Archive | December 2014

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ

(ኢሳት) በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን
በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡

የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው
የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም
የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ
መሆኑን ደንግጎአል፡፡
በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል፡፡
በተጨማሪም ሥራዎቹ ማንኛውንም የህብረሰተብ ክፍል፣ ብሔር፣ጎሳ፣ቀለም፣ጾታ፣ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት፣ማህበራዊ አመጣጥ፣
ወይንም ሌላ መሰል አቋምንና ክብርን የሚነካ ወይም የሚያዋርድ፣ በህዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቅስ ወይንም ጥላቻ የሚያስፋፋ፣ የግለሰብን ስም የሚያጠፋ፣፣ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን አመለካከት ስሜት የሚጎዳና ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ የሚገፋፋ፣ የህብረሰተቡን ሞራል የሚጥስ ወይንም በሕግ የተከለከለ ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽም መሆን የለበትም ይላል፡፡

ተጠያቂነትም በተመለከተ ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ
አማካይነት የቀረበ ፕሮግራም ለሚያስከትለው ማንኛውም የወንጀል ድርጊት ወይም የፍትሐብሄር ጉዳት የፕሮግራሙ
ሃላፊና የብሮድካስት አገልግሎት ሰጪው በአንድነት ተጠያቂ ይሆናሉ ይላል፡፡

በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ አማካይነት የቀረበ ፕሮግራምን ቁጥጥርን በተመለከተ
ከህብረተሰቡ በቅሬታ መልክ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የመመርመር፣ተቆጣጣሪ የመመደብ ስልጣን ወደፊት ለሚቋቋመው
ባለስልጣን መ/ቤት ሃላፊነቱን ይሰጣል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የቴሌቪዥንን ከአናሎግ ወደዲጂታል ሽግግርን ለማቀላጠፍና የግል ቴሌቪዥን ለመፍቀድ ይረዳል ተብሎአል፡፡
በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢትዮጵያ የሚዲያ ባለስልጣን የሚባል መ/ቤት ይቋቋማል፡፡

የብሮድካስት አግልግሎት የሚመራበትን ሥርዓት ለመደንገግ ከ15 ዓመታት በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 178/1991
የግል ቴሌቬዥን ጣቢያ ፈቃድ ለግል ባለሃብቶች የፈቀደ ቢሆንም ይህ ተግባራዊ ሳይሆን አዋጁ በቁጥር 533/1999
የተሻሻለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተሸሻለውም አዋጅ ቢሆን የግል ቴሌቭዥን ጣቢያ የተፈቀደ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ
መንግስት ኢትዮጵያ ለዚህ ደረጃ ገና አልበቃችም በማለት አዋጁ እንዳይፈጸም እስካሁን ድረስ መከልከሉ የሚታወቅ
ነው፡፡

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ
በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን
በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን  ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡

የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው
የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም
የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ
መሆኑን ደንግጎአል፡፡ 
በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል፡፡
በተጨማሪም ሥራዎቹ ማንኛውንም የህብረሰተብ ክፍል፣ ብሔር፣ጎሳ፣ቀለም፣ጾታ፣ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት፣ማህበራዊ አመጣጥ፣
ወይንም ሌላ መሰል አቋምንና ክብርን የሚነካ ወይም የሚያዋርድ፣ በህዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቅስ ወይንም ጥላቻ የሚያስፋፋ፣ የግለሰብን ስም የሚያጠፋ፣፣ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን አመለካከት ስሜት የሚጎዳና ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ የሚገፋፋ፣ የህብረሰተቡን ሞራል የሚጥስ ወይንም በሕግ የተከለከለ ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽም መሆን የለበትም ይላል፡፡

ተጠያቂነትም በተመለከተ ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ
አማካይነት የቀረበ ፕሮግራም ለሚያስከትለው ማንኛውም የወንጀል ድርጊት ወይም የፍትሐብሄር ጉዳት የፕሮግራሙ
ሃላፊና የብሮድካስት አገልግሎት ሰጪው በአንድነት ተጠያቂ ይሆናሉ ይላል፡፡

በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ አማካይነት የቀረበ ፕሮግራምን ቁጥጥርን በተመለከተ
ከህብረተሰቡ በቅሬታ መልክ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የመመርመር፣ተቆጣጣሪ የመመደብ ስልጣን ወደፊት ለሚቋቋመው
ባለስልጣን መ/ቤት ሃላፊነቱን ይሰጣል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የቴሌቪዥንን ከአናሎግ ወደዲጂታል ሽግግርን ለማቀላጠፍና የግል ቴሌቪዥን ለመፍቀድ ይረዳል ተብሎአል፡፡
በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢትዮጵያ የሚዲያ ባለስልጣን የሚባል መ/ቤት ይቋቋማል፡፡

የብሮድካስት አግልግሎት የሚመራበትን ሥርዓት ለመደንገግ ከ15 ዓመታት በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 178/1991
የግል ቴሌቬዥን ጣቢያ ፈቃድ ለግል ባለሃብቶች የፈቀደ ቢሆንም ይህ ተግባራዊ ሳይሆን አዋጁ በቁጥር 533/1999
የተሻሻለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተሸሻለውም አዋጅ ቢሆን የግል ቴሌቭዥን ጣቢያ  የተፈቀደ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ
መንግስት ኢትዮጵያ ለዚህ ደረጃ ገና አልበቃችም በማለት አዋጁ እንዳይፈጸም እስካሁን ድረስ መከልከሉ የሚታወቅ
ነው፡፡

“ኢትዮጵያን እናድን”

ወ/ዮሐንስ  ቢክሰኝ  ሀ/ልዑል – ከ ጀርመን

ኢትዮጵያ ሀገራችን  ከማን ፣ ከምን ነው የምናድናት ? በርግጥ ችግር ውስጥ ናት ? እነዚህ ጥያቄዎች ለተለያዩ የሀገራችን ዜጎች  ቢቀርብ መልሱ ሁለት ዓይነት ነው የሚሆነው ። በጣት ለሚቆጠሩ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች እና ባለስልጣናት እንደዚህ  አይነት ጥያቄዎችን የሚያነሳ ሰው ወይም ድርጅት አሸባሪ ፣ ፀረ  ሰላም ፣ ፀረ ዲሞክራሲ ፣ ፀረ ልማት እና ወዘተ በማለት  ያስፈራራሉ  ።  ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል እኔን ጨምሮ አዎ ርግጥ ነው  ሀገራችን ዘርፈ ብዙ ችግር ውስጥ ናት ። ከየትኛውም ጊዜ በከፋ መልኩ ሀገራችን እና ዜጎቿ በወያኔ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ የሆነ የሰባዓዊ መብት ረገጣዎች ፣ስደት ፣እስር ፣የኑሮ ውድነት ፣ ግርፍት እናወዘተየተባባሰባት ሀገር ሆናለች ።

በዚህ ጽሁፌ በወያኔ አገዛዝ በ ሀያ ሶስት ዓመታት  ውስጥ  የተደረጉቱን  የሰባዓዊ መብት ረገጣዎች ፣ስደት ፣እስር ፣የኑሮ ውድነት ፣ ግርፍት እናወዘተ መዘርዘር  አላማዬ አይደለም ፤ ምክንያቱም  የወያኔ በደል እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ ተፅፎ የሚያልቅ አይደለም ።

በወያኔ አገዛዝ  ሁሌም ምርጫ በመጣ ቁጥር ሽብር አለ ዜጎችን ማሰቃየት አይቀሬ ነገር ነው ፤ በስራቸው የማይተማመኑ የስርአቱ ባለስልጣናት  የህብረተሰብ ተቀባይነት ስለሌላቸው  እና ስልጣንን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማስረከብ  ስለማያውቁ እና ስለማየፈልጉ  በትግል ሜዳ ላይ ያሉ ዜጎችን የስቃይ በትር ያሳርፉባቸዋል ። በቅርቡ እየሆኑ ያሉትን ግድያዎች፣የጅምላ እስሮች ፣የሰባዓዊ መብትረገጣዎች መጥቀሱ ማሳያ ነው  ። መሳሪያ ያልታጠቀን ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ልታገል ስላለ መግደል ፣   ማሰቃየት መልስ ይሆናል ትላላቹ ?

በርግጥ ይኼ የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ አዲስ አይደለም ። የሚገርመው ሁሌም ከስልጣናቸው እና ሀገርን ከመዝረፍ የሚያደናቅፋቸውን ግለሰብ እንዲሁም ድርጅት የሚሰጡት ተለጣፊ ስሞች አለማለቃቸው ነው።አሸባሪ ፣ ፀረ  ሰላም ፣ ፀረ ዲሞክራሲ ፣ ፀረ ልማት እና ወዘተ።ስለሆነም እኔም በዚህ ጽሁፍ ምክንያት የነዚህ ስሞች ባለቤት ነኝ ፤ በሰላማዊ መንገድ መታገልም የተለጣፊ ስሞች ባለቤት ያደርጋል ፤ ያስቀጣል ያስገድላል በወያኔ ስርአት  ።

በግልፅ ቋንቋ ሳልናገር የማላልፈው ነገር ቢኖር ሰላማዊ ታጋይ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መታግሉ ዋናው ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሀገሩ ሲፈልግ የነበረው ፣ዛሬም ነገም የሚፈልገው እና የሚመኘው ሰላም የሰፈነባት ፣ ልማትዋ የተረጋገጠባት፣በዲሞክራሲያዊ አካሔድ የምትምራ እና ከአሸባሪ መንግስት የጸዳች ሀገርን ነው ።

ethiopian_terrorists-300x225

በቅርቡ ታስሮ ከነበረ ሰላማዊ ታጋይ የፍርድ ቤት ልምድ ካነበብኩት ውስጥ መጥቀስ ወደድኩ ፤ በጅምላ ከታሰሩ ሰላማዊ ታጋዮች መካከል ለዳኛዋ ባሰሙት አቤቱታ የታሰሩበት ሁኔታ ጤናቸውን ስላዛባው ህክምና ያገኙ ዘንድ አቤት ይላሉ ። ዳኛዋም በመልሳቸው ወደ ፖሊሶቹ ዘወር በማለት “ታሳሪዎቹ የጠየቁትን ህክምና እንዲያገኙ አድርጉ ለእናንተም ለመቅጣት እንድትችሉ በህይወት ይቆይላቹ” በማለት ነበር የተናገሩት ።ልብ በሉ እስረኛ በህይወት መቆየት ያለበት ቅጣት ለመቀበል ብቻ ነው  ። በርግጥ እኚህ ዳኛ የስርአቱ ነጸብራቅ ናቸው ፤ ከዝንብ ማር አይጠበቅም ።ስርአቱ የፈጠራቸው ችግሮች ዘርፈ ብዙ ናቸው ፤ መሪ ነን የሚሉ ተመሪዎች ንግግራቸው ፣ድርጊታቸው ወርዷል ከመሪ አይጠበቅም ፤ እንኳን ለመምራት ለመመራትም አይሆኑም አይችሉም ። በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስተሩ ወራቤ ከተማ የተመሰረተችበትን አስርኛ አመት ለማክበር ባገኙት መድርክ በመጠቀም የተለመደ አሉባልታቸውን አውርተዋል ። በዚህ አሉባልታም ስደተኛ ኢትዮጵያውያውንን ገረድ ፣ዱቄት ለማኝ ፣ ኮንቴነር ውስጥ የሚኖሩ እና የሰው መኪና እየተደገፉ ፎቶ የሚነሱ  ብለዋል የሚገርመው አለማፈራቸው ነው፤ እንዴ ? ሀገሩ ላይ ስራአቱ በፈጠረው ችግር ምክንያት መኖር ያልቻለ ዜጋ በስደት በሰው ሀገር ገረድ ቢሆን ቢለምን ውጪ ቢያድር ብሎም ኮንቴነር ውስጥ ቢኖር ምን ይገርማል ? ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው ማን ነው ? በኔ ምልከታ በስደት የሚገኘው ዜጋ ለወያኔ ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ሁኔታ ፈተና እንደሆነባቸው ያሳያል።

በመጨረሻም ፦

የወያኔአገዛዝማብቃት እንዳለበት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ማለቴ ከጥቂት የስርአቱ ተጠቃሚዎቹ በቀር የሚስማሙበት ነው ።ኢትዮጵያ ሀገራችንእናድን !አንድ ሁነን በአንድነት ሰርአቱን በቃህ እንበለው ፤ ከኛ ውጪ ሌላ ሰው ሌላ ዜጋ ይኼን ስርአት በቃህ ሊለው አይችልም ።በቃህ እንበለው በአንድ እጅ አይጨበጨብም ።

ሰላም!

የመናገርና የመጻፍ ነጻነቶች አፈና

ከየካቲት 21/1966 ዓም ጀምሮ መነቃቃትና መደፋፈር ጀምረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ጸሃፊዎችና ጋዜተኞች የመናገር እና የመጻፍን ነጻነት በነጻነት መጠቀም የቻሉት ለስድስት ወራት ያህል ብቻ ነበር:: በነዚህ ወቅቶች ውስጥ ዝነኞቹ የግጥም መጽሃፍቶች እነ ” እሳት ወይ አበባ“ እነ ”በረከት መርገም“ እነ ”ባሻ አሸብር ባሜሪካ“ እንዲሁም ከትውኔት ስራዎች ውስጥ እነ “ሀሁ በስድስት ወር” እና እነ ”እናት አለም ጠኑ“ የታተሙት በዚህ ወቅት ነው:: አዝማሚያው በጣም የዘገነነው የወታደሮች ስብስቡ ደርግ“  በመስከረም 2/1967 ዓም የመጀመርያው አዋጅ በአንቀጽ 8 ድብን አድርጎ የጠረቀመውም ይህን የመናገርን የመጻፍ መብት ነው:: ሙሉ አንቀጽ እንዲህ ይላል:: ”ይህ አዋጅ እስኪነሳ ድረስ ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን አላማ የመቃወም አድማ ማድረግ ስራ ማቆም ያለ ፈቃድ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማድረግ በጠቅላላው የህዝብን ጸጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈጸም ክልክል ነው::“ ፍሬ ነገሩ ያለው ”…… የህዝብን ጸጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈጸም ….“ የሚለው ሃይለ ቃል ላይ ነው:: ደርጎች በህዝብ ጸጥታና ሰላም አሳበው የመናገር የመጻፍ ነጻነትን ደፈጠጡት:: የኢትዮጵያ ትቅደም አላማ አስታከው የዜጎችን ሰብአዊ ነጻነት አንቀው ገደሉት::

free-press-free-press-for-free-people-small-55073

በመስከረም 19/1968 ዓም በአዋጅ ቁጥር 55/1968 የወጣው “የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ” አንቀጽ 3 ነገሮችን ሁሉ አፍረጠረጣቸው:: አንቀጽ 3 /መ/ እንዲህ ይላል ” ህገ ወጥ የሆኑ ጽሁፎችን ሰሌዳዎችን ቅርጻ ቅርጾችን ስእሎችን በሚያዘጋጁ በሚያባዙ በሚጽፉ በሚያከማቹ በሚሰጡ በሚበትኑ በሚያስተላልፉ ወይም በሌላ ማናቸዉም አይነት ዘዴ ሌላው ሰው እንዲደርሰው ወይም እንዲያውቅ በሚያደርጉ /ረ/ ስራ እንዲሰራ በሚያደፋፍሩ፣ በሚደገፉ ፣ በሚያስፈራሩ ፣ በሚያውኩ ፣ ትእዛዝ በሚሰጡ ፣ ሃሳብ በሚያቀርቡ….. ወዘተርፈ“ እያለ ይቀጥላል:: ደርግ „የጸጥታ ሃይሎች“ ላላቸው ሎሌዎቹ የሰጣቸው ከ ­- እስከ የሌለው ስልጣን ነው:: አንቀጽ 5 እንዲህ ይላል „የጸጥታ አስከባሪ ባልደረቦች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ለመፈተሽ ፣ ለመያዝ ፣ እና የዞ ለማቆየት ስለጣን አላቸው“:: አንቀጽ 6 ደግሞ „ያሁኑስ ይባስ ያሰኛል“ የጸጥታ አስከባሪ ባልደረቦች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ለማሰር ሙሉ ስልጣን አላቸው“ ይላል:: ደርግ ጸሃፊዎችን እንደፈለገው ፈነጨባቸው:: የቀለም ቀንዶችንም ሰባበራቸው::

ደርግ የኢትዮጵያንን በሰላሙ ጊዜ የመናገርና የመጻፍ መበትና ነጻነት ለመግፈፍ በቅድሚያ ያወጣው አዋጅ ነበረው:: ያም አዋጅ በህዳር 8/1967 ዓም የወጣ ነው:: “ልዩ የውንጀለኛ መቅጫ ህግና የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ስነ ስርአት”  ይባላሉ᎓᎓ እንዚህን ህጎች አውጥቶ ሁለት ሳምንት እንኩዋን ሳይቆይ አማን አምዶምንና 60ዎቹን የንጉሰ ነገስቱ ዘምን ባለስልጣናትን ረሸኑዋቸው ደርግ ለዚህ ግብታዊ እርምጃው እንዲያመቸው ብሎ ያዘጋጃቸው ሁለት ህጎች መግቢያ እንዲህ የሚሉ ነበሩ᎓᎓ “ …..የ1949ኛው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሆን ብሎ ያልተሸፈኑና ያቀለላቸው ጉዳያቸው መታየታቸውና እንሱንም በህግ ውስጥ ማስገባት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ መስረታዊና ሰብአዊ መብቶችንና የተፈጥሮ ፍትህን በመጠበቅ “ለኢትዮጲያ ትቅደም” አላማ ቅድሚያ መስጠት ከዚህ በፊት እንደተለመደው አሰራር የወንጀል ክስና ቅጣትን በይርጋ ማቆም ወይም ማገድ አስፈላጊ ባለመሆኑ …..ምንጊዜም ቢሆን አፍቅሮተ ንዋይ ይህንንም የወንጀል መርዝ ለማጥፋት በአፍቅሮ ነዋይ ለተሰሩ ወንጀሎች ከእስራቱ ቅጣት ሌላ በተጨማሪ በህጉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የገንዘብ መቀጮ መወስን ተገቢ መሆኑን በማመን ….” እያለ ይቀጥላል:: የዚህ አዋጅ ትርጓሜ ትልቁን የህግ ፍልስፍና የሚጻረር ነው:: ፍልስፍናው “ህግ ወደሁዋላ ተመልሶ አይሰራም”:: ቢልም ደርጎቹ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተሰሩ ድርጊቶችን ሁሉ በአንድ አቃፊ ውስጥ ከተው ዜጎችን በቂም በቀል ፈጁዋቸው::

በወያኔ/በኢህአዴግ ዘመን በአደባባይ መናገርና አቁዋም ይዞ መጻፍ ያስቀጣል ቅጣቱም የገንዘብ የእስር ወይም የስደት መልክ ሊኖረው ይችላል:: በነሃሴ 22/2001 ዓም በአዋጅ ቁጥር 652/2001 ዓም የወጣው እና “ስለ ጸረ ሽብርተኝነት የወጣው አዋጅ ” በይፋ እስኪነገር ድረስ ጸሃፍትና በየአደባባዩ የሚናገሩ ዜጎች የሚሰጣቸው ስያሜ የተለየ ነበር:: በ 1980 ዎቹ የመናገር የመጻፍ ነጻነታቸውን ለመተግበር የጀመሩት ዜጎች አንዳንዴ “ጸረ ሰላም ሃይሎች” በሌላ ጊዜ ደግሞ “ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሱ” ሲያስፈልግ ደግሞ “መንግስትን በሃይል ለመናድ የሚያሴር አክራሪዎች” ….. ወዘተርፈ በማለት ታርጋ ይለጥፍባቸው ነበር ::

የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በ 1997 ቱ ምርጫ ወቅት የቀመሰውን ውርደት ዳግም ላለመከናነብ ዘዴ እና የፖለቲካ ብልጠት ተከተለ በመሆኑም ከ2002ቱ ዓም የክልል እና የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ አስር ወራት ቀደም በሎ  የሚፈጠሩትን የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ለውጥ  ጥያቄዎችን እንደልቡ ለማፈን የሚያስችለውን ህግ አስጠና::

በዚህም አዋጅ ተጠቅሞ የዜጎችን የመናገርና የመጻፍ ነጻነቶች አፈነና 99,6% የ 2002 ቱን ምርጫ አሸነፍኩ አለ የአዋጁ መግቢያ እንዲህ ይላል “በስራ ላይ ያሉት የሃገሪቱ ህጎች በበቂ ሁኔታ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ባለመሆናቸው ጠንካራ የህግ አቅም መፍጠር በማስፈለጉ …….ሽብርተኝነትን ለመከላከል ለመቆጣጠርና ለማመከን በቂ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጠናቀር በሽበርተኝነት የተጠረጠሩ ሰዎችን ወይም ድርጅቶችን ለህግ ለማቅረብ የሚያስችሉ የተጠናከሩ የምርመራና ክስ የማቅረብ አዳዲስ ስልቶችና ስርአቶችን በህግ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ……. ” እያለ ይቀጥላል የዚህ አዋጅ መግቢያ ደርግ በህዳር 8/1967 ዓም ካወጣቸው “የልዩ ወንጀለኛ መቅጫ ህግና ስነ ስርአቱ” ብዙም የራቀ አይደለም:: ይሄኛውም (አዋጅ ቁጥር 652/2001 ዓም) አዋጁ ወደኁላ ተመልሶ ያቆመባቸውን ሰዎች በሃገር ውስጥ የሌሉትን ጸሃፍት ፖለቲከኞች እና  የሲቪክ ማህበርት መሪዎች በሌሉበት የሞት ፍርድ ያከናነባቸው::

by Samson Tamirat

Germany

Govt fires Ethiopia’s top opposition leader

6077360_orig

Ethiopia’s top opposition leader Dr Merera Gudina reportedly lost his job at the government-run city university of Addis Ababa. According to local media reports, the political science professor Dr. Gudina was fired for his political views and his growing popularity among the students as the 2015 national election approaches.

AAU President Admasu Tsegaye has reportedly been under pressure from the city government and the ruling sub-party TPLF regime to remove political opposition voices inside the university. The year 2014 has seen a drastic rise in university student involvement in politics, including the massive student protests in Ambo town of Oromia, which is the hometown of Dr. Gudina.

Despite the TPLF ruling party’s tight grip on the national election board, the party expects riots in the upcoming elections, observers said. During its global bond sale, Ethiopian Finance Minister Sufian Ahmed of the OPDO branch of the ruling party recently depicted the government’s fear of “political turmoil” next year during the election, according to the much publicized report by the Financial Times (FT).

The recent defection of Ethiopian Airlines personal has also increased tension inside the military.

Dr Gudina has been in the Oromo opposition movement for over 40 years, representing the largest ethnic group in Ethiopia. He spent most of his teenage years going in and out of prison due to his activism. He is currently the chairman of the Medrek opposition coalition party.

http://www.somalilandpress.com/govt-fires-ethiopias-top-opposition-leader/#.VJ7XP43EanI.twitter

ምክር እስከመቃብር(በእውቀቱ ሥዩም)

(ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ)
እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር
እየመጣሁ ነው፡፡ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
ይሄም ኣላዋጣ ካለ የኤፍሬም ይሳቅን ቡድን የሚፎካከር ኣስታራቂ ቡድን ኣቋቁሜ” ኣንተም ተው ኣንተም ተው፤ ያስታረቅሁበትን ኪሴ ውስጥ ክተተው” የሚል ኣገልግሎት እሰጣለሁ፡፡ቃሌ ነው፡፡የተናገርኩት ከሚጠፋ በቅርቡ የገዛሁት ጋላክሲ ሙባይል ይጥፋ(በዝች ንግግር ውስጥ የተደበቀ ጉራ እንዳለ እናንተ ሳትሉኝ ኣውቀዋለሁ)
ገና ለገና ካሜሪካ ሊመጣነው በማለት ማጅራቴን ለመመታት እያሟሟቃችሁ ያላችሁ ዱርየዎች እንዲሁም ከዱላ የተረፈች ማጅራቴን በማሸት ትርፍ ለማጋበስ የተሰናዳችሁ ወጌሻዎች ተስፋ ቁረጡ ፡፡ ቤሳቢስትን የለኝም፡፡(ማጅራት መምታት ሲነሳ ፋሲል ደመወዝ ትዝ ኣለኝ፡፡እንኳን እግዜር ማረህ ልለው ብደውል ከዲሲ በርሮ ኣትላንታ እንደገባ ነገረኝ፡፡ለኮንሰርት ይሁን ለስልታዊ ማፈግፈግ ኣልነገረኝም፡፡ ወይ ኣበሳ!እኛ ኢትዮጵያውያንኮ ምስኪን ነን ፤ ኣገር በቀል- ዱላ ሸሽተን ስንሄድ የውጭ ኣገር ዱላ ይጠብቀናል፡፡
ኣሜሪካ ሁለት ወር ስቆይ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ግብዣና ምክር ነው፡፡ዲታው ቢራ ጋብዞ ወደ ኣገርቤት ይዣት የምመለስ ቦርጭ ያወጣልኛል፡፡ቺስታው ቦርጬ እንዴት እንደምቀንስ ይመክረኛል፡፡ኣሜሪካ ፍሪሽ የሆነ ሰው ኑሮው ምክር እስከመቃብር ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ ኣሜሪካ ገንዘብ የተላከለት የመጀመርያው ሰው ሳልሆን እቀራለሁ?
ለምሳሌ ጺም ለመቆረጥ ኣስር ዶላር መከስከስ ነበረብኝ፡፡ ፈርዶብኝ ኣሜሪካ ስገባ ጺሜ ያለወትሮው ቶሎቶሎ ማደግ ጀመረ፡፡ኣዲኣበባ እያለሁ ጺም ኣልነበረኝም፡፡እንዲያውም” ይሄ ልጅ ጺሚ የሚባል ነገር የለውም ስልብ ነው እንዴ?” የሚል ኣሜት በመንደራችን ይናፈስ ነበር፡፡ስልብ ኣለመሆኔን ለማሳየት ኣንድ ሁለት ቀን መንገድ ዳር ሸንቻለሁ፡፡

እንደልማዴ ከቀናኝ የሚጋብዘኝ ከፈረደብኝ የሚመክረኝ ኣላጣም በማለት Fenton መንገድ ላይ ወደሚገኝ ያበሻ ምግብ ቤት ጎራ ኣልኩ፡፡ ኣንዱ መድረክ ላይ የሱዳን ዘፈን ይዘፍናል፡፡ከተስተናጋጆች ውስጥ ኣንድም የሚያዳምጠው የለም፡፡ሁሉም ሙባይሉ ላይ ኣቀርቅሯል፡፡የታደለው ከፍቅረኛው በቫይበር የተላከለትን የክንፈር ምስል እያየ በደስታ ይዋኛል ፡፡ያልታደለው”የትምርት ቤት ክፍያ እየደረሰብኝ ስለሆነ ቶሎ ላክልኝ እንጅ”የሚል ካገር ቤት የተላከ መልክት እያነበበ ተክዟል፡፡ ሌላው ግድግዳው ላይ በተንጠለጠለው ቲቪ ላይ የሚተላለፈውን ያሜሪካ እግርኳስ እየተመለከተ ምድር ጠቦታል፡፡ ያሜሪካ እግርኳስ ቢሏችሁ እንደ ዋናው እግርኳስ እንዳይ መስላችሁ፡፡ ኣንዱ ጠብደል ጥቁር ሙልሙል ኳስ ይዞ ይሮጣል፡፡ሌላው ኣሳድዶ ይደርስበትና ዘርጥጦ ይጥለዋል፡፡ ለኔ ይህ ጨዋታ ሳይሆን ህጋዊ እውቅና ያለው ኣምባጓሮ ነው፡፡በዚህ መሃል ዘፋኙ “ከ እኔ ጋ ናችሁ?” እያለ ኣስሬ ቢጣራም ማንም ተጉዳይ ኣልጣፈውም፡፡ ልምምድ ላይ ያለ ይመስል ለራሱ ዘፍኖ ወረደ ፡፡ስላሳዘነኝ ባንኮኒውን እንደመቋሚያ ተደግፌ በጥሞና ኣዳመጥሁት፡፡ድምጹ ከዛፍ ላይ ኣምፖል ያረግፋል፡፡ቢሆንም ዘፈኑን ኣለቅጥ ያስረዝመዋል፡፡የሱን የሱዳን ዘፈን ታግሶ መጨረስ ሱዳንን በእግር እንደማቋረጥ ነው፡፡

ጥግ ላይ ክበበው ገዳ ተቀምጧል፡፡ ወንበር ስቤ ኣጠገቡ ተሰየምሁ፡፡ ራት ይጋብዘኛል ብየ ስጠብቅ ከራት ጋር የተያያዘ ገጠመኝ ጋበዘኝ፡፡
ክበበው ገዳ ጎረምሳ እያለ የለቅሶ ቤት እራት ኣያመልጠው ነበር፡፡ እንድያውም እንዲያባላኝ እያለ ቃሪያ በኪሱ ይዞ መዞር ጀምሮ ነበር፡፡ ኣንድ ለቅሶ ላይ ታድያ እራት ሲቀርብ ክበበው ከቤቱ ይዞት የመጣውን ቃርያ ከኪሱ ኣውጥቶ ኮርሸም ሲያደርግ የተመለከተ የሰፈር ልጅ ወደ ኣስተናጋጆች እያጨበጨበ “እዚህ ጋ ቃርያ ኣልደረሰኝም” ብሎ ጮከ፡፡

ኣለፍ ብሎ፤ የጃንሆይ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታና ያሬድ ጥበቡ ቁጭ ብለዋል፡፡ያሬድ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሲሆን ዘውዴ የተንቀጠቀጠው ተራራ ነው፡፡ኣሁን ዲማሚቱና ተራራውም ባንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምው ሳያቸው ገረመኝ፡፡

ከማጅራቴ ኣካባቢ “ልትጽፍ ነው የመጣህ ኣይደል”የሚል ሹክሽክታ ሰማሁ፡፡ወይንሸት ናት፡፡ ባለፈው ኣመት ከባህል ቡድናችን ጋር ስትመጣ ኮከብ ድምጻዊ ነበረች፡፡ኣሁን እዚሁ ቀርታ ኮከብ ኣስተናጋጅ ሆናለች፡፡ኣፍንጫዋ ላይ የወርቅ ቡግር የመሰለ ሎቲ ለጥፋለች፡፡እዚህ ኣገር ሴቶች ሎቲ የሚያንጠለጥሉት ጆሮኣቸው ላይ ሳይሆን ኣፍንጫቸው ላይ ነው፡፡ ስለወይንሸት በሌላ ምእራፍ እተርካለሁ፡፡

በሩ ኣጠገብ ተኬን ኣየሁት፡፡ ተኬ በደርግ ዘመን ካይሮ ላይ ከጠፋው የብሄራዊ ቡድናችን ገንዘብ- ያዥ ነበር፡፡ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ባደረገችው በግጥምያ ዋዜማ ላይ በረኛውን ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስለኮበለሉ እሱ የበረኛውን ቦታ ተክቶ ተሰልፏል፡፡ ከተቃራኒ ቡድን የተለጋች ኳስ ወደእሱ ኣቅጣጫ ስትመጣ በገንዘብ ቆጠራው ለምዶበት ጣቱን በምላሱ እያጣቀሰ ሲርበደበድ ፤ ኣስራ ሰባት ጎል ገበቶበታል፡፡ (ምንጭ፡ የይድነቃቸው ተሰማ ሪፖርት)ተኬ ጉዳዩ ሲነሳበት ያማርራል፤“ይሄ ውለታ ቢስ ህዝብ የገባብኝን ኣስራ ሰባት ጎል እንጂ ያዳንሁትን ሰባት መቶ ጎል ኣላሰበልኝም” ይላል፡፡ካገሩ ወጥቶ መቅረት ኣሳብ ፈጽሞ ኣልነበረውም፡፡ይሁን እንጅ ይህን ሽንፈት ይዞ ጓድ መንግስቱ ፊት መቆም የሚያመጣውን ነገር ኣስቦ በዛው” ነካው“፡፡

ኣሁን በሩ ኣጠገብ ቁጭ ብሎ ”ብሉ ሙን“ ቢራ ይጠጣል፡፡ የቢራ ጠርሙሱን በጥርሱ ከፍቶ ቆርኪውን ጠረጴዛ ልይ ተፋው፡፡ቢራ መክፈቻ ቢቀርብለትም ተጠቅሞበት ኣያውቅም፡፡እግዜር መንጋጋን የፈጠረው ሲርብህ ኣጥንት እንድትቆረጥምበት ሲጠማህ የቢራ ጠርሙስ እንድትከፍትበት ነው ይላል፡፡

bewketu

የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
captured-ethiopian-mi-24-by-eritrea
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::

አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::

በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል::

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና /ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ/

ክፍል 2
ተመስገን ደሳለኝ
(ከዝዋይ እስር ቤት)
በዚህ አውድ ለማቅረብ የተገደድኩበትን ዘግናኝ ታሪክ፣ ወደር በሌለው አስከፊነቱ የተነሳ ለንባብ ባላበቃው በወደድኩ ነበር፡፡ ግና! ይህ መንግስታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡
“ጄል-ኦጋዴን”
ጄል ኦጋዴን በሱማሌ ክልል ርዕሰ-መዲና የሚገኝ፤ ለ800 እስረኞች ታቅዶ በ1992 ዓ.ም የተገነባ እስር ቤት ነው፡፡ የግቢውን ዙሪያ ከከበበው አጥር በግምት 15 ሜትር ፈንጠር ብሎ ሌላ ተደራቢ የድንጋይ አጥር ተበጅቶለታል፡፡ እስከ ሚያዝያ 24 1999 ዓ.ም ድረስ እስር ቤቱ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ካሉ መሰል ማጎሪያዎች ብዙም የተለየ አልነበረም፡፡ በዚህ በተጠቀሰው ቀን የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ታጣቂዎች፣ አቦሌ እና ሰንደሬ ወታደራዊ ካምፖችን ጨምሮ፣ በነዳጅ ዘይት ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ቻይናውያን ባለሙያዎች መኖሪያ ሰፈር ላይ የሰነዘሩትን ከባድ ጥቃት ተከትሎ የፖለቲካ እስረኞች ብቻ የሚታጎሩበት እስር ቤት ከሆነ ወዲህ ግን በዋይታ የሚናወፅና በደም ጅረት የሚጥለቀለቅ ምድራዊ ሲኦል ለመሆን በቅቷል፡፡ መንግስት በጥቃቱ ከዘጠኙ ቻይናውያን ጋር 74 ሲቪል ዜጎችና ወታደሮች መገደላቸውን ቢያምንም፤ የአካባቢው የአይን እማኞች ከሰራዊቱ ብቻ እስከ 300 እንደተሰዉ ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኦብነግ እንደ አል-ቃይዳ እና አል-ሸባብ የአባላቱን አስከሬን ትቶ የመሸሽ ልምድ ስለሌለው በቡድኑ ላይ የደረሰውን ጉዳት በትክክል ለማወቅ አዳጋች እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
የሆነው ሆኖ ከዚህ ጥቃት በኋላ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የሚመራ አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያካተተ የደህንነትና (ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ጌታቸው አሰፋ ያሉበት) የፀጥታ ኮሚቴ ተቋቁሞ የሚከተሉትን (ዛሬም ድረስ እየተተገበሩ ያሉ) አስቸኳይ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ ‹‹ከጅጅጋ ውጭ ባሉ በክልሉ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ፣ ትዕዛዙን ጥሶ የተገኘ ከነጭነቱም ሆነ ተሳፋሪዎቹ በከባድ መሳሪያ እንዲመታ፤ አብዛኛውን ህዝብ በፍጥነት ከመኖሪያ ቀዬው በማፈናቀል ለቁጥጥር ወደሚያመቹ ከተሞች ማስፈር (በ2006 ዓ.ም መጀመሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ካሳ ተክለብርሃን 2300 መንደሮችን ወደ ተመረጠ ቦታ ማስፈሩ እንደተሳካ መናገሩን ልብ ይሏል)፤ ወታደራዊ መኪና ላይ ምንም አይነት የደፈጣ ጥቃት ከደረሰ በአቅራቢያው የሚገኝ መንደርን ያለርህራሄ ማውደም (ለማሳያ ያህልም ፍልቼ፣ ቃሙዳ፣ ሳስባኒ፣ ሁለሌ፣ ለንካይርተ፣ ቻለሌን… የመሳሰሉ ከተሞች ወደ ፍርስራሽነት መቀየራቸውን መጥቀስ ይቻላል) እና ከአንድ ሻምበል ያነሰ ኃይል ለአስቸኳይ ጉዳይም ቢሆን ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ›› የሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከዚህ በኋላም ኤታማዦር ሹሙ ጄነራል ሳሞራ የኑስ በክልሉ የሚገኘውን የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ወታደራዊ አዛዦችን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሰብስቦ ማብራሪያ ሰጥቶ ሲያበቃ ውሳኔውን ያለምንም ማቅማማት ተግባራዊ እንዲያደርጉት በጥብቅ አሳስቧል፡፡
ደቡብ ምስራቅ ዕዝ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት (ከ1993 ዓ.ም) በኋላ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሰፈረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 1999 ዓ.ም ድረስ በሜ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ሲመራ ቆይቷል፡፡ ከታህሳስ 1999 እስከ 2000 ዓ.ም ደግሞ ብርጋዴር ጄነራል ስዩም አስተዳድሮታል፤ በዚሁ ዓመት ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ ድረስ ባሉት ጊዜያትም በብ/ጄነራል ሙሉጌታ በርሄ ስር የቆየ ሲሆን፤ ከሚያዚያ 2000 ዓ.ም አንስቶ አሁን ድረስ እየተመራ የሚገኘው በሌ/ጄነራል አብርሃም ወ/ማርያም (ቅፅል ስሙ ‹‹ኳርተር››) እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ዕዝ ውስጥ በዋናነት ሶስት ክፍለ ጦሮች (12ኛ፣ 13ኛ እና 32ኛ) ክልሉን ሶማሊያ ድንበር ድረስ እንዲቆጣጠሩት ተመድበዋል፡፡ ሰፈራቸውን ነገሌ ቦረና ያደረጉት 43ኛ እና 44ኛ ክፍለ ጦሮችም፣ ኦጋዴን ድረስ እንዲንቀሳቀሱ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በአናቱም የአግአዚ ኃይል በቀድሞ ምክትል አዛዡ ብ/ጄኔራል ገ/መድህን ፈቀደ (‹‹ወዲ ነጮ››) ስር ሆኖ አልፎ አልፎ በተደራቢነት እየተላከ በነዋሪዎቹ ላይ በደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ እና ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፈ ስለመሆኑ ከወታደራዊ መረጃ ምንጮቼ ሰምቻለሁ፡፡ ይህም ሆኖ ለደረሱ እልቂቶችና ጭፍለቃዎች በግንባር ቀደምትነት ተጠያቂ ተደርገው የሚጠቀሱት ከጄነራል ሳሞራ፣ ከጀኔራል ‹‹ኳርተር›› እና ከክልሉ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ በብ/ጄነራል በየነ ገ/እግዚአብሔር (‹‹ወዲ አንጥር››) የተመራው 12ኛ ክ/ጦር እና በብ/ጄነራል ፀጋዬ ገ/ጨርቆስ (‹‹ጀብጀብ››) ዕዝ ስር የነበረው 13ኛ ክ/ጦር እንደሆነ ይነገራል፡፡ ኦብነግ በስፋት ይንቀሳቀስባቸዋል ተብለው የሚታሰቡት፡- ደገሃቡር፣ ቀብሪደሃር፣ ዋርደር፣ ጎዴ እና ቪቅ ከተሞች መደበኛ የጦር ቀጠናዎች ከሆኑ 15 አመት ያለፋቸው በመሆኑ፣ ከሌሎች የክልሉ አውራጃዎች በተለየ ሁኔታ የችግሩ ቀጥተኛ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም የሚፈፅማቸውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ለመሸፈን እንደ ቀይ መስቀል፣ ዓለም-አቀፍ ሚዲያዎች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና መሰል ተቋማት ከጅጅጋ ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ በኃይል አግዷል፡፡ ይህ ኩነትም በ ዙ-23 እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ተደብድበው ከምድረ-ገፅ የጠፉ መንደር ነዋሪዎች፣ የቤት እንስሳት እና ቁሳዊ ንብረቶች በአንድነት ተቃጥለው መውደማቸውን ዛሬም ድረስ በምስጢርነት ሸሽጎ ለማቆየት አስችሎታል፡፡
የሆነው ሆኖ የመከላከያ ሰራዊቱ እና በክልሉ ከ70-80 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ላይ መንቀሳቀስ የቻለው ኦብነግ፣ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ከባድ ውጊያ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ ግጭቱ አሁንም ሳያበራ የመቀጠሉ ምክንያት አማፂው ቡድን ያን ያህል ከመንግሥት አቅም በላይ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የጄነራሎቹ እጅ በዘወርዋራ ስላለበት መሆኑን ወታደራዊ ምንጮቼ ያስረግጣሉ፡፡ ‹‹የኦብነግ ህልውና በተለይም ለከፍተኛ መኮንኖች ዋነኛ ንግድ (ቢዝነስ) ነው›› ይላሉ፡፡ የክልሉ መንግስት ‹‹የመረጃ እና ፀጥታ ባጀት›› በሚል ሽፋን በዓመት የሚመድበውን ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ሀብት እንዲያወራርዱ አዛዦቹ አይገደዱም፡፡ መከላከያ ራሱም ‹‹የመረጃ እና የበረሃ ፍሳሽ›› በሚል የሚበጅተው አመታዊ ወጪ በብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚቆጠር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ በጀት እስከ ኃይል አመራሮች ድረስ ወርዶ እንደየድርሻቸው መጠን የሚመዘበርበት አሰራርም ተዘርግቶለታል፡፡ እናም ጀነራሎቹ ኦብነግ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ የገቢ ምንጫቸው እንዳይደርቅም ሆነ፤ ከአቅም በላይ ተጠናክሮ በብቃት ማነስ እንዳያሳጣቸው (እንዳያስወቅሳቸው) ተቆጣጥረው ለመዝለቅ የቻሉበትን ቀመር እንዲከተሉ ይህ የገቢ ምንጭነት ገፊ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከመከላከያ ሠራዊቱ እና ከፌዴራል ፖሊስ በተጨማሪ በቀጥታ የክልሉ አስተዳደር የሚያዝዘውና ‹‹ልዩ ኃይል›› ተብሎ የተቋቋመው ታጣቂ ቡድን ዛሬም ድረስ የሎጅስቲክ አቅርቦቱን ያለጨረታ ጠቅላላ የያዘችው የሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ (በአሁኑ ወቅት ጀነራል አበባውን ተክቶ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ነው) ባለቤት ሃዋ መሆኗ በራሱ የሚነግረን ነገር አለ፡፡ (በነገራችን ላይ ክልሉን የሚያስተዳድሩት በህዝብ የተመረጡት ሳይሆኑ ‹‹የፀጥታ አማካሪ›› በሚል በየወረዳው የተመደቡ የሻለቃ ወይም የሻምበል አዛዦች ከጀርባ ሆነው ነው፡፡ ለነርሱ ያልተመቸ ኃላፊን በሌላ እስከመቀየር ድረስ የሚንጠራራ ስልጣን አላቸው፡፡ የፕሬዚዳንት አብዲና እና የጄነራል ‹‹ኳርተር››ን የ‹‹ሥራ ግንኙነት›› መመልከቱ ጉዳዩን ፍንትው አድርጎ ለመረዳት ያስችላል፡፡ በርግጥም አስራ ሦስት ፕሬዚዳንቶች የተፈራረቁበት ክልል ዛሬ እንዲህ በጨካኙ አብዲ መርጋት መቻሉ እንቆቅልሽ ሊሆን አይችልም)፡፡
‹‹ጄል-ኦጋዴን›› ከደረቅ ወንጀለኞች ማረሚያነት፣ በኦብነግ አባልነት የሚጠረጠሩ ንፁሃንን ወደማሰቃያ እስር ቤት እንዲቀየር የተደረገበት መግፍኤ ከላይ የጠቀስኩትን (የ1999 ዓ.ም የኃይል ጥቃትን) ተከትሎ ሟቹ አምባ-ገነን ጠ/ሚኒስቴር በደህንነት ኮሚቴው ስም የሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡ መቼም ዕድል ፊቷን አዙራበት ወደዚህ ግቢ የተላከ ምስኪን፣ በቀን አንድ መናኛ እንጀራ እየተወረወረለት፣ በ‹‹ምርመራ›› ስም የተወለደበትን ቀን ከመርገም አልፎ ዘላለማዊ ዕረፍት የሚያጎናፅፈው መልአከ-ሞት ቶሎ መጥቶ እንዲገላግለው እስከመናፈቅ ለሚያደርስ ስቀየት (ቶርቸር) ይዳረጋል፡፡ እስር ቤቱ የተገነባው 800 ታሳሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ ቢሆንም፣ ወደምድራዊ ገሃነም ከተቀየረ ወዲህ ግን ከ5000 በላይ ሰዎች የሚታጎሩበት የሰቆቃ ግቢ ሆኗል፡፡ ሁሉም ታሳሪዎች ከጠዋት 2፡30 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ አንድ ቦታ ተሰብስበው ክብርን፣ ሞራልን እና ሰብዕናን የሚያጎድፍ ግፍ ይፈፀምባቸዋል፡፡ በተለይም ሴት እስረኞች በየተራ እንዲቆሙ ይደረግና ወንዱ አንድ በአንድ እየተነሳ ሴተኛ አዳሪ መሆኗን፣ እሱ እና ጓደኞቹ ከእርስዋ ጋር ግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈፀማቸውን፣ ወዘተ እንዲናገር ይገደዳል፡፡ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ሆኖ ካልተገኘም በጨካኝ ታጣቂዎቹ ፍዳውን ይበላል፡፡ ሁኔታውን መራር የሚያደርገው ደግሞ ‹‹ስብሰባው›› ሲጠናቀቅ፣ ሰብሳቢው እስረኞቹ ወደየክፍላቸው እንዲገቡ ትዕዛዝ የማይሰጥ መሆኑ ነው፤ ይልቁንም ወፋፍራም ዱላ ጨብጠው ዙሪያውን ለከበቡት ፖሊሶች በአይኑ ምልክት ያስተላልፋል፤ ይሄኔ በያዙት ቆመጥ ከአቅራቢያቸው ያገኙትን ሁሉ መቀጠቀጥ ይጀምራሉ፤ እስረኛውም ከዱላው ውርጅብኙ ለማምለጥ ባገኘው አቅጣጫ ይተራመሳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት በየቀኑ የተለመደ በመሆኑ የዕለቱ ፕሮግራም ሊገባደድ በተቃረበ ቁጥር፣ ሁሉም ለመሸሽ ዝግጁ ሆኖ ይጠባበቃል፤ ከድብደባው ማምለጡ ግን ብዙም የሚሳካ አይሆንም፡፡
በ‹‹ጄል-ኦጋዴን›› ሴት እስረኞችን አስገድዶ መድፈር፣ ሙዝ ልጦ እንደመብላት ቀላል ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ በዚህም በርካቶች በየጊዜው ለውርጃ ወደሆስፒታል ሲላኩ ይስተዋላል፡፡ አልፎ አልፎ እዚያው ለመውለድ የሚገደዱ እህቶችም አሉ፡፡ አብዛኞቹ ሴት እስረኞች ፀጉራቸውን ከማሳደግ ይልቅ መላጨትን ይመርጣሉ፤ ምክንያቱ ደግሞ የሚፈፀምባቸው ስቅየት የበሰበሱ ቆሻሻዎችንና ፈሳሽ-ሰገራዎችን ፀጉራቸው ላይ መደፋትን ስለሚያካትት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እዚህ ቦታ ሴቶች አንድ ላይ እንዲሰበሰቡ እና ልብሶቻቸውን እንዲያወልቁ ከተደረገ በኋላ እርቃናቸውን የሚገረፉበት ጊዜም እንዳለ ከአይን እማኞች ሰምቻለሁ፡፡ ከሁሉ የከፋው ደግሞ ንፅህናን ካለመጠበቅና በምግብ እጥረት የሚነዛው ወረርሽኝ ነው፡፡ በ2004ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ በሽታው ተከስቶ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ 700 ያህል ሰዎች በሞት መቀጠፋቸው ይነገራል፡፡ በወቅቱ አስከሬን ቶሎ ስለማይነሳ እስረኞቹ ከአስከሬኑ ጋር እስከ 3 ቀን ድረስ ጋር ለመቆየት ይገደዱ ነበር፡፡
በ‹‹ጄል-ኦጋዴን›› ግቢ ከሚገኙ ማጎሪያዎች መካከል 3ኛ፣ 4ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ‹‹የቅጣት ቤት›› ሲሆኑ፤ አሰራራቸውም ሶስት በሶስት ሜትር የሆነ እጅግ በጣም ጠባብ፤ ውስጣቸውም ሃምሳ ሳንቲ-ሜትር ጥልቀት ባለው ውሃ የተሞላ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክፍልም የግድ ከ25 እና ከዚያ በላይ እስረኞች እንዲይዝ ስለሚደረግ ለቅጣት ወደግቢው የተላከ እስረኛ ለሳምንት ያህል እንቅልፍ በዓይኑ ሳይዞር ለመሰንበት ይገደዳል፡፡ በአናቱም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደዚህ ግቢ እየተላኩ ስቅየትም ሆነ ግድያ እንደሚፈፀምባቸው ሰምቻለሁ፡፡ በግቢው ለአራት ወራት ገደማ ያሳለፈው ሀሰን፣ በውል በማያስታውሰው በአንድ የተረገመ ቀን 3 ወታደሮች ሲረሸኑ ማየቱንና ከመካከላቸው አንዱም ‹‹እባካችሁ አትግደሉኝ! የ3 ልጆች አባት ነኝ!›› እያለ ሲማፀን መስማቱን ያስታውሳል፡፡ እስረኞቹ ላይ የጭካኔ ተግባር የሚፈፅሙት ደግሞ ከዚህ ቀደም ‹‹አል-ኢትሀድ አል-ኢስላሚያ›› በሚል ስም ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ፤ በኦብነግ ተሸንፎ ከኦጋዴን የተባረረው አማፂ ቡድን አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች መንግስት ምህረት አድርጎላቸው ወደ ሰላማዊ ህይወት ከተመለሱ በኋላ የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዛኛውን አሰባስቦ ‹‹ልዩ ኃይል›› ብሎ አደራጅቷቸው ሲያበቃ፤ ከኦብነግ ጋር ተያይዞ የሚጠረጠሩ እስረኞች ላይ ያሻቸውን እንዲፈፅሙ ባልተፃፈ ሕግ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም የቀድሞ ሽንፈታቸውን ለመበቀል እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ዛሬ በክልሉ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ የእስር ቤት ግቢዎች ውስጥ የጅምላ መቃብር መመልከት አስገራሚነቱም አስደንጋጭነቱም እየቀረ የመጣው ከዚህ አኳያ ይመስለኛል፡፡