የመናገርና የመጻፍ ነጻነቶች አፈና


ከየካቲት 21/1966 ዓም ጀምሮ መነቃቃትና መደፋፈር ጀምረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ጸሃፊዎችና ጋዜተኞች የመናገር እና የመጻፍን ነጻነት በነጻነት መጠቀም የቻሉት ለስድስት ወራት ያህል ብቻ ነበር:: በነዚህ ወቅቶች ውስጥ ዝነኞቹ የግጥም መጽሃፍቶች እነ ” እሳት ወይ አበባ“ እነ ”በረከት መርገም“ እነ ”ባሻ አሸብር ባሜሪካ“ እንዲሁም ከትውኔት ስራዎች ውስጥ እነ “ሀሁ በስድስት ወር” እና እነ ”እናት አለም ጠኑ“ የታተሙት በዚህ ወቅት ነው:: አዝማሚያው በጣም የዘገነነው የወታደሮች ስብስቡ ደርግ“  በመስከረም 2/1967 ዓም የመጀመርያው አዋጅ በአንቀጽ 8 ድብን አድርጎ የጠረቀመውም ይህን የመናገርን የመጻፍ መብት ነው:: ሙሉ አንቀጽ እንዲህ ይላል:: ”ይህ አዋጅ እስኪነሳ ድረስ ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን አላማ የመቃወም አድማ ማድረግ ስራ ማቆም ያለ ፈቃድ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማድረግ በጠቅላላው የህዝብን ጸጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈጸም ክልክል ነው::“ ፍሬ ነገሩ ያለው ”…… የህዝብን ጸጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈጸም ….“ የሚለው ሃይለ ቃል ላይ ነው:: ደርጎች በህዝብ ጸጥታና ሰላም አሳበው የመናገር የመጻፍ ነጻነትን ደፈጠጡት:: የኢትዮጵያ ትቅደም አላማ አስታከው የዜጎችን ሰብአዊ ነጻነት አንቀው ገደሉት::

free-press-free-press-for-free-people-small-55073

በመስከረም 19/1968 ዓም በአዋጅ ቁጥር 55/1968 የወጣው “የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ” አንቀጽ 3 ነገሮችን ሁሉ አፍረጠረጣቸው:: አንቀጽ 3 /መ/ እንዲህ ይላል ” ህገ ወጥ የሆኑ ጽሁፎችን ሰሌዳዎችን ቅርጻ ቅርጾችን ስእሎችን በሚያዘጋጁ በሚያባዙ በሚጽፉ በሚያከማቹ በሚሰጡ በሚበትኑ በሚያስተላልፉ ወይም በሌላ ማናቸዉም አይነት ዘዴ ሌላው ሰው እንዲደርሰው ወይም እንዲያውቅ በሚያደርጉ /ረ/ ስራ እንዲሰራ በሚያደፋፍሩ፣ በሚደገፉ ፣ በሚያስፈራሩ ፣ በሚያውኩ ፣ ትእዛዝ በሚሰጡ ፣ ሃሳብ በሚያቀርቡ….. ወዘተርፈ“ እያለ ይቀጥላል:: ደርግ „የጸጥታ ሃይሎች“ ላላቸው ሎሌዎቹ የሰጣቸው ከ ­- እስከ የሌለው ስልጣን ነው:: አንቀጽ 5 እንዲህ ይላል „የጸጥታ አስከባሪ ባልደረቦች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ለመፈተሽ ፣ ለመያዝ ፣ እና የዞ ለማቆየት ስለጣን አላቸው“:: አንቀጽ 6 ደግሞ „ያሁኑስ ይባስ ያሰኛል“ የጸጥታ አስከባሪ ባልደረቦች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ለማሰር ሙሉ ስልጣን አላቸው“ ይላል:: ደርግ ጸሃፊዎችን እንደፈለገው ፈነጨባቸው:: የቀለም ቀንዶችንም ሰባበራቸው::

ደርግ የኢትዮጵያንን በሰላሙ ጊዜ የመናገርና የመጻፍ መበትና ነጻነት ለመግፈፍ በቅድሚያ ያወጣው አዋጅ ነበረው:: ያም አዋጅ በህዳር 8/1967 ዓም የወጣ ነው:: “ልዩ የውንጀለኛ መቅጫ ህግና የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ስነ ስርአት”  ይባላሉ᎓᎓ እንዚህን ህጎች አውጥቶ ሁለት ሳምንት እንኩዋን ሳይቆይ አማን አምዶምንና 60ዎቹን የንጉሰ ነገስቱ ዘምን ባለስልጣናትን ረሸኑዋቸው ደርግ ለዚህ ግብታዊ እርምጃው እንዲያመቸው ብሎ ያዘጋጃቸው ሁለት ህጎች መግቢያ እንዲህ የሚሉ ነበሩ᎓᎓ “ …..የ1949ኛው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሆን ብሎ ያልተሸፈኑና ያቀለላቸው ጉዳያቸው መታየታቸውና እንሱንም በህግ ውስጥ ማስገባት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ መስረታዊና ሰብአዊ መብቶችንና የተፈጥሮ ፍትህን በመጠበቅ “ለኢትዮጲያ ትቅደም” አላማ ቅድሚያ መስጠት ከዚህ በፊት እንደተለመደው አሰራር የወንጀል ክስና ቅጣትን በይርጋ ማቆም ወይም ማገድ አስፈላጊ ባለመሆኑ …..ምንጊዜም ቢሆን አፍቅሮተ ንዋይ ይህንንም የወንጀል መርዝ ለማጥፋት በአፍቅሮ ነዋይ ለተሰሩ ወንጀሎች ከእስራቱ ቅጣት ሌላ በተጨማሪ በህጉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የገንዘብ መቀጮ መወስን ተገቢ መሆኑን በማመን ….” እያለ ይቀጥላል:: የዚህ አዋጅ ትርጓሜ ትልቁን የህግ ፍልስፍና የሚጻረር ነው:: ፍልስፍናው “ህግ ወደሁዋላ ተመልሶ አይሰራም”:: ቢልም ደርጎቹ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተሰሩ ድርጊቶችን ሁሉ በአንድ አቃፊ ውስጥ ከተው ዜጎችን በቂም በቀል ፈጁዋቸው::

በወያኔ/በኢህአዴግ ዘመን በአደባባይ መናገርና አቁዋም ይዞ መጻፍ ያስቀጣል ቅጣቱም የገንዘብ የእስር ወይም የስደት መልክ ሊኖረው ይችላል:: በነሃሴ 22/2001 ዓም በአዋጅ ቁጥር 652/2001 ዓም የወጣው እና “ስለ ጸረ ሽብርተኝነት የወጣው አዋጅ ” በይፋ እስኪነገር ድረስ ጸሃፍትና በየአደባባዩ የሚናገሩ ዜጎች የሚሰጣቸው ስያሜ የተለየ ነበር:: በ 1980 ዎቹ የመናገር የመጻፍ ነጻነታቸውን ለመተግበር የጀመሩት ዜጎች አንዳንዴ “ጸረ ሰላም ሃይሎች” በሌላ ጊዜ ደግሞ “ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሱ” ሲያስፈልግ ደግሞ “መንግስትን በሃይል ለመናድ የሚያሴር አክራሪዎች” ….. ወዘተርፈ በማለት ታርጋ ይለጥፍባቸው ነበር ::

የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በ 1997 ቱ ምርጫ ወቅት የቀመሰውን ውርደት ዳግም ላለመከናነብ ዘዴ እና የፖለቲካ ብልጠት ተከተለ በመሆኑም ከ2002ቱ ዓም የክልል እና የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ አስር ወራት ቀደም በሎ  የሚፈጠሩትን የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ለውጥ  ጥያቄዎችን እንደልቡ ለማፈን የሚያስችለውን ህግ አስጠና::

በዚህም አዋጅ ተጠቅሞ የዜጎችን የመናገርና የመጻፍ ነጻነቶች አፈነና 99,6% የ 2002 ቱን ምርጫ አሸነፍኩ አለ የአዋጁ መግቢያ እንዲህ ይላል “በስራ ላይ ያሉት የሃገሪቱ ህጎች በበቂ ሁኔታ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ባለመሆናቸው ጠንካራ የህግ አቅም መፍጠር በማስፈለጉ …….ሽብርተኝነትን ለመከላከል ለመቆጣጠርና ለማመከን በቂ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጠናቀር በሽበርተኝነት የተጠረጠሩ ሰዎችን ወይም ድርጅቶችን ለህግ ለማቅረብ የሚያስችሉ የተጠናከሩ የምርመራና ክስ የማቅረብ አዳዲስ ስልቶችና ስርአቶችን በህግ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ……. ” እያለ ይቀጥላል የዚህ አዋጅ መግቢያ ደርግ በህዳር 8/1967 ዓም ካወጣቸው “የልዩ ወንጀለኛ መቅጫ ህግና ስነ ስርአቱ” ብዙም የራቀ አይደለም:: ይሄኛውም (አዋጅ ቁጥር 652/2001 ዓም) አዋጁ ወደኁላ ተመልሶ ያቆመባቸውን ሰዎች በሃገር ውስጥ የሌሉትን ጸሃፍት ፖለቲከኞች እና  የሲቪክ ማህበርት መሪዎች በሌሉበት የሞት ፍርድ ያከናነባቸው::

by Samson Tamirat

Germany

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s