Archive | September 2014

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ /EPPFG/ የጀርመንን መንግስትን ጨምሮ ለአለም ታላላቅ መንግስታትና ድርጅቶች ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ባለ 6 ገጽ ደብዳቤውን አቀረበ

EPPFG Stamp 2

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ የጀርመንን መንግስትን ጨምሮ ለአለም ታላላቅ መንግስታትና ድርጅቶች ባለ 6 ገጽ ደብዳቤውን አቀረበ::

ድርጅቱ በደብዳቤው የወያኔን የ 23 አመት የግፍና የጭካኔ አገዛዝ አንድ በአንድ ጠቅሶ ያቀረበ ሲሆን ይህም መቀጠል እንደሌለበት ያመነው  የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ጠንክሮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ዘግቧል:: ሃገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት በማዕድን ሃብትዋ እና በስው ሃይል ትልቅ ብትሆንም በአስተዳደር ችግር ግን በአለም ከመጨረሻዎቹ ሃገሮች ተርታ ተመድባ መቀመጥዋ ለዚህ ትግል እንዳነሳሳውም ገልጾዋል::

ደብዳቤውንም :-

  • ለጀርመን መንግስት
  • ለአውሮፓ ህብረት
  • ለ አሜሪካ እስቴት ዲፓርትመንት
  • ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል
  • ለጀኖሳይድ ዎች መላኩን ኣሳውቆዋል

ሙሉውን ንባብ ይህን PDF በመጫን እንድታነቡት በአክብሮት እንጋብዛለን

ሕግ መንግሥታዊነት እና የሐሳብ ነጻነት በኢትዮጵያ /በዞን ዘጠኝ ጦማርያን/

/ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ/

ዞን ዘጠኝ የአራማጆች እና ጦማሪዎች ኢ-መደበኛ ቡድን ነው፡፡ ቡድኑ በአብዛኛው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ
በጦማሩ አስተያየቶችንና ትንታኔዎችን በማስፈር እና በየሦስት ወሩ የበይነመረብ ዘመቻ በማካሄድ
የአራማጅነት ሥራ ይሠራል፡፡ ከተመሠረተ ጀምሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት ዘመቻዎችን (በሕገ
መንግሥቱ ይከበር፣ የሐሳብ ነጻነት ይከበር፣ እና የሰላማዊ ሰልፍ ይከበር በሚል) ያካሄደ ሲሆን ከ150
በላይ ጽሑፎችንም በጦማሩ በኩል አስተናግዷል፡፡
ከነዚህ ጦማሮች መካከል አብዛኛዎቹን በዚህ ጥራዝ ውስጥ ያዘጋጀናቸው ሲሆን፣ በወጡበት ቅደም
ተከተል ከማዘጋጀት ይልቅ በየርእሰ ጉዳዩ በማሰባሰብ አንባቢ በመረጠው ርዕስ ላይ አትኩሮ እንዲያነብ
በማድረግ አሰናድተነዋል፡፡ ይህንን በምናደርግበት ሰዓት የዞን ዘጠኝ አባላት የጻፉትን በሙሉ ስማቸውን
ሳንጠቅስ ያስተናገድን ቢሆንም፣ ከሌሎች ሰዎች ተልከውልን በጦማራችን ያስተናገድናቸውን ጽሑፎች
ጸሐፊዎች ግን ገልፀናል፡፡
ጽሑፎቹ በተለያዩ ጊዜ የተጻፉ እንደመሆናቸውና የተጻፉበት ጊዜንም የሚያንፀባርቁ በመሆናቸው ብሎም
ጦማሩ ላይ የሰፈሩበትን መልክ ሳንቀይር የሰበሰብናቸው በመሆኑ ያለፈባቸው ነገሮች ሊያጋጥሙ
ይችላሉ፤ በተጨማሪም ጥቃቅን የአርትኦት እንከኖች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንባቢዎች፣ እነዚህን ክፍተቶች
እየሞሉ እንዲያነቡ ከይቅርታጋ እንጠይቃለን፡፡
ጽሑፎቹን ሰብስበን በኤሌክትሮኒክ ኮፒ ማስቀመጥ ያስፈለገን፣ ለወደፊቱ ማነፃፀሪያ ይሆናሉ ብለን
በማመናችን መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
መልካም ንባብ!

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ከታች ያለውን Pdf ይጫኑ

Zone9 – Compiled Book of Year One
Email: zone9ners@gmail.com
Twitter: @zone9ners

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኞች በመልካም አስተዳደር እጦት ተማረናል አሉ

 press

“የደሞዝ ጭማሪው ለሌላው ሲደርስ ለጋዜጠኛው አልደረሰም” ጋዜጠኞች

“ጭማሪው ሰሞኑን በቦርዱ ተወስኗል፤ በቀጣዩ ወር ይደርሳቸዋል” አቶ ሽመልስ ከማል

“ድርጅቱ በደመነፍስ ይመራል የሚለው አጉል አሉባልታ ነው” የፕሬስ ድርጅት ሥ/አስኪያጅ

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የሚታተሙት አዲስ ዘመን፣ ኢትዮጵያን ሄራልድ፣ በሪሳ እና አል-አለም ጋዜጠኞች በመስሪያቤታቸው የመልካም አስተዳደር እጦት እየተማረሩ መሆኑን ገለፁ፡፡ መንግስት በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር እያወቀ ምላሽ አለመስጠቱ እንዳሳዘናቸው ጋዜጠኞቹ ተናግረዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ ለመንግስት ሰራተኞች የተደረገው የደሞዝ ጭማሪ ለጋዜጠኞች አለመድረሱን የገለፁት ሰራተኞቹ፤ ላለፉት አራት ዓመታት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እያገለገሉ ያሉት አቶ ሽመልስ ከማል አንድም ቀን ሰብስበው አወያይተዋቸው እንደማያውቁ በምሬት ገልፀዋል፡፡

“ድርጅቱ በዚህ ዓመት ይህን እሰራለሁ ብሎ ያስቀመጠው ግብ የለም፣ ጋዜጠኛው የሚመራው ብቃት በሌለው ስራ አስኪያጅ ነው፣ ይህንንም በስብሰባ ለራሳቸው ለስራ አስኪያጁ ተናግረን ችግሩን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ያጣራውን ለሚመለከተው አካል ቢያቀርብም የተሰጠ ምላሽ የለም” ብለዋል – ጋዜጠኞቹ፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው፤ አንድም ቀን አወያይቶን አያውቅም የሚለው ፍፁም ሀሰትና የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ገልጸው፣ በየጊዜው ከጋዜጠኞችና ከኤዲተሮች ጋር እንደሚወያዩና በኤዲተሮችና ዋና አዘጋጆች ፎረም ላይ የተለያዩ ሃሳቦች እየተነሱ በምክክር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

“ከሰራተኛው መካከል የራሳቸው ጥቃቅን የጥቅም ግጭት ያላቸው አንዳንድ ግለሰቦች የሚነዙት አሉባልታ እንደ አጠቃላይ የሰራተኛው ችግር ተደርጎ መነሳቱ መሰረተ ቢስ ነው” ብለዋል – አቶ ሽመልስ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግረናቸው በሰጡት ምላሽ “ድርጅቱ በእቅድና በፕሮግራም እንደሚመራ በቢሮ ተገኝቶ አሰራሩን ማረጋገጥ ይቻላል” ያሉ ሲሆን፣ አንዳንድ የግል ችግር ያለባቸው ግለሰቦች የድርጅቱንና የአመራሩን ስም ለማጥፋት ሆን ብለው የሚነዙት ተጨባጭ ያልሆነ ወሬ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ ችግር ቢኖርበት ኖሮ ሰራተኛውን የሚያወያይበት የስብሰባ መድረክ እያዘጋጀ አያወያይም ነበር” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ በቅርቡ አጠቃላይ ስብሰባ ተጠርቶ ከሰራተኞች የተለያዩ አስተያየቶች መሰጠታቸውንና በውይይት መድረኩ ላይ የተነሱትን አንዳንድ ክፍተቶች እንደግብአት በመጠቀም የአሰራር ማስተካከያ እየተደረገ እንደሆነ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

ጋዜጠኞቹ በበኩላቸው ለመልካም አስተዳደር እጦቱ እንደዋና ማሳያ ያቀረቡት የድርጅቱ ህንፃ በሁለት ዓመት ተገንብቶ ይጠናቀቃል ቢባልም አራት አመት ፈጅቶ እንኳን አሁንም ይቀረዋል፣ የሰራተኛ የቅጥር ሁኔታው ግልፅነት የለውም፣ ሹፌር ሳይቀር በፍሪላንስ የሚቀጠርበት ሁኔታ አለ፣ የደሞዝ ጭማሪና የእድገት ሁኔታ በአድሎአዊ አሰራር የተተበተበ ነው፤ በዚህም የተነሳ ለጋዜጦቹ አለኝታ የሚባሉ ወደ 50 ሰራተኞች ባለፈው ዓመት ለቀዋል፤ ዘንድሮም የለቀቁ አሉ በማለት ተናግረዋል፡፡ መንግስት ይህን ሁሉ ችግር ያውቃል፤ ግን ማስተካከያ አልተደረገም ብለዋል፡፡ ፕሬስ ውስጥ በሲቪል ሰርቪስና በቦርድ የሚተዳደር ሁለት ዓይነት ሰራተኛ መኖሩን ጋዜጠኞቹ ገልጸው፣ በሲቪል ሰርቪስ የሚመራው ሰራተኛ ጭማሪው ሲደርሰው የእኛ ዘግይቷል ብለዋል፡፡

“በአንድ ወቅት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ጋዜጠኞች ደሞዝ የፕሬሱ ጋዜጠኞች ይበልጥ ነበር” ያለው አንድ ቅሬታ አቅራቢ ጋዜጠኛ፤ ኢዜአዎች ፕሬስ አቻ ድርጅት ሆኖ እንዴት ደሞዝ ይበልጡናል በሚል ላነሱት ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቷቸው ደሞዛቸው መስተካከሉን አስታውሶ፤ የእኛ አቻ ድርጅት በሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) በቅርቡ እስከ 200 ፐርሰንት የደሞዝ ጭማሪ ቢደረግም በእኛ ድርጅት ምንም የተባለ ነገር ባለመኖሩ ጋዜጠኛው በድርጅቱ ተስፋ እየቆረጠ ነው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ጭማሪውን በተመለከተ በሰጡት ምላሽ፤ በሲቪል ሰርቪስ የሚተዳደሩት የሚከፈላቸው በመንግስት በመሆኑ እንደማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ጭማሪው ቀድሞ እንደረሳቸው አምነው፣ ሆኖም በቦርድ ለሚተዳደሩት ጋዜጠኞች የሚከፈለው ድርጅቱ ከማስታወቂያና ከጋዜጣ ሽያጭ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በመሆኑና ስኬሉ ስለሚለያይ ቦርዱ ተወያይቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት ሲጠበቅ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ “ውይይቱ ተጠናቅቆ ቦርዱ ከትላንት በስቲያ ስለወሰነላቸው ጭማሪው በቀጣዩ ወር ይደርሳቸዋል” ብለዋል – ሥራ አስኪያጁ፡፡

በስብሰባው ላይ የአመራር ብቃት የለዎትም፤ ቦታውን ይልቀቁ በሚል ከጋዜጠኞች ቅሬታ ስለመቅረቡ አቶ ሰብስቤን ጠይቀናቸው፤ “እኔ ስብሰባ ላይ እንዲህ የሚባል ትችት አልቀረበብኝም” ያሉት አቶ ሰብስቤ፤ እርግጥ በስነ-ምግባርም ሆነ በእውቀት ብቃት የሌለው አንድ ጋዜጠኛ “ቦታውን ልቀቅ” ብሎ በግል ተናግሮኛል፤ ጋዜጠኛው አሁን ስራ ለቋል” ብለዋል፡፡ ብዙ ጋዜጠኞች ከድርጅቱ ይለቃሉ ስለሚባለው አንስተንባቸው በሰጡት ምላሽ፤ “ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ ጋዜጠኞች ይለቃሉ፣ የተሻለ ደሞዝ ሲያገኙ የትኛውም መ/ቤት እንደሚልቁት ሁሉ እዚህም ይለቃሉ፤ በዚያው ልክ እኛም እንቀጥራለን” ብለዋል፡፡ ሰራተኞቹ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሩ በአስቸኳይ ካልተቀረፈ፣ እንደአቻ ድርጅት ማግኘት የሚገባንን የደሞዝ እድገት ካላገኘንና አድሎአዊ አሰራር ካልቀረ ድርጅቱን ለመልቀቅ እንገደዳለን ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ በበኩላቸው፤ በድርጅቱ ውስጥ መሻሻሎችን ለመፍጠርና ወደ ኮርፖሬት አደረጃጀት ለመቀየር ስራዎች ተሰርተው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን እንዲፈታ አዲስ ጥሪ ቀረበ

ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) መሰረት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ለስደት በመዳረግ ኤርትራን ተከትላ ከአፍሪቃ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ መንግስት በአከራካሪው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ጋዜጠኞችን ለእስር፤እንግልትና ስደት ይዳርጋል ሲሉ አለም አቀፍ ተቋማት ይተቻሉ።

Symbolbild Zeitungen in Ketten

ተቋማቱ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች እንዲፈታ በተጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የታሰሩት በሙያቸው አለመሆኑን በመግለጽ ይከራከራል። የአፍሪቃ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን እንዲፈታ አዲስ ጥሪ አቅርቧል።እሸቴ በቀለ ዘገባ አለው።

Symbolbild Spickzettel

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፤ አስማማው ሃይለጊዮርጊስና ኤዶም ካሳዬ ከዞን ዘጠኝ ስድስት የኢንተርኔት ጸሃፊያን ጋር በኢትዮጵያ የታሰሩት ሚያዝያ 17 / 2006 ነበር። በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጅ ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች በኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ለፍርድ ቤት ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆኖ ዛሬም በእስር ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር አምስት የመጽሄቶችና አንድ ጋዜጣ አሳታሚዎችና ሥራ አስኪያጆችን ሃሰተኛ ወሬዎች በማውራት፣ ለአመፅ የሚያነሳሱ ፅሁፎችን ለህዝብ በማድረስ፣ በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርአቱ ላይ አመፅ

Karte Äthiopien englisch

ለማስነሳት ሞክረዋል በሚል መክሰሱን ተከትሎ በርካታ ጋዜጠኞች ተሰደዋል። እነዚህን ጨምሮ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ የደረሰው እስርና ስደት የአለም አቀፍ የብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ማህበራት ዘንድ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ትችት እንዲሰነዘርበት አድርጓል። መቀመጫውን በሴኔጋል ዳካር ያደረገው የአፍሪካ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽንም መንግስት በእስር ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች እንዲፈታ የተሰደዱትም ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻች ጥሪ አቅርቧል። በአዲስ አበባ ተገኝተው መንግስትና ጋዜጠኞችን ያነጋገሩት በዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን የአፍሪቃ ዳይሬክተር ጋብሬል ባግሎ የተመለከቱት የመገናኛ ብዙሃን ይዘት ለመንግስት ያደላ መሆኑን ይናገራሉ።

”በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦችን በማንበብ ይዘታቸውን መገምገም ባልችልም በእንግሊዝኛ ከሚታተተሙት ጥቂቶቹን ለመመልከት እድል አግኝቼ ነበር።ብዙዎቹ ከመንግስት የተለየ አቋም አልተመለከትኩባቸውም።የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችንም አነጋግሪያለሁ።በጥቃቅን የተጠያቂነት ጉዳዮች ጋዜጠኞች ለእስርና ስደት እየተዳረጉ በመሆኑ ደስተኞች አይደሉም።ለዚህ መፍትሄው መንግስት መገናኛ ብዙሃንን ማሳተፍ ይኖርበታል።ሁለቱም ለአንድ ሃገር የሚሰሩ በመሆኑ የጋራ መግባባት መኖር አለበት።መንግስትም የመገናኛ ብዙሃንን ህግ በመረዳት ስራቸውን እንዲሰሩ ሊፈቅድ ይገባል።”

ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን የሙያውን ስነ-ምግባር በማክበር መስራትና መንግስትን መተቸት ይችላሉ የሚሉት ጋብሬል ባግሎ ውይይትና ንግግር እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ።

”ጋዜጠኞች የሙያውን ስነምግባር እንደማያከብሩ የኢትዮጵያ ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ባለስልጣናት ነግረውናል።እኛም በተጠያቂነት ስም ጋዜጠኞችን በሙሉ ወደ እስር ቤት መላክ እንደማይቻል ነግረናቸዋል።በአንድ ሃገር ማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ሊኖር ይገባል።ጋዜጠኞቹም ተስፋ ባይኖር እንኳ መንግስት የመገናኛ ብዙሃንን ጥቅም እስኪረዳ ድረስ የመንግስት አካላትን በማሳተፍ ውይይቱን ማሳደግ አለባቸው። የጋዜጠኛ ቦታ እስር ቤት ሳይሆን የዜና ቢሮው ነው።”

Symbolbild Zensur Pressefreiheit

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የጋዜጠኞች ማህበራት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን የሚደርስባቸውን እስርና ስደት አስመልክተው በተደጋጋሚ መንግስትን የሚተቹ መግለጫዎች አውጥተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የታሰሩት በጋዜጠኝነታቸው ምክንያት አለመሆኑን እና አንድም ጋዜጠኛም አለመሰደዱን በተለያዩ ጊዜያት ሲናገር ተደምጧል።በኢትዮጵያ ሊቋቋም ነው የተባለውን የሚዲያ ካውንስል እኛም እንደግፋለን የሚሉት ጋብሬል ባግሎ አሁንም የታሰሩት ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ይጠይቃሉ።

”ሰዎች ከመግስት አቋም ጋር ያለመስማማት እንዲያውም የመተቸት መብትም አላቸው።ይህ በየትኛውም ሃገር የተለመደ ነው።በእስር ላይ ያሉት ሰዎች መንግስት እንደሚለው ጋዜጠኞች ባይሆኑ እንኳ የታሰሩት ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለጻቸው ነው ማለት ነው።ሰዎች ሃሳባቸውን ስለገለጹ ሊታሰሩ ይገባል ብለን አናምንም።እናም የኢትዮጵያ መንግስት የታሰሩትን ጋዜጠኞች እንዲፈታ፣ የተሰደዱትም ተመልሰው ለሃገራቸው እንዲሰሩ እንዲፈቅድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።”

እሸቴ በቀለ

አርያም ተክሌ

EPPFGUARD GROUP MEMBERS IN ASCHAFFENBURG HAVE ORGANIZED AN ALL MEMBERS MEETING ON OCTOBER 11-2014

ለኢትዮጵያ ህዝቦች አርበኞች ግንባር ዘብ አባላት በሙሉ

TO ALL MEMBERS OF ETHIOPIAN PEOPLES PATRIOTIC FRONT GUARD,

gerom

የኢትዮጵያ ህዝቦች አርበኞች ግንባር ዘብ ለሁለተኛ ጊዜ በጀርመን / አሻፍንበርግ ከተማ ስብሰባ አዘጋጅቷል ።ስለሆነም ማንኛዉም የኢህአግዘብ አባላት በሙሉ በስብሰባው ላይ እንደትሳተፉ ጥሪያችንን እያቀረብን በዕለቱም አቶ ልዑል ቀስቅስ የኢ.ሕ.አ.ግ.ዘብ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን ጉደታ የኢ.ሕ.አ.ግ.ዘብ የጀርመን ጸሃፊ, አቶመራ አ ብርሃ የባየር ሊቀመንበር , አቶ ጸጋዬ መርጊያ በኢ.ሕ.አ.ግ.ዘብ የቅስቀሳ እና ፕሮፓጋናዳ ክፍል ሃላፊ ወ/ሪት ዘውድነሽ ንጋቱ በኢ.ሕ.አ.ግ.ዘብ የሄሰን ሊቀመንበር እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

ቀን ፤ ኦክቶበር 11 – 2014 ከቀኑ 13.00-16.00 ቦታ ፤ Platanenalle strasse ,1 ከሲቲ ጋለሪ ጎን (Aschaffenburg)
ለበለጠ መረጃ ፤ 015215385478 or 015213877998
EPPFGUARD GROUP MEMBERS IN ASCHAFFENBURG HAVE ORGANIZED AN ALL MEMBERS MEETING ON OCTOBER 11-2014 IN ASCHAFFENBURG.

WE INVITE ALL MEMBERS AND SUPPORTERS OF THE PARTY ON THE MEETING.INVITED GUESTS ARE MR.LUEL KESKIS CHAIRMAN ,MR.TILAHUN GUDETA SECRETARY , MR.TSEGAYE MERGIYA HEAD OF AGITATAION AND PROPAGANDA OF EPPFGUARD AND MISS ZEWEDENESH NEGATU CHAIRMAN OF EPPFGUARD IN HESSEN AND DATE : OCTOBER 11-2014 FROM 13.00-16-00 OTHERS.
PLACE : PLATANENALLE STRASSE , 1 NEAR TO CITY GALLERIE(ASCHAFFENBURG)FOR MORE INFORMATION CALL : 015215385478 or 015213877998

ያልታተመው “የሎሚ አዘጋጆች አጣብቂኝ!” ዘገባ

የሎሚ መጽሔት አዘጋጆች ከሀገር ከተሰደዱ አንድ ወር ያለፋቸው ሲሆን፤ ይህ ጽሁፍ ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ ማለትም ነሐሴ 17/2006 ዓ.ም ለህትመት ሊበቃ ከነበረው እና ከታገተው የመጨረሻ ዕትም (ከቁጥር 120) ላይ የተወሰደ ነው፡፡ ጽሁፉም መንግስት የመሰረተውን ክስ እና በወቅቱ የነበረውን ነባራዊ ስሜት የሚያንጸባርቅ ሲሆን፤ ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድም እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ አንባቢም ጽሁፉን በወቅቱ የነበረውን ስሜት ከግንዛቤ በማስገባት እንዲያነብ እንጠይቃለን፡፡ 

abonesh
ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ባለጠመንጃውን ወታደራዊ መንግስት በጠመንጃ ኃይል አሸንፎ የአራት ኪሎ ቤተ መንግስትን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ዜጎች በሃገሪቱ የይስሙላ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይዘረጋል የሚል ተስፋ አሳድረው ነበር፡፡ ሕዳር 29/1985 ዓ.ም የፀደቀው ሕገ መንግስት አንቀፅ 39ን ጨምሮ (መገንጠልን የሚፈቅደው) አወዛጋቢ ጉዳዮች የሰፈሩበት ቢሆንም፣ በአንቀፅ 29 የተካተተውን (ሃሳብን በነፃ የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት መብት) እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑ ይህንኑ ተስፋ ከፍ አድርጎታል ማለት ይቻላል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን የሀገሪቱ የበላይ ሕግ የሆነው ሕገ መንግስቱ ሃገሪቱን በሚገዛው ፓርቲና በሹማምንቱ እየተጣሰ፣ አፋኝ አዋጆችና ሕጎች እየጸደቁ ሲሄዱ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከእኛ በኋላ የዲሞክራሲ ጎዳና ጠረጋ የጀመሩት እንደ ቦትስዋና እና ጋና የመሳሰሉ የአፍሪካ ሀገራት በትክክለኛው መንገድ በመጓዛቸው የትና የት ጥለውን ሲሄዱ ገዢዎቻችን ግን ዛሬም “ዲሞክራሲ ሂደት በመሆኑ በአንድ ጀንበር አይመጣም” የሚለውን የተለመደ ዜማ መቀየር አልቻሉም፡፡ መንግሥት አጣብቂኝ ውስጥ ካስገባቸው መሠረታዊ የዲሞክራሲ ጎዳና ጥርጊያዎች አንዱ ሃሳብን በነፃ የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት አንዱ ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ በመጣው የመብት ጥሰቶች እጅግ አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ ከገቡት መሀል መጽሔታችን “ሎሚ” እና አዘጋጆቿ ይጠቀሳሉ፡፡

ይህ ዕትማችን ከአንባቢያን ጋር የምንገናኝበት የመጨረሻው ሕትመት ባይሆን መልካም ነበር፤ “ሎሚ” መጽሔት ከተመሠረተችበት ነሐሴ 2003 ዓ.ም አሁን እስካለንበት ነሐሴ 2006 ዓ.ም፣ ብዙ ራዕይ ሠንቃ ለሕትመት በበቁ 120 ዕትሞቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ የጥራት ደረጃዋን ጨምራ ስትጓዝ ቆይታለች፡፡ በጠበበው የነፃ ፕሬስ ምሕዳር ውስጥም ሆና የሚደርሱባትን ጫና ተቋቁማ ለሦስት ዓመት ዘልቃለች፡፡

“ሎሚ” የተለያየ አቋም ያላቸው ምሁራንና ባለሙያዎች በጥናት ላይ ተመርኩዘው ያቀረቧቸውን ትንታኔዎች አስተናግዳለች፤ ከራሱ ድምፅ ውጪ መስማት የማይፈልገው የገዢው ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊያቸው አቋማቸውን በሎሚ እንዲያንፀባርቁ የቀረበላቸውን ግብዣ በተደጋጋሚ ባይቀበሉትም ዜጐቹ አማራጭ መድረክ በመሆን አመለካከታቸውን፣ ሃሳባቸውንና አቋማቸውን በነፃ እንዲገልፁ ዕድል ፈጥራለች፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተነባቢነቷ በማደጉ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በወር ከ40 ሺህ ኮፒ በላይ ከሚያሳትሙ ሦስት የነፃው ፕሬስ ቀዳሚ መጽሔቶች ሎሚ አንዷ ሆናለች፡፡ ለ80 ሚሊዮን ህዝብ በወር 40 ሺህ ኮፒ ማሳተም ባያኩራራም፡፡

በነዚህ ጊዜያት በበርካታ ፈታኝ፣ አዳጋችና ተስፋ አስቆራጭ ሂደቶች ውስጥ አልፋለች፡፡ የባለስልጣናት ማስፈራሪያ፣ የደህንነቶች ማዋከብና ማሸማቀቅ፣ አዘጋጆቿ በተደጋጋሚ እየተከሰሱ ዋስትና እያስያዙ ከማዕከላዊ በሹማምንቱ በሚሰነዘር ዛቻና ሥጋት የተነሳ በማተሚያ ቤት እጦት መንገላታት… አብረውን የቆዩ በመሆናቸው “ተላምደናቸዋል” ማለት ይቻላል፡፡ ለአዘጋጆቹ በአንድ “የግል ባንክ በኩል የሚያማልል ዶላር በምንዛሪ በመላክ ከአሸባሪዎች ጋር ለማነካካት የተሰራውን ድራማ አዘጋጆቹ ለንዋይ ባለመንበርከክና ለሙያቸው ታማኝ በመሆን ገንዘቡን ባለመቀበል ፉርሽ ያደረጉበት አካሄድንም መጥቀስ አይከብድም፡፡ የመጽሔቱ አዘጋጆች ላይ ይደርስ የነበረው ማስፈራራት ውጤት ሳያመጣ ሲቀር ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ስልክ እየተደወለ “ይህን ሥራውን ካላቆመ ለሚደርስበት መከራ ተጠያቂ እንደሌለ እንድታውቁት” ዓይነት ዛቻዎች የፈጠሩት ሰቀቀንና ስጋትም እንደዋዛ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ለምርጫ 97 ኪሳራ የነፃው ፕሬስ ውጤቶችንና አባላትን ተጠያቂ ከማድረግ ቦዝኖ የማያውቀው ገዢው ፓርቲ በ1999 የግል ፕሬሶችን አንዴት “መዋጋት” እንዳለበት የያዘውን አቋም በሰነድ መልክ አዘጋጅቶ ለአመራሮቹ መበተኑ ይታወቃል፡፡ በገዢው ፓርቲ አመራርነት ውስጥ ቢገኙም የፕሬስ ነፃነት መሰበር ይኖርበታል ካሉ ከራሱ ሰዎች በደረሰን በዚህ ሠነድ ላይ “ጋዜጠኞችን ማሠር”፣ “ፕሬሱን ማገድ” በመፍትሄ አቅጣጫነት ሠፍሮ ተመልክተናል፡፡ ይህንንም ምርጫ 2007 ከመድረሱ በፊት “በአስተዳደራዊ” ውሳኔ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ከደረሱን መረጃ ተገንዝበነዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በፍትህ ሚኒስቴር፣ በብሮድካስት ባለስልጣናት፣ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ መ/ቤት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሎሚን ጨምሮ በስድስት የነፃው ፕሬስ ውጤቶች ላይ እየተወሰዱ ያሉ “ዘመቻዎች” ነገ የሚወሰደውን እርምጃ ከወዲሁ ጠቋሚ ናቸው፡፡ የቀደመውን ጊዜ አፈና ወደ ጎን ብለን ባለፈው ሐምሌ ወር የተወሰዱትን እርምጃዎች ብንቃኝ ከወዲሁ መልሱን በግልፅ እናገኘዋለን፡፡ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ጠ/ሚ/ር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ባሰሙት ንግግር “ሁሉንም ነገሮች አፅድተን ወደ ምርጫው እንገባለን” ማለታቸው ምርጫው ከመድረሱ በፊት ከነፃው ፕሬስ ላይ እርምጃ የመውሰጃ የመጀመሪያ ፊሽካ ነበር፤ ሐምሌ 3/2006 ዓ.ም ምሽት ኢቲቪ “ዶክመንተሪ” ብሎ ባቀረበው “ድራማ” በነፃው ፕሬስ ላይ “ዘመቻ ፀሐይ ግባት” እወጃ ተጀመረ፡፡ በማግስቱ ጠ/ሚ/ሩ “በሕጋዊ ሁኔታ የተመሰረተ ፓርቲ አባል መሆን ወይም በጋዜጠኝነት ከለላ መንቀሳቀስ ከሽብርተኝነት አያድንም” በማለት የታሰረ ጋዜጠኛ በሌለበት ሁኔታ ምን ሊፈፀም እንደታሰበ ተጨማሪ ምንጭ ሰጡ፡፡
ሐምሌ 7/2006 ዓ.ም ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሠራተኞች “ያለ ንግድ ፈቃድ ነው መጽሔት የምታትሙት”፣ በድንገት “ያለፉትን ዓመታት የሂሳብ ሠነዳችሁን ልታቀርቡልን ይገባል” የሚል ሠበብ በመስጠት፣ ሆኖም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ ከሃያ ባላነሱ መሣሪያ የታጠቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ታጅበው የ“ሎሚ” መጽሔት ቢሮን አሸጉ፡፡ ከቀናት በኋላ “ቢሮውን እንክፈት” ብለው ከመጡ በኋላም የሎሚ መጽሔትን ፋይል ወስደው መልሰው አሸጉት፡፡ ከቀናት በኋላ በየዕትሙ በመፅሔቱ ላይ ማስታወቂያ ያወጡ ድርጅቶች ለሎሚ ምን ያህል ብር ከፍለው ማስታወቂያ እንደሰሩ ከተጠቀሱት መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች እየተጠየቀ መሆኑን ገለፁልን፡፡ ከውስጥ አዋቂዎች በደረሰን መረጃም የግብር ቁልል እየተዘጋጀ መሆኑ ታወቀ፡፡ ሐምሌ 28/2006 ዓ.ም ደግሞ ፍትህ ሚኒስቴር ሎሚን ጨምሮ ስድስት የሕትመት ውጤቶች በፍርድ ቤት መከሠሣቸውን ገለጸ፡፡ የክስ መጥሪያ ሳይደርሳቸው የቆዩት አሳታሚዎችም የመዘጋጃ ጊዜ እንዳያገኙ በሚመስል መልኩ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ሁለት ቀን ሲቀራቸው መጥሪያው ደረሳቸው፡፡ ከነዚህ መሀልም የሎሚ መጽሔት አሳታሚ ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና ፕሬስ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ. ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ ናቸው፡፡ ሌሎችም ተከሳሾች እንዳሉ ለአቃቤ ሕግ ተገለፀ፡፡

የሆነው ሁሉ እንደሚሆን ከአስተማማኝ ምንጮች መረጃ የደረሳት ሎሚ ሊፈፀም የታቀደውን በርዕሰ አንቀጿ በመጠቆም፣ መፍትሄው ግን ይህ እንዳይደለ ለማመላከት ጥራለች፡፡ ለአብነት ያህል ከአንድ ወር በፊት ሐምሌ 12/2006 ለንባብ የበቃችው “ሎሚ” በርዕሰ አንቀፅዋ የመንግስትን አቅጣጫ ተንብያ ነበር፡፡
አሁን የፕሬሱ ህልውናና የሎሚ አዘጋጆች አጣብቂኝ በሆነ አደገኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከአስተዳደራዊ ውሳኔ መፅሔቷ ከመታገድ፣ አዘጋጆቿም አስራ ስምንት ዓመት እና ከዚያም በላይ በሚያስፈርደው ፀረ ሽብርተኝነት ተከስሰው እንደሚቀጡ ከስጋት ያለፉ ምልክቶች በርክተዋል፡፡ ከገዢው ፓርቲ ጋር ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂዎችም “ሁለት ምርጫ” እንደቀረበልን፣ እስካሁን አለመረዳታችንም አሳስቧቸዋል፡፡ ምርጫው ሁለት እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡ “ጋዜጠኞቹ ታስረው የመፅሔቷ ሕትመት ይቋረጣል”፤ አሊያም ደግሞ “ወደ ስደት እንድታመሩ “የማርያም መንገድ” ተከፍቶላችኋል” የሚሉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሁለቱን መምረጥ አይቻልም፡፡ ምርጫው አንድ ነው፡፡ የሎሚ መጽሔት ክስ ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል፡-
ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወ/ችሎት
አዲስ አበባ
ከሳሽ፡- የፌዴራል አቃቤ ህግ
ተከሳሾች፡- 1ኛ/ ግዛው ታዬ ወርዶፋ
አድራሻ ጉለሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 03
2ኛ/ ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አድራሻ ጉለሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 03
1ኛ ክስ
ወንጀሉ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ለ፣ 34/1/44/1/ እና 257/ሀ እና ሠ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡፡
የወንጀሉ ዝርዝር ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ወንጀሉና ወንጀሉ የሚሰጠውን ውጤት በመቀበል መንግስት የሚለወጠው ሕገ-መንግስታዊ በሆነ መርህ በምርጫ ብቻ ሆኖ እያለ ኢ-ሕገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ በአመፅ ስርዓቱን ለማፍረስ በማሰብ 1ኛ ተከሳሽ ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር በስራ አስኪያጅነት፣ 2ኛ ተከሳሽነት በተጠቀሰው ድርጅት “ሎሚ” በሚል እየታተመ በሚወጣ መፅሔት በቅፅ 3 ቁጥር 109 በግንቦት 2006 ዓ.ም በወጣው ዕትም በገፅ 3 ላይ “በአለም በጨቋኝነቱ አቻ የማይገኝለት የሚዲያ ምህዳር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በገፅ 3 ላይ ሰብዓዊ መብት የሚባል በኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ በሙሉ ተረስቷል፡፡ የምንገኝበት አለም የመራጮች እና የለውጥ ማዕበሎች የሰፈነበት በመሆኑ ኢትዮጵያን በቀጣይ ዓመት በሚደረገው አገራዊ የአጠቃላይ ምርጫ በመንተራስ ለበርካታ አመታት ከዘለቀው የግፍ፣ የጭቆና አገዛዝ ለማላቀቅ የማይቀረውን የለውጥ ማዕበል ለማምጣት ራሳቸውን ለተጠናከረ ህዝባዊ አመጽ ማደራጀት መጀመራቸው ሊበረታታ የሚገባው ነው” በማለት በማሳተም 2007 ዓ.ም ምርጫ ከመካሄዱ በፊት አዋጪ የሚሆነው ለአመጽ መደራጀት፣ የኃይል ተግባር መፈጸም ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን በመጥቀስ ሕትመቱን ያሳተሙና ለህዝብ እንዲደርስ ያደረጉ በመሆኑ፤ በአጠቃላይ ተከሳሾች ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ከሕገመንግስታዊ ሥርዓት ውጪ በአመጽ መንገድ ለማፍረስ
ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ለአመፅ የሚያነሳሱ ፅሁፎች አትመው በማውጣት በዋና ወንጀል አድራጊነት ቅስቀሳ ያካሄዱ በመሆኑ በፈፀሙት መገፋፋት እና ግዙፍ ያልሆነ መሰናዳት ወንጀል ተከስሰዋል፡፡
2ኛ ክስ
ወንጀሉ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 (1) ሀ እና ለ፣ 34/እና 44/1፣ 486/ሀ እና ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡፡
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን 1ኛ/ ተከሳሽ ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ በመሆን፣ 2ኛ/ ተከሳሽ በተጠቀሰው ድርጅት ሎሚ በሚል እየታተመ የሚወጣ መፅሔት ላይ በሃሰት ወሬዎችን በማሳተም ህዝብን ለማነሳሳት በማሰብ በቅፅ 3 ቁጥር 91 ከጥር 24 እስከ የካቲት 1 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው ዕትም በገጽ 6 ላይ “የአሸባሪነት ፈርጦች” በሚል ርዕስ ስር “ኢህአዴግም ከማን አንሼ በሚል ስሜት ተቃራኒ ሃሳብ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን፣ ለስልጣኔ /ለወንበሬ/ ያስጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን እያደነ በአሸባሪነት ስም ወህኒ ያወርዳቸው ከጀመረ ሰንብቷል” በሚል የሀሰት ዘገባ በማሳተሙ እንዲሁም በገፅ 23 ላይ “የኢህአዴግ የሽብርተኝነት መመዘኛ ምንድነው” በሚል ርዕስ “ኢህአዴግ” የህዝብ ተቀባይነት ያገኘ አይመስለውም፡፡ ሕዝብ የተቀበለውና አምነዋለሁ የሚለው ሰው ለኢህአዴግ ጠላት ነው፣ ሽብርተኛ ተብሎ ይከሰሳል” በማለት በሽብር ሕግ ተከስሰው የተቀጡ ተከሳሾች በሕዝብ የሚወደዱ እና ለገዢው ፓርቲ ተቀናቃኝ በመሆናቸው ብቻ በግፍ የተቀጡ ንፁሀን እንደሆኑ የሚያስመስልና ሃሰተኛ ወሬ አትመው በማውጣታቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በሀሰት ወሬዎች ህዝብን ማነሳሳት ወንጀል ተከስሰዋል፡፡
የማስረጃ ዝርዝር
የሰነድ ማስረጃ
1. ሎሚ መፅሄት ቅፅ 3 ቁጥር 91 ገጽ 1፣ 6 እና 23 ገፅ 03 ገጽ ኮፒ
2. ሎሚ መፅሄት ቅፅ 3 ቁጥር 109 ገጽ 1፣ እና 3 03 ገፅ ኮፒ
3. ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግል/ ማህበር በንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት የሰጠ የንግድ ፈቃድ ኮፒ 01 ገጽ ይላል ከፍትህ ሚኒስቴር የተላከልን የክስ ዝርዝር፡፡
የአፍርሮ ታይምስ ጋዜጣ እና የጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው የክስ ዝርዝር ደግሞ የሚከተለውን ይመስላል፤
ለፌዴራል1 የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ወ/ችሎት
አዲስ አበባ
ከሳሽ፡- የፌዴራል አቃቤ ህግ
ተከሳሾች፡- 1ኛ/ ቶማስ አያሌው ተካልኝ፤
አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 136
2ኛ/ ግዛውና ቶማስ ኢንተርቴይመንት የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 136
1ኛ ክስ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ለ፣ 34/1/44/1/ እና 486/ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡፡
የወንጀል ዝርዝር
ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን አንደኛ ተከሳሽ ግዛውና ቶማስ ኢንተርቴይመንት የፕሬስ ኃ/ የተ/የግ/ማህበር ሥራ አስኪያጅ በመሆን በሁለተኛ ተከሳሽነት በተጠቀሰው ድርጅት አፍሮ ታይምስ በሚል እየታተመ በሚወጣ ጋዜጣ ላይ በሃሰት ወሬዎችን በማሳተም ህዝብን ለማነሳሳት በማሰብ ህዝቡ በሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ አመኔታ እንዳይኖረው፣ ጥርጣሬ እንዲገባው ለማድረግ በማሰብ በቁጥር 9 ሚያዝያ 21 እና 22 2006 ዓ.ም በወጣው የጋዜጣ ሕትመት በገጽ
1 ላይ “ልዩ ኃይሎችና መከላከያ ሠራዊት ተፋጠዋል” በሚል ርዕስ ስር “ቀደም ባሉት ጊዜያት በጋምቤላ ክልል ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የፈለገውን ሰው ሲያስር፣ ሲገድል፣ ሴቶችን አስገድዶ ሲደፍር ቆይቷል፡፡ ይህም የሰራዊቱን ስርዓት አልበኝነት እና ሕገ-ወጥ ድርጊት ለማስቆም የሞከረ መንግስታዊ አካል አልነበረም” በማለት አገሩንና ሕገ መንግስቱን በመጠበቅ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ እና መንግስታት በመልካም ስነ-ምግባር ተግባሩ እያከናወነ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህዝቡ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ፣ ጥርጣሬ እንዲገባው ለማድረግ ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ሐሰተኛ ወሬዎችን በመንዛትና ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል ተከስሰዋል፡፡
የሰነድ ማስረጃ
የሰነድ
1.ቅፅ 1 ቁጥር 9 ሚያዝያ 21 እና 22 2006 ዓ.ም የወጣውን አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ 02 ገፅ ኮፒ፣
2.በንግድ ሚ/ር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ በአንደኛ ተከሳሽ ስም ዳይሬክቶሬት የተሰጠ የንግድ ፈቃድ ኮፒ 01 ገፅ ኮፒ ሲል ይደመድማል፡፡

ፌስቡክ ወርሃዊ ክፍያ ሊጠይቅ ነው

ከ1 ነጥብ 317 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስቡክ የተሰኘው ማህበራዊ ድረገፅ ከህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ተጠቃሚዎች በየወሩ ሶስት የአሜሪካን ዶላር (60 ብር ገደማ) እንዲከፍሉ ወሰነ።

facebook-addiction
የፌስቡክ መሥራችና ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ማርክ ዙክምበርክ ከትላንት በስቲያ በአሜሪካን ሀገር በጉዳዩ ላይ ይፋዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ለወርሃዊ ክፍያው የሰጡት ምክንያት የአስተዳደራዊ ወጪ እየናረ መምጣትን ነው።

ፌስቡክ አሁን ካሉት 1 ነጥብ 317 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች 75 በመቶ ያህሉ በየወሩ የአባልነት 3 ዶላር ሊሰበስብ እንደሚችል የገመተ ሲሆን ይህም ገንዘብ በዓመት እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኝለታል።

የፌስቡክ ቃለአቀባይ ሚስተር ፓውል ሆናነር ስለጉዳዩ ለሲ.ኤን. ኤን የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት አስተያየት በየቀኑ ፌስቡክን በ100ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚቀላቀሉ አስታውሰው የወርሃዊ የአባልነት ክፍያው መጣሉ ፌስቡክም ራሱ እንዳላስደሰተው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የፌስቡክ አካውንት ያላቸው ከ902 ሺ 440 በላይ ያህል ዜጎች መሆናቸውን መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን በሀገሪቱ ካለው የውጪ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ ዶላር በባንክ ማስተላለፍ ስለማይቻል በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የማኅበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ከአገልግሎቱ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ የብዙዎች ግምት ሆኗል።

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች – ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Temesgen-Desalegn41

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ
ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል
አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር
ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ለጥቆ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞው
የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በኤምባሲው ግቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁት የዕራት ግብዣ ላይ (ግንቦት 19/2001
ዓ.ም) ድንገት ተገናኝተን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤ ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው፣ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ግንቦት 7 እና እነጀነራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ዕለት እንደ አፄ ኃይለሥላሴ የክብር ዘብ፣ ከሽመልስ
ከማል ጋር በረከት ስምዖንን ግራና ቀኝ አጅቦ በተገኘበት ወቅት ነው፡፡ በተቀረ በመንግስት ሥልጣን ሲገለጥ ብዙም
አላስተዋልኩም፡፡ ከዚህ ይልቅም ኢህአዴግነቱን ለማሳየት የሞከረበትን አንድ ገጠመኝ አስታውሳለሁ፤ ይኸውም “የፍትሕ”
ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው እና አሁን በስደት ሀገር የሚገኘው ባልደረባዬ ማስተዋል ብርሃኑን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባለው
ቢሮው ድረስ በመጥራት ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ከሰነዘረበት በኋላ፣ ዛሬ የቀድሞ ጓዶቹ ሥራዬ ብለው እንደቀጠሉበት አይነት
በጋዜጣው ላይ የሀሰት ውንጀላ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ከኃላፊነቱ ራሱን እንዲያገል አስጠንቅቆት እንደነበር ከራሱ ከባልደረባዬ
ማስተዋል አንደበት ሰምቻለሁ፡የሆነው ሆኖ አቶ ኤርሚያስ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፉ በተመላኪው ሰው አመራር “ሁሉን
አዋቂነት” ላይ የቆመው መንግስት ምን ያህል በጠባብ የወንዝ ልጅነት የተተበተበ እና በዘራፊ ባለሥልጣናት የተዋቀረ
እንደሆነ በስፋት ተርኮልናል፡፡ በተለይም ሙስና እና የህወሓት ካድሬዎች የበላይነትን በተመለከተ በማስረጃ
አስደግፎ በተዋበ ስነ- ጽሑፋዊ ቋንቋ ዘርዝሮልናል (በርግጥ“የጋዜጠኛው” አሊያም “የደራሲው ማስታወሻ” የሚያነቡ እስኪመስልዎ

ድረስ የመጽሐፉን አርትኦት ተስፋዬ ገ/አብ ወይም የተስፋዬ ብዕር ተፅእኖ ያለበት ደራሲ ብዙ እንደለፋበት በግልፅ ማስታወቁን መካድ አይቻልም)፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ዛሬም
ከአገዛዙ ጋር የተሰለፉ የቀድሞ ጓዶቹ ለህሊናቸው ሲሉ በድብቅ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ደፍረው እንዲያጋልጡ
በጠየቀበት ብዕሩ፣ የራሱንም ጥፋቶች እና በትዕዛዝም ይሁን በግል ተነሳሽነት በደል ያደረሰባቸውን ንፁሃን በይፋ ይቅርታ
ቢጠይቅ መልካም ነበር፤ አሁንም ቢሆን ለዚህ አይነቱ ቅንነትና በጎ አርአያነት ገና አልረፈደም፡፡ ርግጥ ነው የስደት ምርጫው

ባደረጋት ሀገረ-አሜሪካ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ድርጅቱ ኢህአዴግ ይሰራው በነበረው ሕገ-ወጥ ድርጊትና የጭካኔ እርምጃ
አልፎ አልፎ ቢሮውን ዘግቶ እንደሚያለቅስ፣ ባስ ሲልም ህሊናውን ቆጥቁጦት ታምሞ አልጋ ላይ እንደሚውል በመግለፅ የራሱን
ጲላጦሳዊነት ለመስበክ መልፋቱን ስናስተውል፤ ጸሐፊው የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሪ በነበረበት ወቅት የበደለውን ሕዝብ ይቅርታ
የመጠየቅ ዝግጁነትም ሆነ ፍላጎት (ቢያንስ በዚህ ሰዓት) የለውም ብለን ማዘናችን አይቀርም፡፡
እንዲሁም ከሀገር እንዲወጣ የተገደደበት ምክንያት ተብሎ ስለተናፈሰው ወሬ ትንፍሽ አለማለቱ በበኩሌ አስተዛዛቢ ሆኖ
አግኝቸዋለሁ፤ በወቅቱ የስደቱ መነሾ ተደርጎ በከተማዋ በስፋት የተናኘው፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቹ እና “የግንቦት 7 አባላት
ናችሁ” የተባሉ ግለሰቦች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ለአንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ “ሙከራው መፈንቅለ መንግስት ነው” የሚል
መግለጫ በመስጠቱ እንደነበረ ነው፤ በዚህም እጅግ የተበሳጨው ጠ/ሚኒስትሩ፣ አለቃው በረከት ስምዖን ላይ ጭምር የጭቃ-
ጅራፉን ከማወናጨፉም በላይ፣ ኤርሚያስን ያለ ሥራ እንዳንሳፈፈው መወራቱን አስታውሳለሁ፤ ይህንን መረጃ አምኖ
ወደመቀበሉ የሚገፋን ደግሞ በዚያው ሰሞን መለስ ዜናዊ ራሱ በቴሌቪዥን ቀርቦ ‘…የተደረገው ነገር እዚህ ግባ የሚባል
አይደለም፣ ከአልቃይዳና አልሸባብ ጋር ሲነፃፀሩ የእኛዎቹ አማተሪሽ (ልምድ አልባ) ናቸው’ እያለ የሚኒስትር ዴኤታውን ንግግር
ለማስተባበል ሲዳክር የመስተዋሉ እውነታ
ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ከዚህ ግልፅ ሹክሹክታ በኋላ በትምህርት ሰበብ ሀገር ለቅቆ መሰደዱ የአንድ ሰሞን የከተማ ወሬ ሆኖ
ነበር፡፡ እነሆም ወንድም ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ጉዳይ ዳጉስ ባለው መጽሐፉ ውስጥ ሽራፊ ገፅ ሊሰጠው አለመቻሉ እዚህ ጋ
በትዝብት እንዳነሳው መገደዴን በትህትና እገልፃለሁ፡፡ አሸንፈሀልና በዝብዘህ ብላ!
ህወሓት-ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ በግርማ ብሩ አነጋገር “ደሀ-ዘመም” (በመጽሐፉ የተጠቀሰ) እንደሆነ
ለማሳመን የሚሞክርበት ብልጠት፣ ራሱን ለሙስና ፅዩፍ አስመስሎ በማቅረብ ነው፤ ይህን አይነቱን ስሁት አመለካከት በሕዝብ
ውስጥ ለማስረፅ ጥቂት የፖለቲካ መታመን-ጉድለት ጥርስ ያስነከሰባቸውን ጉምቱ ጓዶቹን “ሙሰኛ” በሚል ወንጅሎ በወህኒ
የቃየል መስዋዕት ሲያደርጋቸው ተስተውሏል፤ እርምጃውንም በፓርላማው መድረክ ሳይቀር ሲኩራራበትና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ
ሲያውለው ተመልክተናል (ከሩቁ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ስዬ አብርሃ፤ ከቅርቡ
ደግሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ፣ የደህንነት ኃላፊው ወ/ስላሴ እና መሰል ባለሥልጣናትን እስር ልብ ይሏል)፡፡
የሚኒስትር ዴኤታው መጽሐፍ፣ መለስ እና ጓዶቹ ካደነቆሩን በግልባጩ ‘የዘረፋ መሪዎች’ የሚላቸው ሁለት የህወሓት ሰዎች፣
በባላንጣነት ተሰልፈው እንዴት የሀገር ሀብት ለመቀራመት ይሽቀዳደሙ እንደነበር አጋልጧል፤ አዜብ መስፍንን እና አርከበ
እቁባይን፡፡
“እነ አርከበ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው ጥቂት ወራት በፊት በህወሓት ውስጥ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡
የህወሓት ዳግም መከፋፈል ምክንያት ደግሞ በወ/ሮ አዜብ እና አርከብ ቡድኖች መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው ነበር፡፡
መነሻው መረን የለቀቀ የጥቅም ግጭት ሲሆን ዓላማው የህወሓት ኢንዶመንቶችን መቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነበር፡፡” (ገፅ 25)
ከዕለት ተዕለትም ይህ ሁኔታ የተካረረ ልዩነት ፈጥሮ፣ ፖለቲካዊ ቁመና በመላበሱ፤ አርከበ እቁባይ፣ ህወሓት መገፋቱን እና መለስ
በበረከት በኩል የድርጅቱን ካድሬዎች እያስጠቃ ነው የሚል ክስ ከማጎኑም ባሻገር፤ ወደኋላ ተጉዞ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት
የተጠናቀቀበትን መዛግብት አቧራ በማራገፍ፣ ተጠያቂነቱን ከፍ ሲል ወደ መለስ ዜናዊ፣ ዝቅ ሲል ደግሞ ወደ በረከት ስምዖን
በመወርወር ማጠቋቆሩ ያመጣውን ውጤት እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- “በሂደት አቶ አርከበ ይዞ ብቅ ያለው መቀስቀሻ የካድሬውን
እና አባሉን ቁስል የነካ በመሆኑ ተቀባይነት አገኘ፡፡ በትግራይ ፕሮፓጋንዳ እና ድርጅት ተመድበው የሚሰሩ ቁልፍ ካድሬዎች
ተቀላቀሉት፡፡” (ገፅ 26)
ይህንን ተከትሎ ወትሮም በደፋር ንግግሯ የምትታወቀውና አንጋፋ ታጋዮችን ሳይቀር በቁጣ የምታስረግደው ቀዳማዊት እመቤት
የሰነዘረችው የመልስ ምት በመጽሐፉ ላይ እንደሚከተለው ሰፍሯል፡- “ወ/ሮ አዜብ በበኩሏ አርከበና ቡድኖቹ በሙስና
ተዘፍቀዋል የሚል ክስ ይዛ ብቅ አለች፡፡ አርከበ በሚስቱና ቤተሰቦቹ የያዘውን ንብረት በመረጃ አስደግፋ አራገበች፡፡ ላውንደሪ
ቤት፣ ፋርማሲ፣ ክሊኒክ፣ ሱፐር ማርኬት፣ መስታወት ማስመጣትና መሸጥ…፡፡ በትግራይና አዲስ አበባ የተፈጠሩት አዳዲስ
ባለሀብቶች የአርከበና ቡድኖቹ እንደሆኑ በስም ዘርዝራ አሳወቀች፡፡ ስዬ በታሰረበት የሌብነት ወንጀል አርከበ እጁ እንደነበረ፣
በተለይም የስዬ ወንድም ለገዛቸው በርካታ መኪናዎች ቅናሽ እንዲያገኝ ማግባባቱን የፈፀመው አርከበ መሆኑን አጋለጠች፡፡” (ገፅ
26)
እዚህ ጋ አቶ ኤርሚያስ ‹‹አርከበ በሚስቱና በቤተሰቦቹ…›› ስለያዛቸውና አዜብ መስፍን በስም እየጠራች አጋለጠች ስላላቸው
የንግድ ድርጅቶች በስም አንድ በአንድ እየጠቀሰ ይፋ ቢያደርግልን ኖሮ መረጃው ምሉዕ (ከ‹ኮሪደር ሀሜት› የዘለለ) ይሆን ነበር
ብዬ አስባለሁ፡፡ ከሁሉም ቁጭታችንን የሚያንረው፣ ደራሲው የንግድ ተቋማቱን ባለቤቶች በስም መጥቀስ እየቻለ (አቀራረቡ
ለይቶ እንደሚያውቅ ያሳብቃልና) በደፈናው ያለፈው ወንጀል (ሕገ-ወጥ ዘረፋ) ይህ ብቻ አለመሆኑ ሲገባን ነው፤ በዚሁ ገፅ ዝቅ
ብሎ የሰፈረው እንዲህ ይላልና፡- “በወቅቱ ሁለቱም ቡድኖች ‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት፣ የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም› የሚል
ፖሊሲ ቀርፀው የህወሓት ባለሀብቶችን ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህ ፖሊሲ ምክንያት በአንድ ሌሊት ከሹፌርነት ወደ
አስመጪና ላኪነት፣ ከጋራዥ ሰራተኛነት ወደ መኪና ዕቃ መለዋወጫ አስመጪነት፣ ከታጋይነት ወደ ሪል እስቴት ባለቤትነት፣
ከወታደርነት ወደ ፋብሪካ ባለቤትነት፣ ከህወሓት ምድብተኛ ካድሬ ወደግል ባንክ ከፍተኛ አክሲዮን ባለድርሻነት የተቀየሩ
ሰዎችን መስማት የተለመደ ነበር፡፡” (ገፅ 26) እነዚህ ‹‹ተላላኪ›› እና ‹‹ሹፌር›› ባለሀብቶችን በስም አለመጥቀሱ ያስቆጫል፤
በተለይም ለመረጃው ከነበረው ቅርበት አኳያ ይሄ ጉዳይ እንደተራ ነገር በደፈናው ባይታለፍ ኖሮ፣ ለተቃውሞው ስብስብ
በዋናነት ሁለት ታላላቅ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኘቱ አይቀሬ ነበር፡የመጀመሪያው በጅምላ ህወሓት፣ መላው ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪን ተጠቃሚ

ያደረገ የሚመስለው ኢትዮጵያዊ ስህተቱን
እንዲያጠራ ስለሚያስችለው፣ በድርጅቱ እና በብሔሩ መሀከል ያለውን ነጭና ጥቁር ልዩነት እንዲያስተውል ይረዳው ነበር፤
ሌላው ደግሞ እነዚህን በፖለቲካ ውሳኔ ወደሀብት ማማ የወጡትን ግለሰቦች የትላንት ማንነት አብጠርጥሮ የሚያውቀው
ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ… የዘረፋ ወንጀላቸውን ተፀይፎ በኢኮኖሚያዊ ማግለል (ሸቀጦቻቸውን ባለመግዛትም ሆነ
አገልግሎታቸውን ባለመጠቀም) በተቃውሞ ጎራ እንዲሰለፍ ገፊ-ምክንያት ይሆነው ነበር የሚለው ጭብጥ ነው፡፡ ‹‹የመለስ
ትሩፋቶች›› መጽሐፍ በሀገሪቱ ውስጥ ከመጋረጃው ጀርባ ስለተፈፅሙ ህልቆ-መሳፍርት ያሌላቸው አሳፋሪ የህወሓት ሕገ-ወጥ
ድርጊቶች እና እብሪቶችን ተንትኖ አስነብቦናል፡፡ ከእነዚህ መሀልም የስምንቱ ኮሎኔሎች ‹‹ጀብድ››ን እዚህ ጋ መጥቀሱ አግባብነት
አለው ብዬ አምናለሁ፤ ከ268-269 ባሉ ገፆች እንደተተረከው፣ በምርጫ 97 ማግስት በአንዱ ዕለት በወታደራዊ የደንብ ልብስ
የተንቆጠቆጡ ስምንት ከፍተኛ መኮንኖች በሶስት ሄሌኮፕተር ተሳፍረው አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ፤ በቀጥታም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ወደነበረው አባተ ስጦታው ቢሮ በማምራት፣ መሬት እንደሚሰጥ መረጃ ደርሷቸው ከጦር
ግንባር እንደመጡ ይነግሩታል፤ እያንዳንዳቸውም ‹‹ዘመቻ ፀሀይ ግባት የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ኃየሎም አርአያ የቤት ማሕበር››፣
‹‹ዛላአንበሳ የቤት ማሕበር››… የሚል እና መሰል የማህደር ስያሜ ያላቸው የአስራ ሁለት መኮንኖች ስም ዝርዝርና ፊርማ የያዘ
ወረቀት ይሰጡታል፤ እንደ ብራ መብረቅ ድንገት ባጋጠመው ክስተት ክፉኛ የተረበሸው ከንቲባም እንዲህ ያለ መመሪያ
እንዳልወረደ ለማስረዳት ሲሞክር፣ ለዚህ ዓይነቱ እሰጥ-ገባ ጊዜ ያልነበራቸው የጦር አበጋዞቹ አብረቅራቂ ሽጉጦቻቸውን
በመምዘዝ ግንባሩ ላይ ደቅነው በወቅቱ ፋሽን በነበረው ኢህአዴጋዊ ፍረጃ ‹‹የቅንጅት ተላላኪ መሆንህን ደርሰንበታል››፣
‹‹ኢህአዴግ እንዲሸነፍ ያደረጋችሁት እንዳንተ ያሉ ሰርጎ-ገቦች ናቸው››፣ ‹‹እዚሁ ደፍተንህ እንሄዳለን››… የሚሉ ማስፈራሪያዎችን
አዥጎድጉደው በማስጠንቀቅ ነፍስ-ውጪ፣ ነፍስ ግቢ ወጥረው ይይዙታል፤ ይህን ጊዜ የህወሓት አባል የሆነው ምክትል ከንቲባው
ነጋ በርሔ፣ የአባተን ቢሮ በርግዶ ሳይታሰብ ዘው በማለቱ፣ አንደኛው ኮሎኔል ያነጣጠረውን መሳሪያ ከአይን በፈጠነ ቅፅበት
አዙሮ ይደቅንበታል፡፡ ሁኔታውን ከጉዳይ ያልጣፈው ነጋ በርሔም ባለሽጉጦቹን የጦር አበጋዞች በባዶ እጁ እንዲህ ሲል
ተጋፈጣቸው፡-
“ነፍጥ ከእናንተ በፊት አንግበን ተራራ ደርምሰናል፡፡ የምታስፈራሩትን ሂዱና ሌላ ቦታ አስፈራሩ!”
ከፍተኛ መኮንኖቹም በድንጋጤ መሳሪያዎቻቸውን በመዘዙበት ፍጥነት ወደአፎቱ መልሰውና የምክትል ከንቲባውን የስድብ
ውርጅብኝ በፀጥታ አዳምጠው ሲያበቁ፣ አባተን ይቅርታ እንዲጠይቁት ይታዘዛሉ፤ እንዲያ በጥንካሬያቸው ለማንም የሰው ልጅ
የማይበገሩ መስለው ሲንጎማለሉ የነበሩት ቆፍጣናዎቹ ኮሎኔሎች ባንዴ እንደፊኛ ተንፍሰው በፍርሃት የታዘዙትን ይፈፅማሉ፤
ከዚህ በኋላም ህወሓቱ ነጋ በርሔ በተረጋጋ አንደበት ዋናው ከንቲባውም ጭምር እንዲሰማ ድምፁን አጉልቶ የሚከተለውን
‹‹ምርጥ›› ምክር ለገሳቸው፡ –
“ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ጥያቄያችሁን ብታቀርቡ ኖሮ አባተ እንኳን ቤተሰባችሁን ጥላችሁ ግንባራችሁን ለጥይት
ለምትሰጡት ቀርቶ ለሌላውም አይጨክንም፡፡ ያውም ከቀናት በኋላ ጠላት (ቅንጅት) ተረክቦ ለሚዘርፋት አዲስ አበባ!” (ገፅ
255) ከንቲባውም መሬቱን ፈቀደ፤ ነጋም ወደ መቀሌ እንዲዘዋወር ተደርጎ፣ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴን እና የትግራይ ክልል
ካቢኔን ተቀላቀለ፤ ከጊዜ በኋላም በበረከት ስምዖን በተመራ ግምገማ ላይ በአስቸኳይ አዲስ አበባ መጥቶ ይህንን ጉዳይ
እንዲያስረዳ ቢጠየቅ አሻፈረኝ ብሎ ይቀራል፡፡ ደራሲውም ‹‹ዘመን አለፈና አዲሱ ለገሰን ለማገዝ ኢህአዴግ ቢሮ የሥልጠና
ማዕከል በምክትል ሚኒስትርነት ማዕርግ ተመደበ›› ሲል የሆሊውድ ፊልምን የሚያስንቀውን ታሪክ ይደመድማል፡፡ በርግጥ
አባተም ቢሆን ይህ አስፈሪ ገጠመኙ እንደድንቅ ቃለ-ተውኔት ሁሉ፣ በህወሓት መሪዎች ተደርሶ በኮሎኔሎቹ እና በነጋ የተተወነ
መሆኑን ለመረዳት በርካታ ወራት እንደፈጀበት
ተጠቅሷል፡፡
በሌላ ምዕራፍ ደግሞ፤ በምርጫው ቀን እኩለ ሌሊት ተቋቁሞ፣ በአርከበ እቁባይ እና በጄነራል ታደሰ ወረደ እንዲመራ የተደረገው
‹‹የፖለቲካ ፀጥታ ጥምር ኮሚቴ››፣ ከ1978 ዓ.ም በፊት ወደ ትግል የገቡና ማዕረጋቸው ከኮሎኔል በላይ የሆነ የህወሓት መኮንኖች
ቦሌ ላይ መሬት እንዲያገኙ ማመቻቸቱን አስነብቦናል፡፡ በአናቱም፣ ከኮሎኔል በታች ያሉ የህወሓት ታጋዮች በሌሎች ማስፋፊያ
ከተሞች መሬት ማግኘታቸውን ተከትሎ የተፈጠረውን ሁኔታ ሚኒስትር ዴኤታው እንዲህ ያወጋናል፡- “…ወሬው ባድመና ጾረና
ጦር ግንባር ድረስ ተዳረሰ፡፡ ወታደራዊ መኮንኖቹ ምሽጋቸውን እየለቀቁ በጦር ሂሊኮፕተሮች ጭምር እየተሳፈሩ አዲሳባን
ወረሯት፡፡ የክፍለ ከተሞች ግቢ አቧራ በጠጣ የኮከብ ጋሻና ጦር ክምር የተሸከመ ካኪ ተጥለቀለቀ፡፡” (ገፅ 255-256) ዘመነኛው
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ‹‹…አንዳንድ እንሰሳት ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል ያልተፃፈ ሕግ ማደሩን ከውስጥ-አወቅ ምስክርነት
የምንረዳው ከህወሓት ውጪ ያሉት ኢህአዴግን የመሰረቱ ድርጅቶች የአመራር አባላት ብቻ የወሰዷትን መሬት በግምገማ
እንዲመልሱ መገደዳቸው በዚሁ መጽሐፍ መስፈሩን ስናስተውል ነው፡፡ በወቅቱም በግምገማው ፊት-አውራሪ በረከት ስምዖን
የተዘጋጀ ‹‹ከምርጫው በኋላ የድርጅታችንን ስም ያጎደፉና የሕዝቡን ቅሬታ ያባባሱ ተግባራት›› የሚል ሃያ ገፅ ሰነድ የመነሻ ሃሳብ
ሆኖ ቀርቦ ነበር፤ የግምገማው ውጤትም የተዘረፈ መሬት ማስመለሻ ፎርምን ህወሓት ያልሆኑ ከ600 በላይ የኢህአዴግ
ካድሬዎች እንዲሞሉ አስገድዶ ተጠናቅቋል፡፡
ለአብነትም ደራሲው ‹‹ለታሪክ የተቀመጠው የይቅርታ ፎርም›› ብሎ በመጽሐፉ ያሰፈረውንና በአንድ የብአዴን አመራር
የተሞላውን እንደወረደ ልጥቀሰው፡- “ለቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር እኔ ህላዊ ዮሴፍ ድርጅቴ ኢህአዴግና መንግስት
የጣለብኝን አደራና ኃላፊነት ወደጎን በመተው ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የመሬት ወረራ ላይ በመሰማራት አንድ መሬት ወስጃለሁ፡፡
በመሆኑም ይህን ያለአግባብ የወሰድኩትን መሬት አስተዳደሩ እንዲረከበኝ በማክበር እጠይቃለሁ፡፡ ድርጅቴ ኢህአዴግና በእሱ
የሚመራው መንግስትም ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ከእንግዲህ ወዲያ በየትኛውም የድርጅቴንና የመንግስት ስም በሚያጎድፍ
ተግባራት ላለመሰማራት ቃል እገባለሁ፡፡ከሰላምታ ጋር ህላዊ ዮሴፍ
ግልባጭ
ለአዲስ አበባ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለቦሌ ክፍለ ከተማ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለኢህአዴግ ጽ/ቤት” (ገፅ 257)
የሆነው ሆነ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ መጽሔት ላይ እንዲህ በቀላሉ ጠቅሰን የማንጨርሳቸውን በርካታ አይን ያወጡ ድርጅታዊ እና
ግለሰባዊ ዘረፋዎችን ልባችን ቀጥ እስኪል ድረስ አስነብቦናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ዛሬ በየመድረኩ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›፣ ‹መለስ
መሲህ ነው!›… አይነት ፕሮፓጋንዳ በማድመቅ ግንባር-ቀደም እየሆነ የመጣው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ራሱ የዘረፋው
ተቋዳሽእንደነበረ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡-
“ከሁሉም የሚያሳዝነው ሀገራችንን በዓለም መድረክ በማስጠራቱ የምንወደው ኃይሌ፣ በአስታራቂ ሽማግሌነቱ የምናመሰግነው
ኃይሌ፣ በዓለም አደባባይ አልቅሶ ያስለቀሰን ኃይሌ ‹ኃይሌና አለም ሪል ስቴት› በሚል የድርጅት ስም በመስከረም 7/1998 ዓ.ም
በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ 50,000 ካሬ ሜትር ሕጋዊ ሰውነት በነዋሪው ድምፅ ከተገፈፈው አርከበ እቁባይ እጅ
ወስዷል፡፡ መቼም ታላቁ ሯጭ እየተካሄደ ያለው ውንብድና አዲስ አበባን ማጥፋት እንደሆነ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡”
(ገፅ 400-401)
…የወዶ ተሳዳጁ የኦህዴድ ካድሬ፣ ከሁለት ዓስርታት በላይ ሲነገርና ሲፃፍ የነበረውን ርዕሰ-ጉዳይ ለማጠናከር በርካታ የመጽሐፉን
ገጾች ሰውቷል፡፡ ይህ የህወሓት ብቸኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጠቅላይነት ትርክት፣ ገዢ የተቃውሞው መከራከሪያ መሆኑን በሚገባ
የሚያውቀው ኤርሚያስ፣ በተለይም ባገለገለበት አዲስ አበባ ዙሪያ ያልተገለጡ የሚመስሉ ሁነቶችን አስተሳስሮ ለመተረክ
ጥሯል፡፡ በርግጥ ለእግረ-መንገድ ያህል አንድ ጥርጣሬ ጥለን እንለፍ፤ ይህን መስመር አብዝቶ ማብራራት፣ ተደማጭነትን እና
የፖለቲካ ሁለተኛ ዕድልን እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ከመረዳቱ አኳያ፤ የተባሉትን በምልዐት መቀበሉ ጥቂትም ቢሆን አስቸጋሪ
መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ አልፎም፣ የትግሪኛ ተናጋሪውን እና ህወሓትን ቀላቅሎ ወደመመልከት እንዳያሻግረን ብርቱ ጥንቃቄ
ማድረጉም ሊታወስ ይገባል፡፡
(በሚቀጥለው ሳምንት ይህንኑ መጽሐፍ በማጣቀሻነት እያወሳን፣ የህወሓትን የፖለቲካ የበላይነት እና ጠቅላይነት የሚያሳዩ ወጎችን እንዳስሳለን)

UN experts urge Ethiopia to stop using anti-terrorism legislation to curb human rights

By United Nations – Office of the UN High Commissione

Click for Full Image Size

GENEVA, Switzerland, September 18, 2014/African Press Organization (APO)/ — A group of United Nations human rights experts* today urged the Government of Ethiopia to stop misusing anti-terrorism legislation to curb freedoms of expression and association in the country, amid reports that people continue to be detained arbitrarily.

The experts’ call comes on the eve of the consideration by Ethiopia of a series of recommendations made earlier this year by members of the Human Rights Council in a process known as the Universal Periodic Review and which applies equally to all 193 UN Members States. These recommendations are aimed at improving the protection and promotion of human rights in the country, including in the context of counter-terrorism measures.

“Two years after we first raised the alarm, we are still receiving numerous reports on how the anti-terrorism law is being used to target journalists, bloggers, human rights defenders and opposition politicians in Ethiopia,” the experts said. “Torture and inhuman treatment in detention are gross violations of fundamental human rights.”

“Confronting terrorism is important, but it has to be done in adherence to international human rights to be effective,” the independent experts stressed. “Anti-terrorism provisions need to be clearly defined in Ethiopian criminal law, and they must not be abused.”

The experts have repeatedly highlighted issues such as unfair trials, with defendants often having no access to a lawyer. “The right to a fair trial, the right to freedom of opinion and expression, and the right to freedom of association continue to be violated by the application of the anti-terrorism law,” they warned.

“We call upon the Government of Ethiopia to free all persons detained arbitrarily under the pretext of countering terrorism,” the experts said. “Let journalists, human rights defenders, political opponents and religious leaders carry out their legitimate work without fear of intimidation and incarceration.”

The human rights experts reiterated their call on the Ethiopian authorities to respect individuals’ fundamental rights and to apply anti-terrorism legislation cautiously and in accordance with Ethiopia’s international human rights obligations.

“We also urge the Government of Ethiopia to respond positively to the outstanding request to visit by the Special Rapporteurs on freedom of peaceful assembly and association, on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment and on the situation of human rights defenders,” they concluded.

http://www.thenigerianvoice.com/news/157646/1/un-experts-urge-ethiopia-to-stop-using-anti-terror.html?utm_source=feedburner&utm_medium=feed&utm_campaign=Feed%3A+TheNigerianVoiceNews+%28The+Nigerian+Voice+News%29

በሳዑዲ በሽብርተኝነት የተከሰሰው ኢትዮጵያዊ የ5 አመት እስር ተፈረደበት

1912529_564460577016140_2563645850287923070_n

   የሪያድ ልዩ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፤ የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል በሚል ክስ በተመሰረተባቸው አራት የሳኡዲ አረቢያ ዜጎችና በአንድ ኢትዮጵያዊ ላይ ከአንድ እስከ አምስት አመት የሚደርስ የእስራት ቅጣት መጣሉን አረብ ኒውስ ዘገበ ፡፡ ስሙ ያልተገለጸው ኢትዮጵያዊና አራቱ ግብረ አበሮቹ፣ የቅዱስ ቁርአንን አስተምሮት በሚጥስ መልኩ ከሚንቀሳቀሱ የአገሪቱ ጽንፈኛ ሃይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ብጥብጥ ለማስነሳት ሞክረዋል፤ ሌሎችንም ለአመጽ አነሳስተዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ፣ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው፣ ኢትዮጵያዊው የአምስት አመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡ የእስር ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ወደ አገሩ እንዲመለስ የተፈረደበት ኢትዮጵያዊው፣ ለሃጂና ኡምራ ጸሎት ካልሆነ በቀር፣ ከአሁን በኋላ ወደ አገሪቱ እንዳይገባም ተከልክሏል፡፡

ሁለቱ ግብረ አበሮቹ የአንድ አመት ከስድስት ወራት እስራትና ለሶስት አመታት የሚቆይ የጉዞ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ሁለቱ የአንድ አመት እስራትና ለሶስት አመታት የሚቆይ የጉዞ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡ተከሳሾቹ በ30 ቀናት ውስጥ ይግባኝ ማለት እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በተከሳሾቹ ላይ የተላለፈው ውሳኔ፣ ባለፉት ወራት ከተላለፉት መሰል ውሳኔዎች ጋር ሲነጻጸር ቀላል የሚባል መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፤ ፍርድ ቤቱ በቅርቡ ከ10 በላይ በሆኑ ተጠርጣሪዎች ላይ እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ቅጣት መጣሉን አስታውሷል፡፡

አሁን የምንኖርበትን ዘበናይ ዓለም በራሳቸው አምሳል ጠፍጥፈው የፈጠሩት ስኮቶች ናቸው /በዕውቀቱ ስዩም

bewketu

ጀርመን ገብተን፣በራሂን ወንዝ ዋኝተን፣ ኔዘርላንድ ገብተን፣ በአምስተል ወንዝ ግብርውሀ ወጥተን፣ ኦስሎ ገብተን፣ በኖቬል ሽልማት-ቤት ፊትለፊት ፎቶ ተነሥተን፣የሁለት ሰንበት ዙረታችንን አጠናቅቀን ለሚወደንና ለምንወደው ህዝባችን ጥቅም ስንል ወደ ሸገር ተመልሰናል፡፡ በተመልስንበትም ቀን ስኮትላንድ ከታላቋ ብሪታኒያ ጋር የመሠረተችውን ትዳር ማደሷን አወጀች፡፡
ፍቅር ያሸንፋል ይሉሀል ይህ ነው፡፡
እስቲ በስማም ብየ፣ ዝናሽን ልናገር
የቀሚስ ለባሾች፣ የነዋላስ አገር
አንዳንዴ ሳስበው፣እናንተ የዓለም ጨው ናችሁ የሚለው የመሲሕ ቃል የተፈጸመው በስኮቶች ይመስለኛል፡፡አሁን የምንኖርበትን ዘበናይ ዓለም በራሳቸው አምሳል ጠፍጥፈው የፈጠሩት ስኮቶች ናቸው፡፡ምነው ወዳጄ ለሙገሳም ለከት አለው፣ ትንሽ አላጋነንከውም የሚለኝ ሰው ካለ <How the Scots invented the modern world››የሚለውን የአርተር ሄርማንን መጽሀፍ እጋብዘዋለሁ፡፡
የሰው ልጅን ህይወት ታምራዊ በሆነ መንገድ የቀየሩ ብዙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ግኝቶች የስኮት አእምሮ ውጤት ናቸው፡፡
አንች ወዲህ ማዶ፣
እኔ ወዲህ ማዶ
አንገናኝም ወይ ተራራው ተንዶ
የሚል የጨነቀው የድሮ አፍቃሪ የዘፈነው ዘፈን ትዝ ይላችኋል?፡፡ተራራው ሳይናድ ፣ወድያ ማዶ የምትኖር ቆንጆ ወዲህ ማዶ ካለው ወዳጅዋ ጋር እንድትገናኝ ያደረገው የስልክ ፈጣሪ እስክንድር ቤል ስኮቴ ነው፡፡እነ ቲቪ፣እነ የእንፋሎት መርከብ እነ ብስክሌት፣እነ መኪና ጎማ-ከብዙ በጥቂቱ የስኮት አእምሮ ውጤቶች ናቸው፡፡
የዘመናዊ ፍልስፍና ፈጣሪ ዳዊት ሂውም፣የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ሊቅ አዳም ስሚዝም እዚያው ናቸው፡፡
ስኮቶች በኢትዮጵያ ላይም አሻራቸውን ትተዋል፡፡
የአባይን መፍለቂያ ለመጀመርያ ጊዜ ያገኘው አንድ ስሙ ያልታወቀ፣የወይጦ አሣ አጥማጅ መሆን አለበት፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ያሠሠው ግን የስኮትላንዱ ተወላጅ ያቆብ (James)ብሩስ ነው፡፡በዘመነ መሳፍነት ዋዜማ ላይ ኢትዮጵያ ይልቁንም ጎንደር ምን እንደምትመስል የምናውቀው፣ጀምስ ብሩስ በጻፈልን፣ባለ አምስት ጥራዝ ማስታወሻ ነው፡፡
ባገራችን ባህላዊ ፍልስፍና ሱሪ የጀግንነት መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡‹‹እገሌን ብፈራው ሱሪ አልታጠቅሁማ›› ይላሉ አባቶቻችን ሲፎክሩ፡፡እድሜ ለስኮቶች፣ቀሚስ የጀግነነት ምልክት ሆነ፡፡
ስኮቶች፣የበደልና የጭቆና ታሪክ ማሳለፋቸውን ይናገራሉ፡፡ተነጥለው ጎጆ የመቀለስ አቅሙም ነበራቸው፡፡ግን በመከባበር ላይ የተመሰረት አንድነት መምረጣቸው ጀግንነት ነው እላለሁ፡፡ አርአያቸውን በልቦናችን ያሳድረው ከማለት በቀር ምን ይባላል?

the Proclamation undermine international protections on freedom of expression

940x615_website  The anti-Terror Proclamation in Ethiopia, Amnesty International warns that the law could restrict freedom of expression, peaceful assembly and the right to fair trial, with serious implications in the elections. Although the Ethiopian government faces legitimate security concerns, any anti-terror legislation must be in accordance with international human rights standards. “The Government of Ethiopia has a history of stifling dissent and it is worrying that this law now risks further violating Ethiopia’s obligations under international human rights law,” said Erwin van der Borght, Amnesty International’s Africa programme director. “The Anti-Terror Proclamation is expected to provide Ethiopian authorities with unnecessarily far reaching powers which could lead to further arbitrary arrests”. Based on the law, “acts of terrorism” are vaguely defined and could encompass the legitimate expression of political dissent. The law defines “acts of terrorism” as including damage to property and disruption to any public service, for which an individual could be sentenced to 15 years in prison or even the death penalty. Thousands of protesters, political party leaders, journalists and human rights defenders were arrested and detained following the disputed previous elections in which the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) retained political power.

As reviewed the 2009 Anti-Terrorism Proclamation and find that a number of the sections of the Proclamation undermine international protections on freedom of expression. Of particular concern is the broad definition of terrorism, which would appear to apply to many legitimate acts of expression; the undermining of protection of journalists sources including by surveillance and an excessive duty to cooperate and provide information; and vaguely defined provisions on “encouraging” terrorism that would criminalise the legitimate exercise of freedom of expression and have a real chilling effect on debate on matters of public interest.
1. Anti-Terrorism and Free Expression
The protection of freedom of expression in the context of combating terrorism has been a matter of significant debate for a number of years, especially since the events of 11 September 2001. It is well understood that freedom of expression may be restricted in order to protect public order and national security and recognised that the State has a duty to protect its people from terrorist threats. However, we are concerned in the use of anti-terror laws to stifle legitimate political and social protest. Anti-terrorist laws trigger executive powers that are very restrictive on human rights, often with reduced judicial oversight.
2. Definition of Terrorism
As a preliminary matter, the definition of terrorism set out in the Proclamation is both overly broad and vague. Under international human rights law, criminal offences and any executive measures that interfere with rights such as free assembly, expression and privacy must be clearly and narrowly defined by law, serve a legitimate aim and be “necessary” in a democratic society. We believe that the definition of “terrorism” in the Proclamation fails this test, and we urge serious reconsideration of the definition. Under Article 3(6) of the Proclamation, a terrorist act would include anything that causes “serious interference or disruption of any public service”. It applies to many types of legitimate, non-violent protest and dissent. This can include public transport or communications “systems established to give public service”.
3. Protection of sources and information The Proclamation sets out a series of powers for government bodies and duties for private individuals including the media to facilitate the collection of information about terrorist offenses. These sections collectively raise serious issues about the right of journalists’ to protect their confidential sources and the role of the media in acting as an independent investigator in society.
• Article 12, “Failure to Disclose Terrorist Acts”, requires all persons, including the media, to provide information or evidence relating a terrorist act.
4. Criminalizing “Encouraging” Speech Article 6 of the Proclamation, entitled “Encouragement of Terrorism” sets out broad prohibitions on speech directly or indirectly “encouraging” or “inducing” terrorist acts. There is no definition of encouragement. The introduction of these penalties is likely to result in the criminalization of perfectly lawful statements and the chilling of much political speech and debate. It is very clear that these prohibitions violate the right to freedom of expression. The offences of “direct or indirect encouragement or other inducement” are extraordinarily broad and vague offences that fail the limitations for restrictions on rights required under international human rights law.
The Proclamation seriously undermines freedom of expression rights in a manner that is unlikely to improve security. It gives broad and vaguely defined powers to authorities to criminalize speech that is not directly inciting terrorism and undermines the media’s fundamental right to protection of sources. In doing so, it violates Ethiopia’s obligations under international law. It should be amended to fully recognise free expression rights under international and regional human rights law.
The human rights experts reiterated their call on the Ethiopian authorities to respect individuals’ fundamental rights and to apply anti-terrorism legislation cautiously and in accordance with Ethiopia’s international human rights obligations.

sources –      http://www.amnesty.org/en/for-media/press-releases/ethiopia-new-anti-terrorism-proclamation-jeopardizes-freedom-expression-

–       http://www.article19.org/data/files/pdfs/analysis/ethiopia-comment-on-anti-terrorism-proclamation-2009.pdf

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኖኞች ግንባር ዘብ ETHIOPIAN PEOPLE PARTION FRONT GUARD ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን /ፍራንክፈርት

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኖኞች ግንባር ዘብ ETHIOPIAN PEOPLE PARTION FRONT GUARD ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመ ን /ፍራንክፈርት,

2nd timedemo-1
በአሁኑ ወቅት የወያኔ መንግስት ከመቸውም በበለጠ በሀገራችን ህዝብ ላይ የጭካኔ በትሩን በማሳረፍ ላይ ይገኛል። በዚህ ምክንያት ሐገራችን ኢትዮዽያ በከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ትገኛለች። እንደሚታወቀው የምርጫ ጊዜውን መቃረቡን ተከትሎ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጸመውን ማሳደድ፣ እስር፣ አፈና እና ግድያ ለጀርመን መንግስት ና ህዝብ እንዲሁም ለአለም ማህበረሰብ ማሳወቅ ግድ ይለናል። በተጨማሪም ነጻ ፕሬስ ማፈኑን፣ ጋዜጠኞችን እና ብሎገሮችን ማሳደድ እና ማሰሩን፣ በዕምነት ተቌማት ጣልቃ መግባቱን፣ ዕንዲሁም የዩኒበርስቲ ተማሪውችን በግዳጅ የወያኔ አባል ዕያደረገ መሆኑን ለመቃወም ,
የኢትዮዽያ ህዝብ አርበኞ ግንባር ዘብ (EPPFG) ለማንኛውም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ፍራንክፈርት መጥራቱን በደስት ይገልጻል።
መሪ መፈክራችን;-
በመላው ዓለም ያሉ የቆንስላ ፅፈት ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክልም የካሃዲዎች ና የባንዳዎች ነው።ይልቀቅልን!!
ቀን  19/09/2014-    ሰዓት – ከ 12 – 16
ቦታ: መንሻ: ሃዉፕት ባን ሆፍ (Hauptwache)
መድረሻ: ወያኔ ኢምባሲ
ለተጨማሪ መረጃ: 0152785114566- –015210110979

The Timing of ER’s Rampage against G7 is a Calculated One (Neamin Zeleke)

Neamin Zeleke

The timing of ER’s rampage against G7 is a calculated one. It is a calculated timing to deflect and derail the momentum the struggle gained in recent weeks. It is timed to dampen the spirit of Ethiopians around the world. It is a calculated move to create confusion and diversion in the otherwise gathering of momentum the Ethiopian people in their struggle against the ethnic minority dictatorship of the TPLF. Past trends and patterns of stories published by ER Intelligence Unit prove that ER has no qualms to pen fictions and distortions. Its latest, so-called “special report” is not a special report, but a deliberate act of to attract online traffic. ER’s claim to know many facts is simply hogwash, at least everything that he said and stated regarding Ginbot 7. We at Ginbot 7 can easily refute ER’s obdurate fictions in public line by line, but unlike ER we are indebted to the Ethiopian public. Hence, we spend our valuable time planning and excusing our vital tasks of removing the ethnic minority regime.

Neamin in Atlanta AAAAIt is indeed easy to debunk these fictions in the so called special report and the latest one, the laughable “advice to G7”.Laughable indeed! The ER editor thinks he is an institution by himself, otherwise, where is he getting this inflated sense of self, the moral authority, and the political acumen to give an advice to an organization that has more than enough politically experienced and highly capable leaders and members in thousands?

I have known and worked with ER’s editor for the past so many years to champion human rights and democracy in Ethiopia. He is a hard worker. I admire his dedication. But he fails to see left and right, backwards and forward. He fails to handle contradictions and complexities. He thinks that the world revolves around him; he thinks that he has a monopoly on facts, solutions and ideas about the how, the ways and means of the struggle to bring about the desired end.

ER’s editor had projects, and those projects failed due to several reasons. His failure is not Ginbot 7’s failure. Let it be known that I have no interest to respond and engage the editor of ER further in refuting each of the fabrications and lies. Ginbot 7, as an organization, does not consider diversionary fictional stories deserve a formal reply.

I am writing this last note in my personal capacity and as person who happen to know the details of what ER’s editor otherwise claims them to be the “facts”, the” truth “, and Lo and Behold, the only “truth“ concerning everything about G7, its internal working, its relationships with governments, including the Eritrean government, and other organizations, and many of G7 projects. And unlike ER, there is no way I would dwell on these matters in public. We owe it the struggle; we owe it the Ethiopian people not to do so. That is what any responsible person who understands the stakes involves would do.

Thank you and sincerely,
Neamin Zeleke