እርስ በርስ መበላላት አቁመን በቅንነት አብረን እንሥራ


 

በመጀመሪያ ኢትዮጵያ አገራችን ዛሬ ለምትገኝበት አስከፊ ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታ ሆነ መንፈሳዊ ኪሳራዎች ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው ብለን ወቀሳችን፣ እርግማናችን፣ ዝልፊያችን እና ማስፈራሪያችን ሁሉ ወያኔ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። የሚያሳዝነው ታዲያ በጩኸታችን እና በእርግማናችን ለሁለት አሥዕርት ዓመታት የተሸከምናቸው ግፈኞች ከጫንቃችን ማውረድ አለመቻላችን አይደለም። ይልቁንም እስከዛሬ ድረስ ከመረጋገም፣ ከመጠላለፍ፣ ከመጯጯህ አባዜ ሳንላቀቅ ከወያኔ ጋር ያሳለፍነውን የሰቆቃ ዘመን እያደስን ማራዘማችን ነው። በወያኔ መንግሥት ሰብዓዊ መብት መጣስ ሃገርንና ሕዝብን ማዋረድ፣ ዘረኝነት ማስፋፋት፣ በሙስና የሃገሪቷን ሀብት በመመዝበር ሕዝቡ ግፍ ከፍቶት እንዲሰደድ ማድረግ ዓለም ያውቀዋል።ቀሪውም ዓለም እዚህ ያደረስነውን እኛንም ጭምር ነው። እንደኔ እምነት ይኼንንያደረግነው እኛው ራሳችን ነን። ምክንያቱም አንድ መሆን ስላቃተን ለወያኔ በተገዢነት ለመኖር ምቹ ሁኔታ ፈጥረንለታል። በአብዛኛው የኛ አገር ፓለቲካ ማንም የማያተርፍበት ፖለቲካ ነው። በተለይ ተወያይቶ አለመፍታት፣ ተደራድሮ አለመታረቅ፣ ተነጋግሮ አለመደማመጥ፣ ተባብሮ አለመሥራት፣ ተነጣጥሎ መውደቅ… ብቻ የእኔ ሀሳብና የፖለቲካ ርእዮት ብቻ ነው ትክክል ብሎ ማሰብ፣ ከእኔ ሌላ ለዚህች ሀገር የሚያስብና የሚለውጥ የለም ብሎ ማለትና መደንፋት የትኛውንም ድርጅት ከፍ ሲያደርግ ሳይሆን ሲያከስር ነው እስካሁን ያየነው። ወደፊትም በዚሁ ሁኔታ እስከቀጠልን ድረስ ለወያኔ አገዛዝ ምቹ ሆነን ትከሻችንን ለሸክም ማመቻቸት ነው።

3

በተለይ በተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ የሚሰማው የዜሮ ፖለቲካ ድምር ምክንያቱ ለአብዛኞቻችን ግልጽ ነው። በማን አለብኝነት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አንባገነን መሆናቸው እርስ በርስ አለመተማመናቸው፣ አንድ ላይ አለመሥራታቸው ነው። ሁሉም ለኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የሚሠሩ ከሆነ ለምን በአንድ ላይ ሕብረት ፈጥረው በአንድነት አይጓዙም?በቅንነት ለምን አይሠሩም?ለምንስ ሕዝቡ ይሄ ሁሉ መከራ በወያኔ ይደርስበታል? በዚሁ እስከቀጠልን ድረስ መቼም የማይፈታ የፖለቲካ ዜሮ ጨዋታ ነው የሚሆነው።

እንግዲህ እኛም እራሳችንን እንጠይቅ እኛስ ለሥርዓቱ አገሪቷን ፍትህ አልባ ሲያደርግ ሰብአዊ መብት ሲጥስ እያየን ከመጮህ በስተቀር ምን አደረግን?በተበላሸው የፍትሕ ሥርዓት ቀጥተኛ ተጠቂ የሆነውን ያህል ለሥርዓቱ ፍትሕ አልባ ሆኖ መቀጠል በአንድ ወይም በሌላ መንገድ አስተዋጽዖ ላለማበርከታችን እርግጠኞች ነን ወይ? ከወያኔ በተቃርኖ የቆምን ሃይሎች በቀረው ፍትሕ ናፋቂ የሕብረተሰብ ክፍል ውስጥ ለፍትሕ የተሰጠውን ግምትና ቦታ እያገኙ ነው ወይ የሚለውን መቃኘት ግድ ይላል።

Berhanu Baue

Germany

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s