Archive | October 4, 2014

ቴዲ አፍሮ…..!

ስንት ብርሃን ወጣ…..ስንት ፅልመት ተሸነፈ ……ስንት ተራራ ተናደ …..ስንት ቁልቁለት ተሞላ ….ስንት አደይ አበባ አብቦ ስንት አደይ አበባ ከሰመ……ስንት ደመራ ተለኩሶ ሰንት እምነት ተፈተነ …..ስንት ስብሰባ ተሰብስበን ተበተንን …..ስንተ መወድስ ለባለስልጣኖቻችን አቀረብን….. ስንት ቅኔ አፈሰስስን …..ስንት መነዋወፅ ሆነ …..ስንት ግሩምሩምታ ተከሰተ …..ስንት ጊዜ ሰማዩ ዳመነ ….ስንት ጊዜ ሰማዩ ደፈረሰ ግፍንም አሳበቀ ….. ስንት ሰው ተራበ….. ስንት ሰው ተጠማ ….. አንድ ሆነን እንደ ሺሕ ተለያየን ….ማሰብ ….ማወቅ ….መረዳት እየቻልን እንደ አላዋቂዎች ስንት ጊዜ እንጠፋለን…… ስንት ጊዜስ ጠፋን…… በዝምታ ተነዳን….. ባለመናገር ተጎተትን…… ወዴት ነው እየሄድን ያለነው…… መዳረሻችን የት ነው…… ምኞታችን ምንድነው…. በየጥጋጥጉ እየተሞጋገስን …… በየመታጠፊያው እየተሞጋገስን…… ስንት ጊዜ ነው የዛልነው….. የደከምነው ……ስም ሳይኖራቸው ስም የሰጠናቸው….. አንቱ የሚያስብል ስራ ሳይኖራቸው አንቱ ያልናቸው….. የማይጠቅም አሸንክታብ ያንጠለጥንላቸው ስንት ጊዜ ነው…… ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እየተባለ የሚዘፈንልን እስከ መቼ ነው….. ሳንማር የምንጠመጥመው እስከመቼ ነው

Teddy4

በዘመናችን…… በኖርንበት የዘመን ስሌት ብዙ ውጣውረዶች ተከስተዋል….. ፍቅር አጥተን የተሰደድንባቸው ……ፍቅርን የፈራንበት….. አንድ መሆንን የጠላንበት…… ብዙ ወቅቶች ተፈራርቀዋል
ብርሃን በብርሃን ላይ ሲወጣ……ተራራ እየተናደ ሲደለደል ……ቁልቁለት ገደሉ ሲሞላ …..አደይ አበባ ከስሞ አደይ አበባ ሲፈነዳ …..አንድ ያይደል ሺሕ ደመራ ቆመን የለኮስን ሕዝቦች ……ነገር ግን ፍቅር የሌለን… መዋደድ የሌለን …. አፍአዊ በሆነ መዋደድ የምንሞጋገስ ስንቶች እንሆን….. እንደ ኢትዮጵያዊ ለማሰብ የማንፈቅድ….. ብሔራችን እንጂ ኢትዮጵያቂነታችን ግድ የማይሰጠን….. ባለፉት ሺሕ ዓመታቶች ውስጥ ያሳለፍነው ስቃይ…… ያሳለፍነው መከራ…… ያሳለፍነው ሰቆቃ ….ያሳለፍነው የጦርነት ታሪክ ምንም ያልመሰለን….. ከብዙ ሺሕ ዓመታት የእርስ በእርስ መናናቅ…… እኔ ከአንተ እሻላለሁ ከሚለው ትምክሕተኛ አስተሳስብ ያልወጣን….. መኖራችን እንጂ መሞታችን የማናስተውል….. መቆማችንን እንጂ መውደቃችን የማንመለከት እኛ….. ታሪክ ማንበብ እንጂ ከታሪክ መማር ያቃተን እኛ……. እሰከ መቼ ነው እንደ ጅብ መንጋ ተጠባብቀን የምንሄደው…… ቴዲ አፍሮ ዘፈን ዘፈነ ተብሎ የኢትዮጵያዊነትን የሞራል እና ልዕልና ገሎ ባንዲራ ላይ ማላገጥ …… ባንዲራ ላይ ያልተገባ ምስል መለጠፍ….. መቼ የመጣ አስተምሕሮ ነው ……ያሳለፍናቸው የታሪክ ዳራዎች ይበቁናል…… ያቃጠልናቸው እና የዘረፍናቸው የታሪክ መዳረሳቻችን ይበቁናል …… ታሪካች እንዲሕ ነው የሚያወራው …..እገሌ የተባለ ንጉስ ተነስቶ በዚሕ አካባቢ ያሉት ቤተክርስቲያኖችና መስጊዶችን አቃጠለ…… እጅ ቆረጠ….. በጦር ተሸነፈ…. ድል አደረገ …..ብረት አንስቶ ታገለ ……ወዘተ….. ሀገርና ሕዝብ ዘለዓለም ይኖራል….. ሌላው በሙሉ ያልፋል….. የማያልፍ ታሪክ ለትውልድ ማስቀረት ግን የሚበጅ ስራ ነው….. በየጥጋጥጉ ፍቅር አጥተን ተሰደናል
ፍቅራችን የት ነው የተሰደደው ……ማንስ ነው ያሳደደው ….. ማንስ ነው ማንነታችንን የሰለበን ……ማን ነው ኢትዮጵያዊነታችንን አሰትቶ አንድ ባንዲራችንን አስጥሎ…..ዘጠኝ ባንዲራ በየክልላችን አቁም እንድንኮራ ያደረገን የቱጋር ነው…… የተሰለብነው የቱ ጋር ነው…..የቱ ጋር የተሸለት ነው….. አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሆነውን ባንዲራ ምዕራብ አፍሪካዊያን የነፃነት ጎሕ መሆኑን ተረድተው ……የድል አርማ መሆኑን አውቀው …..ብዙዎቹ ሀገራት ከኢትዮጵያ የተቀዳ ባንዲራ ለሀገራቸው ሲያቀናጁ….. እኛ እኛነታችንን ንቀናል….. ተሰለብን የቱ ጋ ነው….. የእኛ የሆነው ንቀን ርቀን የተጓዝነ መቼ ነው….. አንድ መሆን ፈርተን የተናናቅነው መቼ ነው …. ችግሩ ምንድን ነው…… አንድ ብንሆን ምንድነው ችግሩ ……ኢትዮጵያዊነት እንጉርጉሮ የሆነብን ለምንድነው
በፊት ልጅ እያለን ….እኔ እና አንቺ….. እኔ እና አንተ …. ስለምንም ነገር ሳናስብ ስለምንም ነገር ሳንጨነቅ ተቃቅፈን ነበር የምንውለው….. ሀገራችን ብለን የምናስባት ያቺ ኳስ የምንጫወትባትን ትኝሿን ሜዳ….. ሻይ የምንጠጣበትብ ሻይ ቤት…… የምንማርባትን ትምሕርት ቤት….. ከሁሉ በላይ ደግሞ ሀገር ብለን የምናስባት ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ሽቅብ ለመስቀል የምንሽቀዳደመው ባንዲራዋን ነበር …….ዛሬ ግን እያደግን ስንመጣ(በአካል መጠን ነው ግን ያላደገው አዕምሮአችን የሆነ ቦታ ማሰብ ማሰላሰሉን አቁሟል ስታክ አድርጓል)….. እየጎለመስን ስንመጣ…… የተቃፍንባቸውን እጆች ለመፈራረጅ ሰነዘርነው….. አንዳችን በአንዳችን ላይ የቂም ቋጠሮ ለመያዛችን አመላከትንበት…… በፍቅር ትናጋችችን እስኪነቃ የሰቀልናት ባንዲራ ላይ ዘበትንባት አሾፍንባት……. ይሕ የሆነው ምሁራን ናቸው ብለን ማዕረግ ባሸከምናቸው…… ዶክተሮች….. ኢንጅነሮች…. የፖለቲካ አቀኝቃኞች ነው…… ባለመዕረግተኞቹ የራሳቸው ባንዲራ ብቻ ይዘው ሸለሉ….. ፎከሩ ………ግን ለምን
በቅርቡ ቴዲ አፍሮ በሆላንድ ሀገር የዘፈናትን የዘፈን ግጥም በመቃወም ብዙዎች አቀንቃኙን ሰደቡት ……የኢትዮጵያን ባንዲራ እስኪበቃቸው ድረስ አበሻቅጠው ጣሉት …..ባንዲራው ላይ አግባብ ያልሆነ ነገር አሳዩ…… ይሕ ያሳዝናል….. ባንዲራችን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ማለት ከደማችን ጋር የተዋሃደ….. በልባችን የሠረፀ ….ብሔራዊ ኩራታችን…. የነፃነት አርማችን ነው…… እናም ባንዲራችንን ባንዲራዬን መቼ ቢሆን አፈቅራታለሁ…… የሚገርም ሀገር ውስጥ ነው ያለነው…… ያደለው አንድ ስለመሆን ያስባል….. ስለመፋቀር….. …..ስለማደግ…… ስለመበልፀግ ያስባል ….. ያላደለው ደግሞ የኋሊት ይዳክራል …… ከወንዝ ወዲያ ማዶ ያሉ ወፍ ዘራሽ ምሁራን ሲፎክሩ ….. እኛ ሀገር ውስጥ ያለን በእነሱ ሀሳብ እየተመራን እንሰክራለን….. እባካችሁ ያሳለፍነው የችግር ታሪክ ይበቃናል ደሞ ሌላ ችግር አንጥራ እንዋደድ እንድ እንሁን ….ቴዲ አፍሮን እና ሀገርን ለያይተን እንመልከት ….ቴዲ ለዘፈነው ዘፈን መልስ መስጠት እንኳን ቢያስፈልግ በአግባብና በስርዓት መሆን አለበት እንጂ የሀገር ባንዲራ ላይ አይለገጥም አይሾፍም ….እናስተውል

ፀገየ ኃይለሚካኤል