Archive | November 2014

ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የከንቲባው ቢሮ በነገው የተቃውሞ ስብሰባ እየተወነጃጀሉ ነው

የመስተዳድሩ ከንቲባ ጽ/ቤት ሠማያዊ ፓርቲን በጥብቅ አስጠንቅቋል

/አዲስ አድማስ/ ዘጠኝ የ9 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነገ እሁድ የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ የእውቅና ጥያቄውን የሚቀበል የመንግስት አካል ቢያጣም ስብሰባውን ከማከናወን ወደኋላ እንደማይል አስታውቋል፡፡ የከንቲባ ፅ/ቤቱ ቀደም ሲል ህዳር 7 ሊካሄድ የነበረውን የአደባባይ ስብሰባ ተከትሎ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሠጥቷል፡፡
ነገ እሁድ ህዳር 21 ቀን የአደባባይ ስብሰባ ለማካሄድ በመኢዴፓ በኩል የእውቅና መጠየቂያ ደብዳቤው ለአዲስ አበባ መስተዳድር የከንቲባ ለመስጠት በተደጋጋሚ ሞክረው አለመሣካቱን ገልፀዋል፡፡ የከንቲባ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ደብዳቤውን ሊቀበሉን ፍቃደኛ አልሆኑም ያሉት የተቃዋሚ አመራሮች “ቢሮ ውስጥ ደብዳቤውን ስናስቀምጥ ‹ወንጀል ነው› በማለት ሃላፊው ሊያስፈራሩን ሞክረዋል” ብለዋል፡፡
ደብዳቤውን ህዳር 12 ቀን በኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት የፈጣን መልዕክት (ኢ.ኤም.ኤስ) አገልግሎት ልኮናል ብለዋል አመራሮች ነገር ግን አንድም የመስተዳድሩ አካል ደብዳቤውን ለመቀበል ፍቃደኛ እንዳልሆነ ከፖስታ አገልግሎቱ እንደተገለፀላቸው የትብብሩ አመራሮች ሰሞኑን በሠማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
በነገው እለት ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ስብሰባ ትብብሩ እንደማይሠርዝ የገለፁት ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ደብዳቤውን በድጋሚ ወደ ከንቲባ ጽ/ቤት በአካል ይዘው እንደሚሄዱና የማይቀበሏቸው ከሆነም በሩ ላይ እንደሚለጥፉ ገልፀዋል፡፡ የአንድ ወር ጊዜ ተይዞለት በትብብሩ የተጀመረው የአደባባይ ስብሰባ ዘመቻ “ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” በሚል መርህ ከምርጫ በፊት “ስለ ፖለቲካ ምህዳሩ” እና ብሔራዊ መግባባት እንዲሁም ምርጫው ነፃ ፍትሃዊ፣ አሣታፊ፣ ተአማኒ መሆን በሚችልበት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በማሰብ የተጀመረ መሆኑን አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል በሠማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት ህዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ “የትብብሩ አባል በሆነው ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” በሚል መርህ የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ተጠርቶ የነበረ ሲሆን ስብሰባው ጥቂት ሠዎች በተገኙበት ከተጀመረ በኋላ በፖሊስ መበተኑ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ስብሰባውን ሲያስተባብሩ ነበር የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ፍ/ቤት ቀርበው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው መባሉ ተጠቁሟል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት በቀን 11/03/07 በቁጥር አ.አ/ከፅ/03/304/43 በሠማያዊ ፓርቲ “የተደረገውን ህገወጥ ተግባር በማስመልከት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ” በሚል በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው ምንም አይነት የአደባባይ ስብሰባ እውቅና እንዳላገኘ እያወቀ ህዳር 6 ቀን 2007 ዓ.ም የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት በመበተንና ህገ – ወጥ የአደባባይ ስብሰባ ለማድረግ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር አላስፈላጊ ግብግብ በመፍጠርና ጩኸት በማሰማት የአካባቢውን ህብረተሰብ ፀጥታና ሠላም የማወክ ተግባር ተከናውኗል ብሏል፡፡ ድርጊቱም ፓርቲው ህግን ተከትሎ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በህገወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ያለ መሆኑን እንደሚያሳይ በደብዳቤው የጠቆመው ጽ/ቤቱ፤ በቀጣይ ፓርቲው ህግን አክብሮ የማይንቀሳቀስ ከሆነ ድርጊቱ ፀረ – ህገመንግስት ስለሆነና የከተማዋን ህዝብ ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ አስጠንቅቋል፡፡  “የእውቅና ስጡን ጥያቄያችንን የሚቀበለን አካል አጣን” የሚለውን የተቃዋሚዎቹን አቤቱታ በተመለከተ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉትን የስራ ኃላፊ በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ስብሰባ ላይ ናቸው በመባላችን ሊሳካልን አልቻለም፡፡

ስለደፈራ፤ ደፈር ብለን ስናወራ (በእውቀቱ ስዩም)

ኣስገደዶ መድፈር በእንስሳት በኣሶች እንዲሁም በነፍሳት ኣለም ውስጥም ይስተዋላል፡፡ይልቁንም ለሰው እሩብ ጉዳይ በሆኑ ዝንጀሮዎች ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ተፈጥሮ በደፋሪነት ያጨቻቸው ባብዛኛው ወንዶችን ቢሆንም ሞገደኛ እንስቶችም ኣልጠፉም፡፡ለምሳሌ ወንዱ ንብ ከሴቷ ጋር ሲሳረር ሴቲቱ በዚያ ነገር ቆልፋ ትይዝበታለች፡፡በጦዘ ስሜት ውስጥ ሆና ኣልመዝምዛ ትቆርጥበታለች፡፡ወይም በጅንኖች ኣባቶቻችን ኣነጋገር ትሰልበዋለች፡፡ኮርማው ንብ በጀንደረባነት የመቀጠል እድል የለውም፡፡ በደረሰበት ጥቃት ያልጋ ቁራኛ ማለቴ የቀፎ ቁራኛ ሆኖ ይሞታል፡፡ሰራተኛ ንቦች ኣስከሬኑን ከቀፎው ጠርገው ወደ ውጭ ይጥሉታል፡፡

ኣብሬሽ ኣድሬ ሲነጋ ልሙት
ላፈር ኣይደለም ወይ የተፈጠርኩት
የሚለው የሙሉቀን መለሰ ዘፈን የኮርማ ንቦችን ህይወት በደንብ ይገልጣል፡፡

ኣስገደዶ መድፈር ባገራችን ትልቅ ጣጣ ሆኖ ይቆያል፡፡ምክንያቱም ወደ ጣጣው የሚያደርሱ ብዙ መንገዶች ኣሉ፡፡
ሲጀምር መናጢ ደሃ ነን። ሀብትና ስልጣኔ ባላቸው ሃገሮች የሴት ልጅን ዳሌ ላመል ያክል ነካ ካደረግህ ኣዳርህ ዘብጥያ ነው፡፡ኣገራችን ኢትዮጵያ ግን ቺስታ ናት ፡፡ያንድን ልጃገረድ መቀመጫ የሚጠብቅ የፖሊስ ግብረሃይል ማሰማራት የሚያስችል ሃቅም የላትም፡፡ሃቅም እንኳ ቢኖራት ባህሉ የላትም፡፡ የቤተመንግስቱን በር እንጂ ያንድን ሴት ገላ መጠበቅን እንደ ብሄራዊ ግዴታ የሚቆጥር ፖሊስ የለም፡፡
ባገራችን በዋናነት የሃብት ምንጭ ጉልበትና ህገወጥነት ነው፡፡ይባስ ብሎ፡ ባገሪቱ ውስጥ ያለው ሀብት ባብዛኛው በገልቱ ወንዶች እጅ ነው፡፡እኒህ ዲታ ወንዶች ድሃ ሴቶች ላይ ያሻቸውን ለማድረግ ኣቅም ኣላቸው፡፡ከሳሾችን ጸጥ የማሰኘት ጉልበት ኣላቸው፡፡የሀና ገዳዮች የተጋለጡት ወንጀላቸውን የሚሸሽጉበት ሃቅም ስለሌላቸው እንጅ እመቤት ፍትህ ፈጥኖ ደራሽ ስለሆነች ኣይደለም፡፡ተጠቅተው ያለ ኣለኝታ የቀሩትን ምኝታ ቤት ይቁጠራቸው፡፡
ሲቀጥል፤የትምርት ስርኣታችን ወንድ ኣንግስ ነው፡፡ሴት ልጅ የራሷ ነጻ ፍቃድ ያላት ፍጡር መሆኗን እያስረዳ የሚያንጽ የትምርት ስርአት የለንም፡፡ውጤቱ በእለት ተእለት ኣስተሳሰባችን ውስጥ ይታያል፡፡ብዙዎቻችን ሴቶችን” ሚስት እናት ገረድ” ከተባሉት መደቦች ባሻገር አናስባቸውም፡፡ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ሴቶች ለሚይዟቸው መኪናዎች የሚሰጡ ስሞችን ኣስታውስ፡፡ኣንዷ መኪና” በእምሴ” ትባላለች፡፡ሴት በላቧ፤ጥራ ቆጥባ እቁብ ጥላ መኪና ልትገዛ ኣትችልም ከሚል ኣስተሳሰብ የመነጨ ስያሜን ነው፡፡
ኣንድ እውንተኛ ታሪክ እዚህ ላይ ላንሳ፡፡

ባገራችን መሚገኙ ከተሞች ባንዱ ውስጥ(ካርበኞች ጋር ኣላስፈላጊ ሙግት ውስጥ ላለመግባት የቦታውን ስም ዘልየዋለሁ)ኣንዲት ልጃገረድ በሰባት ጎረምሶች በፈረቃ ተደፈረች፡፡ይግረማችሁና ተኣምር በሚያሰኝ መንገድ ተረፈች፡፡ከህመሟ ኣገግማ መንቀሳቀስ ስትጀምር ግን ነዋሪዉ ኣለኝታነቱን ነፈጋት፡ኣንድ ቀን ከተማሪ ቤት ስትመለስ” ሰባት ጎራሽ” የሚል ስም ተወረወረባት፡፡ኣዲሱ ስሟ ከደፋሪዎች ይልቅ ተደፋሪዋን ባለጌ ኣድርጎ የሚያሳይ ነበር፡፡ቀስ በቀስ” ሰባት ጎራሽ” የሚለው ስም እንደ ተስቦ ተዛመተ፡፡ልጂቱ የሰባቱን ወንዶች ደፈራ መቋቋም ችላ ነበር፡፡ህብረተሰብ ተረባርቦ ሲደፍራት ግን ብርክ ያዛት፡፡ከእለታት ባንዱቀን ኣገር ለቅቃ ተሰደደች፡፡

አስገድዶ መድፈር ዋና መንስኤ የብልግና ፊልሞች መስፋፋት መሆኑን ገልጸው በፊልሞች ስርጭት ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚሰብኩ ኣሉ፡፡ይህን ምክር መቀበል አለመቀበል ስለሰው ተፈጥሮ ባለን አመለካከት ላይ የተመሰረተ ይመስለኛል፡፡ ሲመስለኝ፤ሰው ምናብ የሚባል ነገር ይዞ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ የብልግና ስእል ይፈጥራል፡፡የሆሊውድ ጠረን ከማይደርስበት እልም ያለ ገጠር ውስጥ ልጆች እንካስላንትያ ሲጫወቱ የሚያወጡት ብልግና እግዚኦ የሚያሰኝ ነው፡፡እኔና ኣብሮ ኣደጎቼ በልጅነታችን ሁለት ብልት ስላለው የቆሎ ተማሪ የሰማነው ተረት ከ ፕሌይ ቦይ መጽሄት የተቀዳ ኣልነበረም፡፡
በጥንታዊ የውትድርና ስርኣት ውስጥ ከመደበኛው ወታደር የተለየ፡ ሳይታዘዝ የሚዘምት የሰራዊት ዘርፍ ነበር፡፡ፋኖ ይባላል፡፡ዲሲፒሊን የማያውቅ ሀላፊነት የማይሰማው ከየት መጀመርና የት ላይ ማቆም እንዳለበት የማያውቅ ስድ ነው፡፡የሰው ኣእምሮም እንዲሁ ፋኖ ሀሳብ ያዘምታል፡፡ፋንታሲ ይሉታል ሳይኮሊጂስቶች፡፡ የብልግና ፊልሞችን ድርሰቶች የፋኖ ሀሳባችን ነጸብራቅ ናቸው፡፡ወደድንም ጠላንም ሰው የሚባለው ጣጠኛ ፍጡር እስካለ ድረስ ይኖራሉ፡፡ስለዚህ ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ ለማደረግ እንዳይሞክሩ ማሰልጠን እንጂ ሀሳባቸውን እንድያስወግዱ ማድረግ የሚቻል ኣይመስለኝም፡፡
ባንድ ወቅት በኣምስተርዳም ከማስረሻ ማሞ ጋር ስዞር የሰው ሰራሽ- ብልት መሸጫ ሱቅ ተመለከትሁ፡፡የመጀመርያው ስሜቴ ጉደኛው እግሬ ምን ኣይነት ቅሌታም ኣገር ላይ ጣለኝ የሚል ነበር፡፡ እየቆየሁ ሳስበው ሃሳቤን ለወጥሁ፡፡ባንድ ኣገር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በተፈጥሮ የሩካቤ ስሜት ኣላቸው፡፡ግን ሁሉም ወንድ ሴት የመጥበስ እድል የለውም፡፡ሁሏም ሴት በወንድ ደረት ላይ የመተኛት እድል ላይገጥማት ይችላል፡፡ዋናው እስኪገኝ ድረስ ባምሳሉ ከማዝገም ውጭ ምን ኣማራጭ ኣለ፡፡የተጠሙ ሰዎች እምቢባዮችን ኣስገደደው ለመርካት እንዳይነሳሱ ማገጃ ዘዴ ይሆን?

ባገራችን ብቸኛው የስነምግባር ምንጭ ሃይማኖት ነው፡፡የእምነትን በጎ ገጽ ግለሰቦችን ለመግራት ኣስፈላጊ ነው፡፡ያም ሆኖ ለእምነት ሃይሎች ያለን የተጋነነ ኣመኔታ የማታ የማታ ዋጋ የሚያስከፍለን ይመስለኛል፡፡ለምን? ምክንያቱ ግልጥ ነው፡፡የሃይማኖት ኣባቶች የመኖራቸውን ያክል የሃይማኖት እበቶችም በየቦታው ኣሉ፡፡
በዚህ ጉዳይ ኣንድ ሁለት ተምሳሌቶችን ጠቅሼ ዞር ልበል፡፡

የመከራ ቀንበሩን ያቅልለትና ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ቆይታዎቹ ባንዱ ከሁለት ሽሜ እስረኞች ጋር ተገጣጥሞ ነበር፣ የመጀመርያው ስድስት ኣመት ህጻን የደፈሩ ሼህ ሲሆኑ፡ ሁለተኛው ብልታቸውን ማር በመቀባት ህጻናትን ሲያጠቡ የተገኙ መርጌታ ናቸው፡፡የመርጌታን ስልት የፈረንሳዩ ወፈፌ ማርኬስ ደ ሳድ እንኳ የደረሰበት አልመሰለኝም፡፡
ኣዲስ ጉዳይ መጽሄት ባንድ ወቅት በወንጀል ኣምዱ ኣንድ ታሪክ ኣስነብቦ ነበር፡፡ታሪኩን ኣሳጥሬ ስተርከው የሚከተለውን ይመስላል፡፡ሰውየው ፓሰተር ነኝ ብሎ ካንድ ቤተሰብ ጋር ይተዋወቃል፡፡ጥቂት ሳይቆይ ከመላው ቤተሰብ መካከል ልጃገረዶቹን መርጦ ጸለየላቸው፡፡ ከዚያም ሶፍት ዌር ይመስል እጄን ካልጫንኩባችሁ ኣላቸው፡፡ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ የሰራ ኣከላቱን ጫነባቸው፡፡ፖሊስ ጫኝና ኣውራጁን ፓስተር በቁጥጥር ስር ባዋለበት ወቅት ከተደፈሩት ሴቶች መካከል ኣንዷ ራሷን ሰቅላ ነበር፡፡

በመጨረሻም
በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ምክር የማያለዝባቸው፣ ትምርት የማይቀይራቸው ጉዶች ይኖራሉ፡፡የተሻለው መንገድ ልጆቻችንን የኒህ ጉዶች ሙርጥ የማይደርስበት ቦታ ላይ መቀመጣቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ወላጅ የማያንቀላፋ የልጆቹ እረኛ መሆን ግዴታው ነው፡፡

ሀና ላላንጎ የተደፈረችው ሺሻ ቤትውስጥ ነው!

ይህንን መረጃ ያገኘሁት ጦርሀይሎች ሙሉ ወንጌል ከሚገኘው የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ነው፡፡ከታሰሩት አንዳንዶቹ የእነዚሁ መረጃ ሰጪዎችም ጓደኞች ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች የነገሩን ምንነት ከፖሊስም በላይ የሚያውቁ ናቸው ቢባል ሀሰት አይሆንም፡፡የነገሩኝን ነገር እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡በ21/1/07 ዓም ምህረት ሀና በሴት ጓደኛዋ ምክንያት ያለ ወትሮ በምሳ ሰአት ወደ ቤት እንሂድ ብለው ያመራሉ፡፡ ይህ ሀሳብ የተፈጠረው በጓደኛዪቱ ሲሆን ቀድማ በሀና ጉዳይ ከአንድ ሹፍሬ ጋር ተስማምታ ነበር፡፡ ምሳ ይዛ ስለማትመጣ ምሳ እንብላ ብያት ይዣት እመጣለሁ ያኔ ትቀላጠፋለህ በሚል፡፡ ሀና እንደተባለው ወጥመድ ውስጥ ገባችና ጓኛዋ አዘጋጅታቸው በነበሩ ሰዎች መስመር ውስጥ ገባች፡፡ አብረው ወደ ጦር ሀይሎች ጉዞ ተጀመረ፡፡ ሀና፣ ጓደኛዋ፣ ሹፌርና አንድ ረዳት፡፡ሀና ከመውረጃዋ ራቅ ብላ መሄዷ በክፉ አልጠረጠርችውም ፣ ብታቅማማም በጓደኛዋ ግፊት ግን ቶሎ እንመለሳለን ዛሬ ስለደበረን ሻይቡና ብለን ልክ በሰአታችን ወደ ቤት እንሄዳለን ብላ ካግባባቻት በኋላ ጉዞው ቀጠለ፡፡ ችግር የለም ልክ በሰአቱ እኛ እናመጣቿለን፣ ሰፈራችሁ ድረስ እናደርሳቿለን ተብለው ተነገሩ፡፡ የጉዞ መጨረሻ ሙሉ ወንጌል ታክሲ ታራ ነበር፡፡ እዛው ያ እነ ሀና ይዞ የመጣው ታክሲ ለሌላ ሹፌር ተሰጠና እነ ሀና ይዘዋቸው ከመጡት ሰዎች ጋር ከጋና ኤምባሲ ወረድ ብሎ ወደ ሚገኝ ቤት ሆነ፡፡ ተገባ፡፡ውስጥ ሌሎች ወንድችም ነበሩ፡፡ጫት ና ሺሻ እንደ ጉድ የሚደራበት ቤት ነው፡፡የሀና ጓደኛ ከዚህ በፊትም ልማድ አላት ብሎኛል ይህንን ያስረዳኝ ሰው፡፡ ሀና ግን የመጀመሪያዋና ትንሽ እዚህ እንቆይና እንመለሳለን ተብላ ሻይ ተፈልቶላት እዛው ..አትፍሪ ተጫወቺ እየተባለች ቆይታለች፡፡

ጪሱ ጪሳጪሱ የማራት አይመስለም፡፡ ሀና እየቆየች እየደከማት፣ እንቅልፍ እንቅልፍ እያላት ሄደ ከዛም ውስጥ ወደሚገኝ መተኛ ቤት አስገቧት፡፡ ይዟትም የገባው መጀመሪያ ሹፌሩ ነው ፡፡ ሀና ሰውነቷ ሞላ ያለ በሺሻ ቤት አንደበት ያልተበላችና ያረገበች ልጅ ነው የምትባለው፡፡ ከሹፌሩ በኋላም ሌሎች ተከታትለው ገብተው ድርሻቸውን ወስደዋል፡፡የሀና ጓደኛም እዛው ሌላ ክፍል ከሌሎች ወንዶች ጋር ነበረች፡፡ ያ አሺሺ ያነወዘው ስሜት ሀናን ስቃይ ውስጥ ከቷታል፡፡ በዚህ አይነት ጊዜው እየገፋ ሳለ ተማሪዎች የሚለቀቁበት ሰአት ደረሰ፡፡ሀና መንቃት አልቻለችም፡፡እንደ ሌሎቹ ብድግ ብላ እራሻን ጠራርጋ የምትዘጋጅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ቢባል ቢባል አልተቻለም፡፡ ታክሲ መጣ ፡፡ ቢያንስ ታነክሳለች ተብሎ ነበር የተጠበቀው እሷግን ካለችበት መነሳትም አልቻለችም፡፡ እንዲህ ሆና እንዴት ነው የምንወስዳት ተባለው እዛው ውይይት ተጀመረ፡፡ ጓደኛዋ የሆነ መላ ፈጥራ ሀኪም ቤት እንድትወስዳት ሀሳብ ተነሳ፡፡አይሆንም ለብቻዬ እፈራለሁ አለች፡፡ በቃ እስከማታ ልትነቃ ትችላለች እስከዛ አንዳችን ቤት ትረፍ ተባለ፣ ሹፌሩ ባለትዳር ስለሆነ ወደእሱ ቤት አይታሰብም፡፡ ሌላኛው እኔ ዘንድ ትሂድና ትረፍ ብሎ ተቀበለ፡፡ ሀናን ተሸክመው ጫኗት፡፡ የሀና ጓደኛም ምንም እንደማያውቅ ምንም እንደሌለ መስላ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ ከወላጅ ተደውሎ ተጠየቀች አላውቀው አለች፡፡ ከልጆቹ ተደውሎ እስካሁን እንዳልተሸላትና እዛው እንደምታድር ተነገራት፡፡

እንደዚህ የሆነችው ለነገሩ አዲስ ስለሆነች ነው በደንብ ከተደረገች ይሻላታል ተብሎ ማታም በቁስሏ ላይ ቁስል ተጨመረባት፡፡አደረችበት፡፡ ቤተሰብ እስከ ትምህርት ቤት ሄዶ ነገሩን ለማጣራት ተሞከረ፡፡ መልስ አልተገኘም፡፡ ጓደኛ ተጠየቀች፡፡ መልስ የለም፡፡ ሌሎች የክፍል ልጆች ግን አብረው እንደነበሩና አብረው ሲሄዱ እንዳያቿው ተናገሩ፡፡ የክፍል ሀላፊው በፖሊስ ተያዘ፡፡ በጓደኛዋም ላይ ክትትል ቀጠለ፡፡ እስከዛ ጊዜ ድረስ ግን ጓደኛ የተባለችው ልጅ ለሀና የምትቀይረው ልብስ እንደወሰደችላት፣ እየተመላለሰችም ትጠይቃት እንደነበረ ታውቋል፡፡ ይህንን ሁሉ ለወላጅ ባትናገርም፡፡ በአምስተኛ ቀን ፖሊስ አጨናንቆ ሲጠይቃት የሆኑ ልጆች በስልክ እየደወሉ እሷን እንደሚያስፈራሯትና ታክሲ ተራ አካባቢ የሚከታተሏት እንዳሉ አድርጋ ተናገረች፡፡ስልክ ቁጥሩንም ለፖሊስ ሰጠች፡፡ እስከ አምስተኛው ቀን ያለው በዚህ አለቀ፡፡

ከዛ በኋለ ፖሊስ የስልክ ቁጥሩን ባለቤት ሲያፈላልግ ጥቆማ ደረሰው፡፡እነዛ ጠቋሚዎች እራሳቸው ሀና ላይ ሲከመሩ ከነበሩ ታክሲ አስከባሪዎች መካከል ናቸው፡፡ ታክሲ ተራ ወንጀል መደባበቅና ከፖሊስ ጋርም መሞዳሞድ ያለ ነው፡፡ ስልክ ቁጥሩ የታወቀበት መረጃ ደረሰውና ከአካባቢው ተሰወረ፡፡ ለፖሊሶች አዲስ ሀሳብም መጣ በቃ ልጅቷን ይለቋታል እናንተ ወላጆቹን አሳምኑልን የሚል ነገር፡፡ ፖሊስም ነገሩን ጠለፋ አድርጎ ስለወሰደውም ጭምር ነገሩ በሰላማ የሚፈታ ከሆነ ብሎ ለተከታታይ አምስ ቀናት ወላጆችን የማጽናናትና እየደረስንበት ነው ታገሱ እያሉ ቆይ፡፡ ሌላ አምስት ቀንም ቢጨመርበት የሀና ቁስል እያመረቀዘ ሄደ፣እራሷን መቆጣጠር ሳትችል ቀረች፡፡ፖሊስ ቀነ ገደብ ሰጣቸው ለአፋኞቹ፡፡ በቶሎ ካለቀቃችሁ እርምጃ እንወስዳለን የሚል፡፡ በመጨረሻ በ11ኛው ቀን ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አካባቢ በታክሲ አምጥተው ጣሏት፡፡የሐና ጓደኛጨምሮ ሌሎች ሁለት ወንጀለኞች በዛው ታክሲ ከአካባው ተሰወሩ፡፡ የሐና እዛው መጣል ወላጅ ዘንድ ደረሰ፡፡ሄዱ፡፡ፖሊስ ነገሩን እንደማያውቅ ሆኖ ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ነገሩን የአየር ጤና አካባቢ ፖሊስ የነበረ ቢሆንም የሚከታተለው ልጅቷን ከማትረፍ ይልቅ ልጆቹን ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት አድረጓል፡፡

አሁን ወደ እነዛ ታክሲ ተራዎች ስትሄዱ ልጅቷ የተደፈረችው በአምስት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እዛ በሺሻና በጫት መርቅነው የነበረና ለጋ ገላዋን እያዩ ምራቅ ይውጡ የነበሩ ሁሉ ናቸው፡፡ ከአምስት በላይ፡፡አስገድዶ በመድፈር ሁሉም ወንጀሎች ቢሆንም ልጅቷን ለሞት የሚያደርስ ወሲብ የፈጸሙባት ሰዎች ግን ከፖሊስ ጋር ተባባሪና ጠቋሚ መስለው በመቅረባቸው እስካሁን አለመያዛቸውን እየተናገሩ ነው፡፡በተለይ ልጅቷ ወሲብ ሲፈጸምባት ለብዙ ሰአታት እራሷን ስታ ስለነበረ በእሷላ ላይ በትክክል ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱትም ወንጀለኞች መለየት አትችልም፣ ፖሊስ ግን ጥቆማ ተሰጥቶታል ሊቀበል ግን አልፈለገም እየተባለ ነው፡፡ በተለይ የጉሮሮና የፊንጢጣ ችግር ያደረሡባት ሰዎች ተጠቃለው አልታሰሩም፡፡ፖሊስ ልጅቷ በሺሻ ቤት መደፈሯንም እንዲነገርበት አይፈልግም፡፡ ወላጆችን ተጽናኑ እየተገኙ ነው ብሎ ከወንጀለኞች ጋር ሲደራረር እንደነበረም እንዲታወቅበት አይፈልግም፡፡ ሀና ጦር ሀይሎች አካባቢ የተጣለችውም ፖሊስ ያደርገው በነበረው ድርድር መሆኑንም እንዲታወቅበት አይፈልግም፡፡ እዛ መጣሏን እያወቀ ልጅቷን ወደ ሀኪም ቤት ከመውሰድ ይልቅ ወላጅ አባት ሳይቀሩ ሲያመለክቱ በዳተኝነት ነገሩን ለማድበስበስ የሞከሩትም ለዛ ነው፡፡እንዲሁም ፖሊስና የታክሲ ተራ የ1ለ5 አደረጃጀት መዋቅር እንዲፈርስ ስለማይፈለግ በሀና ላይ ችግር ያደረሱ ግን መረጃ በመስጠት ከፖሊስ ጋር የተባበሩ የተባሉ ወንጀለኞች እስካሁንም አልተያዙም፡፡የተያዙት ሀና በነቃ አእምሮዋ ሆና ችግር ሲፈጥሩባት ያየችውን ብቻ ነው፡፡

የሐናም ጓደኛ በተላላኪነት ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት እየመለመለች ለሌሎች የማስበላትና የማታለል ተግባሯ ፣ ወንጀለኞች ያሉበት ቦታና ማንነታቸውንም በደንብ እያወቀች ለወንጀል ተባባሪና ዱላ አቀባይ መሆኗ ግምት ውስጥ ሳይገባ፣ ለፖሊስ መረጃ መስጠቷና በተራ አስከባሪዎች ዘንድ ጥብቅና ስለተቆመላት አልተያዘችም፡፡የእሷ መያዝ ሌሎች አስወጊ ተማሪዎችምን ለስጋት ስለሚዳግና የጠማሪን ገላ የለመዱ ቡድኖችን አንሶላ ስለሚያረቁት እንዲሁም በተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው የወሲብ ንግድ ችግር ያጋጥመዋል ገቢያችንን ያስቀርብና ሰለተባለ ይመስላል(ፖስተን ማራቶን ላይ ቦምብ በተደረገ ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ወንጀሉን እያወቅ እንዳላወቀ ሆነሀል ተብሎ መከሰሱና እንደተፈረደበቴ ልብ ይለዋል)፡፡ፖሊስ ሀና ትማርበት የነበረውን ትምህርት ቤት ስም በመግለጫው እንዳይጠቀም በትምህር ቤቱ ልመና ቀርቦለታል፡፡ የሺሻ ቤት አላፊው አልተያዘም፣ ስሙም አልተነገረም፡፡ፖሊስ ከተወሰኑ ደጋፊ ሚዲያዎቹ ጋር ሆኑ ህዝብና ፍትህ ላይ እየቀለደ ነው፡፡ልመናው ምን እንደሚያጠቃልል ግን በደንብ አልተገለጸም፡፡

አሁን በሀና ጉዳ የፖሊስ ሚና እንዳየነው ፖሊስ እራሱ የወንጀል፣ በሴት ላይ ለሚደረግ ጥቃት ተባባሪ ብቻ ሳይሆነ ከፍ ያለ ተዋናይ ነው፡፡በዚህ አጋጣሚ ሀና ወደ ሀኪም ቤትም ሄዳ ህክምና ማግኘት አልቻለችም፣ ለሀና ሞት የህክምና ተቋማችንም በዋናነት የፖሊስ አሰራርም ጭምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ድርጓል፡፡ አሁን የእየሆኑ ያሉ ዘገባዎችና ዘመቻዎች ባብዛኛው ፖሊስ የሰራውን ወንጀል የመደበቅ ተግባር ነው፡፡ በሀና ጉዳይ ሳይነሳ መተው የሌለበት ግን ትማርበት የነበረው ትምህርት ቤት እንዴት ተማሪዎች በትምህርት ሰአት እንዲወጡ ለምን አደረገ ታማ ከሆነም የተፈቀደላት ለወላጅ ተደውሎ ለምን አልተነገረም የሚል ጥያቄ ነው!!

ከሀና ታረክ ጋር በተያያዘና የሳያት ደምሴንም ጉዳይ ማንሳት ይቻላል፡፡ ሳያት ደምሴ ከጥቂት አመታት በፊት ጦር ሀይሎች አካባቢ አፍሪካ ኮከብ ተብሎ በሚጠራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትማር ነበር፡፡ አስረኛ ክፍል፡፡ እንዲሁ በጓደኛ ግፊት ሺሻ ቤት ገብታ በታክሲ ሹፌሮችና ረዳቶች እንደተደፈረች እናስታውሳለን፣ ለሰባት፡፡ሳያት የተደፈረችበት ቤት እስካሁንም ፖሊሶች የሚቅሙበት ቤት ነው፡፡እንዳውም ቅርንጫፍ ሺሳ ቤት ከቶታል አማኑኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ያለው የራዲካል ት/ቤት ተማሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ይህ ሺሳ ቤት ከራካዲል ት/ቤት ቢያንስ በ400 ሜትር ርቀት ነው የሚገኘው፡፡በጋራጅ ስለተሸፈነ አይታይም ብዙ የት ይደርሳሉ የተባሉ ቆነጃጅት ሴቶች ገብተው በቡድን ሳይቀር የሚደፈሩበት ቦታ ነው፡፡

እኔ በግሌ ብዙ ጊዜ ለፖሊስ አመልክቻለሁ የሰማኝ ግን አላገኘሁም፡፡አሁን አሁን ሊፒስቲክ ተቀብተው እንደሴት የሚያደርጋቸው ወንዶች ሳይቀሩ ሲወጡበትና ሲገቡበት አያለሁ፡፡ እዚህም ባብዛኛው ተማሪዎችን እየቀጠፉ ያሉት፣አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮችና ረዳቶች እንዲሁም ስድ ጋራጅ ሰራተኞች ናቸው፡፡ቦታውን በደንብ ለመጠቆም ከራዲካል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ካለው የወጣቶች ማእከል አቅጣጫ ወደ ኮካ በሚወስደው መንገድ የገንዳ ማስቀመጫው አካባቢ ነው፡፡በጣም ብዙ ህጻናት የሚደፈሩበት ቦታ ነው፡፡ በሺሺ ቤት ምን ያህል የቡድን ወሲብ እንዳለ የሳያት ደምሴን ነገር ሰምተን በቀልድና በማላገጥ ማለፋችን አሁን በሀና ላይ ለደረሰው ነገር እንዳበቃን ልብ ልንልም ይገባል፡፡ ይህ ተማሪዎችን የማጥቃት ዘመቻ እስከ ትልልቅ ሆቴሎቻችን ድረስ እንደሚደርስ እንዲሁም በዚህ ነገር ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ ደላሎች እንዳሉበት እዴሜያቸው ሳይፈቅድላቸው በብርና በተማሪ ደላላ ተታለው ብዙዎች እየተቀጠፉ እንደሆነ በእነ ሀና ላይ የደረሰው ነገርም ሳይቅድሙን እንቅደማቸው በሚል ስሌት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ እንደእውነት የሀና መደፈር በሀገር ውስጥ ሰው መሆኑን እንጂ ህገወጥ ዕያልን ያለነው በየሆቴሉ የብዙዎች ህይወት እንደሚያልፍ ይህም ወንዶች ሳይቀሩ ያሉበት መሆኑን፣ይህም በተለያየ ጊዜ በቪሲድ ሳይቀር ያየነው እውነት መሆኑን የሚታወቅ ነው፡፡ ፍትህ ለተማሪዎቻን!!!ፍትህ ለሃዎች!! ፍትህ ለዜጎቻችን!!
————————————————————————–
ሀና መዳን ጀምራ ነበር ፍርድ ቤት ላይ ቆማ እንዴት እንደምትመሰክርም መለማመዷን ድግሞ አንድ ውስጥ ሌላ ሰው ያስታምም የነበረ ሰው እየነገረን ነው፡፡ ታዲያ ድንገት እየዳነች የነበረች ልጅ የሞተችው እንዴት፣ በማን ስህተትና ጥፋ ወይም ሸር ነው እንበል? ሀና ለምን በምን ሞተች? ስለተደፈረች?
————–
ሀና በዘውዲቱ ሆስፒታል!!

በሰይፈዲን ሙሳ

____________________

እህታችን ሀና ላላንጎ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ህክምና ለማግኘት ስትል የብዙ ሆስፒታል ደጆችን ረግጣለች። ለመጨረሻ ጊዜ ግን ህክምናዋን ስትከታተል የነበረውና ህይወቷም ያለፈው በዘውዲቱ ሆስፒታል ነበር።

ዘውዲቱ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ትከታተል በነበረበት ሰዓት በዚሁ በፌስቡክ ብቻ የማውቀው ወዳጄ ሀና የተኛችበት ክፍል ውስጥ የታመመች ጓደኛውን ያስታምም ነበር። እሱ ጓደኛውን ሲያስታምም የሀናን የህመም ስቃይ አብሮ ተጋርቷል። ብዙ የማይነገሩ ስቃዮች ነበሯት።ይሄ ጓደኛዬ ሀና በሆስፒታል ውስጥ የሆነቻቸውን ሁለት አጋጣሚዎች ለኔ በውስጥ መስመር ነግሮኝ ነበር። እኔ ደግሞ ለናንተ ልንገራችሁ።

አንድ!
_____

ፖሊስ ‘ወንጀለኞቹ ናቸው’ ብሎ ከያዛቸው ተጠርጣሪዎች መሀከል አንደኛውን ተጠርጣሪ ፖሊስ ጥርጣሬውን በማስረጃ ለማስደገፍ ሲል ዘውዲቱ ሆስፒታል ድረስ በካቴና አስሮ ተጠቂዋ ሀና ፊትለፊት አቆመው።

ተጠቂዋ ሀና ‘ተጠርጣሪ’ ተብሎ የመጣውን ‘ሰው’ ስታይ በጣም አለቀሰች። ‘አንደኛው እሱ ነው’ ስትልም እያለቀሰች አረጋገጠች!! ተጠርጣሪው ግን ካደ። ክፍሉ ውስጥ ያሉ አስታማሚዎች ካልገደልነው ብለው ተነሱ። ተጠርጣሪው መካዱ እንደማያዋጣው ሲያስብ ሌላ የሚዘገንን ምክንያት ሰጠ። በኋላ ግን አመነ። በዚያ ክፍል ውስጥ የአስታማሚዎች የታማሚዎች እምባና ጩኸት ሞላው። ፖሊስ ቃሉን ይዞ ተጠርጣሪውን እንደታሰረ ከሆስፒታሉ ይዞት ወጣ!!

ሁለት!
_____

የሀና ህይወት ከማለፉ በፊት ለነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ በአካል ተገኝታ ችሎት ፊት ቀርባ ቃሏን እንደምትሰጥና እንደምትመሰክር ከተነገራት በኋላ ‘ችሎት ፊት ስቀርብ እንዲዚህ ብዬ ነው የምናገረው’ እያለች በሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ ልክ ፍርድ ችሎት ውስጥ እንደቆመችና ዳኛው ፊት እንደቀረበች ሁሉ አክት እያደረገች ክፍሏ ውስጥ ላሉ ታማሚዎችና አስታማሚዎች ፊት ልምምድ ታደርግ ነበር!!

ሀና የሆነ ህልም ነበራት። ጥቃት ያደረሱባትን ወንጀለኞቹን በህግ ተፋርዳቸው ትክክለኛውን ፍርድ አስፈርዳና አስቀጥታቸው ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የእሷ አይነት በደል ለደረሰባቸው ሴቶች የፍትህ ተምሳሌትና ለመሆን ‘ከኔ በኋላ እንደዚህ አይነት በደል ይብቃ!” ለማለት!! ይመስለኛል!!

እናም ለሀና እና ለሀናውያን ትክክለኛና ፍትሀዊ ፍርድ እስኪገኝ ድረስ “ፍትህ ለሀናውያን” እንላለን!!

1404479_646583562131879_7860455378408838965_o

በሽብር የተከሰሱት የተቃዋሚ አመራሮች ዋስትና ተከለከሉ

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew

በሽብር የተከሰሱት የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የአረና ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ተከሳሾች፣ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ከትናንት በስቲያ በፍ/ቤት ውድቅ የተደረገ ሲሆን፤ አቃቤ ህግ የተጓደሉ ማስረጃዎችን አሟልቶ እንዲቀርብ ታዟል፡፡
ከወራት በፊት የታሰሩት ተከሳሾች፤ በዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ጥያቄያቸውን ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የልደታ ምድብ 19ኛ ችሎት ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የሁሉም ተከሳሾች ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በአቃቤ ህግ ክስ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል አንቀፅ የዋስትና መብትን የሚያስከለክል መሆኑን ፍ/ቤቱ ጠቅሶ፣ ሁሉም ተከሳሾች ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ሆነው ይከታተሉ ሲል ብይን ሰጥቷል፡፡
በእለቱ ጠበቆች ከክሱ ጋር ተያይዘው አንዳንድ ማስረጃዎች ያልተሟሉ በመሆናቸው፣ ተሟልተው ከቀረቡልን በኋላ ነው የክስ መቃወሚያ ማቅረብ የምንችለው በማለታቸው ፍ/ቤቱ አቃቤ ህግ ለህዳር 17 ጎደሉ የተባሉትን የማስረጃ ዝርዝሮች አሟልቶ ያቅርብ ብሏል፡፡

habtamu-ayalew
የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እና የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታን ጨምሮ በአስር ሰዎች ላይ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ነው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ተማሪ ዘላለም ወርቅአገኘሁን አንደኛ ተከሳሽ በማድረግ አቃቤ ህግ ያቀረበው መዝገብ፤ ተከሳሹ የግንቦት 7 አባል ነው ብሏል፡፡ ግንቦት 7 በመንግስት አሸባሪ ነው ተብሎ እንደተፈረጀ አቃቤ ህግ ጠቅሶ፣ ተከሳሹ ለግንቦት 7 ሰዎችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ሄደው እንዲሰለጥኑ አድርጓል፤ ህገ መንግስታዊ ስርአቱንና ማህበራዊ ተቋማትን በሽብር ለማፈራረስ ተንቀሳቅሷል የሚል ክስ አቅርቧል፡፡ አራቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ህጋዊ ፓርቲን እንደ ሽፋን ተጠቅመዋል በማለት አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ ደግሞ፤ ተከሳሾቹ ከግንቦት 7 አመራሮች ጋር በመገናኘትና በመመካከር የተለያዩ የሽብር ተልዕኮዎችን ተቀብለዋል የሚል ነው፡፡
በሌሎቹ ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስም የግንቦት 7 አባል በመሆን አላማውን ለማስፈፀም ተንቀሳቅሰዋል ይላል፡፡

በሃብታሙ አያሌው ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር (እንደወረደ)

habtamu ayalew
(ዘ-ሐበሻ) በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው በመንግስት አቃቤ ሕግ የቀረበበት የክስ ቻርጅ በፍርድ ቤት ተሰምቷል:: ሙሉው የክስ ቻርጅ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳል በሚል እንደወረደ ቀርቧል::
habtamu ayalew
habtamu sp


habtamu ayalew2habt 1
habtamu ayalew 1habt1
hab 7habt8habt9habtamu ayalew 4
habt 12habt13habtamu ayalew 5
habt15habtamu ayalew 6
habtamu ayalew 7
habtamu 19

እርስ በርስ መበላላት አቁመን በቅንነት አብረን እንሥራ

 

በመጀመሪያ ኢትዮጵያ አገራችን ዛሬ ለምትገኝበት አስከፊ ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታ ሆነ መንፈሳዊ ኪሳራዎች ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው ብለን ወቀሳችን፣ እርግማናችን፣ ዝልፊያችን እና ማስፈራሪያችን ሁሉ ወያኔ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። የሚያሳዝነው ታዲያ በጩኸታችን እና በእርግማናችን ለሁለት አሥዕርት ዓመታት የተሸከምናቸው ግፈኞች ከጫንቃችን ማውረድ አለመቻላችን አይደለም። ይልቁንም እስከዛሬ ድረስ ከመረጋገም፣ ከመጠላለፍ፣ ከመጯጯህ አባዜ ሳንላቀቅ ከወያኔ ጋር ያሳለፍነውን የሰቆቃ ዘመን እያደስን ማራዘማችን ነው። በወያኔ መንግሥት ሰብዓዊ መብት መጣስ ሃገርንና ሕዝብን ማዋረድ፣ ዘረኝነት ማስፋፋት፣ በሙስና የሃገሪቷን ሀብት በመመዝበር ሕዝቡ ግፍ ከፍቶት እንዲሰደድ ማድረግ ዓለም ያውቀዋል።ቀሪውም ዓለም እዚህ ያደረስነውን እኛንም ጭምር ነው። እንደኔ እምነት ይኼንንያደረግነው እኛው ራሳችን ነን። ምክንያቱም አንድ መሆን ስላቃተን ለወያኔ በተገዢነት ለመኖር ምቹ ሁኔታ ፈጥረንለታል። በአብዛኛው የኛ አገር ፓለቲካ ማንም የማያተርፍበት ፖለቲካ ነው። በተለይ ተወያይቶ አለመፍታት፣ ተደራድሮ አለመታረቅ፣ ተነጋግሮ አለመደማመጥ፣ ተባብሮ አለመሥራት፣ ተነጣጥሎ መውደቅ… ብቻ የእኔ ሀሳብና የፖለቲካ ርእዮት ብቻ ነው ትክክል ብሎ ማሰብ፣ ከእኔ ሌላ ለዚህች ሀገር የሚያስብና የሚለውጥ የለም ብሎ ማለትና መደንፋት የትኛውንም ድርጅት ከፍ ሲያደርግ ሳይሆን ሲያከስር ነው እስካሁን ያየነው። ወደፊትም በዚሁ ሁኔታ እስከቀጠልን ድረስ ለወያኔ አገዛዝ ምቹ ሆነን ትከሻችንን ለሸክም ማመቻቸት ነው።

3

በተለይ በተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ የሚሰማው የዜሮ ፖለቲካ ድምር ምክንያቱ ለአብዛኞቻችን ግልጽ ነው። በማን አለብኝነት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አንባገነን መሆናቸው እርስ በርስ አለመተማመናቸው፣ አንድ ላይ አለመሥራታቸው ነው። ሁሉም ለኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የሚሠሩ ከሆነ ለምን በአንድ ላይ ሕብረት ፈጥረው በአንድነት አይጓዙም?በቅንነት ለምን አይሠሩም?ለምንስ ሕዝቡ ይሄ ሁሉ መከራ በወያኔ ይደርስበታል? በዚሁ እስከቀጠልን ድረስ መቼም የማይፈታ የፖለቲካ ዜሮ ጨዋታ ነው የሚሆነው።

እንግዲህ እኛም እራሳችንን እንጠይቅ እኛስ ለሥርዓቱ አገሪቷን ፍትህ አልባ ሲያደርግ ሰብአዊ መብት ሲጥስ እያየን ከመጮህ በስተቀር ምን አደረግን?በተበላሸው የፍትሕ ሥርዓት ቀጥተኛ ተጠቂ የሆነውን ያህል ለሥርዓቱ ፍትሕ አልባ ሆኖ መቀጠል በአንድ ወይም በሌላ መንገድ አስተዋጽዖ ላለማበርከታችን እርግጠኞች ነን ወይ? ከወያኔ በተቃርኖ የቆምን ሃይሎች በቀረው ፍትሕ ናፋቂ የሕብረተሰብ ክፍል ውስጥ ለፍትሕ የተሰጠውን ግምትና ቦታ እያገኙ ነው ወይ የሚለውን መቃኘት ግድ ይላል።

Berhanu Baue

Germany

የአፍሪቃ ስደተኞች ህይወት በሲሲሊ

/ዶቼ ቬሌ/ ከአፍሪቃ በሜዲትራንያን ባህር አድርገው ወደ ኢጣሊያ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ምንም እንኳን አሁን ቀዝቀዝ እያለ በመጣው የአየር ጠናይ ሳቢያ ረገብ ቢልም፤ ከ መቶ ሺ በላይ ስደተኞች ባለፈው ዓመት ኢጣሊያ ገብተዋል።

Flüchtlingsaufnahmelager der Caritas in Palermo, Italien

« ለ 20 ሰዓታት ባህር ላይ ነበርኩ። ጀልባዬ ውሃ ስለገባባት ሞላች። ከዛ የባህር ኃይል አባላት ጋር ደወልኩ። የባህር ኃይሎቹ በ አምስት ደቂቃ ውስጥ እንደሚመጡ ነገሩኝ። የህይወት ማዳኛ መንሳፈፊያ ጃኬት ሰጥተውኝ ከባህር አወጡኝ። ህይወቴን ስላተረፉዋት ደስተኛ ነኝ።»

Flüchtlingsaufnahmelager der Caritas in Palermo, Italienታምቦ ከወራት ጉዞ በኋላ ነው ኢጣሊያ የገባው

በማለት ነው ታምቦ በዓለም አቀፉ የሊቢያ እና የሲሲሊ የባህር ክልል ውስጥ ሳለ ህይወቱ በኢጣሊያ ግብረ ኃይል እንዴት እንደተረፈ የገለፀው። የ18 ዓመቱ የማሊ ስደተኛ ኢጣሊያ የገባው ባለፈው ሰኔ ወር ነው። አሁን ከሌሎች 37 የአፍሪቃ ስደተኞች ጋር «ካሪታስ» በተባለው የካቶሊካውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት የስደተኞች ማቆያ ፤ ፓሌርሞ በተባለው የሲሲሊ ከተማ ውስጥ ይኖራል።

ታምቦ ከባህር ጠረፉ ወደ አሁኑ መኖርያ ሲመጣ ባዶ እጁን ነበር። አሁን ግን በርዳታ የተሰበሰቡ ልብሶች እና አንድ አሮጌ ስልክ እንዲሁም በጆሮ ማዳመጫ አግኝቷል። ሙዚቃ በስልኩ ያዳምጣል። በስደተኞቹ ማቆያ በነፃ ኢንተርኔት ይጠቀማል። ስልክ ግን ውድ ስለሆነበት ወደ አፍሪቃ አይደውልም። ነገር ግን ይላል ታምቦ « በኋትስ ዓፕ» አማካይነት ማሊ የሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ደህና መሆኑን የሚገልፅ መልዕክት ለእናቱ ይልካል።« እናቴ በህይወት አለች። አባቴ ግን ሞቷል። ስለዚህ ከእናቴ ጋር ልገናኝ እችላለሁ። እዚህ እንደሚገኙት እኔ ባለ ትዳር አይደለሁም። እናቴን ብቻ ነው አፍሪቃ የተውኳት።»

ታምቦ በማሊ በበርሃ አቋርጦ ሊቢያ የባህር ጠረፍ እንደደረሰ ይናገራል። በወቅቱ ተሳፍሮበት የነበረው ታክሲ መዘረፉ ብቻ ሳይሆን « አብረውኝ ተሳፍረው ከነበሩት ሰዎች መካከል የተገደሉም ነበሩ» ይላል ። ወጣቱ ሊቢያ ውስጥ ስራ ይሰራ ነበር። ይሁንና አረቦች እንደደበደቡት ነው የሚያስታውሰው። በመጨረሻም የእንጨት ጀልባ የሚሸጥለት ሰው አግኝቶ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ቆርጦ ተነሳ።

ፓሌርሞ የሚኖሩት ስደተኞች ተመሳሳይ ታሪክ ነው የሚናገሩት። እንደ ታምቦ ከማሊ የመጣው ማማዶ 24 ዓመቱ ነው። ወጣቱ ገበሬ በኢጣልያ ባህር ኃይል «ማሬ ኖስትሩም» አማካይነት ነው ከ5 ወር በፊት ከባህር ከመስመጥ የተረፈው። እሱ በተሳፈረበት የአሳ ማጥመጃ ጀልባ ላይ 115 ሰዎች ተሳፍረው ነበር። ለሁለት ቀን ያክል ጀልባ ላይ ከቆዩ በኋላ የሚበሉት እና የሚጠጡት እንዳለቀባቸው ማማዶ ይናገራል። እሱ የተሳፈረበትም ጀልባ ውኃ ስለገባበት አደጋ ላይ ነበሩ። ኋላም ጀልባዋ ልትሰምጥ ትንሽ ሲቀራት የኢጣሊያ የባህር ኃይል አዳናቸው።« ማሬ ኖስትሩምን ሊያቆሙ እንደሆነ ሰምቼያለሁ። ካቆሙት ከፍተኛ አደጋ ነው። የነፍስ አድኑን ቡያቆሙ እንኳን ሰዎች መምጣታቸውን አያቆሙም ብዬ አምናለሁ። ሰዎቹን ካላዳኗቸው ደግሞ ጀልባዎቹ መገልበጣቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጀልባዎቹ ጠንካራ አይደሉም። ከ አንድ እና ሁለት ቀናት በላይ እዛ ላይ መቆየት አይችሉም። ስለዚህ ካላዳንዋቸው ጀልባው ይገለበጣል። »

Palermo Flüchtlinge 5.ማማዶ ወደ ጀርመን ቢሄድ ምኞቱ ነው

ይህ ነው የማማዶ ዕምነት። ማሬ ኖስትሩም ስራውን ካቋመ 15 ቀናት አለፏ። ይህንን ግብረ ሀይል የተካው «ትሪቶን» አዲሱ የአውሮፓውያን የባህር ተልኮ ዋና ተግባር የአውሮጳ ህብረትን የባህር ድንበር ማስከበር እንጂ የነፍስ አድን ተግባር አይደለም። ብቻ ማማዶ ነፍሳቸው ተርፋ ኢጣሊያ ከገቡት ስደተኞች አንዱ ነው። እሱም በርሃ አቋርጦ ነው ሊቢያ የገባው። ወጣቱ ሊቢያ በቆየበት የአንድ ዓመት ጊዜ ስራ ሰርቷል፣ ወህኒ ቤትም ነበር። አንዱን ሌሊት ግን ማሊ ያሉ አማፂያንን እንዲቀላቀል ወደ ባህር ዳር ሲወሰድ «ለማምለጥ ተሳካልኝ » ይላል።« እኔ የጠፋሁት፤ በሀገሬ ፤ በተለይ እኔ በምኖርበት በነበረው አካባቢ አብዮት በመቀስቀሱ ነበር። አንድ ቀን አማፂያኑ የኛ መንደር ላይ ጥቃት መጣል ጀመሩ። በዚህ ተግባራቸው ወንድሞቼን፣ እኔን እና የተወሰኑ ጓደኞቼን ወደ ጫካ ወሰዱን። እነሱ የመንግሥቱን ጦር እንድንዋጋ ነበር የፈለጉት። »

ማማዶ ሁለት ወንድሞች እና አንድ እህት አሉት። እነሱን ምን እንደገጠማቸው እና በህይወት ስለመኖራቸው እንኳን አያውቅም። ፓሌርሞ የሚገኙት ስደተኞች ትዕግስት ያስፈልጋቸዋል። በተገን ጠያቂዎች ኮሚሽን ተገኝተው ቃል መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ከዛም የተገን ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ አንድ ዓመት ያክል ሊፈጅ ይችላል ይላሉ ፍራንሴስኮ ቪዛኒ ከ ካሪታስ የካቶሊክ ርዳታ ድርጅት።

በካሪታስ ስር ያሉት ወጣቶች የግድ በስደተኞቹ መኖርያ መቆየት የለባቸውም። ሲፈልጉ ወደ ከተማ መሄድ ይችላሉ። አንዳንዶች የኪስ ገንዘብ ለማግኘት የቀን ስራ ይሄዳሉ። ሌሎች ደግሞ በዛው በስደተኞቹ መኖርያ ግቢ ውስጥ በሰዓት እየተፈራረቁ ይሰራሉ።

ስደተኞቹ የሚኖሩት ቀደም ሲል የአዛውንቶች መኖርያ የነበረ ፎቅ ውስጥ ነው። የመጀመሪያው ፎቅ ላይ አሁንም ርዳታ የሚያስፈልጋቸው አዛውንቶች ይኖራሉ። እነሱንም የካቶሊክ መነኩሴዎች ይረዷቸዋል። ጎረቤቶቻቸው ስደተኞቹን ሰላም ይሏቸዋል። ነገር ግን ስደተኞቹ የጠረጴዛ ቴኒስ ሲጫወቱ ድምፃቸው ስለሚረብሽ በሚል፤ ጎረቤታቸው ለካሪታስ ወቀሳ አሰምተው ነበር። በዚህም የተነሳ ካሪታስ ምሳ ሰዓት ላይ ፀጥታ እንዲከበር አውጇል። ስደተኞቹ ጠዋት ጠዋት ጣሊያንኛ ይማራሉ። ከትምህርት ቤት መልስ ፣ በቡድን ሆነው ቴሌቪዥን ይመለከታሉ፣ ያርፋሉ፣ ይጫወታሉ። ከዚህ በተረፈ ግን ከ 3-5 አልጋዎች ባሉበት ክፍል የሚኖሩት ስደተኞች በመቀመጥ ነው ጊዜያቸውን የሚያሳልፏት። « ማስረጃ ኖሮ መስራት ቢቻል ይሻሻል። እንደዚህ ቁጭ ከማለት ይልቅ»

Italienisch-Kurs für Flüchtlinge in Palermo, Italienበየቀኑ ስደተኞቹ ጣሊያንኛ ይማራሉ

ይላል ታምቦ። ማማዶ ደግሞ ወደ ሰሜን አውሮፓ መሄድ ቢችል ይመርጣል።ሳቅ እያለ ጀርመን የምመኛት ሀገር ናት ይላል። ስደተኞቹ ምንም እንኳን ከግቢ መውጣት ቢችሉም የፓሌርሞን ከተማ ለቀው መሄድ አይፈቀድላቸውም ይላሉ ፍራንሲስኮስ ቪዢኒ። ይሁንና አንዳንድ ጥለው የሚሄዱ እንዳሉ ከሌሎች የካሪታስ ጣቢያዎች እንደሚያውቁ ቪዢኒ ይናገራሉ።

ሮም የሚገኘው የተገን ጠያቂዎች ምክር ቤት ባልደረባ ክርስቶፈር ሀይን፤ ኢጣሊያ በማሬ ኖስትሩም አማካይነት ሀገሪቱ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ብዙ ስለሆነ ፤ ሀገሪቱ ከአቅሟ በላይ እንደሆነባት ያስረዳሉ። ስለሆነም የአፍሪቃ እና የሶርያ ስደተኞች ዘመድ ወይም የሚያውቁት ሰው እያፈላለጉ ወደ ሰሜን ይጓዛሉ።« ከደቡብ ኢጣሊያ ወደ ኦስትሪያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን፣ ኔደርላንድስ እና ስዊዲን ሌላ ሁለተኛ እንቅስቃሴ ይታያል። ሰዎቹ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት አድርገው ወደ ሌሎች ሀገራት ለመግባት ይሞክራሉ። በድጋሚ በህገ ወጥ መንገድ አድርገው ለመጓዝ እና ለደላሎች ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።»

በአውሮፓ ህብረት የደብሊን ህግ መሰረት ስደተኞች መቆየት የሚፈቀድላቸው ተገን የጠየቁበት ሀገር ነው። የካሪታስ ሥራ አስኪያጅ ቄስ ሴርጂዎ ማታሊአኖ እኢአ ህዳር 1 ቀን 2014 ዓም ማሬ ኖስትሩምን የተካው የ « ትሪቶን» ግብረ ሃይል ተግባር ብዙም አላሳመናቸውም።« የትሪቶን ዘመቻ ምናልባት የባህር ጠረፉን ለመቆጣጠር እና አውሮፓን ለመዝጋት ጥሩ ሊሆን ይችላል። አላማው ህይወት ለማትረፍ ሳይሆን አውሮፓን ለማጠር ነው።»

Palermo Flüchtlinge 6.አባቴ ብለው ነው የሚጠሩኝ ይላሉ ሴርጂዮ

ቄስ ሴርጂዮ መርዳት ነው አላማቸው። በስደተኞቹ መኖሪያ የሚገኙት 38 ወጣት አፍሪቃይናንን ቤተሰብ አድርጎዋቸዋል። ስደተኞቹም በካቶሊኩ መንፈሳዊ ይተማመናሉ።ምንም እንኳን አብዛኞቹ ስደተኞች ሙስሊም ቢሆኑም ፤ ሀይማኖት ለማንኛቸውም ሚና አይጫወትም።« እኔ ልክ እንደ አባታቸው ነኝ። ከኔ ጋር ስለ ገጠማቸው ችግር መወያየት ይችላሉ። በሲሲሊ፣ በኢጣሊያ ህልማቸውን እውን ለማድረግ ይፈልጋሉ እና ጥሩ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተስፋ አላቸው። »የማሊ ስደተኛ ታምቦ እጁን ቄሱ ትከሻ ላይ አድርጎ አቅፎዋቸዋል። የሚሉት በደንብ ባይገባውም ቄስ ሴርጂዮ በጣልያንኛ ቀስ ብለው ታምቦን ይመክሩታል።

የስደተኝነት ህይወት በሲሲሊ እንዴት እንደሚቀጥል ግን ማንም አያውቅም ። ታንቦ የመጣውን ለመቀበል ዝግጁ ነው።« ህይወት እንግዲህ እንደዚህ ነው። ከዚህ በፊት ሌላ ህይወት ነበረኝ ። አሁን ደግሞ እዚህ ህይወቴ የሚመጣውን አያለሁ። ነገ ኢጣሊያ ልቀር ወይ ወደ ጀርመን ልሄድ እችላለሁ። ህይወት እንዲህ ናት።»

በፖሌርሞ ከታንቦና ማማዶ ጋር የሚኖሩት አፍሪቃውያን ስደተኞች መጠለያ ፣ ምግብ ፣ መዝናኛ እና የቋንቋ ትምህርት የመሣሰሉትን ቢያገኙም ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ለተጓዙት ጉዞ፤ ገና ከዚህ የተሻለ ህይወት እንዲጠብቃቸው ይመኛሉ።

በርት ሪገርት / ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ