Archive | August 8, 2014

እንጦጦ አካባቢ አንድ የከተማ አውቶብስ በሰባት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አደረሰ

  bas

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ወደ ሺሮ ሜዳ ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ በሰባት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አደረሰ።

እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ትናንት ምሽት 2 ስአት ከ25 ላይ ነው አደጋው የደረሰው።

በአደጋው ሶስት ሶስት ሰዎች ወዲያውኑ ህይዎታቸው ሲያልፍ ሶስቱ ደግም ወደ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ሊደረግላቸው ሲል መንገድ ላይ አርፈዋል። አንደኛው ደግሞ ዛሬ ጠዋት ላይ ህይወቱ አልፏል።

በአደጋው ህይዎታቸው ያለፈው ሁሉም መንገደኞች ሲሆኑ፥ የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

በርካታ ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑም ተገልጿል።

አውቶብሱ ከኤሌክትሪክ ምሰሶ ጋር ተጋጭቶ ስለነበር የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበርም ተነግሯል።