Archive | October 2014

የእንግሊዙ ጠ/ሚ የአቶ አንዳርጋቸው የሞት ፍርድ እንዳይፈጸም ጠየቁ

“ክቡር ጠ/ሚ አባታችንን ከሞት ያድኑልን”  የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጆች

Andargachew

(አዲስ አድማስ) የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በእስር ላይ በሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ከአምስት አመታት በፊት የተጣለው የሞት ፍርድ ተፈጻሚ እንዳይሆንና በቆንስላ ሰራተኞች መጎብኘት እንዲችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ከትናንት በስቲያ ዘገበ የአቶ አንዳርጋቸው ልጆች አባታቸውን ከሞት እንዲታደጉላቸውና ከእስር ተፈትተው ዳግም የሚገናኙበትን መንገድ በማመቻቸት በኩል ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የሚጠይቅ ልብ የሚነካ ደብዳቤ እንደላኩላቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን፣ የልጆቹን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደብዳቤ መላካቸውን አስታውቀዋል፡፡
የእንግሊዝ የስራ ሃላፊዎች በእስር ላይ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በቋሚነት መጎብኘት እንዲችሉ ግፊት ቢያደርጉም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በጎ ምላሽ እንዳልሰጡ ለልጆቹና ለእናታቸው በሰጡት ምላሽ የገለጹት ዴቪድ ካሜሩን፣ ከዚህ በፊት የተደረገው ጥረት ውጤታማ አለመሆኑን በማጤን በግላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አመልክተዋል፡፡የእንግሊዝ መንግስት የቆንስላ አባላት አንዳርጋቸው ጽጌን በቋሚነት መጠየቅና ማማከር የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችና መንግስታቸው ሲቃወመው የቆየው የሞት ፍርድ ተፈጻሚ እንደማይሆን ማረጋገጫ እንዲሰጥ በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን የገለጹት ዴቪድ ካሜሩን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማርያም ለደብዳቤያቸው በጎ ምላሽ እንደሚሰጧቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የሆነችው የ7 አመቷ ምናበ እና መንታ ወንድሟ ይላቅ፣ ለጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን በላኩት ደብዳቤ፣ “አባታችን ልጆቹን የሚወድና የሚንከባከብ መልካም አባት ነው፡፡ አባታችንን ከእስር ለማስፈታት ምንድን ነው የሚያደርጉልን?” በማለት መጠየቃቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ የመጀመሪያ ል©cW የ15 አመቷ ህላዊት በበኩሏ፣ “አባታችን በጣም ናፍቆናል፡፡ እባክዎት በቅርብ ጊዜ መልሰው ወደ ቤታችን ያምጡልን” በማለት ስሜቷን እንደገለፀች ዘገባው ጠቁሟል፡፡

12 ፓርቲዎች መጪውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ቅሬታዎቻቸውን በጋራ ለምርጫ ቦርድ አቀረቡ

በ2005 ዓ.ም በትብብር ሲሰሩ የቆዩ 12 ፓርቲዎች ከአሁን ቀደም የጠየቅናቸው ጥያቄዎች ባልተመለሱበት ሁኔታና አሁንም ከአሁን ቀደም የተነሱትን ጥያቄዎች የሚያጠናክሩ ተግባራት እየተፈጸሙ በመሆኑ ከሀገራዊ ምርጫው በፊት ሊፈቱ ይገባቸዋል ያሏቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ምርጫ ቦርድም ኃላፊነቱን እንዲወጣ በጋራ በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ፡፡

ፓርቲዎቹ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. በጻፉትና ዛሬ ለቦረወዱ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት በመንግስት/ገዢው ፓርቲ በማንአለብኝነት የተወሰዱ ህገ-ወጥ እርምጃዎች ዘላቂ ልማትና ሠላም፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ፣ ህገ-መንግስታዊ፣ ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አከባበርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በጋራ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል፡-

1ኛ/ በተለያየ የመዋቅር ደረጃ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ማስፈራራት፣ የአካላዊና የንብረት ጉዳት ማድረስ፣ በሃሰት ውንጀላና የፈጠራ ክስ ማሰር፣ እየተጠናከረ መምጣትና በዚህም የፓርቲዎችን በዕቅዳቸው መሰረት የመሥራትና የዕለት ተዕለት ነጻ ህጋዊ እንቅስቃሴ መገደብ፤

2ኛ/ በአንድ በኩል የሠላማዊ ትግል ስልቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ በመዝጋት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እዳይገናኙና ዓላማቸውን፣ ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለህዝብ እንዳያደርሱ በማድረግ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በፊት በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን፣ መንግስታዊ መዋቅርና ሃብት በመጠቀም ለት ተለት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየጠመቀ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረገበትና እያደረገ ያለበት ሁኔታ ግልጽ መሆኑ፤

3ኛ/ ገዢው ፓርቲ ከመንግስት ካዝና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብሎ ያለምንም መስፈርት ለሚፈልጋቸው ፓርቲዎች በማከፋፈል በፓርቲዎች መካከል አላስፈላጊ የአቅም ልዩነት በፈጠረበትና የጥቅም ትስስር/ድጋፍ በገዛበት ሁኔታ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተግባርና ኃላፊነቱ ውጪ ተሳታፊ መሆኑ፤
4ኛ/ ገዢው ፓርቲ የመንግስት መገናኛ ብዙሃንን በብቸኝነት በሚጠቀምበት እውነታ ለህዝብ አማራጭ መረጃዎችን የሚያቀርቡና በሥርዓቱ ላይ ትችቶች የሚያቀርቡ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንና አሳታሚዎችን በመክሰስ አንድም ለወህኒ ያሊያም ለስደት (በቅርብ ጊዜ ብቻ ከ10 በላይ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን መታሰራቸውን፣ ከ20 በላይ ጋዜጠኞችና አሳታሚዎች መሰደዳቸውን ያጤኑኣል) በመዳረግ መራጩን ህዝብ ከአማራጭ መረጃ የማግኘት መብት ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል ሁኔታ የተገደበበት፤

5ኛ/ በተለያዩ ቦታዎች በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ የሚታየው ግጭትና ይህን ተከትሎ የሚታየው የህይወት መጥፋት፣ የንብረት ውድመት፣ መፈናቀልና ማኅበራዊ ምስቅልቅል አሳሳቢ መሆኑ በግልጽ የሚታይና በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለ እውነታ መሆኑ፤
የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ጥያቄዎች 2005 ዓ.ም ወቅት የቀረቡ ከነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጋር በቀጥታ የተገናኙ ናቸው ያለው ትብብሩ ከ2005 ዓ.ም እስከ ዛሬ ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻች እንዲመለሱ፣ ገዢውን ፓርቲና አጋሮቹን ጨምሮ ሁሉም ህጋዊ ፓርቲዎች በጋራ ተገናኝተው በምርጫና የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ላይ የሚወያዩበት የጋራ መድረክ እንዲዘጋጅ ተጠይቋል፡፡

‹‹እነዚህ ጥያቄዎች ባልተመለሱበት የሚደረግ የምርጫ ተሳትፎ ለኢ-ህገ-መንግስታዊነትና ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ዕውቅና በመስጠት አገሪቷንና ህዝብን ወደባሰ አዘቅት መወርወር በመሆኑ በታሪክና ትውልድ ፊት የሚያስጠይቅ ነው›› ያለው የትብብሩ ደብዳቤ ምርጫ ቦርድ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠውና ተገቢ ምላሽ በመስጠት ሚዛናዊነቱን፣ ከወገንተኝነት የጸዳ፣ በምርጫ ህጉ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚሰራ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ጠይቋል፡፡

በትብብር እየሰሩ ያሉት ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጸኃፊ የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ ‹‹በ2005 ለምርጫ ቦርድ ያነሳናቸውና ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ባልተመለሱበትና እንዲያውም ያነሳናቸውን ጥያቄዎች የበለጠ የሚያጠናክሩ ሁኔታዎች በተፈጠረበት፣ አንደኛ እነዚህን ጥያቄዎች መንግስት እንዲመልስ፣ ሁለተኛ ባነሳናቸው ጥያቄዎች ላይ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ ውይይት እንድናደርግባቸው ነው ጥያቄዎቹን ያነሳናቸው›› በሚል ለምርጫ ቦርድ ያስገቡትን ደብዳቤ አላማ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ደብዳቤውን ካስገቡ በኋላ ምርጫ ቦርድ ‹‹የሚስተካከል ነገር አለውና ተመልሳችሁ እንደትመጡ›› ማለቱ የታወቀ ሲሆን አቶ ግርማ በበኩላቸው ‹‹ያቀረብነው አቤቱታ እንዲስተካከል አቤት ከተባለበት አካል አቤቱታውን እንድናስተካክል የሚመጣ ማስተካከያ መኖር የለበትም ብለን ገልጸንላቸዋል›› ብለዋል፡፡

10698571_597897170335945_7341856883932653494_n

10497948_597897317002597_4508240341264100990_o

10710532_597897537002575_4071513948700190760_n

1379307_597897447002584_1390968221248572103_n

ከፍቶኛል፡፡ በጣም ቅር ብሎኛል፡፡ ደስ የሚል ስሜት አይሰማኝም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መታሰር ነው (መስፍን ጌታቸው የሰው ለሰው ድራማ ደራሲ )

መስፍን ጌታቸው (የሰው ለሰው ድራማ ደራሲ )
ተመስገን ደሳለኝ ??
ከፍቶኛል፡፡ በጣም ቅር ብሎኛል፡፡ ደስ የሚል ስሜት አይሰማኝም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መታሰር ነው፡፡
ተሜ በጣም የማከብረው ወዳጄ ነው፡፡ ትህትናወ፤ቅንነቱ፤ሰው አክባሪነቱና አገር ወዳጅነቱ ወዘተ ተሜን በቀላሉ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ የሚያደርጉት ባህሪያት ናቸው፡፡
ከዚህ ውጪ ተሜ ላመነበት ነገር በድፍረት እራሱን አሳልፎ ለመስጠት የማያመነታ ጎበዝ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በሀገራችን ነፃ ሚዲያ ታሪክ አንድ የህትመት ውጤት ሲዘጋበት ወይም ከገበያ ውጪ ሲሆንበት ” አከተመ ” ብሎ ባለመቀመጥ ከፍትህ እስከ ፋክት ድረስ በተለያየ መንገድ እምነቱን ዳር ለማድረስ እስከመጨረሻው በፅናት የቆመና አዲስ ታሪክ መስራት የቻለ ብርቱ ጋዜጠኛ ነው፡፡
ከሙያው ባሻገር በግል ህይወቱም ቢሆን በጣም ደግና ተግባቢ የሆነ መልካም ሰው ሲሆን ሌሎችን መርዳትና ማገዝም ልዩ መታወቂያው ነው፡፡ ሁለት መንታ ወንድማማች ህፃናትን አጠቃላይ ወጪያቸውን በመቻል እያስተማረና እሳሳደገ እንደሚገኝ አውቃለሁ፡፡
ከሱ መልካም ስብዕና አንፃር የሚረዳቸው ሰዎች ከዚህ በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የቅርብ ወዳጆቹ ሁሉ ያምናሉ፡፡ነገር ግን ይሄን በጎ ተግባሩን መናገርና ለገበያ ማቅረብ የማይፈልግ በመሆኑ ቁጥራቸውን በትክክል ማወቅ አይቻልም፡፡ሁለቱን ወንድማማቾች እያሳደገ መሆኑን እኔ የሰማሁት ከሱ አንደበት ሳይሆን ስሙን አንስተው ከማይጠግቡት የህፃናቶቹ ወላጆች ነው፡፡ እናም ወዳጆቼ ተሜ ብቻውን ሳይሆን የታሰረው ቢያንስ የነገይቷ ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ መሆን ከሚችሉ ሁለት ህፃናት ጋ ጭምር ነው፡፡
የተሜን ፅሁፎች ሁሉንም አይደለም የምወዳቸው፡፡ ሰው እንደመሆኔ መጠን እዚህ ጋ ልክ አይደለም እንዲህ ባይል ኖሮ ጥሩ ነበር በማለት የምነቅፋቸውና ለራሱ የምነግራቸው የተወሰኑ ፅሁፎች ይኖራሉ፡፡በአጠቃላይ ግን የወርቃማ ብዕሩ ትልቅ አድናቂ ነኝ፡፡
እናም አኔ የማውቀው ተሜ የተሸለ ነገር ለማድረግ ከማሰብ ባለፈ በብዙ መልኩ አገር የሚያጠፋ ክፉ ተግባር ውስጥ ይገባል ብሎ ማሰብ በጣም ይከብዳል፡፡
ተሜ አንድ ቀን ሊታሰር እንደሚችል በእርግጠኝነት ደጋግሞ እየተናገረና አገር ለቆ እንዲሰደድ የሚቀርቡለትን ተደጋጋሚ ምክሮች ፊት እየነሳ ቅንጣት ሳይሸበር በልበ ሙሉነት ስራውን ለመጀመር ደፋ ቀና ሲል የቆየውስ ያለ ምክኒያት ይመስላችኋል?…..እኔ አይመስለኝም

mesfin

መደበኛ የስብሰባ ጥሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አባላት በሙሉ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ

መደበኛ የስብሰባ ጥሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አባላት በሙሉ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ

meeeing

Ethiopian authorities convict journalist in Addis Ababa

Temesghen Desalegn has been convicted in connection with a 2012 defamation case. (CPJ)

Temesghen Desalegn has been convicted in connection with a 2012 defamation case. (CPJ)

Nairobi, October 15, 2014An Ethiopian court on Monday convicted journalist and magazine owner Temesghen Desalegn in connection with a 2012 defamation case, according to news reports and local journalists.

The Federal High Court in the capital, Addis Ababa, found Temesghen guilty of incitement, defamation, and false publication in connection with a series of opinion pieces published in Feteh (“Justice”), the journalist’s now-defunct weekly newsmagazine, according to local journalists’ translation of the charge sheet that was reviewed by CPJ. Authorities took Temesghen into custody Monday afternoon.

If convicted, the journalist could face up to 10 years in prison, according to his lawyer, Ameha Mekonnen. His sentencing is scheduled for October 27, according to news reports.

Information Minister Redwan Hussein said the case stemmed from articles published in Feteh about two years ago, according to news reports. Two of the articles discussed the peaceful struggles of Ethiopian youth movements for political change and two columns criticized alleged government efforts to violently suppress student protesters and ethnic minorities, according to the charge sheet.

Temesghen was briefly arrested in August 2012 on the same charges, but authorities dropped the charges and released him five days later without explanation, he told CPJ at the time. A judge in the Federal High Court revived the charges in February 2013 after a state prosecutor announced in court in December 2012 that the charges would be refiled against him.

The court on Monday also convicted in absentia Mastewal Birhanu, the former publisher of Feteh, with inciting the public to violence by printing the magazine, according to the charge sheet.

“In case the recent crackdown on current publications in Ethiopia did not illustrate authorities’ fear of independent voices, they have now resorted to convicting a journalist on two-year-old criminal defamation charges,” said CPJ East Africa Representative Tom Rhodes. “We urge Ethiopian authorities to drop this case–as they did once before–and free Temesghen Desalegn immediately.”

Authorities have routinely targeted Temesghen’s writing. In May 2012, he was given a four-month suspended prison sentence and fine after Feteh published a statement made by imprisoned journalist Eskinder Nega during his trial. Temesghen paid the fine.

The government ordered printers to block the distribution of Feteh in July 2012 in connection with a series of articles about the health of the late Prime Minister Meles Zenawi, local journalists said. Authorities blocked three other subsequent publications started by Temesghen, including Addis Times, Le’ilena(“Magnanimity”), and the latest, Fact, according to local journalists.

The last edition of Fact was published in September 2014 after authorities ordered printers to cease publishing the magazine, local journalists told CPJ. In August, the Justice Ministry accused Fact and five other independent weekly publications of inciting violence, publishing false news, and undermining public confidence in the government. All publications have since ceased publication.

Last week, an Ethiopian court sentenced in absentia to three-year jail terms the general managers of three of the publications, including Fact, Addis Guday, andLomi. The general managers are accused of inciting the public by spreading false information and subverting the constitutional order, according to news reports.

A state crackdown on independent publications and bloggers has taken place in Ethiopia this year, prompting several Ethiopian journalists to flee into exile in 2014, according to CPJ research. With at least 17 journalists in jail, Ethiopia is the second leading jailer of journalists in Africa, second only to its neighbor Eritrea,CPJ research shows.

http://cpj.org/2014/10/ethiopian-authorities-convict-journalist-in-addis-.php

ጋዜጠኛ ሚሊዮን በመጨረሻዎቹ ሰዓታት….

ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ከ12 አመት በላይ የሰራ ወጣት ጋዜጠኛ “ነበር”፡፡ በነሃሴ ወር ውስጥ በመንግስት ወከባ ህይወቱን ከእስር ለማትረፍ ተሰዶ ወደሀገሩ በሳጥን ለመመለስ እየጠበቀ ያለ ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ…ሚሊዮን፡፡ ተስፋ የነበረው ስደተኛ ጋዜጠኛ የመልካም ባህሪ እና ስብእና ባለቤት የነበረው ሚሊዮን፣ ስለሀገሩ ፍቅር ብዙ መሰናክሎችን ሊጋፈጥ ስደትን መርጦ ባሰበበት ሳይሆን በታሰበለት ሊኖር የተገደደው ሚሊ እንደወጣ በሰው ሀገር ልጄን እህቶቼን ቤተሰቦቼን ሃገሬን እንዳለ በድንገት ታሞ እንደፈራው ላይመለስ አሸለበ፡፡
ከሚሊ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንት አብረን ኖረናል፡፡ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ እንደመጣ ከጓደኛው መላኩ ጋር ከኖረው እና ሆስፒታል እስከገባበት የመጨረሻዎቹ ሶስት ቀናት፤ የተረፉትን ሶስት ሳምንታት አብረን ነበር፡፡ እኔ ባሴ እና ሚሊ በጠባቧ ክፍላችን ያለፉትን ሶስት ሳምንታት ተጋርተን ነበር፡፡ ሚሊ ከሃገሩ ከወጣ በኋላ ወደ ሃገሩ በድጋሚ እንደማይመለስ ሲያውቀው አንድም ቀን ከጭንቀት ወጥቶ አያውቅም ነበር፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ “ከሃገሬ ስወጣ ሰማዩን አይቼ አለቀስኩ ካሁን በኋላ ሃገሬን አላይም” ብሎ ከመጨነቀን እና ከመተከዝ ያረፈበትን ጊዜ አላስታውሰውም፡፡ የህመም ስሜት እየተሰማው እንደሆነ ሲነግረን ስለምትጨነቅ ነው ነገሮችን አምነህ መቀበል አለብህ እያልን እናጽናናው ነበር፤ ቅሉ ሚሊ በድጋሚ እስከመጨረሻው ለሃገሩ እንደማይበቃ ያወቀው ይመስል የሃገሩን ሰማይ እያየ እንዳለቀሰ እያለቀስን በሳጥን ልንሸኝው እየተዘጋጀን ነው ….
ሚሊ ከመስቀል በዓል ጀምሮ የጤንነት ስሜት እየተሰማው አልነበረም፡፡ ራሱን በጣም ያመው ነበር፡፡ ስለ ልጁ ስለእህቶቹ ስለቤተሰቦቹ በጣም ይጨነቅ ስለነበር ሀገሩ አለመግባቱን ናፍቆቱን እያሰበ እንባ ይተናነቀው ስለነበር የህመሙን ምክንያት ጭንቀት ነው ስለዚህ አትጨነቅ እያልን ልናረጋጋው ብዙ ሞክረን ነበር፡፡ በኋላ ላይ በምንኖርበት አቅራቢያ ወደሚገኝ ክሊኒክ ወሰድነው፡፡ ታይፎይድ እንደታመመ እና ምን አልባት ለሃገሩ አዲስ ስለሆነ የምግብ አለመስማማት እንደሚሆን ገልጾልን ግሉኮስ ወስዶ መድሃኒት ተሰጥቶት ወደቤት ተመለሰ፡፡ ሃሙስ ቀን ንጋት11 ሰዓት ተንስቶ በጣም ራሱን እየታመመ እንደሆነ እየገለጸ “ወይኔ በስደት ልሞት” እያለ ሲያለቅስ በድንጋጤ እኔ እና ባሴ ተነስተን መጀመሪያ ወደወስድነው ክሊኒክ ወሰድነው፡፡ ዝግ ነበር፡፡ ከዛ የተሻለ ህክምና ያገኝበታል ብለን ወደአሰብነው ሆስፒታል ወሰድነው፡፡ ሶስት አይነት ምርመራ ካደረጉለት በኋላ መድሃኒት አዘውለት ወደቤት ተመለስን፡፡ ሚሊ የጤናው ሁኔታ እየተሻሻለ ነበር፡፡ ግን የምግብ ፍላጎቱ አነስተኛ ስለነበር አቅም እያነሰው ነበር፡፡ መዳህኒቱን እየወሰደም በቅርባችን ባለ ክሊኒክ ግሉኮስ ይወስድ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ አቅሙ እየተዳከመ መጣ፡፡ የመጨረሻዎቹ ሶስት ቀናት ግን ፍጥነቱን ያልገመትነው እና ያልጠበቅነው ነገር ተከሰተ፡፡
ሆስፒታል ከመግባቱ ሁለት ቀን በፊት ጓደኛው መላኩ ቤት ሄዶ ህክምናውን እየተከታተለ ነበር፡፡ ቅዳሜ ጤንነቱ መሻሻሉን አይቼ ደስ ብሎኝ ነበር ወደቤት የገባሁ፡፡ የዛን ቀን ምግብ ስለማይበላ ግሉኮስ ለመውሰድ እንደሚፈልግ ነግሮን ከባሳዝነው ወንድምነህ (ባሴ) ጋር ወደ ክሊኒክ ሄዱ፡፡ ማታ ላይ ሚሊ በጣም ደክሞ ነበር፡፡ ህመሙ በፍጥነት እየተባባሰ መጣ፡፡ የመጨረሻዎቹን ሁለት ቀናት ሚሊ ራሱን አያውቅም ነበር፡፡ ሆስፒታል ተኝቶ መታከም ቢጀምርም ሚሊ ራሱን እንደሳተ ሳይሰናበተን “ሀገሬን አላይም ዳግመኛ እንዳለ” አሸለበ፡፡ ሚሊዬ አንተ ራስህን አታውቅም እንጂ በመጨረሻዎቹ የጭንቅህ ቀናት በምን ያህል ጋዜጠኛ ተከበህ፤ ምን ያህል ሰው አብሮህ እንደነበር ብታየው እንዴት ጥሩ ነበር፡፡
ፍርሃታችን እውን ይሆናል ብለን አልጠበቅንም፡፡ ፈጣሪ በስደት ይጠብቀናል እግዚአብሔር አለን ብለን አስበን ክፉን ከኛ ያርቀዋል ብለን ሁላችንም ተመኝተን ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ሚሊዬ ሃገሬ ናፈቀኝ ልጄ እህቴ ጓደኞቼ…ከእንግዲህ አላያቸውም እኮ እንዳለ ከሃገሩ ከወጣ ከአንድ ወር ከ10 ቀን በኋላ ህይወቱ አለፈ፡፡ መጨረሻ በኦክስጅን በሚተነፍስበት ሰአት እግዚአብሔር እንዲያድነው አልቅሰንለት ነበር፤ ራሴን ያመኛል ምግብ መብላት አልቻኩም ብሎ በተጨነቀበት ሰዓት እግዚአብሄርን ለምነን ነበር…. ሚሊየ “ወይኔ ከሀገሬ እንደወጣሁ ልሞት” ብለህ እንደፈራህ እውን ሆኖ ተለየኸን፡ ምን ማድረግ እና ለማን መደወል እንዳለብን ማወቅ ሳንችል በሰው ሀገር እንደልባችን ማልቀስ ሳንችል ወደየትኛው ቤታችን አስክሬንህን ይዘን መሄድ እንዳለብን ግራ ገብቶን መሃል ሆስፒታል የሰው ያለህ ብለን ብንጮህም ሰሚ አጥተን…ሀገር ማለት ፣..ሰው ማለት ….ስደት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አንተን ውድ ጓደኛችን አልፈህ …ምን ማድረግ ለማን መናገር እንዳለብን ግራ ገብቶን ሁላችንም ከአስክሬንህ ጎን አለን ….፡፡ከተሳካልን በክብር ለሀገርህ አፈር እናበቃሃለን፡፡ ሚሊ እስከመጨረሻው ሰዓት ይሄ ይመጣልን ብለን አልበቅንም፡፡ ግን በፈጣሪ ስራ መግባት አንችልም፡፡ ቤተሰቦችህ ምን ይሉ እህት እንዴት ትችዋለች.. ለልጅህ እንዴት ይነግሯት ይሆን…ለጓደኞችህ እንዴት ብለን….
ጋዜጠኛው ስደተኛው ሚሊ ቁመህ ወጥተህ በሳጥን አሽገን እንዴት እንደምንልክህ ዛሬም በሰው ሃገር ሰው በሞላበት የሰው ያለህ እያልን ነው፡፡ ሚሊ ፈጣሪ ነፍስህን በገነት እንደሚያኖራት አምናለሁ፡፡ በሞትህ መጨረሻ ቀናት በድካም 1 ቀን በፊት መድሃኒያም ቤተክርስቲያን ሄደህ ጸበል ተጠምቀህ ንስሃ ገብተህ በብጹህ አባታችን ቅባ ቅዱስ ተደርጎልህ ነበር፤ “ይቅር ላላችኋቸው ይቅር እላቸዋለሁ” ይላልና መጽኀፉ ፤ ፈጣሪ በሰማይ በመልካም ቦታ እንደሚያኖርህ አምናለሁ፡፡ ቤተክርስቲያን ሆነን የጸለይከውን ድህነት በሰማይ እንደሚከፍልህ አመንኩ፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ የነበረህን ተስፋ ፈጣሪ በሰማይ ቤት እንደሚሰጥህ አመንኩ፡፡ ከቤተክርስቲያን ከህመም እንዲያሳርፍህ የጸለይከውን ጸሎት በሰማይ በሰላም ያሳርፍ ዘንድ አመንኩ፡፡
እሽ ሌላ ምን ልበል ..ሚሊ የሃገርህ ሰማይ እንደናፈቀህ ሀገሬን እንዳልክ ነገን በተስፋ እንዳየህ ላይሳካ መኖር ሳትጀምር መንገድ አጭር ሆኖ በዚህ ተቋጨ፡፡ የመኖርህን የመጨረሻ ቀናት በስደት ሞት…በስደት ሞት… ከቤተሰብ ርቆ ህመምን አየህ፡፡ በስደት እንኳን ለቅሶ እንኳን ህመም መልካም ነገር መልካም አልነበረም …ሚሊ እውነት ይሆን…እንደ አፈታሪኩ ሞትህን “ለማመን ስትቅበር የማየት” እድሉ ባይኖረንም ፈጣሪ አስክሬንህን ለሃገርህ ለማብቃት ሃይል ይስጠን …
መታመምህን ሰምተው…ስደትህን ሰምተው ጭንቀትህ ሰምተው ሳይጨርሱ ሞትህን የሰሙት ምን ይሉ ይሆን …እኛ ሁሉም ነገር ጨልሞብናል ሚሊየ ድንገተኛ ህመም አፋጥኖ ላፈር አበቃህ፡፡ አሁንም የስደት ጣጣውን ፈጣሪ ሸፍኖ ለሃገርህ አፈር ያብቃህ፤ ሚሊ ሚሊ ሚሊ ስደተኛው ጓዴ ሚሊ ሚሊ……….. ሚሊ

by Samuel Ali

Mili

‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››
‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው››
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ
*******************************
‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡

Temu 2Temu 3
ከተሜ ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ተወያይተናል፣ በተወሰኑ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በየግል እምነቶታችንን በማንሳት ሃሳቦችን ተለዋውጠናል፡፡ ጥያቄዎችን አንስተን ምላሾችን ተደማምንም ነበር፡፡ …
ተመስገን፣ በመጨረሻ ካነሳቸው ሀሳቦች መካከል ጥቂቱን እንዲህ ላስነብባችሁ፡-
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ ‹‹በአሁን ወቅት የእስር፣ የስደት፣ …ወዘተ ነገሮች መብዛት ሰላማዊ ትግል ሥራውን እየሰራ መሆኑን ማሳያ ነው›› ያለው ትክክል ነው፡፡ እኔም ይህንን የእስክንድርን ሃሳብ እጋራለሁ፡፡ የእስር መብዛት ወደፊት፣ ነገ ላይ በሀገራችን የሚያመጣው ለውጥ አለ፡፡››
ተመስገን፣ እስከግማሽ ቀን ድረስ በዚሁ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረ ሲሆን፣ ከሰዓት በኋላ ወደቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚሄድ ነግሮናል፡፡
ተሜ፣ የሚመጣውን ነገር ሁሉ በሀገሬ ሆኜ እቀበላለሁ ላልከው ጽናትህ ትልቅ ክብር እሰጥሀለሁ!
ብርታትና ጥንካሬውንም ይበልጥ ፈጣሪ ይስጥህ!
***FJ 2007****