Archive | January 2015

የዓለም ባንክ የሞራል ኪሳራ በኢትዮጵያ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ኢትዮጵያውያን/ት ለዓለም ባንክ የጭካኔ ቢሮክራሲያዊ የቀልድ ማካሄጃ የመድረክ ትወና ዒላማነት ተዳርገዋል፡፡

dollar-billበምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ እየተባለ በሚጠራው ክልል የዓለም ባንክ ቢሮክራቶች ዜጎችን ከሰፈሩበት ቦታ ያለፈቃዳቸውወደ ሌላ ቦታ በማዛወር፣የአካባቢው ዜጎች በቋሚነት ባህላቸውን አዳብረው ከሚኖሩበት ቦታቸው በግዳጅ በማፈናቀል እናየተለሳለሰና እና በጎ መስሎ በእሬት የተለወሰ የዘርማጽዳት እኩይ ምግባር በማካሄድ “የማታለል ጨዋታ” በመጫወት ላይመሆኑን አንድ ያለም ባንክ የራሱ የምርመራ ዘገባ ባለፈው ሳምንት ይፋአድርጓል፡፡

በጋምቤላ ክልል በቋሚነት የሚኖሩ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የአኙዋክ ብሄረሰብ ተወላጆችን ጥንት ቀደምቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው ቀያቸውየሚያፈናቅል ፖሊሲንበመንደፍ ዓለም ባንክ ህገወጥ በሆነ መልኩ ምንም ዓይነት ውኃ በማይገኝበት እና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎቶችባልተሟሉበትአካባቢ በግዳጅ ተፈናቅለው እዲሰፍሩ በማድረግ በአሁኑ ጊዜ የተፈናቃዮች ህይወት በቋፍ ላይ ወይም ደግሞምንም ዓይነት ተስፋ ሊሰጥ በማይችልአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡

ለበርካታ ዓመታት የዓለም ባንክ ቢሮክራቶች እና በኢትዮጵያ ያሉ ተመሳሳዮቻቸው በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት)አምባገነናዊ ወሮ በላ ቡድንበመካሄድ ላይ ባለው “የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት” እየተባለ በሚጠራው እና“በመንደር ምስረታ ፕሮግራም” መካከል አለ እየተባለየሚነገረውን መሰረታዊ ግንኙነት ሙልጭ አድርጎ በመካድ ህዝቡንበሚጎዳ ድርጊት ላይ ሙዝዝ ብለው ይገኛሉ፡፡ (“የመንደር ምስረታ ፕሮግራም”የሚለውን ቃል የአኟክ ብሄረሰብ ኗሪዎችጥንታዊ ቀደምቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው ኋላቀር የአኗኗር ዘይቤ ተላቅቀው “በዘመናዊ መልክ በስልጣኔ”መኖር መቻልነው ከሚለው ቃል ጋር መሳ ለመሳ ያደርጉታል፡፡) የዓለም ባንክ ዓይን ባወጣ መልኩ በጋምቤላ ክልል ከመሰረታዊአገልግሎት ጥበቃፕሮጀክት (መአጥፕ) ጋር በተያያዘ መልኩ የሚቀርቡበትን ትችቶች ባለመቀበል ምንም ዓይነት የሰብአዊመብት ረገጣዎች ለመፈጸማቸው ሊያመላክቱየሚችሉ ማስረጃዎች የሉም በማለት በተደጋጋሚ በማስተባበል ላይ ይገኛል፡፡
የህዝቡ ፍላጎት ተገዥ ለመሆን ተባባሪ ያለመሆን፣ ህዝቡን ከፍላጎቱ ውጭ በኃይል በማስገደድ እንዲሰፍር ማድረግ እና ሆንብሎ የሀሰት ወሬዎችንማሰራጨት የዓለም ባንክ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያእና በኢትዮጵያ የልማት እርዳታ ቡድን (27የሁለትዮሽ እና የብዙሀን መንግስታትን አካትቶ የያዘ ስብስብ) እየተባለየሚጠራው በኢትዮጵያ የተጠያቂነት ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ የሰብአዊ መብት ረገጣወንጀል መፈጸማቸው እንዳይታወቅለመከላከያነት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ናቸው፡፡ የእንግሊዝ ፓርላማ ዓለም አቀፍ የልማት ኮሚቴ ሊቀመንበርየሆኑት ጌታማልኮም ብሩስ እ.ኤ.አ ማርች 2013 እንዲህ በማለት በድፍረት ተናግረዋል፣ “ስለመንደር ምስረታው የሚነገሩ አሉባልታዎችሁሉ መሰረተቢስናቸው፣ እናም የእንግሊዝ ፕሮግራም ጥሩ ውጤት እየሰጠ ነው፡፡“
የአቤ ሊንኮልን አባባል በመዋስ “የዓለም ባንክ እና የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች “የልማት እርዳታ ቡድን” እየተባለየሚጠራው የበርካታ ሀገሮች ስብስብሁሉንም ኢትዮጵያውያንን/ትን አንድ ጊዜ ሊያታልል ይችላል፣ እንደዚሁም ደግሞጥቂት ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁልጊዜ ሊያታልል ይችላል፣ ሆኖም ግንሁሉንም ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያውያት ሁልጊዜሊያታልል አይችልም፡፡“ እነዚህ የጉሮሮ ላይ አልቀቶች (ተባይ) በሚጫወቱት የማታለል ጨዋታ ምክንያትኢትዮጵያውያን/ትተታለዋል! ተጭበርብረዋል! እንዲሳሳቱ እና ግራ እንዲጋቡ ተደርገዋል፡፡ የማልኮምን አባባል በመዋስ “ኢትዮጵያውያን/ትጭካኔበተሞላበት ሁኔታ የጉልበታሙ የዓለም ባንክ መጫወቻ አሻንጉሊት ተደርገዋል፡፡“
ስለሆነም ከዓለም ባንክ ነጻ “የተጠያቂነት የምርመራ ቡድን” (ኢንስፔክሺን ፓኔል) (ምቡ) ጋር መነጋገር አስፈላጊ ነው፡፡በእርግጥ ምቡ ንጹህ በሚመስል፣በተበጣጠሰ እና ቢሮክራሲያዊ በሆነ የቋንቋ አገላለጽ ይናገራል፡፡ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ እናስሜታዊነት የተሞላባቸው እንቆቅልሽ የሆኑ አስደንጋጭ የሆነየሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ቋንቋ በፍጹም አይጠቀሙም፡፡የሰዎች ሰብአዊ መብቶች በይፋ እየተደፈጠጡ እያዩ ድርጊቱን የሞራል ኪሳራ ብለውአይናገሩም፡፡ ሸክስፒር በሮሚዮ እናጁሌት እንዲህ በማለት ጽፈዋል፣ “እነዚህን እንቆቅልሾች ግልጽ እስከምናደርግ ድረስ ለጊዜው የሞራል ስብዕና ኪሳራንአፍእንዲሸበብ ያደርጋሉ…” ይህንን አስደንጋጭ ሁኔታ እንዲዳፈን አላደርግም ምክንያቱም የዓለም ባንክ የእራሱ የምርመራ ቡድንሁሉንም እንቆቅልሽ የሆኑነገሮች ሁሉ ግልጽ አድርጎልኛልና!
እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 2012 ሁለት ደርዘን እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል የሚገኙኢትዮያውያን/ት የመጠለያ ላይ ተረጅዎችቀደምቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው መሬታቸው በግዳጅ እንዲፈናቀሉ ተደርገውየመሬት ይዞታቸው ለመሬት ነጣቂዎች የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ይህእኩይ ድርጊት እንዲጣራላቸው ዓለም ባንክንጠይቀው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 24/2012 አንድ ስሙ ባልተገለጸ የአኟክ ተረጅ በተጻፈ ደብዳቤ በዓለምባንክ የገንዘብድጋፍ እየተደረገለት የሚተገበረው የኢትዮጵያ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት (መአጥፕ) እና በቀጥታየኢትዮጵያን “መንግስት”የመንደር ምስረታ ፕሮግራም የሚረዳውን የዓለም ባንክን ክፉኛ ወንጅሏል፡፡ በተለይም፣
1ኛ) በመአጥፕ ፕሮግራም የአኟክ ቋሚ ኗሪዎች ይኖሩበት ከነበረው ለም ከሆነው መሬታቸው በግዳጅ እንዲፈናቀሉ ተደርገውመሬታቸው ኢንቨስተርእየተባሉ ለሚጠሩ መሬት ተቀራማቾች በርካሽ ዋጋ በኪራይ ይሰጣል፣
2ኛ) የአኟክ ማኅበረሰብ አባላት ለእርሻ ምቹ ባልሆኑ እና ለምነታቸው በተሟጠጠ ጠፍ መሬቶች ላይ እንዲሰፍሩ ሆኖ አዲስመንደሮች እንዲመሰርቱይገደዳሉ፣
3ኛ) የተሻሻሉ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ለህዝቡ በማቅረብ የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ እናሻሽላለን በሚል የውሸትማደናገሪያ ብዙሀኑ ህዝብ ከኖረበትቀየው በግዳጅ እንዲፈናቀል ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ሰፋሪዎቹ አንድ ጊዜ ከሰፈራ ቦታውከደረሱ በኋላ ለም የሆነ መሬት ብቻ አይደለም የማያገኙት ሆኖምግን ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ የውኃ ጉድጓዶች ወይምደግሞ ሌሎችንም መሰረታዊ አገልግሎቶች ጭምር አያገኙም እንጅ፣
4ኛ) አኟኮች የመኸር ሰብሎቻቸው ለመሰብሰብ በደረሱበት ጊዜ ሰብሎቻቸውን ሳይሰበስቡ እንዳለ ትተው በግዳጅእንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሰፋሪዎችበመንግስት በግዳጅ እንዲንቀሳቀሱ በሚደረግበት ጊዜ ከመንግስት ምንም ዓይነትየምግብ እርዳታ አይሰጣቸውም፣ እና አብዛኞቹ ሰፋሪዎች በረሀብ አለንጋእንዲገረፉ ይደረጋል፡፡ በመንደር ምስረታፕሮግራሙ ምክንያት ጥቂት ለአደጋ ተጋላጭ ህዝቦች እና ህጻናት በሚከሰተው ረሀብ ምክንያት ህይወታቸውንያጣሉ፡፡
5ኛ) ደመወዛቸው በህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት (መአጥፕ) እየተከፈላቸው በወረዳ የሚሰሩ የመንግስትሰራተኞች ይህንን ፕሮግራም በተግባርላይ እንዲያውሉት ይገደዳሉ፣
6ኛ) የሰፈራ ፕሮግራሙን የሚቃወሙ አርሶ አደሮች እና ፕሮግራሙን በስራ ላይ ለማዋል ተቃዋሚ የሆኑ የመንግስትሰራተኞች፣ የሰፈራ ጠያቂዎች እናየእነርሱን ዘመዶች ጨምሮ በቁጥጥር ስር የመዋል፣ የድብደባ፣ የማሰቃየት እና የግድያ ሰለባዒላማ የመሆን ዕድል ይጠብቃቸዋል፣
7ኛ) የሰፈራ ጠያቂዎች እነዚህ ሁሉ ጉዳቶች የሚመጡት ከዓለም ባንክ የትግበራ ፖሊሲዎች እና ከአሰራር ሂደቶች አናሳነትእና መስተጋብራዊ ቅንጅትጉድለት ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 “ሞትን ቁጭ ብሎ መጠበቅ፡ በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል ህዝቦችን ማፈናቀል እና የመንደር ምስረታ“ በሚልርዕስ ሂዩማን ራይትስ ዎችየተባለው ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባለ 115 ገጽ ዘገባ አቅርቦ ነበር፡፡ ያዘገባ በአኟክ ህዝቦች ቀርቦ የነበረውን ውንጀላ አግባብ በሆነመልኩ የደገፈ እና የልማት ድጋፍ ቡድኑን ስህተቶች እናጉድለቶች ነቅሶ በማውጣት በኢትዮጵያ በመንደር ምስረታ ፕሮግራም ሰበብ ታላቅ ውርደት እናውደቀትን ያስከተለ መሆኑንዘገባው ይፋ አድረጓል፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንዲህ በማለት የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥቷል፡
የኢትዮጵያ መንግስት በመንደር ምስረታ ፕሮግራሙ አማካይነት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩትን በምዕራብ ጋምቤላ ለዘመናትከቀደምቶቻቸው ጀምሮ ሰፍረውከቆዩባቸው ቀዬዎች በግዳጅ በማፈናቀል ወደ አልለመዱት እና አዲስ ወደሆኑ አካባቢዎችእንዲሰፍሩ አድርጓል፡፡ እንደዚህ ያሉት ህዝቦችን ከአንድ ቦታወደ ሌላ ቦታ የማፈናቀሉ ፕረግራም ምንም ዓይነት ጥናት እናምክክር ያልተደረገበት እና ለግዳጅ መፈናቀሉ ሰለባ ለሆኑት ወገኖችም ምንም ዓይነት ካሳሳይሰጥ የተካሄደ ፕሮግራምነበር፡፡
መንግስት መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን እና የመሰረተ ልማት አውታሮችን ለማሟላት ቃል የገባ ቢሆንም አዲሶቹ የሰፈራመንደሮች የምግብ እጥረትያለባቸው፣ የግብርና ድጋፍ ጨርሶ የሌለበት፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶች ፈጽሞየሌሉባቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ የሰፈራ ፕሮግራሙንየሚቃወሙ ካሉ እነዚህን ሰዎች በማስፈራራት፣ አደጋ በማድረስ፣ እናከህግ አግባብ ውጭ የዘፈቀደ እስራትን በማካሄድ በግዳጅ በመከናወን ላይ የሚገኝየሰፈራ ፕሮግራም ነው፡፡ ባለፈው ዓመትየመንግስት የደህንነት ኃይሎች ቢያንስ 20 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን በመፈጸም የሰፈራ ፕሮግራሙንአስቸጋሪነትየበለጠ ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ፍርኃት እና ማስፈራራት በጥቃቱ ሰለባ ህዝቦች ላይ በገፍ ተንሰራፍተውይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ እየፈጸመ ባለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ላይ ያለው እውነታ፣
የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን የአኟክ ህዝቦች ያቀረቡትን ቅሬታ በመቀበል አጣሪ ኮሚቴ እንዲሄድ እና እንዲያጣራበማድረግ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 21/2014የምርመራ ውጤት የሆነውን ዘገባ በማዘጋጀት ዘገባው ለውስጥ ፍጆታ ብቻ እንዲውልበማድረግ ለዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት፣ ለዋና አስፈጻሚ ዳሬክተሮች፣ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሌሎች እንዲደርስአሰራጭቷል፡፡ ይህ ውሱን ስርጭት ያለው የምርመራ ዘገባ የዓለም ባንክ ስራ አስኪያጆችን የስራ ግድየለሽነትደረጃንለማሳየት እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ስራ አስኪያጆች እና በሌሎች አገሮች ያሉት አለቆች ድርጊት በዓለም ህዝብ ዘንድእንዲታወቅ በማሰብሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በድረ ገጽ ላይ እንዲለቀቅ ብቻ ነበር የተደረገው፡፡ ግን የሚስጥሩ ዘገባባልታወቀ መንገድ ለሕዝብ አንድከፋፈል ተደርግዋል ።
የምርመራ ቡድኑ “ኢትዮጵያ፡ ክፍል 3 የመሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስፋፋት (P128891)” በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን እጅግበጣም አስደንጋጭ እና ለህሊናየሚዘገንን ዘገባ አቅርቧል፡፡ (የጥናቱን ግኝት የበለጠ አጽንኦ ለመስጠት በማሰብ የፊደሎቹፎንቶች ደማቅ ቀለም እንዲሆኑ እና ልዩ የሆኑ ግኝቶችንለማመላከት በተራ ቁጥርነት የሚያገለግሎ ቁጥሮችም በሮማውያንእንዲሆኑ አድርጊያለሁ፡፡)
[ለአንባቢዎቸ ማስታወሻ፡ በምርመራ ቡድኑ በቀረበው ዘገባ መሰረት አንባቢዎቸ የጥናቱን ግኝቶች በጥንቃቄ እናበጥሞናእንድታነቡ እጠይቃለሁ፡፡ አብዛኞቹ አንባቢዎች በቢሮክራሲያዊ የማደናገሪያ ቃላት እና ሀረጎች የቋንቋአጠቃቀም ምክንያትሊያደናግሩ እና በቀላሉም ግንዛቤ ለመውሰድ አስቸጋሪ ሊሆኑ እንደሚቸሉ ይታመናል፡፡ባለስልጣኖች የዘገባውን መግለጫበሚሰጡበት ወቅት ወዲያውኑ ከስር የእንግሊዝኛውን (በቀላል አማርኛ)ትርጉም አዘጋጅቸዋለሁ፡፡]
[I]…የቡድኑ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው የፕሮጅክቱ አስተዳደር በአራት ክልሎች ሊተገበር የተዘጋጀውን የክፍል 3የመሰረታዊ አገልግሎቶች የጉዳትትንተና/risk analysis ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት ፈጽሞ አላከናወነም፣ ወይም ደግሞበየጊዜው ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች ማቀለያ የሚሆኑ የመፍትሄእርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችሉ በቂ የሆኑ ዝግጅቶችአልተደረጉም፡፡ የምርመራ ቡድኑ እንዳረጋገጠው የአስተዳደሩ አቀራረብ ደረጃውን የጠበቀወይም ደግሞ የጉዳቱ ሰለባሊሆኑ ለሚችሉት የማህበረሰብ ክፍሎች አስቀድሞ በመከለካያነት ሊያገለግል የሚችል አጠቃላይ የሆነ የጉዳት ትንተናየድርጊትማዕቀፍ መመሪያ (ጉትድማመ) በተሟላ መልኩ እና በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅቶ አልቀረበም፡፡ የምርራ ቡድኑ እነዚህየተዘለሉ እና የተረሱ ነገሮችን በፕሮጀክትሰነዱ 2.20 ከተቀመጠው ጋር ሊሄዱ እንዳልቻሉ እና ይልቁንም ከዚህ ጋር በተጻረረመልኩ እንደሆኑ በግልጽ አሳይቷል፡፡
[II] … በህዝብ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍል 3 ፕሮጀክት ማጽደቅ ወቅት እና ከላይ እንደተጠቀሰው ፕሮጀከቱንለመተግበር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎችጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉት ጉዳቶች በቂ በሆነ መልኩ ጥናት ያልተካሄደባቸው ወይምደግሞ በአግባቡ ያልተያዙ እንዲሁም በክፍል 3 የፕሮጀክት ትግበራወቅት ሊከሰቱ የሚችሉን ጉዳቶች እንዴት ማስወገድእንደሚቻል ያልተየ እንደነበር የምርመራ ቡድኑ ግለጽ አድርጓል፡፡
[III] በማስፈጸሚያ የፕሮጀክት ሰነዱ ቁጥር 4.10 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የፕሮጀክት አስተዳደሩ ይህ የህዝብመሰረታዊ አገልግሎት ክፍል 3 ሰነድሲዘጋጅ ከዚህ ጋር እኩል ተመጣጣኝ የሆነ ወይም የበለጠ ጥቅም ለአካባቢውህብረተሰብ ሊሰጥ ይገባ ነበር፡፡ የጥናት ቡድኑ ከአኟክ ህዝብ ጋር ቀጥተኛግንኙነት ያላቸውን እንደ የኑሮ ሁኔታ፣ ደህንነት፣መሬት እና የተፈጥሮ ሀብቶች የማግኘት መብትን የፕሮጀክቱ ክፍል 3 የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶችሰነድ ሲዘጋጅእንዲካተቱ አላደረግም፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች እንዳሉ በሙሉ ከግንዛቤ ውስጥ ሳይወሰዱ የተዘለሉ ስለሆነከፕሮጀክት ሰነዱቁጥር 4.10 ጋር በተጻረረ መልኩ ተግባራዊ ሳይደረጉ ቀርተዋል፡፡
[IV] … ከባንኩ ፖሊሲዎች አንጻር የህብረተሰቡን የልማት ፕሮግራም እና የህዝቡን መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከማረጋገጥአኳያ በትግበራ አካሄዱ መካከልበፕሮጀክት ሰነድ ማጽደቅ እና በትግበራ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶች እና ችግሮችበተለይም እንደ ጋምቤላ ባለ ክልል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውቤተሰብ የመንግስት የልማት የሰፈራ ፕሮግራም እናየመሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ በሆነበት ማህበረሰብ ውስጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መታየትነበረበት፡፡ በምርመራ ቡድኑየጥናት ግኝት መሰረት በጋምቤላ መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን በግብርናው ዘርፍ እና በሌሎች የኑሮ ሁኔታዎች በጥራትእናበበቂ ሁኔታ ለማግኘት እንዲቻል የፕሮጀክቱ አስተዳደር በየጊዜው የሚከሰቱ ችግሮችን እና ችግሮቹን ለማስወገድ በስራ ላይየሚውሉ የአካሄድስልቶችን ከግንዛቤ በማስገባት በሰነዱ ላይ እንዲካተቱ አላደረግም፡፡
[V]…የክፍል 3 የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ትግበራ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 3 የጋራ የምክክር ፕሮግራሞች እናየትግበራ ድጋፍ ተልዕኮዎችተካሂደዋል፣ ሆኖም ግን ከላይ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ የቀረቡ ዘገባዎች ምንም ነገር ትንፍሽ ሳይሉእንዲታለፍ አድርገዋል፡፡ የምርመራ ቡድኑ የክትትል እናየቁጥጥር ስርዓቱ በፖሊሲው ላይ ከተጠቀሰው በተጻረረ መልኩተግባራዊ ሆኗል፡፡
[VI]… የምርመራ ቡድኑ ይፋ እንዳደረገው በሰነዱ ላይ በተራ ቁጥር 10.02 በተጠቀሰው መሰረት የፕሮጀክት አስተዳደሩከተቀመጡት መስፈርቶች አንጻርበህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍል 3 ዝግጅት እና ማጽደቅ ጊዜ እየታዩ ተግባራዊእንዲሆኑ አላደረግም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምርመራ ቡድኑለመጠቆም እንደሞከረው ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያየተመደበው ገንዘብ በወረዳ ደረጃ ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገበት በስራ ላይ ይውላል የሚለውየባንኩ እምነት ቀጣይነትባለው ሁኔታ ሊካሄድ እንደማይችል የጥናት ቡድኑ በግልጽ አሳውቋል፡፡
[VII]…የልማት ፕሮጀክት ቢሮው የውጤት አመልካቾች በመጀመሪያው የዕቅድ እና በተከታታይም የገንዘብ ብክነት አደጋአናሳ መሆኑን ቢያመላክቱምበቀጣዮቹ ጊዚያት ሊፈጸም ስለሚችልበት ሁኔታ ግን የተዘጋጀ ነገር እንደሌለ የጥናት ቡድኑጠቁሟል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እነዚህ ከገንዘብ አጠቃቀም ጋርየተያያዙ ጉዳዮችን ለመቆጣጠር እና ለመከታተል እየተደረገያለው ጥረት በፕሮጀክት ሰነዱ ላይ የተገለጸው ከባንኩ ፖሊሲ OP/BP 10.00 ጋር ተጻራሪበሆነ መልኩ የተቀመጠ ነው፡፡
የምርመራ ቡድኑ ዘገባ በቀላል የእንግሊዝኛ (አማርኛ ) ቋንቋ ሲተረጎም፣
የቢሮክራቶች ቋንቋ ቢሮክራሲያዊ አገላለጽ ወይም ደግሞ ባለስልጣናዊነት መንፈስ የሰፈረበት ሆኖ ይገኛል፡፡ በቀላሉ ግንዛቤሊወሰድባቸው በማይችሉ፣አደናጋሪ በሆኑ፣ በአዳዲስ የአባባል ቃላት እና ሀረጎች የተሞሉ፣ መንታ ምላሶችየሚግተለተሉባቸው፣ አዳዲስ ስያሜዎች የሚጎርፉባቸው፣ ቀጥተኛ ባልሆኑአገላለጾች የተሸሞነሞኑ፣ እንደሰም እና ወርቅዓይነት አቀራረብ የታጀለባቸው እና በቀላሉ ግልጽ ሊሆኑ በማይችሉ አደናጋሪ አህጽሮተ ቃላት እና ሀረጎችየተሞሉ ናቸው፡፡ቢሮክራሲያዊነት ስለግልጽነት እጦት ጉዳይ ነው፣ ግልጽ ያለመሆን ወይም ደግሞ ቀጥተኛ ሆኖ ያለመቅረብ ጉዳይ ነው፡፡ቢሮክራሲያዊዘገባዎች ሁልጊዜ ግልጽነት የጎደላቸው፣ የተጣመሙ እና የተንሻፈፉ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ለማንበብወይም ደግሞ አንብቦ ግንዛቤ ለመውሰድ በጣምአስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን እንዲያደናግሩ እና ቀልብ እንዲያሳጡ ሆነውየተዘጋጁ የሸፍጥ ሰነዶች ናቸው፡፡
ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግ በቢሮክራሲው የተካነ እና ቅስናውን የወሰደ የቢሮክራት ጠቢብ በፍጹም አካፋን አካፋ ብሎ በቀጥታአይጠራም፡፡ ከዚህ ይልቅአካፋን ጫፉ ስለትነት ያለው፣ አራት ማዕዘን የሆነ፣ በረዥሙ የእንጨት እጀታው ጫፍ ላይ ብረትየተሰካለት ወይም ደግሞ ጥብቅ የሆነ ፕላስቲክየተገጠመለት እና ከበርካታ ተግባራቱ መካከል የከብቶችን አዛባ ለመፈንጨትወይም ለመበተን የምተቂም መሳርያ በሚል መግለጽ እና ማደናገርይቀናቸዋል፡፡ ብዙዎቹ ቢሮክራቶች የተካኑበት እንደዚህያሉ አቀራረቦችን በማራመድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
[ጥቂቶች የአጥኝ ቡድኑን የጥናት ግኝት የቢሮክራሲ ዋና መለያ ባህሪ ሆኖ አግኝተውታል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው በጥናትቡድኑ የምርመራ ግኝት ላይተመስርቶ ስለቢሮክራሲ የተገለጸ የእራሴ የእንግሊዝኛ (ያማርኛ ትርጉ) ትርጉም ነው፡፡የምርመራ ቡድኑን ግኝት በተመለከተ ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰውየሮማውያን ቁጥሮችን እንደዋቢ ማጣቀሻ መውሰድይቻላል፡፡]
[I] በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ አስተዳደር እና በሌሎች አገሮች የሚገኙት የባንኩ ኃላፊዎች የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶችየሚል ፕሮግራም ነድፈውበህዝቦች ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አያስከትልም ብለው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያያሉ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ምንም ዓይነት ስራ የማይሰሩለይስሙላ የተቀመጡ ናቸው ፡፡ ፕሮግራሙን በስራ ተርጉመውእንዲያሳዩ በኃላፊነት ቦታ ላይ ብቃት አላሳዩም፡፡
የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ወይም ደግሞ ኃላፊዎች በጋምቤላ ህዝቦች የመንደር ምሰረታ ፕሮግራም ለውጥ አመጣ አላመጣወይም ደግሞ ፋይዳ ያለው ነገርአስገኘ አላስገኘ ደንታቸው አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ስለይፋ የፖሊሲ እና የመመሪያሰነዶቻቸው ስለጋምቤላ ህዝቦች መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማቅረብጥናት ሲጠና በፕሮጀክት ትግበራ ሂደቱ ወቅት በአኟክማህበረሰብ ላይ ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ጉዳቶች እና አደጋዎች የተጠናና እና በሰነዱ ላይ የተካተተምንም ዓይነት ነገር የለም፡፡የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ወይም ኃላፊዎች ይህን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮግራም በአራት ክልሎች ላይ በአንድጊዜለመተግበር የመሞከራቸው ሁኔታ ሲታይ ሊውጡት ከሚችሉት በላይ እያኘኩ የሚገኙ መሆናቸውን በግልጽ ያመላክታል፡፡በፕሮጀክት ማጽደቅ ወቅትበባንኩ የፖሊሲ ሰነድ በተራ ቁጥር 2.20 ላይ ከተጠቀሰው ጋር አብሮ የማይሄድ መሆኑእየታወቀ ወደተግባር እንዲገባ መደረጉ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎችወይም ኃላፊዎች ከሚከተሉት ውስጥ አንደኛውን ሊሆኑእንደሚችሉ ያመላክታል፡ የሙያ ብቃትየለሽነት፣ የለየላቸው የስራ ጸር የሆኑ ሰነፎች፣ ለምንም ነገርየማያስቡ ግዴለሾች፣በቀጣይነት በህዝቦች ላይ ሊመጣ ስለሚችለው ጉዳት እና አደጋ የማያውቁ ክህሎቱ የሌላቸው ደንቆሮዎች፣ ምንም ዓይነትደንታየሌላቸው እና የሞራልም ሆነ የሙያ ስብዕና የሌላቸው ለህዝብ መብት ኬሬዳሽ የሚሉ ከንቱዎች መሆናቸውንያሳያል፡፡ መፍትሄውን ከቦርጫቸው ስርተወሽቆ ያገኙታል!
[II] የዓለም ባንክ ሀገራዊ ፕሮግራም ስራ አስፈጻሚዎች ወይም ኃላፊዎች ምንም ዓይነት ብቃት የሌላቸው እና ኃላፊነትየማይሰማቸው እንዲሁም ደንታቢስ የመሆን እና የሙያ ብቃት የሌላቸው፣ ፕሮጀክቱ በመተግበሩ ምክንያት በአኟክማህበረሰብ ላይ ወደፊት እና አሁንም በትግበራ ወቅት ሊያስከትልየሚችለውን ጉዳት እና አደጋ መለየት የማይችሉ እናየመሰረታዊ አገልግሎት ፕሮጀክቱ ሲተገበር ለህዝቡ ምን ፋይዳ ያለው ነገር እንደሚያመጣ ግንዛቤውየሌላቸው ናቸው፡፡አንድ ጊዜ ጉዳቱ መድረስ ከጀመረ እና የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ነገሮች በመጥፎ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ካወቁስህተቶቻቸውንመቆጣጠር እና በእነርሱ ስር እንዲሆኑ ለማድረግ አይችሉም፣ ወይም ደግሞ የማስተካከያ እርምጃዎችንመውሰድ አይችሉም ምክንያቱም ወደፊት ምንሊሰሩ እንደሚችሉ የሚያውቁት ነገር የሌላቸው የሙያ ብቃት የለሾችናቸው፡፡ ስለሆነም እነርሱ ባለማወቅ ያደረሱትን ታላቅ ጥፋት ለመፍታት የሚችልሌላ ኃይል የለም ብለው በማሰብእጆቻቸውን አጣጥፈው በመቀመጥ ወይም ደግሞ የስራ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ባለመቻል በአቅመቢስነትመሳቂያ፣ሰነፍ፣ የደከመ አቅመቢስ እና ተነሳሽነት የሌለው ሆነው በወራዳ ተግባራት ተፈርጅው ከመቀመጥ ምንም የጨመሩት ነገርየለም፡፡
[III] ፕሮጀክቱን ከማቀድ ጅምሮ እስከ ትግበራው ወቅት ጊዜ ድረስ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች አቅመ ቢሶች ነበሩወይም ደግሞ የባንኩን የፖሊሰሰነድ ተራ ቁጥር 4.10 [መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች የባንኩ ፕሮግራም የሰዎችን ክብር ሙሉበሙሉ እንዲያከብር፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣የኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ነገሮች ሁሉእንዲያከብሩ የሚያረጋግጥ] የሚያስገድደውን ሰነድ ሆን ብለው የማያውቁ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ሆኖም እስከ አሁንም ድረስበአኟክ ማህበረሰብ ላይ የደረሰውን ጉዳት ከግንዛቤ በማስገባት ተመጣጣኝ የሆነ የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድሁኔታውንእንደገና የማሻሻል እና ጉዳቱን የመቀነስ ስራ መስራት ይቻል ነበር፡፡ ይህንንም ለማድረግ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ተጠቃሚይሆናል የተባለውንህዝብ በመሰብሰብ በጋራ ከህዝቡ ጋር መመካከር እና ወደፊት በዚህ ፕሮግራም ጉዳት ሊደርስባቸውይችላል ከሚባሉ ህዝቦች ጋር በመመካከር ባህሉንበማያዛባ መልኩ ጥቅሞቻቸውን ሊያስከብር የሚችል የመፍትሄ እርምጃመውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ቋሚ ህዝቦችን ለዘመናት ከኖሩበትቀያቸው በማፈናቀል ከኖሩበት የተሻለ ጥቅምበሌለበት ሁኔታ ማንገላታት ተገቢ አይደለም፡፡
[IV] በኢትዮጵያ ያሉ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ቆሎ አየቆረጠሙ መራመድ የማይችሉ ፍጡራን ናቸው፡፡ ቀኝ እጃቸውየግራ እጃቸው ምን እየሰራእንደሆነ የሚያውቁ ናቸው ፡፡ የዓለም ባንክ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የኢኮኖሚያዊተጠቃሚነት ያላገኙትን ማህበረሰቦች የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነትባለው መልኩ በማህበራዊ እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታእንዲሁም የመሰረታዊ ትምህርት፣ የጤና፣ ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ እናየህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታእንዲሻሻል ማድረግ ማስቻል ነው፡፡ የጋምቤላ ህዝብ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 የአቅም ግንባታ ስራእንዲጠናከር፣ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ትክክለኛ የሆነ የገንዘብ አስተዳደር በየክልሎቹ እንዲኖር እና መሰረታዊአገልግሎቶች ማለትም እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣የውኃ አቅርቦት እና ንጽህና እንዲሁም የገጠር መንገዶች ተሟልተውእንዲቀርቡ ለማድረግ ነው፡፡
የባንኩ የስራ አስፈጻሚዎች በምቹ ወንበሮቻቸው ላይ ተንፈላስሰው በመቀመጥ ክትትል የማድረግ እና ሁለቱንምፕሮግራሞች የማስተባበር ስራቸውንአልሰሩም፡፡ በዚህም መሰረት የአኟክ ማህበረሰብ ቅሬታውን እንዳቀረበው ሁሉየጋምቤላ ህዝብ ከጉዳት እና ከአደጋ ላይ ተጥሎ ይገኛል፡፡ በሌላ አገላለጽየባንኩ የስራ አስፈጻሚዎች ስራቸውን በአግባቡባለመስራታቸው ምክንያት የአኟክ ማህበረሰብ ለምነቱ ወደተሟጠጠ ጠፍ መሬት ላይ ተወስዶ እንዲሰፍርተደርጓል፣እንዲሁም ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ የውኃ ጉድጓዶች ወይም ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች የሌሉበት አዲስ መንደርበግዳጅ እንዲመሰርትተደርጓል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ጥቂት የአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የአኟክ ማህበረሰብ አባላት እናልጆቻቸው በመንደር ምስረታ ፕሮግራሙ ምክንያት በረኃብህይወታቸው አልፏል፡፡ ሌሎቹ የግዳጅ የሰፈራ ፕሮግራሙንየተቃወሙትን የአኟክ ማህበረሰብ አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል፣ የድብደባ፣ የስቃይ እናየግድያ ሰለባ ዒላማ እንዲሆኑተዳርገዋል፡፡ ይህ ድርጊት የጋምቤላ እና የዓለም ባንክ ከመሆኑ በስተቀር ጥንታዊ የሮማ ከተማ የሆነችውን የፖምፔየእሳትቃጠሎ እና እርባናየለሽ ድርጊትን ከመፈጸም የሚለየው ነገር የለም፡፡
በኢትዮጵያ ባሉ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጸሚዎች እጆች ላይ ደም አለ!
[V] በኢትዮጵያ በአኟክ ህዝብ ላይ የዓለም ባንክ ያደረሰውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ለመደበቅ ሲባል ዓለም ባንክ እራሱጥፋተኝነቱ እንዳይተወቅ የዝምታሽረባ ዱለታ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የጋራ ጉባኤ ተልዕኮ ዋና ዓላማው በፕሮጀክቱ ሁሉምአካሎች ላይ የሚታየውን መሻሻል ለመገምገም እና የትግበራድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡ የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ መስከረም 2012ለህዝቡ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 ማስፈጸሚያ የሚውል 600 ሚሊዮን ዶላርሰጥቷል፡፡ የመሰረታዊአገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 መተግበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የዓለም ባንክ ሶስት የጋራ ግምገማዎች ያደረገ ሲሆን በአኟክህዝቦች ላይስለደረሰው ጉዳት አንዳችም ቃል ትንፍሽ ሳይል አልፎታል፡፡ የዓለም ባንክ “የኢንቨስትመንት የማበደር ፖሊሲ(OP/BP 10.00)” ስለፖሊሲው፣ ስለአካሄድስርዓቱ፣ ስለፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና ክትትል በተበዳሪው ወይም በፕሮጀክቱተጠቃሚዎች፣ ስለፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና ስለስምምነቱ የተፈጻሚነት ደረጃዝርዝር የሆነ የፖሊሲውን መግለጫ ይሰጣል፡፡የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች በስራዎቻቸው ላይ ለጥ ብለው ተኝተዋል ወይም ደግሞ አውቀው ሆንብለው ስለባንኩየኢንቨስትመንት እና ክትትል ፖሊሲ ምንም አናውቅም በማለት አድፍጠዋል፡፡
[VI] በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች የባንኩ ገንዘብ በወረዳ ደረጃ ቁጥጥር ይደረግበታል ሲሉ ግልጽ የሆነውሸትን ዋሽተዋል እንዲሁም ታላቅየልብ ወለድ ትረካን ተርከዋል፡፡ የዓለም ባንክ ሰነድ በተራ ቁጥር OMS 2.20 ላይየተቀመጠው ባንኩ ከሁሉም ነገር በላይ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ተግባራትከተበዳሪው ዓለም አቀፍ ስምምነት አንጻርአካባቢን፣ ጤናን፣ እና አጠቃላይ የህዝቦችን ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ መታየት እንዳለባቸው ያስገነዝባል፡፡OP/BP 10.02 የሰነዱ ክፍል እንደሚያመላክተው በፕሮጀክት ትግበራ ወቅት ባንኩ የገንዘብ አጠቃቀሙን እና አያያዝ ሁኔታእንዲሁም ያለው ገንዘብ በቂመሆን አለመሆኑን መከታተል እና መገምገም እንዳለበት በግልጽ ያመላክታል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች አቅመቢሶች ወይም ደግሞ ሆን ብለው ታላቅ ኃላፊነትን ይዘው ኃላፊነታቸውንግን በአግባቡ ለመወጣት ግንግድ የሌላቸው ደንታቢሶች ናቸው፡፡ ወረዳዎች ከክልሎች እና ከዞኖች በመቀጠል በሀገሪቱያልተማከለ አስተዳደራዊ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ በሶስተኛነትደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ወረዳዎች በጣም ጉልህ የሆነ የሙስናወንጀል የሚፈጸምባቸው ማዕከላት ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫለህወሀት 99.6 በመቶ የድምጽውጤት እንዲገኝ ያደረጉት የወረዳ ምክር ቤቶች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በኢትዮጵያ ያሉ የዓለም ባንክ ስራአስፈጻሚዎችየራሳቸው የሆነውን ስራ እና ሙያዊ ተግባራቸውን እርግፍ አድርገው ትተው በጭፍንነት ታማኝነት ለሌላቸው እና ስለገንዘብአያያዝ እናአስተዳደር ምንም ዓነት እውቀት ለሌላቸው ለወረዳ ሙሰኛ ባለስልጣኖች ሰጥተው በህዝብ ስም ለህዝብ የመጣንየብድር ገንዘብ እንዲባክን በማድረግ ላይይገኛሉ፡፡ (ምንድን ነበር የሚያስቡት? ያንን ጣያቄ እንዲጫር አድርግ!)
[VII] [ይህ ግኝት የገንዘብ ተጠያቂነት ጉዳይ እስከተነሳ ድረስ እጅግ በጣም የሚያስገርምና የሚያስደንቅ ነው፡፡] በኢትዮጵያያሉ የዓለም ባንክ ስራአስፈጻሚዎች የባንኩን ገንዘብ ከሙስና ለመከላከል የሰሩት አንዳችም ነገር የለም፡፡ ለዚህም ነው“በመጀመሪያ ብቁ ያልሆነ የፋይናንስ አደጋ“ የሚል ሀረግየተጨመረው፡፡ የዓለም ባንክ OP/BP 10.00 እና የትንተና መሳሪያዎች (የህዝብ ወጭ እና የገንዘብ ተጠያቂነት) (ህወገተ) በተቀባይ ክልሎች የሚላከውገንዘብ እንዳይባክንየተዘጋጀው፡፡ እነዚህ ፖሊሲዎች እና የትንተና መሳሪያዎች አጠቃላይ በሆነ መልኩ የሙስናን አደጋ ይከላከላሉ ባይባልምአጠቃላይበሆነ መለኩ ግን ዕቅድ፣ ክትትል እና ግምገማዎች የሚካሄዱ ከሆነ በተቀባይ አገሮች ላይ አዎንታዊ የሆነ ውጤትንያመጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የዓለምባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ስለገንዘብ አደጋ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ንእንዳለ ለሙሰኞች እና ለዘራፊዎች ትተውታል!
ስለዓለም ባንክ የአሰራር ሁኔታ እና ቅዱስ ስላልሆነው ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች የልማት አጋርነት ቡድንእየተባለ ለሚጠራው መንግስታዊያልሆነ አካል አዲስ አይደለሁም፡፡ የእነዚህን አካላት ዘገባዎች አጥንቻለሁ፣ እናምፖሊሲዎቻቸውን፣ የትግበራ ሰነዶቻቸውን፣ መመሪያዎችን እና ለህዝብየሚሰጡ መግለጫዎችን እንዲሁም ሌሎችንህትመቶች እስካሁን ድረስ አጥንቻለሁ፡፡ ከዚህ አንጻር ስለፖሊሲዎቻቸው፣ ተሞክሯቸው እና በኢትዮጵያእያከናወኗቸውስላሉት ተግባራት ግንዛቤ አለኝ ብዬ መናገር እችላለሁ፡፡
“በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የተለቀቀውን ባለ 417 ገጽ የዓለም ባንክን ዘገባ ከጸሀፊዎቹበስተቀር ምናልባትም ከማንምበበለጠ ሁኔታ ለበርካታ ጊዜ ደግሜ እና ደጋግሜ ያነበብኩት እኔ እሆናለሁ የሚል ግምትአለኝ፡፡ በእርግጥ ያንን ዘገባ ለበርካታ ጊዜ አንብቤዋለሁ፣ እናምምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ለህዝብ ለመናገር ሀፍረትይሰማኛል፡፡ ያንን ዘገባ በመጠቀም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የህወሀትን የሙስና ግዛት ለማጋለጥ በርካታበሙስና ላይያነጣጠሩ ተችቶችን በማዘጋጅበት ጊዜ ተጠቅሜበታለሁ፡፡
የሙስና ዘገባ ማዘጋጀት ንጹህ አየር የመተንፈስ ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እቀበላለሁ፡፡ የዓለም ባንክ የሙስና ዘገባ እንደዚህእንደ ኢትዮጵያ ያለ ጥልቀት፣ወርድ እና ስፋት ያለው በሌሎች ሀገሮች ላይ እስከ አሁን ድረስ አላየሁም፡፡ አንድ ነገር ህልውከሆነ ለማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያያለውን የሙስናን ጥልቀት እና ስፋት ጥልቀት ባለው ሁኔታ አጥንቶበማቅረቡ እና የህወሀት የሙስና የግዛት አድማስ በመጋለጡ የተሰማኝ ደስታ ወደርየለውም፣ ከዚህም በላይ ይህንን ጥናትያቀረበውን እና እውነታውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ያደረገውን ዓለም ባንክን ከልብ አመስግኘ ነበር፡፡“በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ የሚለው የዓለም ባንክ የጥናት ዘገባ የግልጽነት እና የተጠያቂነትን ጉዳይ አስመልክቶ አዲስምዕራፍ ለመክፈትእንደቻለ እምነት አለኝ፡፡ በኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮች ያሉትን የባንኩን ፕሮግራሞችንየሚያስፈጽሙትን ሁሉንም የዓለም ባንክ ሰራተኞች የመክሰስዓላማ የለኝም፡፡ ጥቂት የሆኑ መልካም ስብዕናን የተላበሱ እናስለኢትዮጵያ እውነቱን ብቻ የሚናገሩ እና በመሸበት ማደር የሚፈልጉ እውነተኛ እና ሀቀኛየዓለም ባንክ ሙያተኞች አሉ፡፡ከእነዚህም መካከል በዓለም ባንክ ውስጥ የሚገኙ ወልፍጋንግ ፌንግለር የተባሉት ታዋቂ የኢኮኖሚ ጠበብትአንዱናቸው፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ረኃብ እና የምግብ እህል እጥረት የለም በማለት ለመካድሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ ፌንግለርግን ሽንጣቸውን ገትረው ፊትለፊት ተከራከሩት፡፡ ፌንግለር እንዲህ አሉ፣ “በአፍሪካ ቀንድያለው የረኃብ ቀውስ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ድርቆች በተደጋጋሚይከሰታሉ፣ ሆኖም ግን ያንን ድርቅ ለማስወገድ በሚል ሌላመጥፎ የሆነ እና ሌላ ድርቅ እና ረኃብን ሊያመጣ የሚችል ፖሊሲ ትነድፋላችሁ፡፡ በሌላአባባል በኢትዮጵያ ለረሀብበተደጋጋሚ መከሰት ትልቁ ችግር ድርቁ ሳይሆን የመልካም አስተዳደር እጦት ነው::”
ሁልጊዜ ስለሚከሰተው ረኃብ ዓለም አቀፍ የእርዳታ እና የብዙህን አገሮች አንድ ዓይነት የቢሮክራሲያዊ ቋንቋን በመፍጠርለማደናገሪያነት በመጠቀም ረሀብየሚከሰተው በመልካም አስተዳደር እጦት እና ትክክለኛ ፖሊሲ ቀርጾ መንቀሳቀስ ሳይቻልበመቅረቱ የሚለውን ቸል በማለት ሌሎችን ፍሬከርስኪ ነገሮችንእያመጡ ህዝብን በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳሬክተር የሆኑት እንደ ጓንግ ዠ ቸን ረዥም ለብ ወለድ ትርኮችን መናገር የሚችሉ ሰዎች አሉ፡፡እ.ኤ.አ ታህሳስ 2012 ቸን እንዲህብለው ነበር፣ “በኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት በመፈጠሩ ምክንያት የድህነትደረጃውን እ.ኤ.አ በ2004/05 እና 2010/11 ባሉት ዓመታት መካከልቀደም ከነበረበት ከ38.7 በመቶ ወደ 29.6 በመቶበማውረድ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለት ሚሊዮን ተኩል የሚሆኑ ዜጎች ከድህነት ተላቅቀዋል…መንግስት እ.ኤ.አበ2014/15 ድህነትን ወደ 22.2 በመቶ ለማድረስ የያዘው ዕቀድ በጣም የተጋነነ ይመስላል፣ ሆኖም ግን ሊደረስበት የሚችልነው፡፡“
እንደ አቡጀዴ ከመቀደድ በላይ የሚያሳፍር ምን ነገር ሊኖር ይችላል ወገኖቼ?!
በአሁኑ ጊዜ ያለንበት ዓመት 2015 ነው! ስለዚህ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ድህነት በ22.2 በመቶ ወርዶ ይታያልን!? አቤትቅጥፈት! ወይ አይን ማውጣት!
ይገባኛል! በርግጥ ጉዳዩ ይገባኛል፡፡ የዓለም ባንክ ሰዎች ህወሀት እራሳቸውን ጥሩ አድርጎ እንዲስላቸው እነርሱ ደግሞህወሀትን ጥሩ ስዕል እንዳለውአድርገው ያቀርባሉ፡፡ የዓለም ባንክ ሰዎች ለህወሀት ትክክለኛውን ነገር ከተናገሩ ለእነርሱለእራሳቸውም ትክክለኛውን ነገር ይናገራሉ ማለት ነው፡፡ እነርሱስለህወሀት ስህተት ተናጋሪ ሆነው መቅረቡን አይፈልጉምምክንያቱም እነርሱም የሚያደርጉትን ያውቃሉና፡፡ በዚህም መሰረት ህወሀትን ለመጠበቅ ሲሉህዝብ በረሀብ እያለቀ እናበድርቅ ሲጎዳ በዓይናቸው እየተመለከቱ ለዝምታ ጸጥታው ዱለታ ተባባሪ ሆነው ህሊናቸውን ሸጠው ይታያሉ፡፡
የህወሀት ሙስና፣ ኢኮኖሚውን ማስተዳደር ያለመቻል እና በጋምቤላ ክልል በሰው ልጆች ላይ እየፈጸሙ ያሉት የመብትድፍጠጣ ተንሰራፍቶ እየታየየዓለም ባንክ ሰዎች ዓይናቸውን ጨፍነው፣ ጆሯቸውን ደፍነው ሆኖም ግን አፋቸውን ከፍተውየቅጥፈት አፈታሪክ በማውራት በኢትዮጵያ ልብወለድ የሆነየኢኮኖሚ ዕድገት እንዳለ አድርገው ይነግሩናል፡፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2012 የዓለም ባንክ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ አህጉር የኢኮኖሚዕድገት ሁለት ጊዜ እጥፍ በሚሆንመልኩ እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ በየዓመቱ በአማካይ በ10.6 በመቶ የሀገር ውስጥ እድገትእያስመዘገበ የመጣ ሲሆን ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች 5.2 በመቶዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ትልቅመሆኑን አንድ የዓለም ባንክ አዲስ ዘገባ ይፋ አድርጓል፡፡“
በእርግጥ የዓለም ባንክ የወያኔ ሸፍጥ እንደሆነ ያውቃል…! ከምንም ጥርጣሬ በላይ በሆነ መልኩ እንደሮኬት እየተተኮሰየሚነገረን የቅጥፈት የኢኮኖሚዕድገት መጣኔ እና ሌሎችም ተመሳሳይ የሆኑ በህዝብ ላይ የሚደረጉ የቅጥፈት አሀዞች ሁሉበመለስ ዜናዊ የቁጥር መመቀያ የስታቲስቲክስ ቢሮ እየተመረቱእየወጡ ለዓለም ባንክ፣ ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እናለሌሎችም እንደ ሀገራዊ እና የውጭ ድርጅቶች እንደ በቀቀን እንዲደግሙት በጸጥታ እየወጡየሚሰጡ እና በመጨረሻምመለስ ሁለተኛ ዘገባ አቅራቢ ሆኖ ባዶ የተፈበረከ ቁጥር እየጠራ እድገት ነው እያለ ከረባቱን እና መነጽሩን እያሳመረሲያሰለችንኖሮ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሲሰናበት አሁን ድግሞ የቅጥፈት ጓዶቹ የሆኑትን ደቀመዝሙሮቹን ተክቶልንአልፏል፡፡ “የመለስ ዜናዊ የቅጥፈት ኢኮኖሚክስ“በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችቴ ላይ ያቀረብኩትን ትንተና ከዓለምባንክ ወይም ደግሞ ከሌላ በመምጣት ማንም ሙያው እና እውነታው አለኝየሚል ቀርቦ ማስተባበል እንዲችል የመሞገቻመድረክ ለመክፈት ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ ሙግቴንም ማንም ተቀበሎ ሊሞግተኝ አልቻለም። ሆኖም ዉቸትአንዴት ዉነትንልሞግት ይችላል?
የሞተ እርዳታ/Dead Aid መጽሐፍ ደራሲ የሆነችው ዳምቢሳ ሞዮ በመጽሐፏ ላይ እንዲህ የሚል ጹሁፍ አስነብባለች፣ “…የዓለም ባንክ የጥናት ግኝትእንደሚያመለክተው 85 በመቶ የሚሆነው የልማት ዕርዳታ ከታቀደለት ዓላማ ውጭ ነውየሚውለው፡፡ ለጋሽ ሀገሮች በጣም ሙሰኛ የሆኑ አገዛዞችንእየፈለፈሉ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1980 እስከ 1996 ባሉት ዓመታትውስጥ ብቻ የዓለም ባንክ 72 በመቶ የሆነው ዕርዳታ ለህጉ ለማይገዙ ሀገሮች የተሰጠ ነው፡፡የለጋሽ ሀገሮችን መለገስእንዲችሉ የሚቀርበው ዕርዳታ የመፈለግ ጥያቄ በምንም ዓይነት ሁኔታ እርካታን የሚያገኝበት ሆኖ አልተገኘም፡፡“
እ.ኤ.አ ህዳር 2014 በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ዘገባ የሞዮን አባባል የሚደግፍ ንጹህ እና አወዛጋቢ ያልሆነማስረጃ አቅርቧል፡፡ ባለፉትሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ ምን ያህል ትንሽ ነገሮች ተለውጠዋል?!
የዓለም ባንክ አስመሳይነት በኢትዮጵያ፣
የዓለም ባንክ ተልዕኮ “በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ትውልድ የእድሜ ጣሪያ ስር አስከፊ የሆነውን ድህነትን ማጥፋት“ እና“የጋራ ብልጽግናን“ ማራመድየሚል ነው፡፡ ባንኩ ይህንን ዓላማ ለማሳካት በሚል በኢትዮጵያ ይህንን ተልዕኮ ለማሳካት ሲልየኢትዮጵያ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ የሚልፕሮጀክት (መአጥፕ) ነድፎ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ እንደ የዓለም ባንክዘገባ ከሆነ መአጥፕ በኢትዮጵያ ውስጥ አራት ክፍሎች አሉት፡፡ እነርሱም፡
1ኛ) በክልል እና በአካባቢ መንግስታት የሚሰጡ መሰረታዊ አገልግቶችን የማከፋፈል ስራ መስራት እና መከታተል፣
2ኛ) ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አገልግሎት ንዑስ ፕሮግራሞች በጣም አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማቅረብየሚያስችል አስተማማኝ የሆነ የገንዘብእገዛ ማድረግ፣
3ኛ) በክልል፣ እና በከተማ አሰተዳደሮች፣ በወረዳ እና በንዑስ ወረዳ ደረጃ አጥጋቢ በሆነ መልኩ ግልጽነት እና የህዝብ በጀትአጠቃቀም ስርዓትን መጠበቅእንዲሁም በበጀት ዝግጅት እና በአገልግሎት አቅርቦት ጊዜ ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉማበረታታት እና ውክልናም እንዲኖራቸው ማድረግ፣ እና
4ኛ) የዜጎችን ድምጽ ለማጠናከር እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዜጎች በበጀት ዝግጅት ሂደትላይ በንቃት መሳተፍ እንዲችሉየተመረጡ አካሄዶችን በመውሰድ የናሙና ሙከራ የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት፡፡
የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመአጥፕ ፕሮግራም እገዛ በማድረግ የ2 ቢሊዮን ዶላር ቃል ገብቶ እገዛበማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉትሁለት ዓመታት ብቻ ባንኩ ከፍተኛ የሆነ ማለትም 600 ሚሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል፡፡
እውነታው ግን የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ተልዕኮ በአሳዛኝ ሁኔታ ከሽፏል፡፡ በአራቱ ክልሎች የሚካሄደውን የመአጥፕየመንደር ምስረታ ፕሮጅከት 3ዝርዝር የጉዳት ትንተና ሳይካሄድ በመቅረቱ ውድቀትን ተከናንበዋል፡፡ የባንኩን የድርጊትመርሀ ግብር እና መመሪያዎችን ሳይከተል የሚሰራ ስለሆነ ከባንኩእምነት ውጭ ተጻራሪ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ስለሆነዓላማውን ስቷል፡፡ ባንኩ ፕሮግራሙን በሚተገብርበት ጊዜ ከአኟክ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦመወያየት እና መመካከርስላልቻለ በህዝቦች ላይ የሚመጣው አሉታዊ ተጽዕኖ በመኖሩ ፕሮግራሙ ውድቀት ደርሶበታል፡፡ ስመአጥፕ ፕሮጀክት 3እናስለማህበረሰቡ የልማት ፕሮግራም ስለጉዳት ትንተና በሰነዱ ማዕቀፍ ላያ በተያዘው መሰረት ስላልተሰራ አቅመቢስመሆናቸውን በግልጽ አመላክቷል፡፡የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ከአኟክ ማህበረሰብ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እና ጥብቅትስስር ካለው ከመሬት እና ከሌሎች ሀብቶች ከማግኘት አንጻርስለህዝቡ የኑሩ መሻሻል ሁኔታ፣ ስለህዝቡ ደህንነት እናስለመሰረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት ደንታ የላቸውም፡፡
በጋራ ግምገማቸው እና ፕሮጀክቱን በመተግበር ጊዜ ስለሚሰጡት እገዛ ዘገባዎች የይስሙላ እየቀባቡ የተሳሳቱ መረጃዎችንበመስጠት ወይም አስፈላጊያልሆኑ እውነታዎች ናቸው ብለው የሚያምኑባቸውን በማጥፋት ግልጽነትን እና ተጠያቂነትንእንዲጠፋ አድርገዋል፡፡ ብዙ የዕቅድ ስራዎችን፣ የክትትልወይም የቁጥጥር ስራዎችን ባንኩ እየሰራ አይደለም፡፡ ሙያዊ የሆነስራቸውን እና ግዴታዎቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው በመቶ ሚሊዮኖችየሚቆጠር ዶላር የሚካሄድ ፕሮግራምማስፈጸሚያን ገንዘብ በሙስና እስከ አንገታቸው ድረስ ለተዘፈቁ የወረዳ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡ እኔ ይኸ ጉዳይበጣምያሳስበኛል፣ ለምን እንደሆነ ለማወቅም ጉጉት ያድርብኛል፡፡ለመሆኑ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጸሚዎች በየዕለቱ ምን ሲሰሩ ነውየሚውሉት? (ነገስታታ ቀኑን ሙሉ ምን ይሰራልይ ብሎ መጠየቁ ይቀላል።)
ድምጼን ከፍ አድርጌ በመጮህ ምን ዓይነት ግራ የሚያጋባ መርሀግብር ነው የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በመተግበር ላይያለው?
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2013 የዓለም ባንክ ቡድን ፕሬዚዳንት የሆኑት ጅምዮንግ ኪም እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣“በመልማት ላይ ባሉ ሀገሮች ሙስናየህዝቦች ቁጥር አንድ ጠላት ነው… ሙስናን በምንም ዓይነት መንገድ ልንታገሰውአንችልም፣ እናም ባለን ስልጣን እና ኃይል ተጠቅመን ይህንን እኩይድርጊት ለማጥፋት ከእርሱ ጋር በጽናት መታገል አለብን…እያንዳንዷ ዶላር በሙስና የተዘፈቀ ባለስልጣን ወይም ደግሞ የቢዝነስ ሰው ወስዶ ከኪሱየሚጨምራት ጤናዋን ለመጠበቅከተሰለፈችው ነፍሰጡር ሴት ወይም ደግሞ ትምህርትን ከምትፈልግ ልጃገረድ ወይም ልጅ፣ ወይም ውኃ፣ መንገድ፣እናትምህርት ቤቶችን ከሚፈልጉ ማህበረሰቦች ሰርቆ የሚውስዳት ናት፡፡ ከዓለምነው ግብ ለመድረስ እና አስከፊ የሆነውንድህነት እ.ኤ.አ በ2030 ከዓለምለማጥፋት እና የጋራ ብልጽግና ለማራመድ እያንዳንዷ ዶላር የወሳኝነት ሚናትጫወታለች፡፡“
ኪም እ.ኤ.አ በ2015 ወደ ጋምቤላ መጥተው ወንድሞቼንና እህቶቼን ቢጎበኙ እና የእርሳቸው ባንክ ስንት ትምህርት ቤቶች፣ሆስፒታሎች፣ ኪሊኒኮች፣መንገድች እና የውኃ ግድጓዶች በ600 ሚሊዮን ዶላር እንደሰራላቸው ለወገኖቸ እንዲነግሯቸውምኞቴ ነው፡፡
ድምጼን ከፍ አድርጌ በመጮህ: አዲስ አበባ ያለውን የዓለም ባንክ ሰራተኞች ቀኑን ሙሉ ሲያዛጉ ነው የሚዉሉት?!

የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር በእስር ላይ ይገኛል

/ሳተናው/ የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው አቶ ፍቃዱ ማህተመወርቅ፤ የሃገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ‹‹ተገቢውን ግብር ለመንግሥት ገቢ አላደረክም›› በሚል ክስ ከጥር 13 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውል አድርጎታል።

inqu

አቶ ፈቃዱ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የቀድሞ ጉምሩክ መ/ቤት ወይም በአሁኑ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀጥታና የሕግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ቅጽር ግቢ በሚገኘው እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን ፖሊስ ሐሙስ ጥር 14 2007 ዓ.ም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ከሠላሳ አራዳ ጊዮርጊስ ፍ/ቤት ያቀረበው ቢሆንም የዋስትና መብቱ ሳይጠበቅ ለጥር 21 ቀን ከቀትር በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶት ወደ እስር ቤት ተመልሷል።

አቶ ፍቃዱን ያሳሰረው የሃገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰቢያ መ/ቤት ‹‹የዕንቁ መጽሔት እየታተመች በነበረችበት ጊዜ የመጽሔቷ አሳታሚና ባለቤት ለመንግሥት ገቢ ማድረግ የሚገባቸውን 600 ሺኅ ብር አስቀርተዋል›› የሚል ሲሆን ፍ/ቤት ቀርቦም ‹‹ግለሰቡን በሕግ የምጠይቅበትን ሠነድ አሰባስቤ ያልጨረስኩ በመሆኑ ለሰባት ቀናት በእስር ላይ ይቆዩልኝ…›› የሚል ጥያቄ አቅርቦ ለጊዜው በፍርድ ቤቱ በኩል ተቀባይነት አግኝቷል።

የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው አቶ ፈቃዱ ማህተመ ወርቅ ‹‹ፖሊስ የመሰረተብኝ ክስ እኔን የሚመለከት አይደለም ›› ያሉ ሲሆን፤ በሕግ የሚጠየቁበት ጉዳይ ካለም የዋስትና መብታቸውን ሊያስነፍግ እንደማይችል፣ ሕጉም በአግባቡ የሚተረጎም ከሆነ ከእስር ነጻ የመሆን ዕድል እንዳላቸው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4118#sthash.Ct50b6c7.dpuf

የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ዳግም የሰላማዊ ሰልፈኞችን ደም አፈሰሱ

 * ነብሰ ጡር ሳይቀር በቆመጥ ቀጠቀጡ (ፎቶዎች ይዘናል)

udj

udj 2

udj 3

udj 4

udj 5

udj 6

udj 7

udj 8

udj 9

udj 10

udj 11

udj1

/ዘ – uበሻ/ ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተነሳው ከ 150 በላይ የሚሆን ሰልፈኛ ከጽ/ቤቱ 100 ሜ/ር ርቀት ላይ ከሚጠብቁ ከ500 በላይ ሰልፈኞች ጋር ከመቀላቀላቀላቸው አስቀድሞ የህወሓት/ኢህአዴግ ፖሊሶች ቆርጠው በመግባት ከባድ ድብደባ አድርሰዋል፡፡ አራት ኪሎ፣ በፒያሳና የሰልፉ ማጠናቀቂያ በሆነው ኢቲዮ ኩባ አደባባይ ይጠባበቅ የነረው ሰልፈኛ ሊበተን ችሏል፡፡ ጉዳት የደረሰባችው 24 ሰልፈኞች ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ፖሊሶች ያደረሱትን ጉዳት በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የአንድነት አመራሮችን እና ጉዳት ደርሶባቸው በየሆስፒታሉ የሚገኙ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችን አነጋግረዋል፡፡ የፓርቲው አመራሮች ከአባላትና ከደጋፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን አንድነት በአዲስ አበባ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል፡፡ አንድነት ፓርቲ ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡

የፍትህና የነፃነት ጥያቄያችን ደም በማፍሰስ አይቀለበስም!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት ገዥው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድና የገዥው ፓርቲ ልሳን በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሚዲያዎች በመተባበር ከምርጫ ለማስወጣትና ተለጣፊ አንድነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፡፡
የተቃውሞ ሰልፉን ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ብናሳውቅም መስተዳድሩ በ12 ሰዓት ውስጥ በፅሁፍ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ሰልፉ እውቅና አለው፡፡ መስተዳድሩ ግን የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደ ጎን በመግፋት የተወሰኑና የማይታወቁ ግለሰቦች ፔቲሽን ተፈራርመው አምጥተዋል በማለት ብዥታ ለመፍጠር ሞክሯል፡፡ ፓርቲያችን ህጉን ጠብቆ ህጋዊ የሆነ ሰልፍ ለማካሄድ ቢሞክርም አሁንም ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ እንዳየነው ፖሊስ ደንብ ማስከበር ሲገባው አድሎ ለፈፀመው አካል በመወገን ድብደባ መፈፀሙ ከወገንተኝነት ያልፀዳ መሆኑን እንድናረጋግጥ አድርጎናል፡፡

ጥያቄያችን አሁንም የፍትህ፣ የእኩልነትና ህግ እንዲጠበቅ የማድረግ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ የመንግስትነት ስልጣኑን በመጠቀም የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም እየከወነ ያለውን ሴራ ማስቆም ነው፡፡ ጥያቄያችን የነፃነትና ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲ ይረጋገጥ የሚል ነው፡፡

ጥቄያችን ምርጫ ቦርድ የገዥው ፓርቲ አጋር መሆኑ ቀርቶ ገለልተኛ ሚናውን ይወጣ የሚል ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎቻችን ደግሞ ደም በማሰስ፤ በድብደባም ሆነ በእስር ፈፅሞ አይቆሙም፡፡ ትግላችን የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ እስከሚያበቃ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንትም በተለያዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሰላማዊ ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን እናሰማለን፡፡ ትግሉ ይቀጥላል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!

ETHIOPIA: MEDIA BEING DECIMATED

Legal, Policy Reforms Crucial Prior to May Elections

(Nairobi) – The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of the May 2015 general elections, Human Rights Watch said in a report released today. In the past year, six privately owned publications closed after government harassment; at least 22 journalists, bloggers, and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country in fear of being arrested under repressive laws.

The 76-page report, “‘Journalism is Not a Crime’: Violations of Media Freedom in Ethiopia,” details how the Ethiopian government has curtailed independent reporting since 2010. Human Rights Watch interviewed more than 70 current and exiled journalists between May 2013 and December 2014, and found patterns of government abuses against journalists that resulted in 19 being imprisoned for exercising their right to free expression, and that have forced at least 60 others into exile since 2010.

Ethiopia’s government has systematically assaulted the country’s independent voices, treating the media as a threat rather than a valued source of information and analysis,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Ethiopia’s media should be playing a crucial role in the May elections, but instead many journalists fear that their next article could get them thrown in jail.”

Most of Ethiopia’s print, television, and radio outlets are state-controlled, and the few private print media often self-censor their coverage of politically sensitive issues for fear of being shut down.

The six independent print publications that closed in 2014 did so after a lengthy campaign of intimidation that included documentaries on state-run television that alleged the publications were linked to terrorist groups. The intimidation also included harassment and threats against staff, pressure on printers and distributors, regulatory delays, and eventually criminal charges against the editors. Dozens of staff members went into exile. Three of the owners were convicted under the criminal code and sentenced in absentia to more than three years in prison. The evidence the prosecution presented against them consisted of articles that criticized government policies.

While the plight of a few high-profile Ethiopian journalists has become widely known, dozens more in Addis Ababa and in rural regions have suffered systematic abuses at the hands of security officials.

The threats against journalists often take a similar course. Journalists who publish a critical article might receive threatening telephone calls, text messages, and visits from security officials and ruling party cadres. Some said they received hundreds of these threats. If this does not silence them or intimidate them into self-censorship, then the threats intensify and arrests often follow. The courts have shown little or no independence in criminal cases against journalists who have been convicted after unfair trials and sentenced to lengthy prison terms, often on terrorism-related charges.

“Muzzling independent voices through trumped-up criminal charges and harassment is making Ethiopia one of the world’s biggest jailers of journalists,” Lefkow said. “The government should immediately release those wrongly imprisoned and reform laws to protect media freedom.”

Most radio and television stations in Ethiopia are government-affiliated, rarely stray from the government position, and tend to promote government policies and tout development successes. Control of radio is crucial politically given that more than 80 percent of Ethiopia’s population lives in rural areas, where the radio is still the main medium for news and information. The few private radio stations that cover political events are subjected to editing and approval requirements by local government officials. Broadcasters who deviate from approved content have been harassed, detained, and in many cases forced into exile.

The government has also frequently jammed broadcasts and blocked the websites of foreign and diaspora-based radio and television stations. Staff working for broadcasters face repeated threats and harassment, as well as intimidation of their sources or people interviewed on international media outlets. Even people watching or listening to these services have been arrested.

The government has also used a variety of more subtle but effective administrative and regulatory restrictions such as hampering efforts to form journalist associations, delaying permits and renewals of private publications, putting pressure on the few printing presses and distributors, and linking employment in state media to ruling party membership.

Social media are also heavily restricted, and many blog sites and websites run by Ethiopians in the diaspora are blocked inside Ethiopia. In April, the authorities arrested six people from Zone 9, a blogging collective that provides commentary on social, political, and other events of interest to young Ethiopians, and charged them under the country’s counterterrorism law and criminal code. Their trial, along with other media figures, has been fraught with various due process concerns. On January 14, 2015, it was adjourned for the 16th time and they have now been jailed for over 260 days. The arrest and prosecution of the Zone 9 bloggers has had a wider chilling effect on freedom of expression in Ethiopia, especially among critically minded bloggers and online activists.

The increased media repression will clearly affect the media landscape for the May elections,.

“The government still has time to make significant reforms that would improve media freedoms before the May elections,” Lefkow said. “Amending oppressive laws and freeing jailed journalists do not require significant time or resources, but only the political will for reform.”

Download (2)

http://www.hrw.org/news/2015/01/21/ethiopia-media-being-decimated

ያለነፃነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይኖርም!

(ኤድመን ተስፋዬ)የሰው ልጅ፣ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ከታደለው ፀጋ ውስጥ አንዱ ስልጣኔ ናፋቂ መሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዝግመተ-እድገት ታሪክ የሚነግረን፣ አለም አሁን ለደረሰችበት የሀያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ስልጣኔ፣ መንስኤው ስልጣኔ ናፋቂ የሆነው የሰው ልጅ በየዘመኑ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤት መሆኑን ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የማሰብ ፀጋ ስለቸረው ነው፡፡ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት” እንዲል ቃሉ፤ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ፤ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነ ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እነሆ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ መንስኤ የሆነው ከፈጣሪ የተቸረው የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በዚህ የውክልና አስተዳደር ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት አንዱ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ፣ ከሚከወኑ ክንውኖች ውስጥ በኢኮኖሚ የዕድገት መጠን ልክ የህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል ዋነኛው ነው፡፡ ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ትልቁ ጥያቄ እና ክርክር፤ በኢኮኖሚ እድገት ሂደት ውስጥ ነፃነት እና የኢኮኖሚ እድገቱ አብረው መጓዝ አለባቸው ወይስ አንዱ መቅደም አለበት? የሚለው ሆኗል፡፡

በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት እስከየትነት

የዲሞክራሲያዊ ስርአትን አይነት ወደ ጎን ትተን፣ በሁሉም ዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት መገለጫን ስናይ፣ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ዋነኛ ማእከል የብዙሀኑ ፍላጎት የሚገዛበት ሆኖ፣ በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ የግለሰቦች፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ በነጻነት የመደራጀት፤ ያለምንም ገደብ የመንቀሳቀስ፣ እንደ ግለሰብ የፈለገውን እምነት የማመን፤ በተመቸው ቋንቋ የመናገር ወዘተ ይጠቀሳሉ በአንድ ወቅት በብዙሀኑ ድምፅ ተበልጠው በቁጥር ስሌት የተሸነፈ አመለካከት የያዙ ሰዎች፤ እነኝህን መብቶች ተጠቅመው አመለካከታቸውን የብዙሀኑ ለማድረግ የመሞከርና በሕግ በተቀመጠው የምርጫ ስነ-ስርዓት ተጠቅመው የቀድሞውን የብዙሀን መንግስት ቀይረው እነሱ ብዙሀን የመሆን ሙከራ የማድረግ መብቶችም እንዲሁ የስርዓቱ አባባዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ በፈቃደኝነት የተመሰረቱ የወል ስብስቦች (የሀይማኖት፣ የብሄር፣ የባህል፣ የሞያ ስብስቦች ወዘተ)፣ ባጠቃላይ የማህበረሰቡን እና የሌሎች ዜጎችን መብቶች በማይነካ መልኩ እስከተደራጁ ድረስ የጋራ ጉዳያቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የማካሄድ መብታቸው የተከበረ ነው፡፡ .ባህላቸውንና እምነታቸውን፣ በፍቃደኝነት የሚቀበላቸው እስካገኙ ድረስ የማስፋፋት፣ የውስጥ ጉዳያቸውን የሚያካሂዱበትን የራሳቸውን ህግ እና መዋቅር የመዘርጋት፣ በሚመቻቸው መንገድ ተደራጅተው በጋራ በተቀመጠው ህግ መሰረት የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ የመንግስትን የጋራ ውሳኔ ለማግባባት መሞከርን፣ በተቀመጠው ህግ መሰረት አቤቱታ የማቅረብ፣ ባደባባይም ተቋውሞ የመግለፅ መብቶችን ያካትታል፡፡ በእኔ እምነት፣ ነፃነት ለኢኮኖሚ እድገት መንስኤ ነው ወይስ ነፃነት ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ የሚመጣ ነው የሚለውን ለመፈተሽ የዲሞክራሲ ስርአትን ማእከል በማድረግ ማየት እንደሚያስፈልግ አመላካች ይመስለኛል፡፡

ዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገት ምን እና ምን ናቸው?

በድህነት የሚኖሩ ህዝቦች፣ ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እስኪያሟሉ ድረስ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁለተኛ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ረሀብ፣ በሽታ እና ድንቁርና መገለጫቸው የሆኑ ደሀ ሀገራት፤ ከምንም በፊት ትኩረት ሊሰጡ የሚገባው የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን ላይ መሆኑን በመግለፅ ነፃነትእና የዲሞክራሲ የሚያስፈልገው የኢኮኖሚ እድገቱ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ነፃነትን ለማጣጣም የሚችል ማህበረሰብ ሲፈጥር ብቻ ስለ መሆኑ ይከራከራሉ፡፡ እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ሁሉ፤ ያለ ነፃነት የኢኮኖሚ እድገት የማይታሰብ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች የሚያቀርቡት ምክንያት የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው፣ ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ መንስኤነት መሆኑን በማንሣት ነው፡፡

ዓለም-አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት፣ እርዳታን እና ብድርን ተቀብለው የህዝባቸውን ኑሮ ባሻሻሉ እና ባላሻሻሉ የአፍሪካ ሀገራት መሀል ያለው ልዩነት መንስኤው በሀገራቱ መንግስታዊው ስርአት ውስጥ ያለው የተጠያቂነት እና የመልካም አስተዳደር ልዩነት ነው፡፡ በተጨማሪም ዲሞክራሲ ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ ነው የሚለው መከራከሪያ ዋጋ ቢስ ስለመሆኑ አመላካች ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የሚገነባው ጠንካራ እና ነፃ ፕሬስ፣ ውስን የሆነውን ሀገራዊ ሀብት ለኢኮኖሚ እድገት በሚል የዳቦ ስም ለግላቸው ጥቅም የሚያውሉ ባለስልጣናትን በማጋለጥ፣ መንግስታዊ ሌብነትን በመከላከል ረገድ ያለው ድርሻ ሌላኛው የዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገትን አይነጣጠሌነት የሚያሳይ ነው፡፡

ለኢኮኖሚ እድገት ዋናው መንስኤ ምርታማነት ሲሆን፣ ለምርታማነት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ደግሞ የሰው ሀይል ነው፡፡ የሰው ሀይልን በዋነኛነት ለምርታማነት መንስኤ እንዲሆን ያደረገው ጉልበቱ ሳይሆን የማሰብ ተሰጥኦው ነው፡፡ ለምርታማነት መንስኤ የሆነው የሰው ሀይል፣ የማሰብ ሀይሉን አበልፅጎ ለምርታማነት ምክንያት እንዲሆን ዋነኛው ግብአት ደግሞ ነፃነት ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ያለማንም ተፅእኖ የማሰብ ነፃነቱ ሲዳብር አዳዲስ ሀሳቦችን የማፍለቅ ችሎታው፣አዳዲስ አሰራር የመጠቀም ድፍረቱ ባጠቃላይ ለምርታማነት ያለው ተነሳሽነቱ ይዳብራል፡፡ ይህም ከምንም በላይ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በራሱ ዲሞክራሲን እና የኢኮኖሚ እድገትን አንድ ላይ ለማስኬድ እንጂ ኢኮኖሚ እድገትን በማስቀደም ዲሞክራሲን በኋላ ለሚል ንድፈ-ሀሳብ ምቹ አለመሆኑን ያሳያል፡፡

መጀመሪያ ድህነትን እንቅረፍ ዲሞክራሲ በሂደት ነው የሚለው ብሂል የአንባገነኖች መቆመሪያ እንደሆነ የሚያፀኽይ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ ብቻ መሆኑን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ (ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት)

ያለነፃነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይኖርም! (ኤድመን ተስፋዬ) http://www.goolgule.com/no-economic-growth-without-freedom/ የሰው ልጅ፣ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ከታደለው ፀጋ ውስጥ አንዱ ስልጣኔ ናፋቂ መሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዝግመተ-እድገት ታሪክ የሚነግረን፣ አለም አሁን ለደረሰችበት የሀያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ስልጣኔ፣ መንስኤው ስልጣኔ ናፋቂ የሆነው የሰው ልጅ በየዘመኑ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤት መሆኑን ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የማሰብ ፀጋ ስለቸረው ነው፡፡ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት” እንዲል ቃሉ፤ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ፤ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነ ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እነሆ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ መንስኤ የሆነው ከፈጣሪ የተቸረው የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በዚህ የውክልና አስተዳደር ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት አንዱ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ፣ ከሚከወኑ ክንውኖች ውስጥ በኢኮኖሚ የዕድገት መጠን ልክ የህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል ዋነኛው ነው፡፡ ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ትልቁ ጥያቄ እና ክርክር፤ በኢኮኖሚ እድገት ሂደት ውስጥ ነፃነት እና የኢኮኖሚ እድገቱ አብረው መጓዝ አለባቸው ወይስ አንዱ መቅደም አለበት? የሚለው ሆኗል፡፡ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት እስከየትነት የዲሞክራሲያዊ ስርአትን አይነት ወደ ጎን ትተን፣ በሁሉም ዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት መገለጫን ስናይ፣ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ዋነኛ ማእከል የብዙሀኑ ፍላጎት የሚገዛበት ሆኖ፣ በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ የግለሰቦች፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ በነጻነት የመደራጀት፤ ያለምንም ገደብ የመንቀሳቀስ፣ እንደ ግለሰብ የፈለገውን እምነት የማመን፤ በተመቸው ቋንቋ የመናገር ወዘተ ይጠቀሳሉ በአንድ ወቅት በብዙሀኑ ድምፅ ተበልጠው በቁጥር ስሌት የተሸነፈ አመለካከት የያዙ ሰዎች፤ እነኝህን መብቶች ተጠቅመው አመለካከታቸውን የብዙሀኑ ለማድረግ የመሞከርና በሕግ በተቀመጠው የምርጫ ስነ-ስርዓት ተጠቅመው የቀድሞውን የብዙሀን መንግስት ቀይረው እነሱ ብዙሀን የመሆን ሙከራ የማድረግ መብቶችም እንዲሁ የስርዓቱ አባባዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ በፈቃደኝነት የተመሰረቱ የወል ስብስቦች (የሀይማኖት፣ የብሄር፣ የባህል፣ የሞያ ስብስቦች ወዘተ)፣ ባጠቃላይ የማህበረሰቡን እና የሌሎች ዜጎችን መብቶች በማይነካ መልኩ እስከተደራጁ ድረስ የጋራ ጉዳያቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የማካሄድ መብታቸው የተከበረ ነው፡፡ .ባህላቸውንና እምነታቸውን፣ በፍቃደኝነት የሚቀበላቸው እስካገኙ ድረስ የማስፋፋት፣ የውስጥ ጉዳያቸውን የሚያካሂዱበትን የራሳቸውን ህግ እና መዋቅር የመዘርጋት፣ በሚመቻቸው መንገድ ተደራጅተው በጋራ በተቀመጠው ህግ መሰረት የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ የመንግስትን የጋራ ውሳኔ ለማግባባት መሞከርን፣ በተቀመጠው ህግ መሰረት አቤቱታ የማቅረብ፣ ባደባባይም ተቋውሞ የመግለፅ መብቶችን ያካትታል፡፡ በእኔ እምነት፣ ነፃነት ለኢኮኖሚ እድገት መንስኤ ነው ወይስ ነፃነት ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ የሚመጣ ነው የሚለውን ለመፈተሽ የዲሞክራሲ ስርአትን ማእከል በማድረግ ማየት እንደሚያስፈልግ አመላካች ይመስለኛል፡፡ ዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገት ምን እና ምን ናቸው? በድህነት የሚኖሩ ህዝቦች፣ ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እስኪያሟሉ ድረስ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁለተኛ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ረሀብ፣ በሽታ እና ድንቁርና መገለጫቸው የሆኑ ደሀ ሀገራት፤ ከምንም በፊት ትኩረት ሊሰጡ የሚገባው የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን ላይ መሆኑን በመግለፅ ነፃነትእና የዲሞክራሲ የሚያስፈልገው የኢኮኖሚ እድገቱ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ነፃነትን ለማጣጣም የሚችል ማህበረሰብ ሲፈጥር ብቻ ስለ መሆኑ ይከራከራሉ፡፡ እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ሁሉ፤ ያለ ነፃነት የኢኮኖሚ እድገት የማይታሰብ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች የሚያቀርቡት ምክንያት የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው፣ ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ መንስኤነት መሆኑን በማንሣት ነው፡፡ ዓለም-አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት፣ እርዳታን እና ብድርን ተቀብለው የህዝባቸውን ኑሮ ባሻሻሉ እና ባላሻሻሉ የአፍሪካ ሀገራት መሀል ያለው ልዩነት መንስኤው በሀገራቱ መንግስታዊው ስርአት ውስጥ ያለው የተጠያቂነት እና የመልካም አስተዳደር ልዩነት ነው፡፡ በተጨማሪም ዲሞክራሲ ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ ነው የሚለው መከራከሪያ ዋጋ ቢስ ስለመሆኑ አመላካች ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የሚገነባው ጠንካራ እና ነፃ ፕሬስ፣ ውስን የሆነውን ሀገራዊ ሀብት ለኢኮኖሚ እድገት በሚል የዳቦ ስም ለግላቸው ጥቅም የሚያውሉ ባለስልጣናትን በማጋለጥ፣ መንግስታዊ ሌብነትን በመከላከል ረገድ ያለው ድርሻ ሌላኛው የዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገትን አይነጣጠሌነት የሚያሳይ ነው፡፡ ለኢኮኖሚ እድገት ዋናው መንስኤ ምርታማነት ሲሆን፣ ለምርታማነት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ደግሞ የሰው ሀይል ነው፡፡ የሰው ሀይልን በዋነኛነት ለምርታማነት መንስኤ እንዲሆን ያደረገው ጉልበቱ ሳይሆን የማሰብ ተሰጥኦው ነው፡፡ ለምርታማነት መንስኤ የሆነው የሰው ሀይል፣ የማሰብ ሀይሉን አበልፅጎ ለምርታማነት ምክንያት እንዲሆን ዋነኛው ግብአት ደግሞ ነፃነት ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ያለማንም ተፅእኖ የማሰብ ነፃነቱ ሲዳብር አዳዲስ ሀሳቦችን የማፍለቅ ችሎታው፣አዳዲስ አሰራር የመጠቀም ድፍረቱ ባጠቃላይ ለምርታማነት ያለው ተነሳሽነቱ ይዳብራል፡፡ ይህም ከምንም በላይ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በራሱ ዲሞክራሲን እና የኢኮኖሚ እድገትን አንድ ላይ ለማስኬድ እንጂ ኢኮኖሚ እድገትን በማስቀደም ዲሞክራሲን በኋላ ለሚል ንድፈ-ሀሳብ ምቹ አለመሆኑን ያሳያል፡፡ መጀመሪያ ድህነትን እንቅረፍ ዲሞክራሲ በሂደት ነው የሚለው ብሂል የአንባገነኖች መቆመሪያ እንደሆነ የሚያፀኽይ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ ብቻ መሆኑን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ (ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት)

In Picture: Ethiopia Freedom Fighters to fight the current dictatorial government of Ethiopia

In Picture: ESAT Journalists with Freedom Fighters

The two top notch ESAT (Ethiopian Satellite Television) journalists Mesay Mekonnen and Fasil Yenealem are in Eritrea to gather news and reports about the Ethiopian patriots (freedom fighters), the following pictures are taken from Mesay Mekonnen’s Facebook page.

4

1

32

56

የህክምና ተለማማጅ ተማሪዎች የሚያደርሱት ጉዳት ትኩረት ይሻል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ

የህክምና ተለማማጅ ተማሪዎች የሚያደርሱት ጉዳት ትኩረት ይሻል

ተለማማጆቹ በህሙማን ላይ የማዘዝ ስልጣናቸው እስከ ምን ድረስ ነው?
ተማሪዎቹ በየሆስፒታሎቹ የሚስተናገዱበት ወጥነት ያለው ሥርዓት የለም
ተማሪዎቹ በሚፈጥሩት ስህተት በህሙማኑ ላይ እስከሞት የሚደርስ ጉዳት ይከሰታል

“በደረሰብኝ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሣቢያ በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ለወራት ተኝቼ ስታከም ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያትም በሆስፒታሉ ውስጥ ለተግባር ልምምድ ከግል የጤና ኮሌጆች በመጡ ተለማማጅ ተማሪዎች ተደጋጋሚ ችግሮች ሲከሰቱ አስተውያለሁ፡፡  በሆስፒታሉ ቆይታዬ እኔም በቀሪው የህይወት ዘመኔ አብሮኝ ለሚዘልቅ የጤና ችግር የዳረገኝ ግን የህመም ማስታገሻ መድሃኒት በመርፌ ለመስጠት ሙከራ ባደረገች አንዲት ተለማማጅ ተማሪ በእግር ነርቮቼ ላይ የደረሰው ጉዳት ነበር፡፡ በመኪናው አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው አንገቴና የራስ ቅሌ የሚደረግልኝ ህክምና ከፍተኛ ህመምና ስቃይ ስለነበረው የህመም ማስታገሻ መድሃኒት በየአራት ሰዓት ልዩነት እወስድ ነበር፡፡ በዚህም ሳቢያ መድሃኒቱ በመርፌ በሚሰጥበት ወቅት ከሚሰማው ስሜት ጋር ተለማምጄ ነበር፡፡ በተለማማጅ ተማሪዋ መርፌውን የተወጋሁ ቀን የተሰማኝ የህመም ስሜት ግን ፈጽሞ ልቋቋመው የምችለው አልነበረም፡፡ ጩኸቴ አስደንግጧት ከሥፍራው የደረሰች አንዲት መደበኛ ነርስ፤ ተማሪዋን መርፌውን በአግባቡ እንዳልወጋችኝና ይህም በነርቮቼ ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል በቁጣ ስትነግራት ሰምቼ ነበር፡፡ እንደተባለውም የሁለት ወራት ከአስራ ስምንት ቀን የሆስፒታል ቆይታዬን አጠናቅቄና በመኪናው አደጋ ሣቢያ ከደረሰብኝ ጉዳት አገግሜ ከሆስፒታሉ ስወጣ በእግሮቼ ነርቮች ላይ ዕድሜ ልኬን አብሮኝ ለሚዘልቅ የጤና ችግር መዳረጌን ተገንዝቤአለሁ፡፡ በግራው እግሬ ላይ በደረሰው ችግርም ያለ ድጋፍ መንቀሳቀስ ተስኖች ካለፉት ስድስት ዓመታት ለዚያች ተለማማጅ ተማሪ ያጋለጠኝን ዕድሌን እየረገምኩ እኖራለሁ፡፡ ይህ ጉዳይ ሃይ ባይ ማጣቱና ትኩረት መነፈጉ ሁልጊዜም የሚገርመኝ ጉዳይ ነው፡፡ ሃኪሞች ጉዳቱ ከመኪናው አደጋ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በመግለፅ ሊያሣምኑኝ ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ በሥፍራው በነበሩ የህክምና ባለሙያዎች መርፌውን ያለአግባብ በመወጋቴ ምክንያት በእግር ነርቮቼ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተነግሮኛል፡፡ በተለያዩ የግል ክሊኒኮችም ህክምና ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ ሆስፒታሉ የደረሰውን ችግር ለማድበስበስ ከመሞከር ይልቅ ችግሩ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ የሚችልበት መንገድ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት፡፡ የእኔ አንዴ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ግን በዚህ መልኩ ተማሪዎቹ በህሙማን ላይ የሚፈጥሩትን የጤና ጉዳት ለማስቀረት ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ኮሌጆቹና መንግስት የሚጠበቅባቸውን ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ችግሩ በሁሉም ሰው ላይ እስኪደርስ ድረስ መጠበቁ አግባብ አይመስለኝም፣ መሸፋፈኑም የትም አያደርስም፡፡ ችግሩን ገልጦ ማየትና መፍትሔ መፈለግ ነው የሚያዋጣው፡፡”
ይህንን ያለችኝ በደረሰባት ድንገተኛ የመኪና አደጋ ምክንያት በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ለወራት ተኝታ ህክምናዋን ስትከታተል የቆየችውና በአካል ድጋፍ (በክራንች) የምትንቀሳቀሰው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት የውጪ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ተማሪዋ ወ/ሪት ኤልሣቤጥ ታምራት ናት፡፡
ከአመት በፊት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተፈፀመ የተባለውና ከጉሉኮስ ጋር በተያያዘ የህክምና ስህተት ሣቢያ የተፈጠረውን ችግር በሆስፒታሉ ረዘም ላሉ አመታት በነርስነት ያገለገሉት (ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ) የጤና ባለሙያ ነግረውናል፡፡ “ለተግባር ልምምድ ወደ ሆስፒታል የማመጡት ተማሪዎች ችኩሎች በመሆናቸው አንድን ነገር አይተው ከመማር ይልቅ በተግባር አድርገው ማወቅን ይመርጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ ዋጋን ያስከፍላል፡፡ በሰው ህይወት ላይ ሙከራ እያደረጉ መማር ማለት እኮ ነው፡፡ ልጆቹን ተከታትሎ የሚመራና የሚያስተምራቸው፣ ማድረግ ያለባቸውንና የሌለባቸውን የሚነግራቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ራሱ ተማሪዎቹ የሚያደርጉትን ነገር በደንብ መከታተል፣ ችግር ያለ መስሎ ከተሰማው ለህክምና ባለሙያው መጠቆም ይገባል፡፡ ያለበለዚያ የሚፈጠረውን ችግር ማቆሙ ቀላል የሚሆን አይመስለኝም” ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በጋንዲ ሆስፒታል በኦፕሬሽን ለመውለድ ዝግጅት ታደርግ ለነበረች ነፍሰጡር ሴት ካቴተር (አርቲፊሻል የሽንት ማስወገጃ መሣሪያ) ለመግጠም ሙከራ ስታደርግ ስህተት በፈፀመች ተለማማጅ ተማሪ ምክንያት በነፍሰጡሯ ላይ የደረሰው ችግር፣ በራስ ደስታ ሆስፒታል ለላብራቶሪ ምርመራ ደም ለመቅዳት ሞክሮ ባልተሣካለት ተለማማጅ ተማሪ የተፈፀመው ችግር፣ በዘውዲቱ ሆስፒታል በዶክተሩ የታዘዘውን መድሃኒት ከታዘዘው መጠን በላይ እንዲወስዱ በማድረግ የተፈፀመ ስህተት፣ በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል በዋናው ሃኪም የታዘዘውን መድሃኒት በሌላ መድሃኒት ቀይሮ በመስጠት የተፈፀመው ስህተት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ለመሆኑ እነዚህና መሰል ችግሮችን እየፈፀሙ የሚገኙትን እነዚህን ተለማማጅ የህክምና ተማሪዎች እንቅስቃሴ የሚከታተል አካል ማነው? ተለማማጅ ተማሪዎቹስ በህሙማን ላይ ያላቸው ስልጣን እምን ድረስ ነው?
የአገሪቱን የህክምና ባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍና የህክምና ባለሙያዎችን ቁጥር ለማሳደግ በሚል ዓላማ በርካታ የግል የጤና ኮሌጆችና ዩንቨርሲቲዎች ተከፍተው ተማሪዎችን በህክምና ሙያ በማሰልጠን ላይ ይገኛሉ፡፡ ኮሌጆቹ የሚያስተምሯቸውን ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብና በተግባር በማሰልጠን ብቁ ባለሙያዎች ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ተማሪዎቹ በክፍል ውስጥ የተሰጣቸውን የንድፈ ሃሳብ ትምህርት በተግባር እንዲያዩና የሥራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉም ወደ ተለያዩ የጤና ተቋማት ይልካሉ፡፡ እነዚህ ተለማማጅ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተናግዱት የጤና ተቋማት፣ ተማሪዎቹ የሚመሩበትና የሚተዳደሩበት ወጥ የሆነ አሰራርና ደንብ ስለሌላቸው በርካታ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የጥቁር አንበሣ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ እንደነገሩን፤ በአገራችን እንደዚህ ባሉ ጉዳዮች ላይ ጥናት ማድረግ የተለመደ ባለመሆኑ በማስረጃ የተደገፈ አሃዝ ለማቅረብ ቢቸግርም በተለማማጅ የህክምና ተማሪዎች በሚፈፀሙ የህክምና ስህተቶች የደረሱ በርካታ አሳዛኝና አስደንጋጭ ጉዳቶች አሉ፡፡ “ተማሪዎቹ በንድፈ ሃሳብ ያገኙትን ትምህርት በተግባር ለማየትና ራሳቸውን ለመፈተን ከፍተኛ ጉጉት አላቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ችኩሎች ሲሆኑ ነገሮችን ተረጋግተው ለማጤን ዝግጁ አይደሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ተማሪዎቹ ለተግባር ትምህርቱ እንግዳ ስለሚሆኑ ድንጉጥና ፈሪ ይሆናሉ፡፡ ይሄ ደግሞ በህሙማን ላይ ችግር እንዲፈጥሩ ያደርጋቸዋል” ብለዋል፡፡
ተማሪዎቹ በህሙማን ላይ ለሚፈጥሯቸው ችግሮች በዋነኝነት የሚጠቀሱት የዕውቀትና ልምድ ማነስ፣ ሁሉንም ነገር የማወቅ ጉጉትና ችኩልነት እንዲሁም በስልጠና ወቅት ተማሪዎችን በመከታተል ችግር እንዳይፈጥሩ የሚቆጣጠር አካል አለመኖር እንደሆኑ የገለፁልን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ዳዊት አለባቸው ናቸው፡፡ ተለማማጅ ተማሪዎቹ በህሙማኑ ላይ ያላቸው የማዘዝ መብትና ስልጣን እስከ ምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ የሚታወቅ ባለመሆኑና ስህተት ከመፈፀሙ በፊት እነርሱን ተከታትሎ የሚመልስ ባለሙያ አብሮአቸው የሚመደብበት አሰራር ባለመኖሩ፣ ህሙማን ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ማየቱ የተለመደ ጉዳይ ነው” ብለዋል – ሃኪሙ፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ የሆኑና ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው፤ ችግሩ በስፋት የሚታይና የተለመደ ቢሆንም እርምት ለመውሰድ የሚችል አካል አለመኖሩ ሁልጊዜም የሚያሳስባቸው ጉዳይ እንደሆነ ገልፀውልናል፡፡ በእነዚህ ተለማማጅ ተማሪዎች ጉዳት ደረሰብን የሚሉ ህሙማንን በምን መልኩ መቀበልና ማስተናገድ እንደሚቻል ግራ እንደሚገባቸውም ነግረውናል፡፡ “እንኳንስ ተለማማጅ የጤና ባለሙያ ቀርቶ በህክምና ሙያ ረዘም ያሉ ጊዜያት የሰሩ የጤና ባለሙያዎች በህክምና ላይ በሚፈጥሯቸው ስህተቶች የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመፍታት የሚችልና በባለሙያዎቹ ላይ እርምጃ የሚወስድ አካል በሌለበት የጤና ስርዓት ውስጥ የተለማማጅ ተማሪዎቹ የሚፈጥሯቸውን ስህተቶችና ጉዳቶች እንዴት መፍታት እንደሚቻል ግራ ያጋባል” ብለዋል፡፡
ለዚህ መፍትሔ ይሆናል ብለው የሚያስቡት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ሆነ ከጤናው ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች የሚመለከታቸው አካላት በጤና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጠበቅ ያለ ደንብ ማውጣትና ተለማማጅ ተማሪዎች የሚመሩበት መመሪያ በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል  ይላሉ ባለሙያው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም “ተለማማጅ ተማሪዎቹ በታካሚው ላይ የሚኖራቸው የማዘዝ ስልጣን እስከ ምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ መታወቅ አለበት፡፡ ይህንንም ራሳቸው ተለማማጅ ተማሪዎቹ፣ የህክምና ተቋሙ፣ የጤና ባለሙያውና ህሙማኑ በአግባቡ እንዲያውቁት ሊደረግ ይገባል፡፡ ተማሪዎቹ ለሚፈፅሟቸው ስህተቶችና ለሚያደርሷቸው ጥፋቶችም ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል” ብለዋል፡፡ በየሆስፒታሉ በተለማማጅ የጤና ተማሪዎች የሚፈፀሙ የህክምና ስህተቶች በእርግጥም ትኩረት ሊሰጣቸውና ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ ችግሩ ህይወትን ያህል  ዋጋን የሚያስከፍል ነውና!

Breaking News- Ethiopia Sentences Three Britons to Jail on Terrorism Charges


british-flag
An Ethiopian court sentenced three British citizens to prison after finding them guilty of trying to establish Islamic rule in the country through acts of “terrorism,” according to a Justice Ministry official.

Ali Adorus was sentenced to 4 1/2 years in Ethiopian prison, while Somalia-born Mohammed Ahmed and Ahmed Elmi were each given jail terms of four years and eight months, Fekadu Tsega, coordinator of the federal center of prosecution, said by phone yesterday from the capital, Addis Ababa.

“They were accused of trying to unconstitutionally change the government and introduce Islamic government inEthiopia by terrorism,” he said.

Ethiopia, where Christianity dates to about the fourth century and is followed by about 60 percent of the country’s 94 million people, sent troops three years ago into Somalia to help African Union peacekeepers battle al-Qaeda-linked al-Shabaab. The group has since 2006 been trying to overthrow the government in Somalia and impose Shariah, or Islamic law, there.

The militants have threatened to attack Ethiopia in revenge for its military presence in Somalia, as they’ve done in other troop-contributing nations, including Kenya and Uganda. Al-Shabaab carried out twin bombings in the Ugandan capital, Kampala, in 2010 that left more than 70 people dead and raided a shopping mall in the Kenyan capital of Nairobi in 2013, killing at least 67 civilians and security personnel.

Terrorism Charges

The three British men were charged with contravening the country’s 2009 anti-terrorism law, Fekadu said. The prosecution and defense have the right to appeal against the sentences. Donors such as the U.S. and theUnited Nations have said that Ethiopia’s 2009 anti-terrorism law is used to silence legitimate dissent from journalists, opposition politicians and other critics of the state.

The men formed a militia in 2006 and first entered Ethiopia in 2011, Fekadu said. The court found they had links with a Yemen-based section of the Oromo Liberation Front, a group banned in Ethiopia that’s fighting for more autonomy for the Oromo, Ethiopia’s largest ethnic group.

Adorus, who was arrested in January 2013 in Ethiopia, signed a false confession under torture, according to Cage, a London-based justice group,

“Ali Adorus was brutally beaten, handcuffed behind his back for extended period of time, beaten on his hands with heavy wires, hooded, electrocuted and denied toilet access,” Cage said in a statement on its website, citing a UN petition. “Without legal assistance, the Londoner eventually signed a false confession in Amharic, a language he does not even speak.”

The U.K. Foreign and Commonwealth Office has provided consular assistance to Adorus, a spokeswoman, who declined to be identified in line with policy, said by phone from Londonyesterday, without providing further information.

The mobile phone of Communications Minister Redwan Hussien didn’t connect today whenBloomberg Newscalled him for comment, while Shimeles Kemal, state minister for communications, didn’t answer a call to his mobile phone.

To contact the reporter on this story: William Davison in Addis Ababa atwdavison3@bloomberg.net

To contact the editors responsible for this story: Nasreen Seria at nseria@bloomberg.net Sarah McGregor, John Viljoen, Paul Richardson

ጣይቱ ሆቴል ከምኒልክ እስክ . . . !

ጋሼ ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው “አጤ ምኒልክ” መፅሐፍ ገጽ 328-330 የሆቴሉ ታሪክ እንዲህ ይነበባል፡፡

በአዲስ አበባ የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ተሠርታ በምትመረቅበት ጊዜ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ መኳንንት ለምረቃው ተጠርtaytu 4ተው ነበር፡፡ ለተጠራው እንግዳ ማሳረፊያ እንጦጦ አይበቃ ስለነበር እቴጌ ጣይቱ ከእንጦጦ ተራራ ሥር ያለው ሕዝብ ሁሉ ለሚጠራው እንግዳ መጠለያ ቤት እንዲሰጥ ለመኑ፡፡ እንግዳ የሚያሳድር ሁሉ ሽሮ፣ በርበሬና ቅቤ፣ ዱቄትና ሥጋ ከቤተ መንግሥቱ እየወሰደ እንግዶቹን እንዲያስተናግድ አዘዙ፡፡ በዚህ ዓይነት የእንጦጦ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ ተፈጸመ፡፡ ከዚህም በኋላ ለሚመጣው እንግዳ ማረፊያና መመገቢያ ችግር እየሆነ መጣ፡፡

ምኒልክ “እህእ” እያሉ ወሬ ያጠያይቁ ጀመር፡፡ “በፈረንጅ አገር ሆቴል የሚባል ቤት ስላለ ማንኛውም እንግዳ ገንዘቡን እየከፈለ ያርፍበታል፤ ምግቡንም ይበላበታል” አሏቸው፡፡ በዚህ መሠረት ሥራው እንዲጀመርአዝዘው ሕንጻው ተሠርቶ ሆቴል ቤቱ በ1898 ዓም በነሐሴ ወር ሥራው ጀመረ፡፡ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ስለ ሆቴል ቤቱ ሲያብራሩ “ስሙም ሆቴል ተባለ” ይላሉ፡፡ ኃላፊነቱም፣ ሥራውንም እቴጌ ጣይቱ ተክበው ይመሩና ያስተዳድሩ ጀመር፡፡ በ1900 ዓም ጥቅምት 25 ቀን ምኒልክ በአዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶችንና የውጭ አገር ሰዎችን ጋብዘው ሆቴሉን አስመረቁ፡፡ የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅም ሙሴ ፍሬደሪክ ሐል ነበር:: በኋላ ግን አቶ ዘለቃ አጋርደው ተሾሙ፡፡

እንደ አገር አባባል ጣይቱ እጅ የሚያስቆረጥም ወጥ እያሠሩ ገበያ ቢጠብቁ ጠፋ:: እንኳን ምግብ መብላት ከግሪኮች ሻይ ቤት ገብቶ ሻይ መጠጣት ነውር ነበረና ጣይቱ ጠዋት የሚያሠሩት ወጥ ለሠራተኞቹ የማታ ራት ይሆን ጀመር፡፡ የሚስታቸው ገበያ ማጣት ያሳሰባቸው አጤ ምኒልክ አንድ ቀን ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በአካባቢያቸው ላሉ መኩዋንንቶች “ጣይቱ ምግብ የሚሸጥበት ቤት ከፍታለችና ኑ እንሂድና ልጋብዛችሁ” ብለው ወሰዱዋቸው፡፡ መኳንንት በላ ጠጣና ምኒልክ 30 ብር ከፈሉ፡፡

በማግሥቱ እንደተለመደው ገበያ ቢጠበቅ ጠፋ ቀጥሎም ጠፋ፤ ቀጥሎም ጠፋ፡፡ እንደገና ምኒልክ ሆቴል ገብቶ መብላት ነውር ያለ መሆኑን ለመኳንንቱ ገልፀው እንደገና ምሣ ጋበዙ፡፡ በሌላው ቀን አሁንም ገበያ አልተገኘም፡፡ ቢጠበቅ ቢጠበቅ ድርሽ የሚል ሰው ጠፋ፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ አጤ ምኒልክ ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በዙሪያቸው ላሉ መኳንንት “ሰማችሁ ወዳጆቼ” አሉ:: “በፈረንጅ አገር አንድ ቀን አንድ ሰው የጋበዘ እንደሆነ ያ የተጋበዘ ሰው በሌላ ቀን ደግሞ ብድሩን ይከፍላል ብድሩን ካልከፈለ ግን እንደ ነውር ይቆጠርበታል፡፡” ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ መኳንንቱ “እርስዎን ፈርተንና አፍረን ነው እንጂ የሚሆንልን ከሆነ የምኒልክን ብድር ለመመለስ እኔ አለሁ” እያለ ተራ በተራ ከሆቴል ቤት ምኒልክንና ጣይቱን ይጋብዝ ጀመረ፡፡ ገበያ እየደራ ሄደ፡፡ ምሳችንን እቴጌ ሆቴል ሄደን እንብላ የሚለው ስለበዛም ስሙ እቴጌ ሆቴል ተባለ፡፡

ዛሬ በታላላቅና በሌሎችም ሆቴል ቤቶች ጋሻና ጦር እየተሰቀለ እናያለን፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አደራረግ የተጀመረው በምኒልክ ነው፡፡

[እምዬ ምኒልክ መጋቢት 3፤ 1900ዓም ለደጃዝማች ሥዩም የላኩት መልዕክት እንዲህ ይነበባል]

ይድረስ ለደጃዝማች ሥዩም፤

“. . . የላክኸው የዝሆን ጥርስ አልጋና ተምቤን የተሠራ ጋሻ ደረሰልኝ፡፡ ጋሳ ግን ለግራኝ ተብሎ ተሠርቶ እንደሆነ ነው እንጂ ሌላ ሰው ይይዘዋል ተብሎ አልተሠራም፡፡ ነገር ግን ለሆቴል ቤት ለላንቲካ እንዲሆን አደረግሁት. . . ”

እጅጋ አሳዛኝ የታሪክ ውድመት

Zeki Kassu's photo.
Zeki Kassu's photo.
Zeki Kassu's photo.
Zeki Kassu's photo.

በተለያየ ዜና እንደሰማችሁት የመጀመሪያው የሀገራችን ሆቴል ጣይቱ ሆቴል ዛሬ ጠዋት በእሳት ተቃጥሏል፡፡ ጣይቱ ሆቴል ለኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ፈር ቀዳጅ የሆነው የጃዝ አምባ ላውንጅ መገኛ ነበር፡፡ ጃዝ አምባ ላውንጅ ደግሞ የ‹ከሰላምታ ጋር› ቲያትር ማረፊያ ነበር፡፡
ጣይቱ ሆቴል – የአርት ጋለሪው፣የመመገቢያው አዳራሹ፣እንግዳ መቀበያ ክፍሎቹ፣ እና በዛ ያሉ መኝታ ክፍሎቹ በእሳት አደጋው ጠፍተዋል፡፡ጣይቱ ሆቴል የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቅርስ እና ታሪክ ነው፡፡ አደጋው የፈጠረው ጉዳት የእያንዳንዳችን ቁጭት ነው፡፡ ታሪካችንን ፣ቅርሳችንን፣መሰብሰቢያ ምቾታችንን አጥተናል፡፡ መፅናናት የሚለው ቃል ከጉዳቱ ስነልቦናዊ ጥልቀት ጋር በምንም አይነፃፀርም፡፡
ህብረት ባንክ እና ከበላዩ ባለ ፎቅ ያሉ የተለያዩ የትንራንስፓርት እና የጉዞ ትኬት ቢሮዎች የእሳቱ ሰለባ ናቸው፡፡ በሆቴሉ ዙሪያ ያሉ ቢሮዎች እና ሠራተኞቻቸው ላጡት ሁሉ መፅናናት እና መካሻ እንመኛለን፡፡
በዚሁ ፎቅ ላይ የሚገኘው የአዲስ ተስፋ ኢንተርቴይመንት ቢሮ እና በውስጡ የነበሩ እየተሰሩ ያሉ አራት ያህል አዳዲስ ፊልሞች እና ሶርሳቸው፣ ከዚህ በፊት የተሰሩ ፊልሞች ክምችት ፣ማስታወቂያ እና ዘጋቢ ፊልም ፋይሎች፣ የ‹ከሰላምታ ጋር› ቲያትር የፎቶ እና የቪዲዮ ታሪኮች፣ ኪባ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ከዚህ በፊት የሰራው ‹ዝነኞቹ› ቲያትር የቪዲዮ ታሪክ ከእሳቱ አልተረፈም፡፡አዲስ ተስፋ ብርቱ እና ቅን ልጅ ነህ ለጠፋውን ንብረትህ መፅናኛ እና ምትክ እጥፍ ድርብ አድርጎ ፈጣሪ እንደሚተካልህ እናምናለን፡፡ እንፀልያለን፡፡
የኢትዮጵያን ጃዝ ሙዚቃ የፈለገ ኢትዮጵያዊ እና የውጪ ዜጋ የሚጎርፍበት ጃዝ አምባ ላውንጅ በእሳቱ ንብረቱ በሙሉ ወድሟል፡፡ በውስጡ የነበረው በገንዘብ ቢተምን እንኳን እጅግ ከፍ ያለ ሀብት የፈሰሰበት የሙዚቃ እና የድምፅ መሳሪያዎች፣ የሙዚቃ ባለሞያዎቻችን ታሪኮች፣ቅርሶች ፣እነዛ ለየት ያሉ ወንበሮች፣የግድግዳ ስዕሎች፣ፎቶዎች፣መብራቶች – – – የጃዝ አምባ ባለቤቶች እና ሠራተኞች መፅናናት እንመኛለን፡፡ ጃዝ አምባ ላውንጅ እሳት የማያጠፋው ታሪክ እና ፍቅር ባለቤት ነው፡፡ሳይዘገይ ወደነበረበት ይዞታው እና ምቹ ድባቡ እንደሚመለስ ሙሉ እምነታችን ነው፡፡
በዛሬው የእሳት አደጋ የ‹ከሰላምታ ጋር› ቲያትር ንብረቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ የቲያትሩ የመድረክ ቁሳቁሶች እና አልባሳትየእሳት ቀለብ ሆነዋል፡፡ የቲያትሩ ከፍ ያለው ኢንቨስትመንት በሰዎች አእምሮ እና ልብ ውስጥ የዋለ ነው፡፡ በእሳቱ የጠፉት ንብረቶቻችን ዲዛይን በእጃችን ይገኛል፡፡ በቅርቡ የጠፉትን ንብረቶቻችን ተክተን እንመለሳለን፡፡ ሀሳብ ፣ ታሪክ፣ፍቅር ከምንም ነገር በላይ ውድ ዋጋ እንዳለው ተምረናል፡፡
ኪባ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን

ከኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ እና የኢትዮጵያ ኣርበኞች ኣንድነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

2445893814

ETHIPIOPIAN  PATRIOTIC  UNITED MOVMENT

ከኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ እና የኢትዮጵያ ኣርበኞች ኣንድነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ  ከወራሪ ሃይሎች ጋር ተፋልሞ ድል ያስመዘገበው ለነጻነቱ በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ምክንያት ነው።  የዚህ ታላቅ ህዝብ ተጋድሎ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ኣፍሪካ ህዝብ የነጻነት ፋና ወጊ ሆኗል።

ይህ ለነጻነት የተከፈለ ትግልና ዉጤቱ እንዲሁ በቀላል ነገር የመጣ ኣልነበረም። ሁሉም የኢትዮጵያዊያን ልጆች ዘር ሃይማኖት ብሄር ቀለም ሳይለዩ ባንዲት ባንዲራና ባንዲት እናት ኣገር ኢትዮጵያ ስም ተሰባስበው ኣንድ ልብ ኣንድ ኣላማ ይዘው ስለታገሉ እንጅ። በዚህ ምክንያትም የኣገራችን መላው ህዝብ በየትኛዉም ቦታ እራሳቸዉን ቀና ኣድርገው የሚሄዱ ነበሩ። በኣሁኑ ወቅት ግን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቸዉም ጊዜ በከፋ ሁኔታ የነጻነት እጦት ዉስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። ያ ነጻነት የለመደ ህዝብ !ያ ተባብሮ በሰላም መኖር ልማዱና ባህሉ ያደረገ  ኩሩ ህዝብ! ዛሬ ግን በነጻነት እጦት ስር ወድቆ ከኣኩሪ ታሪኩ ጋር ወደታች እየሰጠመ ይገኛል። ወያኔ ኢህኣዴግ በዘራው መርዝ ምክንያት እርስ በርሱ ተለያይቶና ተፈራርቶ እንደጠላት እየተያየ ይገኛል።

ከሃያ ሶስት ኣመት በላይ  ሰላም  ኣጥቶ ነጻነት እንደተጠማ  ኑሮዉን እየገፋ ነው የሚታየው። በህወሃት ኣገዛዝ እየተንገፈገፈ ቢሆንም ተባብሮ ግን ከላዩ ላይ የተሸከመዉን የመከራ ሸክም ሊያራግፈው ያልቻለው በከፋፋይ ወያኔ መራሽ የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ገመድ ተጠፍሮ  ስለተያዘ እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል። ለዚህ መፍትሄዉ ደግሞ የተባበረ ትግል  እንደሆነ በጽእኑ እናምናለን።

የነጻነት እጦት የወለዳቸውና  የኢትዮጵያን ህዝብ ከጭቆና ቅንበር ለማላቀቅ የሚታገሉ በርካታ ድርጅቶች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የትግላቸው ዉጤት ግን ግቡን ኣልመታም። ሁላችንም ታጋይ  ድርጅቶች ለምን ስንል ራሳችንን የምንጠይቅበት ወቅት ላይ እንዳለን የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ ያምናል። የዚህ ጥያቄ መፍትሄ ኣቅጣጫ ደግሞ ወደ ኣንድነት የሚወስደን ይሆናል። ያለ ኣንድነት የቱንም ያህል ብንታገል የምንፈልገዉን ዉጤት ልናመጣ እንደማንችል ያሳለፍናቸው የትግል ጊዜያቶች ኣሳይተዉናል።

የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ /EPUM/ ጋር በጋራና በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሷል። ታህሳስ 20 \2014 በጀርመን ኑረንበርግ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ህዝብ  ኣርበኞች  ግንባር ዘብ ኣምስተኛ ኣመት የምስረታ በኣል ላይ የሁለቱ ድርጅቶች ባንድ ኣመራር ጥላ ስር መጠቃለላቸው ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ ሊቀ መንበር የሆኑት ኣቶ ልኡል ቀስቅስ የዉህደቱን ኣስፈላጊነት ኣስመልክተው የሚከተለዉን ብለዋል-

<<ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰላም ዴሞክራሲና ልማት ሰፍኖ ማየት የምንሻ ሁላችንም ኣገር ወዳድ የትግል ድርጅቶች እስካሁን ባካሄድናቸው የትግል እንቅስቃሴወች የምንፈልገዉን ዉጤት ማምጣት ኣልቻልንም። ለዚህም ዋናው ምክንያት ተባብረን ኣለመታገላችን ነው። ይህም ለወያኔ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮለታል። ካሁን በሁዋላ ግን ኣካሄዳችንን ቆም ብለን ኣይተን በመተባበር ኣምባ ገነኑ ስርኣት እንዲወገድ ማድረግ መቻል ኣለብን። ከዚያ በተረፈ ምርጫ በመጣ ቁጥር የምናደርገው እንቅስቃሴና የተናጠል ትግል የትም እንደማያደርሰን ልንገነዘብ ይገባል። የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብና የኢትዮጵያ ኣንድነት ንቅናቄ ያደርጉት ዉህደት ፈር ቀዳጅ ነው >> ብለዋል።

በዉህደቱ ላይ የተገኙት  የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ /EPUM/ ሊቀ መንበር የሆኑትአቶ ጥላሁን ገላው በበኩላቸው በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ እና የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን  ይፋ አድርገዋል። ስለዚህ በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ ጋራአብሮ የመስራት አላማ እንዳላቸው ያረጋገጡት የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ ሊቀ መንበር ሌሎች ድርጅቶች፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦችና በብሄር ደረጃ የተደራጁ ድርጅቶች በጋራ ለመስራት ወቅቱ ስለሚያስገድድ በጥምረት ለመስራት  ከተስማሙት ድርጅቶች  ጋር ለመስራት እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል::

በመላው ኣለም የምትገኙ የድርጅታችን ኣባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያን የሁለቱን ድርጅቶች ዉህደት ተገንዝባችሁ ከጎናችን እንድትቆሙና ኣስፈላጊዉን ትብብር እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ድል ለኢትዮጵያ ::

ሁለት የኢሳት ጋዜጠኞች በድንበር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ለመዘገብ ወደ ኤርትራ መሄዳቸው የበርካታ ኢትዮጵያንን እያነጋገረ ነው።

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በትናንት በዘገባው እንዳስታወቀው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ወደ ኤርትራ ያቀኑት በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የ ኢት ጰያ ተቃዋሚዎች እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ በዓይን
አይቶ ለመዘገብ፤እንዲሁም ከተሳካላቸው በወደፊቱ የኢትዮጰያና የኤርትራ ግንኙነት ዙሪያ የኤርትራ ባለስልጣናትን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ነው። ይህን ተከትሎ እጅግ በርካታ ኢትዮጰያውያን ለጋዜጠኞቹ ያላቸውን አክብሮትና አድንቆት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
እነኚህ ወገኖች ፤ጋዜጠኞቹ- እንደ ጋዜጠኛ በተግባር መሬት ላይ ያለውን ነገር አይተው ለህዝብ ለማሳወቅ ወደ ድንበር ማምራታቸው ፤ ለሙያቸው የተሰጡ መሆናቸውን የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር – ውሳኔያቸው በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል መልካም መቀራረብና ወንድማችነት እንዲኖር የሚያበረክተው አስተዋጻኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መንግስት ለኢህአዴግ ተላልፎ መሰጠቱ ያስቆጣቸው ኢትዮጰያውያን ደግሞ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ወደ ኢሳት ስልክ በመደወል በሰጡዋቸው አስተያየቶች ፤ጋዜጠኞቹ የወሰዱትን ድፍረት በማድነቅ በሰላም እንዲመለሱ ምኞታቸውን ገልጸዋል። እነኚህኞቹ ጋዜጠኞቹ በሰላም እንዲመለሱ ምኞታቸውን እየገለጹ ያሉት ፤ በሀገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞችን ለእስርና ስደት የዳረገውና በኢሳት ክፉኛ የሚበሳጨው የኢህአዴግ መንግስት እንደ አቶ አንዳርጋችው ጽጌ ጋዜጠኞቹን በመንገዳቸው ላይ በገንዘብ እንዳያስጠልፋቸው በመስጋት ነው።
በሌላ በኩል የገዥው ፓርቲ አባላት የሆኑ ካድሬዎች ደግሞ፤ የጋዜጠኞቹ ለዘገባ ወደ ኤርትራ ማቅናት ከተሰማ በሁዋላ ቁጣና ንዴታቸውን ያለመቋረጥ በመግለጽ ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔዓለም በሰላም ኤርትራ ከመግባታቸውም በላይ በነጻነት በመንቀሳቀስ የሄዱበትን ስራ እየከወኑ ይገኛሉ።
ጋዜጠኛ መሳይ በፌስ ቡክ ገጹ አስመራ ከተማን ከሁዋላው አድርጎ በተነሳው ፎቶ ስር ባሰፈረው ጽሁፍ፦<<አስመራ፡ ተራራ ላይ የከተመች፡ ጥንታዊ ገጽታዋን ያለቀቀች ውብ ከተማ። ኢሳት አስመራ ገብቷል፡፡ ሰላማዊውን ትግል በሰፊው እየዘገብን ነው። ዱር ቤታቸው አድርገው በሃይል ህወሀትን ለማስወገድ የተዘጋጁትን ሃይሎች ደግሞ በአካል ተገኝተን ልናያቸው ነው፡፡ባልደረባዬ ፋሲል የኔዓልምም ከአምስተርዳም አስመራ ከቷል። ታሪካዊ ጉዞ ነው፡፡>>ብሏል።
በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ፋሲልና መሳይ በኤርትራ ቆይታቸው ከስፍራው የሚያጠናቅሯቸውን ዘገባዎች በቀጥታ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

mesay

Court Adjourns Ethiopian Bloggers’ Trial for 15th Time

Marthe van der Wolf

ADDIS ABABA— The trial of Ethiopian bloggers known as Zone 9 was adjourned yet again Monday after prosecutors failed to amend terrorism charges as ordered by the court. The development raises the likelihood that some charges against the young bloggers and journalists may be dropped.
Zone9-Fractial-Element-Tadias-Cover-July-8th
The six members of the Zone 9 blogging collective and three affiliated journalists were imprisoned in April, accused of using social media to incite violence in Ethiopia. They were charged under Ethiopia’s anti-terrorism law in July. This was the 15th adjournment of their trial, now due to resume January 14.

Ameha Mekonnen, the attorney for eight of the nine defendants, said “this is the last chance” for the prosecution to amend charges. If that’s not done by the next hearing, he said, the judges will exclude them. One is related to digital training allegedly received by the journalists.

The court on Monday accepted other charges: that the defendants formed a clandestine organization, incited, attempted and organized damage to the community, and planned terrorist acts as outlined in Ethiopia’s anti-terrorism proclamation.

Ameha said it would be good for the Zone 9 bloggers and journalists if the prosecution fails to amend the remaining charges.

“It has got only six types of human behaviors that are regarded as terrorist acts,” he said. “… The law itself is not clear – simply, if someone plots to cause damage to the community, it amounts to terrorism.”

Criticized as vague

International human rights organizations have repeatedly criticized Ethiopia’s anti-terrorism proclamation for its vagueness and its use as a tool to silence dissident.

In a recent study, the Committee to Protect Journalists lists Ethiopia as one of the countries with the most imprisoned journalists.

Ethiopia’s government insists that those arrested are criminals and not journalists.

Source: VOA

አንድ ምሽት ከቴዲ አፍሮ ጋር በፍራንክፈርት

(በልጅግ ዓሊ) የቴዲ አፍሮ ዝግጅት በፋራንክፈርት ሲደረግ በቦታው ተገኝቼ ነበር ። ብዙ ጊዜ ዘፋኝ ሲመጣ አልገኝም ። ዘንድሮ ግን ወያኔ በእሱ ላይ ያደረገውን ተንኮል መቃወም የሚቻለው በዝግጅቱ በመገኘት በመሆኑ ሰብሰብ ብለን ተገኝተን ነበር። ሰልፉ ሳይጠነክር ቀደም ብለን ለመግባት በጊዜ ነበር የደረስነው። ሰዓቱን ጠብቀን ከፍለን ገባንና ጥግ ላይ ወንበር ፈልገን መጠበቅ ጀመርን ። እሱ ወደ መድረክ እስከሚወጣ በልዩ ልዩ ዘፈን እየተዝናናን ቆየን ። ወጣት ይጎርፋል፣ አለባበስ ይታያል፣ ዓመት በዓሉን ዓመት በዓል አስመስለውታል። የአዲስ ዓመት ዋዜማ . . . ለቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ዝግጅቱ ተጠናቋል። አዳራሹ እኩለ ሌሊት ላይ እየሞላ መጣ።

የሚጠበቀው ቴዲ አፍሮ ወደ መድረክ ሲወጣ ወጣቶች ያብዱ ጀመር። እሱ “ፍቅር ያሸንፋል“ ይላል። ወጣቶቹ ይጮኻሉ። “እወዳችኋለሁ“ ሌላ ጩኸት። አዳራሹ ድብልቅልቅ አለ ! ደስታና ጩኸት ይፈራረቁ ጀመር። ለአንድ ጊዜ እንኳን ቢሆን ይህንን ዓይነት አቀባበል የኢትዮጵያ ገዥዎች መቼ ይሆን የሚያገኙት ? ብዬ አሰብኩ። በ2015 ይኽንን ብመኝ የተጋነነ ይሆናል?

በተከታታይ አራት ዘፈን ተዘፈነ ። ልዩ ልዩ ዓይነት ጭፈራ ታየ ፣ ውስጥ ሙዚቃ ፣ ደጅ ርችት ፣ መድረኩ ላይ ጭፈራ ቀለጠ ። 2015 በደስታ ተጀመረ ። ለዛሬም ቢሆን ችግራችንን ሁሉ ልንረሳ የተስማማን ይመስላል። ተስፋችንን አንግበን ለፍቅር የተነሳን ሆንን። ፍቅር ያሸንፋል ቴዲ ፣ እኛም ያሸንፋል . . . ። አጠገቤ የነበረው ጓደኛዬ ግን ዘመን መቀየሩን ረስቶት ያሸንፋል እያለ ግራ እጁን ቡጢ ጨብጦ መፈክር ያሰማል። ሌላው አውርድ እጅህን እዚህ ቡጢ አያስፈልግም ይለዋል። የፍቅር ጠላቶችን አደቅበታለሁ ሲል ተሳሳቅን። ወጣቱ መድረኩ አካባቢ እኛ ጥግ ጥጉን ይዘን እስክስታውን ወረድነው።በቴዲ ዘፈን ምንጃርኛም ይሞከራል። ያልተሞከረ አልነበረም። ፍራንክፈርት ቀለጠች . . . ቤት የቀረም ሰው ያለ አይመስልም . . . አዳራሹ ምንም ትልቅ ቢሆን ተጨናንቋል። አዲስ ዘመን በአዲስ ተስፋ ተጀመረ።

እንደ ድንገት አንድ ወጣት ከጭፈራው ብዛት ደክሞት አጠገቤ ተቀመጠ።

ደከመህ ? ብዬ ጠየቅሁት ።

ጭንቅላቱን በማወዛወዝ አዎን አለኝ።

ትንሽ ትንፋሽ እሲከያገኝ ጠበቅሁና ቴዲን ትወደዋለህ ? መልሱን በአማርኛ ስጠብቅ በትግርኛ ቀጠለ። በንግግር ልንግባባ አልቻልንም። አማርኛ አይችልም። ቴዲ አዲስ ዘፈን ሲጀምር ወጣቱ አብሮት ይዘፍናል። ወጣቱ የቴዲን ዘፈን በቃሉ ያወርደዋል። ከቴዲ አፍሮ ጋር በዘፈን ይግባባሉ። ከእኔ ጋር ግን በቋንቋ ልንግባባ አልቻልንም። ለዘመናት የቆየው ጦርነት ምክንያት የወጣቱን ቋንቋ አለመናገራችን ይሆን?? ሃሳብ መጣ ። አሁን ስለ ወጣቱ የማወቅ ፍላጎቴ ጨመረ ።

ሁሉን ዘፈን ታውቀዋለህ ?

አሁን ገባው መሰለኝ አዎ ሁ.. ሉ ን አለኝ በአማርኛ በትግርኛ አነጋገር ። ገና ዘፈኑ ከማለቁ በፊት ልጁ እየሮጠ ወደ ዳንሱ ገባ ። እኔን ጥሎ ከቴዲ ጋር በሙዚቃ ሊግባባ ከነፈ . . . ።

ከጎኔ የነበረው ለጭፈራ የሄደው የጓደኛዬ ትርፍ ቦታ ለወጣቶች መተዋወቂያ ጠቀመኝ ። አንዲት በረጅም ጫማ ላይ የቆመች ወጣት መጣች ።

“መቀመጥ ይቻላል?“ እየተቅለሰለሰች ጠየቀችን ። ባለቤቱ እስከሚመጣ ፈቀድኩ ።

“ይህ ጫማ እግርሽን አያደክመውም?“ ወሬ መጀመሪያዬ ሆነ ።

“ትለምደዋለህ ፤ ከዚያ ብዙም አይሰማህም።“ ስለ ጫማው አስረዳችኝ።

“እዚህ ሃገር ቆይተሻል?“ የሚቀጥለው ጥያቄ ነበር ።

“ ገና አራት ወሬ ነው ?“

“ገና አዲስ ነሻ ? ”

” አዎ ነኝ።”

“የት ነው የተመደብሽ ? ” ከፍራንክፈርት ራቅ ያለ ቦታ ጠራችልኝ ።

“እና ለቴዲ አፍሮ ብለሽ ነው ከዛ ድረስ የመጣሽው ? ”

“ታዲያስ!” አለችኝ በመደነቅ ። አመላለስዋ ለቴዲ ያልተመጣ ለማን ይመጣል? የሚል ጥያቄ ያዘለ ይመስላል።

ቴዲ አዲስ ዘፈን ጀመረ ። ጥያቄዬን ሳልጨርስ ጥላኝ ነጎደች። ጫማዋን ግን እዛው ጥላው በረረች።

እኔም በተራዬ መድረኩ ጋር ብቃ አልኩ። ከዘፈኖቹ ማህል ቴዲ መፈክሩን ያሰማል። “ ፍቅር ያሰኝፋል“ ወጣቶቹ በሞላ በአንደነት እንደ መፈክር ይደግሙታል ። ሲዘፍን ይከተሉታል ፣ ቴዲ አውቆ ማሕል ላይ ሲያቆም እነርሱ ይሰማሉ ። በዚህ ምሽት ሁሉም ደናሽ ፣ ሁሉም ዘፋኝ ሆኗል ። ጩኸቱ ስለበዛ ለዕረፍት ወደ ውጭ ወጣ አልኩ ። አዳራሹ ውስጥ አንድ ሺህ የሚሆን ሰው አለ ። ደጅ ከ200 -300 የሚሆን ሰው ለመግባት ቆሟል። ይህ ሁሉ ሰው እንዴት ሊሆን ነው ራሴን ጠየቅሁ ። ሕዝብ እንደ ጉድ ይጎርፋል። ይዘፈናል ይጨፈራል፣ ይፈከራል ፣ ቴዲ እውዳቸኋለሁ ይላል፣ ወጣቶቹም በጩኸት ፍቅራቸውን ይገልጹለታል።

ተመልሼ ቦታዬ ተቀመጥኩ ። አሁን ከብዙ ወጣቶች ጋር ተዋወቅሁ። ቦርሳና ጫማ እኔጋ እያስቀመጡ መሄድ ተጀመረ ። ለዚህ የታማኝነት ሥራ በመብቃቴ አልከፋኝም። ወጣት ሲደሰት ከማየት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ ። ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ የሚለው ነገር ቦታ አልነበረውም ። ቴዲም ያውቅበታል፣ ፍቅር ያሸንፋል ! እያለ ፍቅርን ይዘራዋል። ወጣት በቡድን ሆኖ አብሮ ይጨፍራል። የመግባቢያ ቋንቋ የቴዲ ዘፈን ሆኗል። እኔም ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ የጫማና የቦርሳ ጥበቃዬን በሰፊው ይዠዋለሁ። ተስማምቶኛል። አይሆንም ብዬ በዘመኑ ቋንቋ አላካብድም ።

ሌላ መጣ ቦታ ጠየቀኝ ። የተለመደው መልስ ተሰጠው ። ኤርትራዊ እንደሆነ ገብቶኛል። ቀስ በቀስ ተግባባን። ለምንድነው ቴዲን የምትወዱት ?

“ቴዲ እንደ ሌሎቹ አያካብድማ ? ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ ገለመሌ ፣ ገለመሌ አይልም ። ይመቻል። ዛሬ እዛ ፍራንክፈርት ሌላም ዘፈን አለ ። “ማህበረኩም“ ያዘጋጀው ነው። ከአስመራ የመጡ ታዋቂ ዘፋኞች አሉ። እዛ ማንም አልሄደ ፣ እዚህ ነው የመጣነው።” ብዙ ነገር አስረዳኝ ። እኔም “ማህበረኩም“ ምን እነደሆነ ማጣራት ጀመርኩ። የሻብያ እጅ ያለበት ድርጅት እንደሆነ ሰማሁ። ገረመኝ ሻዕብያን በዘፈን ማሸነፍ ተቻለ ማለት ነው ? “ቦለኛ“ የሚተሰኘ የቀድሞ የኤርትራውያን የዘፈን ዝግጅት ታሰበኝ ። ያኔ ወርቅና ጌጥ ሳይቀር የሚሰጥበት ዘመን ነበር ። የዛን ጊዜ ማነው ከቦለኛ የሚቀር። አሁን ግን ቴዲ በዘፈን አሸነፈ ። የወጣቱን ፍላጎት የወያኔም፣ የሻዕብያም እንዳልሆነ ታዬ . . . የምን ጦርነት ፣ የምን የሕዝብ እልቂት ፍቅር ያሸንፋል ። ወጣት ተሰብስቦ አንድ ላይ ይጨፍራል ፣ ይፋቀራል፣ ይዝናናል . . . የጦርነት ጡሩምባ ለዛሬም ቢሆን ቆሟል . . . የክፍፍል አባዜ ቆሟል ቴዲ የፍቅር ጦሩን ይዞ ዘመቻውን ካለውጊያ ቀጥሏል።

በዚህ ምሽት አንድ ነገር ተመኘሁ በሚቀጥለው ዓመት እነዚህን ወጣቶች የሚያፋቅር ፣ የቴዲ አፍሮን ጥሪ ቀጣይነት ተመኘሁ። ፍቅር የሚያሸንፍበት ቢሆን ብዬ ተመኘሁ። እነዚህ ወጣቶች የሚያፍሩበትን ሳይሆን የሚኮሩበትን ሃገር ተመኘሁ። ቴዲ አፍሮን አሥመራ ንግስት ሳባ ስታዲዩም ውስጥ መድረክ ላይ ሆኖ ፍቅር ያሸንፋል ሲል መስማትን ተመኘሁ። ከሁሉ በላይ ግን ማካበድን የማያውቅ የወጣትነትን ዘመን ተመኘሁ። . . . በወያኔና በሻብዕያ ትምክህት ሊገዳደሉ የሚችሉ ወጣቶች በአንድነት ሲጨፍሩ ማየትን የመሰለ መልካም ስጦታ ከቴዲ አፍሮ 2015 ተሰጠን። እኛም በደስታ ተቀበልነው ።

ስለ ሕዝብ ፍቅር የሚዘፍኑ በሰላም ይክረሙ !

beljig.ali@gmail.com
ፍራንክፈርት

Teddy4