Archive | August 13, 2014

አጃይብ ነው ዛሬ ጆሮ የማይሰማው የለም

tumblr_lws0ehzzbo1r8w6rjo1_500

 አንድ የቅርብ ወዳጄ ከጥቂት ደቂቃወች በፌት እዚው ፌስ ብክ ላይ በግር በፈረስ ስገልግህ ብሎ ጤናዬን ኑሮዬን ጠየቀኝ ( ጠበቅ አርጎ ) በሆዴ ትግሉን እንደ ሌልች ጀግኖች ልቀላቀል እንዴት ልግባ ይለኛል ብዬ ስጠብቅ …የሱ ትግል ሌላ ሆኖ እርፍ …ዱዲዬ ብሎ ሲጀምር ( ነገር እንዳለው ገባኝ እና ጆሮዬን አሰፋሁኝ …….
ይሄውልህ ሰሞኑን ከኑሮው ከነጻነቱ በላይ …( በሆዴ ከነጻነት በላ ምን ይሆን አልኩኝ ንግግሩን እንዳላደናቅፈው )… ከ ክረምቱ በላይ ቴሌ እየቀለደብን ነው …ደሜ ፈላ እና ምን ሆነሀላ ቴሌ እንደሚቀልድብህ ከ23 አመት በሀላ ዛሬ ነው እንዴ የገባህ ብዬ ብው …ኖኖኖ ዱዲ እንደሱ አይደለም የዚ ሰሞን ለየት ያለ ነው …እንዴት….200..100...50…ብር ሙላው አንተ ሳትደውል ሌላ ሰው ደውሎልህ ባወራኽው ገንዘቡ የለም ባዶ በረጅሙ ተንፍሶ …ሰው ባደውልልህ እንኩዋን አጥፍተህ ብታስቀምጠው ስታበራው የለም ….እኔም በረጅሙ ሳኩኝ ወዳጄም በረጅሙ ጮኽ …ግን ውይይታችን አልተቃረጠም ( በኛ ሰፈር አባባል የፈለገኝ ለፈለጣ ስለሆነ )…ብመታውም ይችለዋል ….. (-_-)
የሚገርም ደግሞ አለኝ በንዴት ተሞልቶ እየሳኩኝ በጀ አልኩት ….ከትናት ወድያ ማታ ቴሌ መግለጫ ሰጠ አለኝ ( ይፈልገኝ የበረው መግለጫው ከወጣ ጀምሮ ነው kkkk )…እኔም እባክህ መላገጫውን ብለህ ቀጥል አልኩት …ሳይወድ በግዱ እንደፈለክ ብሎ ቀጠለ …ከዛሬ ጀምሮ የማስፋፍያ ስራችንን ጨርሰናል እና ደንበኞቻችን እንኩዋን ደስ አላቹህ ከዛሬ ጀምሮ የምስራች አለን አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ዙርያ ላሉ ከተማውች የ4G አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ለን …እኔም እምባዬ እስኪረግፍ ሳኩኝ ከዛም 4G መጠቀም ጀመርን ብለህ ነው እንዲ ተጨንቀህ የፈለከኝ አልኩኝ በሆዴ ምሳ መብላት ካቆምኩኝ በጣም ቆየው ብሎ አንዴ አሳዝኖ የፈለጠኝ ትዝ እያለኝ …..እሺ ቀጥል ይቅርታ ጨምሬበት…..
የሚገርምህ ዱዲዬ ..( መፈለጫዬ ደረሰ kkk )….እነዚህ የማይፍሩ ደደቦች የ 4G አገልግሎት የምንሰጠው በነጻ ነው ብለውን እንዳልነበር አሁን ደግሞ ለ40,000 ሰወች ብቻ ነው እና ቀድማቹህ በመክፈል ተመዝገቡ አይሉን መሰልህ …መክፈሉንስ ይከፈል አለኝ…. ( ልማታዊ ካድሬ ሆነ እንዴ አልኩኝ በሆዴ እንዲጨርስ በመናፈቅ )….ታድያ መክፈል ከቻልክ ምን አበሳጨህ አልኩት ..አትቀልድ ብሎ ብሎ እንደ መቆጣትም አለ….የበለጠ ሳኩኝ ጎድሎኛል ብሎ ሊፈልጠኝ እያዘጋጀኝ መሆኑ ስለገባኝ ….4G አገልግሎት መጠቀም የሚቻለው iphone 5s and samsung s5 ብቻ ሲኖርህ ነው ብለው አረፍት ..ሳቅ አፈነኝ የፈለገኝ ጉድ ስለደረሰ….እና የፈለኩህ ዱዲዬዬ አሞላቆኝ kkkkk…. ከሁለት አንዱ ላንተ የሚቀልህን እንድትተባበረኝ ነው አለኝ …..ዛሬ አፕሬል ዘፍል ነው እንዴ በኢትዮጵያ አልኩት አትቀልድ ዛሬ ነሓሴ 7 ነው አለኝ ….እኔም ለመሞጣሞጥ ጉሮሮዬን አጸዳው እና ለምን ኑሮ ከተወድደ ይቅርታ ማለቴ ቴሌ እንደዚ ካማረራችህ ሰልፍ አትወጡም …አይፎን 5s ይቀነስልን ብላችህ ሰብሰብ ብላችህ አትወጡም …ድሮም ገብተኅኛል ነጻነትን ከስልክ ማሳነስህ ግን አሁንም ቤተሰቦችህ ቤት ነው የምትኖረው አልኩት አዎ አለኝ (የቀበሌ ቤት ነው ቤቱ )…በህሊናዬ አንዳርጋቸውን አሰብኩት ከምቾት ኑሮ ልጆቹን ጥሎ ለእንደዚ አይነቱ _____________ ምን ልበለው …ጠግቦ እንዲበላ የመንፈስ ሀብታም እንዲሆን ማንነቱን እንዲያቅ ድንጋይ ላይ ተኝቶ አፈር ተንተርሶ እሱን የመሰሉ ጀግኖችን አፍርቶ ወደ ነጻነት ባቡር የጫናቸውን ጀግኖች ሳስብ እና አሁን ድግሞ በትግራይ ዘረኞች እና ጨካኞች እጅ ገብቶ የሚደርስበትን መከራ እና ግፍ ሳስብ ከንደዚ አይነት እንስሳ ጋር ማውራት ልቤን አቅለሽለሸኝ…..ግን እነት ነው እና ቻልኩት መሶም እንዳያገኘኝ ነግሬ ሸኘውት !!
ግን የአንዳርጋቸውን መዝሙር አሰብኩት በዛ በረሀ ውስጥ ሆኖ ድንጋይ ላይ ተጋድሞ በአረብ ሀገራት ኢትዮጵያውያን የሚደርስባቸውን መከራ እና ግፍ ..ባህር የሚበላቸውን ሲያስብ….በሀገራቸው ላይ ደግሞ በትግራይ አውሬወች በዘረኝነት እውር የሚደርሰውን መከራ እያሰበ የራሱን ምቾት ማጣት እረስቶ የጻፈው መዝሙር…ከዛውስጥ አንዱን ፓርት አስፍሬ እንለያይ ነጻነታችን የሚያሳየን መራራ ነገሮች ብዙ ስላሉ ..ግን በጽናት አንድነታችንን ይዘን …እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ብለን አላማችንን እናሳካለን ነጻነታችንን እናውጃለን …ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር ማለታችንን እናሳያለን ..ያም ቀን ቅርብ ነው !!
……………ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው ሃገሬ ደሜን የማፈሰው።
በባርነት ሸክም ጀርባሽ ለጎበጠው
በባላጌ መዳፍ ክብርሽ ለጎደፈው
የስቃይሽ ሲቃ ሰማይ ለነደለው
አይንሽ እስኪጠፋ ደም ለምታነቢው
ላንቺ ነው ሃገሬ
ህይወት የገበር ነው…………….

Andargachew

ሰናይ ቀን ..ዱዲ አንዳርጋቸው
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!
ነሓሴ 7.