሲባል፣አክሱም ላሊበላ፣ፋሲል ሶፍኡመር ጀጎል እንላለን፡፡ ካሜራው በኒህ ቅርሶች ላይ አፍጥጦ ኖሯል፡፡ ታሪክ አክሱም ላይ ጀምሮ ጀጎል ላይ የተጠናቀቀ ይመስል፡፡

ብዙዎቻችን በሸገር ላይ አድልኦ ስንፈጽም ኖረናል፡፡ አዲስ አበባ ለአቅመ ቅርስ የምትበቃ ከተማ አትመስለንም፡፡ሸገር ታሪክ ሲሠራባትና ሲሠራላት እንደኖረች አናውቅም፡፡ ወይም ለማወቅ አንፈልግም፡፡ ቴዲ ይህንን እይታ ቀየረው፡፡

ሁለተኛ፣

ከላይ የጠቀስኳቸው ቅርሶች የጌቶች መታሰቢያ ናቸው፡፡ የምድራዊና ሰማያዊ መሪዎችን የሚወክሉ ናቸው፡፡የስም የለሹን፣የተርታውን ሰው ኑሮ የሚያሳዩ ቅርሶች ግን ደምቀው አልወጡም፡፡አይተን እንዳላየን፣ቸል ብለናቸው ቆይተናል፡፡ቴዲ ግን ማንም ሲወጣበትና ሲወርደበት ለኖረው አንድ መንገድ ዘፈነለት፡፡መዝፈን ቢሉህ ዝም ብሎ መዝፈን ብቻ አይደለም፤ አንድ ውብ የሆነ የፍቅር ታሪክ ተረከበት፡፡ነጠላ ዜማው ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሰባ ደረጃን በድሮ ዓይናችን አናየውም፡፡አሪፍ ጥበብ ዓይን ገላጭ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

የቴዲ አፍሮ በሰባ ደረጃ ነጠላ ዜማና የበእውቀቱ ስዩም ዕይታሦስተኛው ነጥብ፣

ዘፋኞች ልዩ ቦታን ሲያሳዩ ኖረዋል፡፡ቴዲ ደግሞ አንድን ልዩ ዘመን ለማሳየት ሞክሯል፡፡የቴዲን ዘፈን ስሰማ፣ በካሳሁን ግርማሞ ዘመን የኖረ አንድ ሮሚዎ ይታየኛል፡፡ሸዋ ዳቦ ሳይቋቋም፣ከአርመን ሱቅ ፉርኖ በሚሸመትበት ዘመን፣ምኒባስ ሳይገባ ፣ሰዎች ሴቼንቶ የሚሳፈሩበት ዘመን፣ከጄኔራሎች በላይ ሴቼንቶ ነጂዎች ስመጥር የነበሩበት ዘመን፣ሴቶች የጥላቸውን ቁመት አይተው ሰአት ከመገመት ወጥተው፣ክንዳቸው ላይ ሰአት ማሰር የጀመሩበት ዘመን – በዚያ ዘመን የኖረ አፍቃሪ ይታየኛል፡፡አንድን ልዩ ዘመን በሲኒማና በልቦለድ ማሳየት የተለመድ ነው፡፡ በጣም አጭር ቆይታ ባለው ዘፈን ውስጥ ዘመንን ለማሳየት በመሞከር ግን ቴዲ ፋና -ወጊ ይመስለኛል፡፡

ዜመኛ ስላልሆንሁ ስለቴዲ ዜማ ምንም ማለት አልችልም፡፡ያም ሆኖ ፣ግጥሙ የተዋጣለት እንደሆነ መመስከር እችላለሁ፡፡አንድ ቦታ ላይ‹‹አንደ አርሚዴ ሜሪ››የሚል ሐረግ ሰምቻለሁ፡፡ ዜመኛው፣ሜሪ አርምዴን ፣አርምዴ መሪ ብሎ መጥራት የገጣሚነት ነጻነቱ ይፈቅድለታል፡፡ገጣሚ እንደ ህጻን ልጅ፣እንደ እብድና እንደ ቅዱሳን ከቋንቋ ሕግ በላይ ነው፡፡እንደ ጋዜጠኛ፣በሰዋስው ህግ አይታሠርም፡፡እንዲያውም ሳይራቀቁ መግጠም ፣ፈሳሽ ውስጥ ሳይገቡ መስጠም አይታሰብም፡፡

በነገራችን ላይ በድሮ ዘመን በኢትዮጵያ የአባት ስም ከልጅ ስም ቀድሞ ይጻፍ ነበር፡፡ቴዲን ትውፊትም ያግዘዋል ለማለት ፈልጌ ነው፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ፣በሚቀጥለው ጽሁፌ እናወጋለን፣

እስከዛ ድረስ ያንን ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም!

Court denies bloggers, journalists bail

 

Zone 9.1

The Federal High Court 19th bench decided against the appeal presented by the bloggers and journalists who are suspects and are charged by the federal prosecutor and held under custody for the last 125 days. The court passed the decision on August 20.

The six bloggers in custody are Atnaf Berhane, Befekadu Hailu, Abel Wabela, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, and Zelalem Kibret. Soliana Shimeles was charged in absentia. The three journalists are Tesfalem Waldyes, Edom Kassaye, and Asmamaw Hailegiorgis, an editor at the weekly magazine, Addis Guday.

The suspects argued that one can deny the bail only if the charge falls under article three of the anti terror proclamation No. 652/2009 and they further argued that a suspect is denied bail if the suspect has committed one or more actions listed under article three of the proclamation.

However, they mentioned that the federal prosecutor could not provide at least one action listed in the article and the prosecutor rather mentioned article four of the proclamation, which is not appropriate and hence added that the charge is not presented based on the anti terrorism proclamation and requested that their case be seen in a regular procedure of law and grant them bail.

On the other hand, the suspects also claimed that their case needs constitutional interpretation and the charge brought to them is against the constitution and bail right is denied from the presumption that if bail is secured, the suspects may disappear. 

According to the court decision, the prosecutor charged suspects for the protection of the public and the government and therefore it can present the case narrowly or widely and say that the court is examining the charges brought against them based on the anti terror proclamation. Whether the case been seen by the regular law or by the anti terror proclamation the charge is presented by the country’s the anti terror law.

Another appeal by the suspects that is the case of constitutional interpretation. The court decided that the charge brought against the suspect and the articles in the constitution are not against each other, therefore the court has dismissed their appeal.

Another objection that the suspects brought to the court was that the prosecutor said the defendants were organizing other members who are not yet detained. For that allegation, they argued that the prosecutor did not provide the list of the names of those suspects and this in turn narrows their right to defend and also creates a state of fear on others who might be witness in favor of them.

Moreover, in relation to the items that the prosecutor holds as exhibit, since the items have got nothing to do with the charge, they requested the court to order the reimbursement of the items. 

In relation to the charge that states that they were disseminating articles that incite public violence, the suspects said that the prosecutor did not refer to anything about the where, when and what of the dissemination of articles and present their objection by requesting the court to drop or change the charge.

After the court passed the decision of granting the defendants bail the lawyers of the bloggers and journalists stated that they will appeal the case to the Federal Supreme Court.

The court adjourned for October 15, 2014 to hear the preliminary objection by the federal prosecutor.

()

 

በአሶሳ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ተከስቷል

 

Ethiopia-Asosa

አንድ ሰው በበሽታው ሞቷል
የክልሉ ጤና ቢሮ በሽታው ኢቦላ አይደለም ብሏል
በሽተኞች ላይ ደም ማስመለስና ማስቀመጥ ተስተውሏል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ በሁለት ሰዎች ላይ መከሰቱንና አንደኛው መሞቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታዬ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን የኢቦላ በሽታ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ አልተከሰተም ብለዋል፡፡
የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ በሚገኘው ባምባሲ የስደተኞች ጣቢያ በሽታው ተከስቷል ሲሉ ያሰራጩት መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊው፤ ለጊዜው በትክክል ምንነቱ ያልታወቀው በሽታ የተከሰተው ከስደተኞች ጋር ምንም አይነት ንክኪ በሌለው የአሶሳ ከተማ መንደር 47 በሚባል አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በህክምና ባለሙያዎች የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል በተባለው በዚህ በሽታ የተያዙት ሁለት ግለሰቦች ላይ የታየው ምልክት ደም ማስመለስና ማስቀመጥ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሃብታሙ፤ በሽተኞቹ ለብቻ ተገልለው በጥንቃቄ እንዲታከሙ ተደርጓል፣ የአንደኛውን ህይወት ማትረፍ ባይቻልም ሌላኛው ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡
የኢቦላ በሽታ ምልክቶች ከሌሎች በሽታዎች ጋርም ሊመሳሰል ይችላል ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ነገር ግን በህክምና ባለሙያዎች በሽታው ኢቦላ አለመሆኑ ተረጋግጧል፤ በሽታው የምግብ መበከል ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠርጥሯል ብሏል፡፡
በድንበር አካባቢ በሽታው ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የጠየቅናቸው ኃላፊው፤ ሱዳን ውስጥ በሽታው ስለሌለ ስጋት የለብንም ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ በሽታው ኢቦላ ነው በሚል እንዳይደናገጥ በክልሉ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ትናንት ጠዋት ቀርበው በሽታው ኢቦላ አለመሆኑን ማስረዳታቸውን አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪም ግብረ ሃይል በማቋቋም ምንነቱ በትክክል ያልታወቀውን በሽታ ለማጣራት ባለሙያዎች የተከሰተበት ቦታ ድረስ በመሄድ የማጣራት ስራ መስራታቸውንና ኢቦላ በክልሉ የትኛውም አካባቢ እንዳልተከሰተ ማረጋገጣቸውን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡  የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አህመድ አማኖ፤ በሃገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ኢቦላ አለመከሰቱን ከየክልሎች በሚሰበሰቡ መረጃዎች መረዳት መቻሉን ለአዲስ አድማስ ገልፀው፤ ምናልባትም ከሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ትኩሳት፣ የአፍንጫ መንሰር ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል፡፡ አሶሳ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲዎች የተሰራጨውም ትክክለኛ መረጃ አይደለም ብለዋል ኃላፊው፡፡

Source :- (addisadmassnews)

New charges against Ethiopian publications further diminish critical voices (CPJ)

 

Five independent magazines and a weekly newspaper have been charged by Ethiopia’s Justice Ministry, a move that may add to the long lists of shuttered publications and Ethiopian journalists in exile. In a press release issued August 4, the ministry accused the journals of publishing false information, inciting violence, and undermining public confidence in the government, news reports said.
The ministry said it pressed charges after running out of patience with the publications for “encouraging radicalism and terrorism.” The state broadcaster aired the ministry’s announcement, but none of the publications received the charge sheet, local journalists told me. The six independent publications are Afro Times, a weekly newspaper, and magazines Addis Guday, Enku, Fact,Jano, and Lomi. All are popular alternatives to the state-run press, which espouses an increasingly positive narrative. Local journalists and news reports said the charges could be a way for the ruling party to silence critics ahead of elections expected in May 2015.
Repeated calls to the Justice Ministry and a government spokesman went unanswered.
The ministry’s charges are not unexpected. In February, the pro-government Ethiopian Press Agency, a state-controlled news wire, conducted a study analyzing the content of the publications and concluded they were responsible for inciting violence and upholding opposition viewpoints, according to local news reports. Many local journalists at the time said they feared the study would be used as a pretext to target the publications later. “It’s a strategy the government uses when they want to stop a newspaper,” Habtamu Seyoum, an editor at popular magazineAddis Guday, told me by phone. “They will prepare an article claiming that a journalist or media house should be closed. The next step is to jail or close the media house; it’s done as a sort of formality.”
The Justice Ministry’s charges reflect a trend of authorities silencing critical media. Since 2009, the government has banned or suspended at least one critical independent publication per year, according to CPJ research.
Addis Guday stopped publishing on August 9. Several staff went into exile shortly after the government announcement, fearing imminent arrest. CPJ research shows their fears are likely justified. “We had police surrounding our offices, insults printed by the government press, constant phone threats–and now [these charges]. It was just too much,” Addis Guday Deputy Editor Ibrahim Shafi told CPJ. A week before the staff members fled, police raided their offices twice in one week, ostensibly to investigate financial records, he said.
The country’s politicized justice system coupled with the ruling party’s near zero-tolerance approach to criticism has led a steady flow of journalists to flee the country. CPJ has directly assisted at least 41 journalists fleeing Ethiopia since 2009, and the total number of exiles is likely higher. Those who have fallen out of favor with authorities, whether from independent or state media, feel exile or imprisonment are their only options.
Authorities arrested another Addis Guday editor, Asmamaw Hailegeorgis, in Aprilon terrorism charges, and arrested photojournalist Aziza Mohamed in July on vague accusations of incitement. Ethiopian authorities have a penchant for sentencing journalists to jail after presenting charges, no matter how spurious the charges may be. Data collected from the registrar of Ethiopia’s Federal High Courtsuggest 95 percent of journalists accused by authorities are found guilty, according to TrialTrackerBlog.org, which publishes news about detained journalists in Ethiopia.
Lomi (“Lemon”) failed to print on August 8 and is unlikely to do so again, local journalists told me, because printers fear publishing anything that has fallen out of the ruling party’s favor. Last month, police searched Lomi‘s offices and accused the staff of working without a license, a charge they denied, local journalists said.
According to the state-run Addis Admas, all but one of the magazines failed to publish recently.
A court in the capital, Addis Ababa, summoned the general managers of three publications–FactAddis Guday, and Lomi–on August 13, but only the general manager of Lomi appeared, according to news reports. Local journalists told CPJ they expect the other three publications to be summoned to court soon.
CPJ was not able to reach journalists from Afro TimesEnkuFact, or Jano.
If these publications close down due to this latest government challenge, Ethiopia’s meager circulation of weekly independent publications–roughly 60,000 for a population of 90 million people–will decrease further. There is only one television station, run by the state, and out of five radio stations, three are staunchly pro-government. The state-run telecommunications company is the sole Internet service provider for a country with the second lowest Internet penetration rates in sub-Saharan Africa, according to the International Telecommunication Union. With limited independent voices, voters’ access to critical news sources and informed debate ahead of Ethiopia’s May 2015 elections may be negligible. The ruling party would probably not want it any other way.
[Reporting from Nairobi]
Tom Rhodes is CPJ’s East Africa representative, based in Nairobi. Rhodes is a founder of southern Sudan’s first independent newspaper. Follow him on Twitter: @africamedia_CPJ