እውን የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ይሄ ነው?


3

ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ የመጣው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ሃገሪትዋን  መውጣት ወደ አልቻለችበት ድህነት እና ሰቆቃ ከቶዋት ህዝቡ ከዘመናት ዘመናት በረሃብ ፣ በድህነት ፣ በጦርነት እና በዘር በጎሳ በመከፋፈል ያለ ማቁዋረጥ እየማቀቀ ይገኛል::

ይህንንም ተረድተው ደሞ ሃገሪትዋን ካለችበት ችግር ለማላቀቅ የሚጥሩትንም ሰዎች የማይሆን ስም በመስጠት ከህዝብ ጋር እንዲቃቃሩና ትግላቸው ከግብ ሳይደርስ መና እንዲቀሩ የተደረጉ ሰዎች ብዙ አሉ::

ህዝባችንን አንድነትን ፈጥሮ በጋራ ከማቆም ይልቅ ጥቃቅን ስብእናን የሚያጎድፉ ነጠላ ሃሳቦችን ይዞ እርስ በእርስ ከማጠላለፍ ይልቅ ለህዝብ የሚጠቅመውን ከምንም በላይ በዚህ ሰአትና ወቅት ብዙ የሚያስጨንቀንና እንቅልፍ የሚነሳን ከአንድነት ይልቅ መከፋፈልን ፣ ከመተባበር ይልቅ መጠላለፍን በማናፈስ ለወያኔ የፖለቲካና ስልጣን ማራዘሚያ የሚውል ፕሮፖጋንዳ እራሳችን እየፈጠርን የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር ለማባባስ በወቅቱ ጥቂት ግለሰቦች የፈጠሩት ውዥምብር አንዱ ማሳያ ነው::

እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ማሰብና ማተኮር ያልቻለው ትልቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆነውን የወያኔን መንግስት ከስር መሰረቱ ከመንቀል ይልቅ እርስ በእርስ በመከፋፈል እና በመካሰስ አባላትንና ደጋፊዎቻቸውን አላስፈላጊ እና ወቅታዊ ባልሆነ ውዥምብር  ውስጥ መክተት እንደስራ በያዙ ግለሰቦች እንዲሁም የማተራመስ ተልኮዎቻቸውን በወያኔ ቀቢጸ ተስፋ በመመራት ወይም ሃገር ቤት በመመላለስ የሚያገኙትን ጥቂት ፍርፋሪ ላለማጣት ህሊናቸውን ሸጠው የወገኖቻቸውን ቸግር በጊዜያዊ ጥቅም ለመቀየር እየተንቀሳቀሱ ያሉትን አሉባልተኞች ለዚህ አፍራሽ ተልኮዋቸው ተገቢውን ቅጣት ማግኘት እንዳለባቸው ሊገነዘቡት ይገባል::

ከውዥምብሮቹም አንዱ በቅርቡ በአውሮፓ የሚገኙ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ላይ እየተዛመተ ያለው አሉባልታና ስም ማጥፋት አንዱና ዋነኛው የውዥምብሩ ገጽታ ነው::

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ አመራር እና አባላቶቹ ጋር አንድ ላይ በመሆን ቀን ከለሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅረፍ በመንቀሳቀስላይና በሃገሪትዋ ላይ የሚደረጉትን ግፍ እና በደሎች ለአለም በማሳወቅ የበኩሉን አስተዋጽዎ በማድረግ ላይ እያለ ይህንን የመሰለ አሳዛኝ የመከፋፈል እና ለማፍረስ መሩዋሩዋጡ የሚያስተዛዝብ ሆኖ  አግኝተነዋል::

የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር የዲሞክራሲ እጦት እና የፍትህ ጥማት ሆኖ እያለ በቀላሉ የሚገኙ እና በሚፈበረኩ ሶሻል ሚድያዎች እንደ ፌስ ቡክ ባሉ ገጾች የሚያወጡትን የስም ማጥፋት ህግ በሚከበርበት ሃገር ላይ ተቀምጠን በዝምታ የምናልፈው ነገር እንደማይሆን ሊያውቁት ይገባል!!

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አመራር እና አባላቶቹ ድርጅቱን አሁን ላለበት ደረጃ ለማድረስ በፊት ያለፉበት ከባባድ ፈተናና ችግሮች አሁን የተነሳንባቸውን ከእውነት የራቀ ውንጀላና አሉባልታ እንዲያውም ወደፊት የበለጠ ሊያጠናክራቸውና የበለጠ ትግላቸውን ከግብ የሚያደርስ ጥንካሬያዊ መልእክት እንደሆነ የነዚህ ለሆዳቸው ያደሩ ህሊናቢሶች ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት ይገባል በሚል የግል አስተያየቴን እቌጫለሁ::

ከአውግቸው ከበደ

ነሃሴ 24/12/2006 አውስትራልያ

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

 

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s