Archive | February 2015

የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አቶ ጸጋዬ አላምረው አገር ለቀው ተሰደዱ

(ሳተናው) የአንድነት ፓርቲ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑትና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀሉት አቶ ጸጋዬ አላምረው፣ ከወያኔ የፀረ-ሽብር ግብረ ኅይል እንዲታሰሩ የማዘዣ ወረቀት በመዉጣቱ፣ ለተወሰነ ቀናት አገር ቤት ራሳቸውን ሰዉረውከቆዩ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

20526_774706749280928_86029102619422382_nአቶ ጸጋዬ የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው ከታሰሩ በኋላ የመኢአድ አመቻች ኮሚቴ ዋሃ ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል።፣ ሕወሃቶች መሰናክል ፈጠርበት እንጂ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ዉህደቱ ጫፍፍ እንዲደርስ፣ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱ የአመራር አባላት መካከል አንዱ ነበሩ። የአንድነት ፓርቲ ያደርግ በነበረው የምርጫ ዘመቻም፣ የምርጫ ኮሚቴ አባል በመሆን ትልቅድርጅታዊ ሥራ ይሰሩም ነበር።

የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ፣ የሕወሃት ታጥቂዎች በሰላማዊ ዜጎችን ላይ ኢሰባአዊ የሆነ ከፍተኛ ድብደባ በፈጸሙበት ወቅት፣ በአካል ከተጎዱት ወገኖች መካከል አንዱ አቶ ጸጋዬ ነበሩ። ከስድስት ወራት በፊትም በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም፣ አንድነት እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ በፈረሙበት ጊዜም፣ የአገዛዙ ካድሬዎች ስብሰባዉ ለመረበሽ በሞከሩበት ወቅት ተፈንክተው ትልቅ ጉዳት ደሮባቸውም ነበር።

ሕወሃቶች በአቶ ጸጋዬ ላይ ያነጣጠሩት፣ በርካታ የአንድነት አባላትን ይዘው አቶ ፀጋዬ ሰማያዊን ከተቀላቀሉ በኋላ ሲሆን፣ ዋና ክስ አድርገው የወሰዱትም “አንድነት ፓርቲ የገንዘብ እርዳታ ከሽብርተኞች ይቀበላል፣ የሚቀበለዉም በአቶ ጸጋዬ አላምረው በኩል ነበር” የሚል እንደሆነ ታውቋል። ሕወሃቶች በሚቆጣጠሩት ኢቲቪና ራዲዮ ፋና ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአንድነት ላአይ የጅመሩ ሲሆን፣ እነ ትግስቱ አወሉንም በሜዲያ፣ የአቶ ጸጋዬ አላምረዉን ስም እየጠሩ “ገንዘብ ተቀባይ እርሱ ነበር” እያሉም እንዲናገሩ እያደረጓቸው ነው።

የአንድነት ፓርቲ በዉጭ አገር ካሉ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያገኝ እንደነበረ ይታወቃል። በዉጭ ያሉ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶችም፣ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በሰማዊ ትግል የሚያምኑ እንደመሆናቸው፣ በነርሱ በኩል ተሰብስቦ የሚላክን ገንዘብ ከሽብርተኞች እንደመጣ አድርጎ መቁጠር በሕግ፣ በሞራልም በአሰራር ተቀበያነት እንደሌላው የድጋፍ ድርጅቱ አባላት ይናገራሉ።

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4572#sthash.NPGz1MYr.dpuf

ህዝብን በጅምላ እየፈረጁ መሰዳደብን ትግል አድርገው ለሚያስቡ ሁሉ ቦታ ልንሰጣቸው አይገባም።

(አበበ ገላው)አልፎ አልፎ በፌስቡክና በተለያዩ ድረገጾች ላይ የሚታዩት በጣም አሳፋሪ የዘረኝነት ስድድቦች ለመጪው ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል መርዝ መርጨት መሆኑን ህሊና ያለው ሁሉ የሚገነዘበው ሃቅ ነው። ህዝብን በጅምላ እየፈረጁ መሰዳደብን ትግል አድርገው ለሚያስቡ ሁሉ ቦታ ልንሰጣቸው አይገባም። በታሪካችን በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ስርአቶች እንጂ የትኛው ህዝብ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ስልጣን ላይ ያሉት ጨቋኞች በህዝብ ስም የሚነግዱ ወንጀለኛ ግለሰቦች እንጂ ህዝብ አለመሆኑን እንገነዘባለን። በጨቋኙ ህወሃትና በጭቁኑ የትግራይ ህዝብም መካከል ያለው ልዩነትም ለማንም ግልጽ ነው። ጭቁኑ የትግራይ ህዝብ ብዙ መከራና ችግርን የተጋፈጠ የጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ አካል ነው። ይህ እውነታ ደግሞ እንደ ጨቋኝ ስርአቶች በየግዜው የሚወድቅና የሚከስም ጉዳይ አይደለም። የዘመኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ህወሃትና ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጡ ሎሌዎቹ እንጂ የትኛውም ህዝብ አለመሆኑ ግልጽ ስለሆነ በህወሃቶች ጅረት ገብተን አብረን እንዳንፈስ መጠንቀቅ አለብን።

Abebe Gellaw

አልፎ አልፎ በፌስቡክና በተለያዩ ድረገጾች ላይ የሚታዩት በጣም አሳፋሪ የዘረኝነት ስድድቦች ለመጪው ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል መርዝ መርጨት መሆኑን ህሊና ያለው ሁሉ የሚገነዘበው ሃቅ ነው። ህዝብን በጅምላ እየፈረጁ መሰዳደብን ትግል አድርገው ለሚያስቡ ሁሉ ቦታ ልንሰጣቸው አይገባም። በታሪካችን በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ስርአቶች እንጂ የትኛው ህዝብ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ስልጣን ላይ ያሉት ጨቋኞች በህዝብ ስም የሚነግዱ ወንጀለኛ ግለሰቦች እንጂ ህዝብ አለመሆኑን እንገነዘባለን። በጨቋኙ ህወሃትና በጭቁኑ የትግራይ ህዝብም መካከል ያለው ልዩነትም ለማንም ግልጽ ነው። ጭቁኑ የትግራይ ህዝብ ብዙ መከራና ችግርን የተጋፈጠ የጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ አካል ነው። ይህ እውነታ ደግሞ እንደ ጨቋኝ ስርአቶች በየግዜው የሚወድቅና የሚከስም ጉዳይ አይደለም። የዘመኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ህወሃትና ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጡ ሎሌዎቹ እንጂ የትኛውም ህዝብ አለመሆኑ ግልጽ ስለሆነ በህወሃቶች ጅረት ገብተን አብረን እንዳንፈስ መጠንቀቅ አለብን።

ሰማያዊ ፓርቲ ጸ/ቤቱን እንዲለቅ ክስ ቀረበበት

• በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል

1186718_600650739977528_2059123344_n

ሰማያዊ ፓርቲ የካ ክ/ከተማ በቀድሞው መጠሪያው ቀበሌ 15 እንዲሁም በአዲሱ መጠሪያው ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 460 የሆነውን ጽ/ቤቱን 25000 ሺህ ብር ቅጣት ከፍሎ እንዲለቅ በአከራዮቹ በኩል ክስ ቀረበበት፡፡ በከሳሽ እነ አቶ ሚስጥረ ሽበሽ የተመሰረተው ክስ ‹‹ቤቱን ለቀው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው …በወር ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ሒሳብ ከጥር 16 ቀን 2007 ጀምሮ ቤቱን ለቀው እስከሚያስረክቡ ድረስ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ከሳሽ ቤቱን ለማደስ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በገባነው ውል መሰረት የደረሰብንን 250 ሺህ ብር ኪሳራ እንዲተኩልን›› ሲሉ ከሰዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚፈልግባቸው ጊዜያት የቀበሌ ካድሬዎች አከራዮቹና ደላሎቹ ለፓርቲው እንዳያከራዩ ሲያስጠነቅቁ የቆዩ ሲሆን በተለይ በጥር ወር 2007 ዓ.ም ይህ ጽ/ቤት እንዳይከራይ ግፊት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ደብዳቤ

የማለዳ ወግ ...የተገፊዋ እናት ደብዳቤ ...!
* ያልተመቻቸው የእኛ እናቶችን እንባ ..

  ታሪካችን በጦርነት ተከቦ ዘመን በዘመን ሲተካ ፣ የቀደመው ይሁን ቢባል እንኳ በዘመነችው አለም መካከል ያለች ቀሪ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የሃገሬ እናቶች እንባ የሚጠርገው አጥቷል። ከዘመነ ጃንሆይ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እስከ ደርግ ፣ ከዚያም አሁን እስካለንበት የኢህአዴግ አገዛዝ ለሀገር ሰላም ፣ ለዲሞክራሲና ፍትህ የዜግነት ድርሻቸውን የሚወጡ ፣ የተጉና " ስለ ሃገሬና ህዝቤ ያገባኛል " ያሉ ልጆችን በአብራካቸው ያፈሩ እናቶች መከረኛ እናቶች ናቸው። ልጆቻቸው ፍትህን ናፋቂ ፣ መብታቸውን ጠይቂ ናቸውና " እንደ ጋሪ ፈረስ ጋሪ አንነዳም " ያሉ ኩሩ ዜጎችን አፍርተዋልና ህግና መመሪያ እየወጣ ፣ የወጣው ህግና መመሪያ እየተጣሰ ቤታውን አጨልሞታል ። ትናንት የነበረው ዛሬም የቀጠለው ደረቅ አሳዛኝ እውነት ይህ ነው ! 

   አዎ የእናት አብራክ ጀግና ማፍራቱ አላቆመምና የጀግና አርበኛ እናቶች እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም የእኛ እንደ ከፋቸው ፣ ሰርክ እንደተሸበሩና ሰላማቸውን አጥተው ኑሮን ለመግፋት ተገደዋል። የእሳተ ነበልባል ለወጥ አራጅ እናቶች ናቸውና ይገፋሉ ፣ በገዛ ሃገራቸውና በቀያቸው ፣ በስጋትና በሽብር ተከበው ኑሮን በመከራ ፣ በደል እየተፈጸመባቸው ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ከቀደመው እስከ ቀረበው ፣ ከቀረበው እስከምንገፋው የለው የእኛ ሀገር የፖለቲካ ምህዳር የፈጠረው አሳዛኝ የተገፊ እናቶች ታሪክ ዋቢ ነው ... ! 

ትንታጉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ...

  ተመስገን ደሳለኝ ደርግ በወደቀ ማግስት "ክፉው ዘመን አለፈ ፣ መጨራረስ መገዳደል እልባት አገኘ " ተብሎ ተስፋ በተጣለበት ፣ "ዲሞክራሲ ሰፈነ !" ተብሎ አዋጅ ነጋሪት በተጎሰመ ፣ በተነገረበት " የዲሞክታሲያዊ እኩልነት ህገ መንግስት " የጸደቀ ሰሞን የአንደኛ ደረጃ አስኳላ ትምህርቱን ያላጠናቀቀ ገና በአስራዎቹ የእድሜ ክልል የነበረ ወጣት ነው ። ባለፉት 23 አመታት ግን ተግቶ ትምህርቱ የተከታተለው ብትቱ ታዳጊ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ዘልቆ እውቀትን በመገብየት በተገቢ መንገድ አጠናቀቀ ። 

  ጎልማሳው ተሜ ....የሃገር ፍቅሩን ከቀሰመበት የትምህት ረድፍ አልፎ ተርፎ ፣ ከጎረቤት ፣ ከከባቢው ወርሷም አደገ ... እናም ከጥቂት አመታት በፊት ነፍሱ ሲፈቅድ በተሰጠው የመጻፍና ማንበብ መብት ማዕቀፍ ብዕር ጨበጠ .. ተመስገን አውነትን ይዞ ፣ ዲሞክራሲን መከታ አድርጎ ያልተመቸውን የፖለቲካ አካሔድ ተቃዋሚ ፣ ገዠ ፖርቲ ሳያይና ግራ ቀኝ ሳይለይ ይሞግት ገባ ። የተዋጣለት ጋዜጠኛና የፖለቲካ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትንታኝ ጸሃፊ ለመሆን ከበቁት የዘመናችን ትንታግ ሰላማዊ ትግል አርበኞች መካከል አንዱ ለመሆን ለተመስገን ጊዜ አልፈጀበትም ! እናም ስራውን ተግቶ ቀጠለ ...

 ጋዜጠኛ ተመስገን የመጻፍ የመናገር መብቱን ተጠቅሞ ፣ በሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሃገሩ ይሆናል ያለውን ሰላማዊ የትግል ስልት በማመላከት ፣ ወጣቱ ፍርሃትን አስወግዶ ለሰላማዊ ትግል እንዲተካ መስበክ ያዘ ፣ መሰናክል ጋሬጣው ከማንሳት ይልቅ ... ጋዜጠኛ ተመስገን ብዙ ታገለ ፣ አታገለ ... ማለቱ ብቻ ይቀላል ! 

    የቆየው ውርስ ተከትሎናልና ፣ ጥላቻውን አድገንበታልና የዚያ ወጣት ትንታግ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንገድ በዘባተሎው ፖለቲካ ተሰናከለ ! ... ባለ ራዕዩን ብዕረኛ ፓለቲካው ጠልፎ ጣለው ! ተሜ ግን የዋዛ አይደለም "  ... ለእኔ ሳይሆን ለታገልኩለት አላማ ጸንታችሁ ታገሉ ! " እያለ የወህኒውን ህይዎት በጸጋ ተቀብሎት ኑሮን መግፋት ይዟል ! ... 

ተገፊዋ የተመስገን እናት ...

   ... የተሜ እናት ግን እያነቡ ነው  ... ብዙ ማለት አልችልም ፣ የተገፊዋን እናት ደብዳቤ ደርሷል ፣ አዝኛለሁ ! የምንሰማቸው ከሆነ ...ተገፊዋ እናት በአብራካቸው ክፋይ በልጃቸው በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ወህኒ ቤት ውስጥ ህግ እየተጣሰ የሚፈጸምበት መበት ገፈፋ ሰላም ነስቷቸው " የሰው ያለህ ፣ የህግ ያለህ! " ብለውናል ። የእኒህ እናት ጩኽትና ሮሮ የሀገሬ ለውጥ አራማጅ ጀግና ልጆችን የወለዱ እናቶች ሁሉ ጥሪ ለመሆኑ ላፍታ አልጠራጠርም ። ምንም እንኳን ይህ አሁን ድረስ የቆየና የቀጠለው የሀገሬ እናቶች መከራ አንዱ ክፍል ቢሆንም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት 30 ቀናት ከማንም ጋር እንዳይገናኝ መደረጉና የእናቱ አቤቲታ ጉዳዩን ጀሮ ገብ መልስ የሚያሻው ቀዳሚ ጉዳይ አድርጎታል ። 

 ዛሬ ጋዜጠኛ ተመስገን ጥፋት ምንድን ነው? ፍርዱስ ፍትሃዊና ተመጣጣኝ ነውን ብለን አንጠይቅም ፣ አንሞግትም ! ዛሬ የምንሞግት የምንጠይቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር መብቱ አይጣስ ፣ ህገ መንግስቱ ይከበር እያልን ነው ። ተመስገን ከሚወዱ ከሚናፍቁት አቅመ ደካማ እናቱ ፣ ከቤተሰብ ከቅርብ ዘመዶቹ ፣ ከሐይማኖት ፣ ከሐኪምና ከህግ አማካሪ ጋር የመገናኘት ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲያከብርለት እንደ ዜጋ ድምጻችን የማሰማት ቢያንስ የሞራል ግዴታ አለብን ! ግፍ ሲበዛ ጥሩ አይሆንም ፣ ጆሮ ያለው ይስማ ! 

ፍትህ እንሻለን !

ነቢዩ ሲራክ 
የካቲት 3 ቀን 2007 ዓም 

===================================

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ደብዳቤ
===========================
                         ቀን 02/06/2007 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉብኝት ይመለከታል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአብራኬ የወጣ ሁለተኛ ልጄ ነው፡፡ ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለሰው አሣቢ፣ ሀገር ወዳድና ታታሪ ስለመሆኑ ከእኔ በላይ የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡ ልጄ ተመስገን ለወገኔ አሰብኩ ባለ በእስር ቤት ያለጎብኚ እየተሰቃየብኝ ይገኛል፡፡ መቼም፣ የእናት ሆድ አያስችልምና እባካችሁ ልጄን ታደጉት፡፡ እባካችሁ ቢያንስ ካለበት እየሄድኩ የልጄን አይን እንዳይ እንዲፈቀድልኝ ተባበሩኝ፡፡ 

  የልጄን ድምጽ ከሠማሁ ይኸዉ አንድ ወር ሞላኝ፡፡ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለወንድሙ ብሎ የቋጠረዉን ምሣ ይዞ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢሄድም በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ተደብድቦ የያዘውን ምግብ እንኳ ሣያደርስ ሜዳ ላይ ተደፍቶ ተመልሷል፡፡ መቼም እናንተም ልጆች ይኖራችኋል፤ ደግሞም የልጅን ነገር ታውቁታላችሁ፡፡ እኔ አሁን በእርጅና ዕድሜዬ ላይ እገኛለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ብቆይም ለትንሽ ጊዜያት ነው፡፡ በዚህች ጊዜ ውስጥ ልጄን እየተመላለስኩ እየጠየኩ፣ ድምፁን እያሰማሁ፣ አይዞህ እያልኩ ብኖር ለእኔ መታደል ነበር፡፡ እባካችሁ እርዱኝ የልጄ ድምጽ ናፈቀኝ፡፡ እሱን መጎብኘት የተከለከለበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንኳን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ ከወንድሙ ድብደባ በኋላም ጥር 10 ወደ ጠዋት አካባቢ የሄዱት ጓደኞቹ እና ወንድሞቹ ሳያዩት ተመልሰዋል፡፡

ተምዬ ስታመም የሚያስታምመኝ፣ “አይዞሽ እማዬ” የሚለኝ ረዳቴ ነው፡፡ ሌላ ዘመድ የለኝም፡፡ የምተዳደረውም ልጆቼ ለፍተውና ደክመው በሚያመጧት ትንሽ ብር ነው፡፡ ዛሬ ግን ይኸዉ ልጆቼም ወንድማቸውን ለማየት እየተንከራተቱ ነው፡፡
በእናታችሁ ይዣችኋለሁ፤ ከቻላችሁ ልጄ እንዲፈታልኝ እና እኔም ያለችኝን ቀሪ የእድሜ ዘመን አይን አይኑን እያየሁ እንድኖር እንድታደርጉልኝ፤ ይህን ማድረግ ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ካለበት ድረስ እየተመላለስኩ እኔና ሌሎች ልጆቼ እንዲሁም ወገኖቹ እንዲጠይቁት ቢደረግልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ፡፡ ልጄን አውቀዋለሁ፡፡ አንድ ነገር ሲገጥመዉ ሆድ ይብሰዋል፡፡ ቢያንስ እንኳን ቤተሰቦቹን ሲያይ ስለሚፅናና ይኸዉ እንዲፈቀድልኝ እማፀናለሁ፡፡ እኔ ምንም አቅም የሌለኝ አሮጊት ነኝ፡፡ ሁሉንም ለናንተ ሠጥቻችኋለሁ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር እንደምታስተካክሉልኝ እና እንደገና የልጄን ፊት እንዳይ እንደምታደርጉኝ ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡

እንግዲህ የየካዉ ቅዱስ ሚካኤል ይከተላችሁ፡፡ መቼም የእናትን ሆድ ታውቁታላችሁ፤ የልጅ ነገር አያስችልም፡፡ ሆድም ቶሎ ይሸበራል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ እኔንም ልጆቼንም እርዱን እንላለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ወ/ሮ ፋናዬ እርዳቸው

ግልባጭ

- ለጠ/ሚኒስተር ፅ/ቤት  
- የህግና፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ             - ለአፈ-ጉባኤ ፅ/ቤት  - የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)  - ለእምባ ጠባቂ      - ለአሜሪካ ኢምባሲ             - ለእንግሊዝ ኢምባሲ
===================================
#Ethiopia_allow_to_visit_and_Medical_Care_for_Temesgen_Desalegn

Updated
የማለዳ ወግ …የተገፊዋ እናት ደብዳቤ …!

* ያልተመቻቸው የእኛ እናቶችን እንባ ..

ታሪካችን በጦርነት ተከቦ ዘመን በዘመን ሲተካ ፣ የቀደመው ይሁን ቢባል እንኳ በዘመነችው አለም መካከል ያለች ቀሪ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የሃገሬ እናቶች እንባ የሚጠርገው አጥቷል። ከዘመነ ጃንሆይ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እስከ ደርግ ፣ ከዚያም አሁን እስካለንበት የኢህአዴግ አገዛዝ ለሀገር ሰላም ፣ ለዲሞክራሲና ፍትህ የዜግነት ድርሻቸውን የሚወጡ ፣ የተጉና ” ስለ ሃገሬና ህዝቤ ያገባኛል ” ያሉ ልጆችን በአብራካቸው ያፈሩ እናቶች መከረኛ እናቶች ናቸው። ልጆቻቸው ፍትህን ናፋቂ ፣ መብታቸውን ጠይቂ ናቸውና ” እንደ ጋሪ ፈረስ ጋሪ አንነዳም ” ያሉ ኩሩ ዜጎችን አፍርተዋልና ህግና መመሪያ እየወጣ ፣ የወጣው ህግና መመሪያ እየተጣሰ ቤታውን አጨልሞታል ። ትናንት የነበረው ዛሬም የቀጠለው ደረቅ አሳዛኝ እውነት ይህ ነው !

አዎ የእናት አብራክ ጀግና ማፍራቱ አላቆመምና የጀግና አርበኛ እናቶች እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም የእኛ እንደ ከፋቸው ፣ ሰርክ እንደተሸበሩና ሰላማቸውን አጥተው ኑሮን ለመግፋት ተገደዋል። የእሳተ ነበልባል ለወጥ አራጅ እናቶች ናቸውና ይገፋሉ ፣ በገዛ ሃገራቸውና በቀያቸው ፣ በስጋትና በሽብር ተከበው ኑሮን በመከራ ፣ በደል እየተፈጸመባቸው ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ከቀደመው እስከ ቀረበው ፣ ከቀረበው እስከምንገፋው የለው የእኛ ሀገር የፖለቲካ ምህዳር የፈጠረው አሳዛኝ የተገፊ እናቶች ታሪክ ዋቢ ነው … !

ትንታጉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ …

ተመስገን ደሳለኝ ደርግ በወደቀ ማግስት “ክፉው ዘመን አለፈ ፣ መጨራረስ መገዳደል እልባት አገኘ ” ተብሎ ተስፋ በተጣለበት ፣ “ዲሞክራሲ ሰፈነ !” ተብሎ አዋጅ ነጋሪት በተጎሰመ ፣ በተነገረበት ” የዲሞክታሲያዊ እኩልነት ህገ መንግስት ” የጸደቀ ሰሞን የአንደኛ ደረጃ አስኳላ ትምህርቱን ያላጠናቀቀ ገና በአስራዎቹ የእድሜ ክልል የነበረ ወጣት ነው ። ባለፉት 23 አመታት ግን ተግቶ ትምህርቱ የተከታተለው ብትቱ ታዳጊ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ዘልቆ እውቀትን በመገብየት በተገቢ መንገድ አጠናቀቀ ።

ጎልማሳው ተሜ ….የሃገር ፍቅሩን ከቀሰመበት የትምህት ረድፍ አልፎ ተርፎ ፣ ከጎረቤት ፣ ከከባቢው ወርሷም አደገ … እናም ከጥቂት አመታት በፊት ነፍሱ ሲፈቅድ በተሰጠው የመጻፍና ማንበብ መብት ማዕቀፍ ብዕር ጨበጠ .. ተመስገን አውነትን ይዞ ፣ ዲሞክራሲን መከታ አድርጎ ያልተመቸውን የፖለቲካ አካሔድ ተቃዋሚ ፣ ገዠ ፖርቲ ሳያይና ግራ ቀኝ ሳይለይ ይሞግት ገባ ። የተዋጣለት ጋዜጠኛና የፖለቲካ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትንታኝ ጸሃፊ ለመሆን ከበቁት የዘመናችን ትንታግ ሰላማዊ ትግል አርበኞች መካከል አንዱ ለመሆን ለተመስገን ጊዜ አልፈጀበትም ! እናም ስራውን ተግቶ ቀጠለ …

ጋዜጠኛ ተመስገን የመጻፍ የመናገር መብቱን ተጠቅሞ ፣ በሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሃገሩ ይሆናል ያለውን ሰላማዊ የትግል ስልት በማመላከት ፣ ወጣቱ ፍርሃትን አስወግዶ ለሰላማዊ ትግል እንዲተካ መስበክ ያዘ ፣ መሰናክል ጋሬጣው ከማንሳት ይልቅ … ጋዜጠኛ ተመስገን ብዙ ታገለ ፣ አታገለ … ማለቱ ብቻ ይቀላል !

የቆየው ውርስ ተከትሎናልና ፣ ጥላቻውን አድገንበታልና የዚያ ወጣት ትንታግ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንገድ በዘባተሎው ፖለቲካ ተሰናከለ ! … ባለ ራዕዩን ብዕረኛ ፓለቲካው ጠልፎ ጣለው ! ተሜ ግን የዋዛ አይደለም ” … ለእኔ ሳይሆን ለታገልኩለት አላማ ጸንታችሁ ታገሉ ! ” እያለ የወህኒውን ህይዎት በጸጋ ተቀብሎት ኑሮን መግፋት ይዟል ! …

ተገፊዋ የተመስገን እናት …

… የተሜ እናት ግን እያነቡ ነው … ብዙ ማለት አልችልም ፣ የተገፊዋን እናት ደብዳቤ ደርሷል ፣ አዝኛለሁ ! የምንሰማቸው ከሆነ …ተገፊዋ እናት በአብራካቸው ክፋይ በልጃቸው በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ወህኒ ቤት ውስጥ ህግ እየተጣሰ የሚፈጸምበት መበት ገፈፋ ሰላም ነስቷቸው ” የሰው ያለህ ፣ የህግ ያለህ! ” ብለውናል ። የእኒህ እናት ጩኽትና ሮሮ የሀገሬ ለውጥ አራማጅ ጀግና ልጆችን የወለዱ እናቶች ሁሉ ጥሪ ለመሆኑ ላፍታ አልጠራጠርም ። ምንም እንኳን ይህ አሁን ድረስ የቆየና የቀጠለው የሀገሬ እናቶች መከራ አንዱ ክፍል ቢሆንም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት 30 ቀናት ከማንም ጋር እንዳይገናኝ መደረጉና የእናቱ አቤቲታ ጉዳዩን ጀሮ ገብ መልስ የሚያሻው ቀዳሚ ጉዳይ አድርጎታል ።

ዛሬ ጋዜጠኛ ተመስገን ጥፋት ምንድን ነው? ፍርዱስ ፍትሃዊና ተመጣጣኝ ነውን ብለን አንጠይቅም ፣ አንሞግትም ! ዛሬ የምንሞግት የምንጠይቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር መብቱ አይጣስ ፣ ህገ መንግስቱ ይከበር እያልን ነው ። ተመስገን ከሚወዱ ከሚናፍቁት አቅመ ደካማ እናቱ ፣ ከቤተሰብ ከቅርብ ዘመዶቹ ፣ ከሐይማኖት ፣ ከሐኪምና ከህግ አማካሪ ጋር የመገናኘት ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲያከብርለት እንደ ዜጋ ድምጻችን የማሰማት ቢያንስ የሞራል ግዴታ አለብን ! ግፍ ሲበዛ ጥሩ አይሆንም ፣ ጆሮ ያለው ይስማ !

ፍትህ እንሻለን !

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 3 ቀን 2007 ዓም

===================================

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ደብዳቤ
===========================
ቀን 02/06/2007 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉብኝት ይመለከታል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአብራኬ የወጣ ሁለተኛ ልጄ ነው፡፡ ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለሰው አሣቢ፣ ሀገር ወዳድና ታታሪ ስለመሆኑ ከእኔ በላይ የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡ ልጄ ተመስገን ለወገኔ አሰብኩ ባለ በእስር ቤት ያለጎብኚ እየተሰቃየብኝ ይገኛል፡፡ መቼም፣ የእናት ሆድ አያስችልምና እባካችሁ ልጄን ታደጉት፡፡ እባካችሁ ቢያንስ ካለበት እየሄድኩ የልጄን አይን እንዳይ እንዲፈቀድልኝ ተባበሩኝ፡፡

የልጄን ድምጽ ከሠማሁ ይኸዉ አንድ ወር ሞላኝ፡፡ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለወንድሙ ብሎ የቋጠረዉን ምሣ ይዞ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢሄድም በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ተደብድቦ የያዘውን ምግብ እንኳ ሣያደርስ ሜዳ ላይ ተደፍቶ ተመልሷል፡፡ መቼም እናንተም ልጆች ይኖራችኋል፤ ደግሞም የልጅን ነገር ታውቁታላችሁ፡፡ እኔ አሁን በእርጅና ዕድሜዬ ላይ እገኛለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ብቆይም ለትንሽ ጊዜያት ነው፡፡ በዚህች ጊዜ ውስጥ ልጄን እየተመላለስኩ እየጠየኩ፣ ድምፁን እያሰማሁ፣ አይዞህ እያልኩ ብኖር ለእኔ መታደል ነበር፡፡ እባካችሁ እርዱኝ የልጄ ድምጽ ናፈቀኝ፡፡ እሱን መጎብኘት የተከለከለበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንኳን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ ከወንድሙ ድብደባ በኋላም ጥር 10 ወደ ጠዋት አካባቢ የሄዱት ጓደኞቹ እና ወንድሞቹ ሳያዩት ተመልሰዋል፡፡

ተምዬ ስታመም የሚያስታምመኝ፣ “አይዞሽ እማዬ” የሚለኝ ረዳቴ ነው፡፡ ሌላ ዘመድ የለኝም፡፡ የምተዳደረውም ልጆቼ ለፍተውና ደክመው በሚያመጧት ትንሽ ብር ነው፡፡ ዛሬ ግን ይኸዉ ልጆቼም ወንድማቸውን ለማየት እየተንከራተቱ ነው፡፡
በእናታችሁ ይዣችኋለሁ፤ ከቻላችሁ ልጄ እንዲፈታልኝ እና እኔም ያለችኝን ቀሪ የእድሜ ዘመን አይን አይኑን እያየሁ እንድኖር እንድታደርጉልኝ፤ ይህን ማድረግ ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ካለበት ድረስ እየተመላለስኩ እኔና ሌሎች ልጆቼ እንዲሁም ወገኖቹ እንዲጠይቁት ቢደረግልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ፡፡ ልጄን አውቀዋለሁ፡፡ አንድ ነገር ሲገጥመዉ ሆድ ይብሰዋል፡፡ ቢያንስ እንኳን ቤተሰቦቹን ሲያይ ስለሚፅናና ይኸዉ እንዲፈቀድልኝ እማፀናለሁ፡፡ እኔ ምንም አቅም የሌለኝ አሮጊት ነኝ፡፡ ሁሉንም ለናንተ ሠጥቻችኋለሁ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር እንደምታስተካክሉልኝ እና እንደገና የልጄን ፊት እንዳይ እንደምታደርጉኝ ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡

እንግዲህ የየካዉ ቅዱስ ሚካኤል ይከተላችሁ፡፡ መቼም የእናትን ሆድ ታውቁታላችሁ፤ የልጅ ነገር አያስችልም፡፡ ሆድም ቶሎ ይሸበራል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ እኔንም ልጆቼንም እርዱን እንላለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ወ/ሮ ፋናዬ እርዳቸው

ግልባጭ

– ለጠ/ሚኒስተር ፅ/ቤት
– የህግና፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ – ለአፈ-ጉባኤ ፅ/ቤት – የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) – ለእምባ ጠባቂ – ለአሜሪካ ኢምባሲ – ለእንግሊዝ ኢምባሲ

በግማሽ ዓመት 47 ሺ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል

 • ሰሞኑን 35 ስደተኞች የያዘ ጀልባ የመን ሳይደርስ ሰጥሟል
 • በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል
 • “በህጋዊ ምዝገባ የስራ ጉዞ መታገዱ ህገወጥ ስደትን አባብሷል”

በህጋዊ ምዝገባ ወደ አረብ አገራት የሚደረግ ጉዞ ከታገደ ወዲህ፣ በየመን በኩል እየተሰደዱ ለአደጋ የሚጋለጡ ኢትዮጵያዊያን መበራከታቸውንና ባለፉት ስድስት ወራት 47ሺ ያህል ስደተኞች የመን እንደገቡ RMMS ሰሞኑን ገለፁ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን እና ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ ያቋቋሙት ይሄው ተቋም እንደሚለው፣ ዘንድሮ የስደተኞቹ ቁጥር ከአምናው በእጥፍ ይበልጣል፡፡ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ 250 ስደተኞች የመን ለመግባት ሲሞክሩ፣ በባህርና በበረሃ ጉዞ ላይ መሞታቸውን ተቋሙ ጠቅሶ ከስደተኞቹ መካከል ሰማኒያ በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ሰሞኑን በባህር ጉዞ ላይ በተፈጠረ አደጋ አንድ ጀልባ መስመጡን የዘገበው ኤኤፍፒ፤ ጀልባዋ 35 ስደተኞችን አሳፍራ ነበር ብሏል፡፡ ከጉዞ አደጋ በተጨማሪ ስደተኞቹ የመን ከገቡ በኋላም ግማሽ ያህሉ በወሮበላ ቡድኖች እንደሚታገዱ የገለፀው RMMS፤ ከእገታ ለመለቀቅ ከቤተሰብ ገንዘብ እንዲያስልኩ ይገደዳሉ ብሏል፡፡ ለስደት የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያቶችን ለማወቅ በሺ በሚቆጠሩ ስደተኞችና በትውልድ አካባቢዎቻቸው ላይ ጥናት ያካሄደው ይሄው ተቋም፤ በኢትዮጵያ ዋናዎቹ መንስኤዎች የኑሮ ችግር እንዲሁም ህይወትን የሚያሻሽል ነገር ፍለጋ ናቸው ብሏል፡፡ የፖለቲካ ችግርም የተወሰነ ጫና እንደሚፈጥር ተቋሙ ጠቅሶ፣ የደላሎች ድርሻ ግን ብዙዎች እንደሚያስቡት አይደለም፤ ከመቶ ስደተኞች መካከል በደላላ ግፊት ለስደት የሚነሳሱት ከሁለት ወይም ከሦስት አይበልጡም ብሏል፡፡
ብዙ ወጣቶች ወደ ስደት የሚያቀኑት አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ባለማወቃቸው ነው ለማለት እንደሚያስቸግር ተቋሙ ሲያስረዳ፤ በአመት ውስጥ ወደ የመን ከገቡት ኢትዮጵያዊያን መካከል ሩብ ያህሉ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተባረሩና ካሁን በፊት ስደትን የሞከሩ ናቸው ብሏል፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ የስደተኞቹ ቁጥር የተባባሰበት ሌላው ምክንያት፣ በህጋዊ ምዝገባ ወደ ሳዑዲ አረቢያና ወደ ኩዌት ሲደረግ የነበረው የስራ ጉዞ በመንግስት መታገዱ ነው ብሏል – የተቋሙ ጥናት፡፡ በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ ከድህነት በተጨማሪ የሰላም እጦት ወጣቶችን ለስደት እንደሚገፋፋ ተቋሙ ገልፆ፤ በኤርትራ ደግሞ ከኑሮ ችግር ሌላ ዋነኛው ግፊት የመንግስት ከፍተኛ የፖለቲካ አፈና ነው ብሏል፡፡ በሊቢያና በግብጽ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሚሞክሩ ስደተኞች መካከል ከሶሪያዊያን በመቀጠል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ኤርትራዊያን መሆናቸውን የጠቀሰው ይሄው ተቋም፤ ባለፉት አራት ወራት 15ሺ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደተሰደዱ ገልጿል፡፡ ስደት የተባባሰው በድህነትና በአፈና ምክንያት አይደለም በማለት የኤርትራ መንግስት ሲያስተባብል፤ ወጣቶች እንዲሰደዱ በማድረግ አገሪቱን ኦና ለማድረግ አለማቀፍ ሴራ እየተካሄደብኝ ነው ብሏል፡፡ (አዲስ አድማስ)

የአንድነት ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡

udj-blue

በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ”ቀድሞው አንድነት ፓርቲ” አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡
“የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል” ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት፤ ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት “በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው” በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄ ማቅረባቸውን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አመልክቷል፡፡
ምንጭ፡ አዲስ ሚዲያ
ዮናታን የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደግሞ በዚህ ጉዳይ የሚከተለው ብሏል።

ትላንት አንድነት አፈረሱት ሲባል ሊጨልም ነው ያልነው ተስፋ ዛሬ ደግሞ አንድነቶች ግርርርር ብለው ሰማያዊን ሲቀላቀሉ፤ ማንሰራራት ጀመሯል። (የፎቶ አስተያየት በ-አበበ ቶላ ፈይሳ)

ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው
በግሌ ውህደትን ሲገፉ ከነበሩት ውስጥ አንዱ ነኝ፡፡ ቀደም ባሉ ጊዜያትም ይህንኑ ሀሳቤን አብራርቻለሁ፡፡ እርግጥ የኔ ምኞትና ትልም አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲነታቸውን እንደያዙ በመተባበር ስርዓቱን የመቀየር ትግል ቢያካሂዱ ነበር፡፡ በኔ እምነት ለሀገራችን ዘመኑን የዋጀ ርዕዮተ ዓለም የሚያራምዱት በህዝብ ተቀባይነት ያላቸው ፓርቲዎች መሆናቸው ለወደፊቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ እና ህዝብን በንቃት የሚያሳትፍ የፖሊሲ እና መሰል ክርክሮችን በፉክክር እያካሄዱ የዲሞክራሲን መርህ በሀገራችን እንዲተገበር ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋልም ብኜ አምን ነበር፡፡
የሁኔታዎች አስገዳጅነት እና የፖለቲካው ተለዋዋጭነት ግን ይህን ትልም መና አድርጎታል፡፡ አንድነት ለትግስቱ አወሉ ተላልፎ ሲሰጥ እጅግ ያዘንኩት አንዱም ምክንያቴ ይኸው በውስጤ የነበረው ምስል አብሮ በመፍረሱ ነው፡፡ ከነበሩኝ ስጋቶች ዋነኛው ደግሞ አንድነትን የመሰለ ሰፊ መዋቅርና የህዝብ ድጋፍ ያለው ፓርቲ እንደው ዝም ብሎ ‘ተበትኖ ሊቀር ነው’ የሚል ቁጭትም ይዞኝ ነበር፡፡
ግና – ነገር ሁሉ ለበጎ ነው እንዲሉ በክፋት እና ሴራ ፓርቲያቸውን የተነጠቁት የአንድነት አባላት(በክፍላተ-ሀገራትም ይሁን በአዲስ አበባ) ትግሉን ትተን ወደቤታችን አንገባም በማለት መወሰናቸው፤ ወደ ሰማያዊም መቀላቀላቸው ቁርጠኝነታቸው አረጋጧልና በይፋ ክብር ልሰጣቸው እወዳለሁ፡፡ በሰላማዊ ትግል አንዱ በር ሲዘጋ ሌላ ማስከፈት፣ እየወደቁ መነሳት ያለና የሚጠበቅ ሲሆን፤ ይህን አውቆ ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት መንቀሳቀሱ ደግሞ በሳልነት ነው፡፡

ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ – በውቀቱ ስዩም

ለምርጫውና ለ ሩጫው ተዘጋጃችሁ? እኔ ካርድ ኣውጥቻለሁ፡፡የሆስፒታል ማለቴ ነው፡፡ኣትልፉ መሪዎች የሚወገዱት በምርጫ ወይም በትጥቅ ትግል ሳይሆን በኮሌስትሮል ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው! ጌቶች በህዝብ ግፊት ባይወገዱ በደም ግፊት ይወገዳሉ:!!!

1003677_538846796175394_679131810_nእንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
ማሽተት የተሣነው፤ የጋሽ ጣሰው ኣገር፡፡
ልክ እንደነ ፓሪስ፤ እንደሎንደን ሁላ
ፏፏቴም ባይኖርሽ፤ ሽቅብ የሚፈላ
ወንዝሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ቱቦ፤ የወጣ ሰገራ፤ ሰንጥቆሽ ይፈስሳል
ሲያቀብጠኝ ያን ሜሪላንድን የመሰለ ኣገር ትቸ ወደ ሸገር ተመለስሁ ፡፡ የተመለስኩበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ኣሜሪካን ኣገር ጥገኝነት ለመጠየቅ ውስጥ ውስጡን በምዘጋጅበት ሰኣት ዲሲ የሚኖሩ ጓደኞቼ የስንብት ፓርቲ ኣዘጋጅተው ጠሩኝ፡፡“የወጣው ሰው ሁሉ ወጥቶ በሚቀርበት በዚህ ቀውጢ ሰኣት ወደ ኣገርህ ለመመለስ ያሳየከው ቁርጠኝነት በጣም የሚያኮራ ነው” እያሉ ትከሻየን ተምተም ተምተም ኣረጉት፡፡ ሼም ይዞኝ ወደ ሸገር ተመለስሁ፡፡ ጸጸት የለበለበኝ ገና ኣውሮፕላኑ ሲነሣ ነው፡፡ እንድያውም ዱባይ ላይ ትራንዚት ስናደርግ ወደ ሳኡዲ ኣረብያ ልሸበልል ኣስቤ ነበር፡፡ የኣረብ ፖሊሶች በኮሌታየ ጠርዘው ኣስገቡኝ፡፡ “ኧረ ጎበዝ የንጉሥ ኣብደላ ቀብር ላይ ለመገኘት ነው” ብል ማን ሊሰማኝ፡፡ ሩቢላው ወደ ሸገር ሲወርድ ቁልቁል ኣገሬን ሾፍኳት፡፡ ልምላሜ የሚባል ነገር ኣልጣፈባትም ፡፡በርግጥ እንጦጦ ላይ የጥልያኑን ተጫዋች የባላቶሊን ቁንጮ የምታክል ጫካ ቀርታለች፡፡
ኢትዮጵያ ኣገሬ
እማማ ኣገሬ
ስንት ገባ ይሆን የውጭ ምንዛሬ?
ኣንባቢ ሆይ በዚህ ግጥም ቅርጽ ላይ እንጂ ጭብጥ ላይ እንዳታተኩር ኣደራ፡፡ ቤት ለማስመታት ያክል ነው እንጅ ከዚህ በፊት እንደተናገርኩት ቤሳቢስትን የለኝም፡፡በዶላር ያለው ሰውየ ቢንጃሚን ፍራንክሊን ይሁን ቢንጃሚን ኔታኒያሁ እማውቀው ነገር የለኝም፡፡
እህ እናንተ የምድር ጎስቋሎች! እንዴት ናችሁ! ለምርጫውና ለ ሩጫው ተዘጋጃችሁ? እኔ ካርድ ኣውጥቻለሁ፡፡የሆስፒታል ማለቴ ነው፡፡ኣትልፉ መሪዎች የሚወገዱት በምርጫ ወይም በትጥቅ ትግል ሳይሆን በኮሌስትሮል ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው! ጌቶች በህዝብ ግፊት ባይወገዱ በደም ግፊት ይወገዳሉ:!!! እስቲ ሁላችንም ግራ እግራችንን እያነሣን የሚከተለውን መፈክር እናስተጋባ፡፡ መጭው ዘመን ከገዥው ፓርቲ ጋር ጭንቅ ነው!! ከጎምዥው ፓርቲ ጋርም ውድቅ ነው!! ይብላኝ ለእናንተ እንጂ እኔ ትንሽ ኮሽ ሲል ውልቅ ነው፡፡ፓስፖርቴን እንዳልነጠቅ ጀርባየ ላይ ተነቅሸዋለሁ፡፡
በእናታችሁ እኔን ምረጡኝ፡፡ምልክቴ ፤ ጠገራ ብር የሚያክለው ማድያቴ ፡፡ጅግናው የውሃ ልማት ሰፈር ህዝብ ሆይ! ተው ምረጠኝ፡፡ ብትመርጥኝ የኩራዝ መለዋዋጫ እቃዎች ኣቀርባለሁ፡፡ተች ስክሪን ፋኖስ ኣስገባለሁ፡፡
በነገራችን የፓርቲዎችን የምርጫ ምልክቶች ልብ ብላችኋቸዋል?የቀረ የዱርና የቤት እንስሳ የለም፡፡ዝሆን ቀጭኔ ኣውራሪስ ግመል ነብር ፡፡ጉማሬ ሁሉ ያየሁ መስሎኛል፡፡
ውድድሩ የስልጣን ነው የኣደን ?
ጉዞው ወደ ፓርላማ ነው ወይስ ወደ ደን?
በነገራችን ላይ የሳኡዲው ንጉስ ኣብደላ ባጭር መቀጨት በማስመልከት ለሰባ ሁለት ኣመቱ ጎረምሳ ኣልጋ ወራሽ የሀዘን ደብዳቤ ጽፍያለሁ፡፡ከደብዳቤው ሥር ፊርማየን ብቻ ሳይሆን የባንክ ኣካውንት ቁጥሬን ኣስፍርያለሁ፡፡ሳኡዲዎች እዝን ለሚደርሳቸው በንፍሮ ፈንታ ዶላር እንደሚያዘግኑ ሰምቻለሁ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ንጉስ ኣብደላን ለመቅበር መሬት ሲቆፈር ነዳጅ ተገኘ ፡፡
የታደለ ኣገር ሁለመናው ጋዝ ያልታደለው ኣገር ሁለመናው መጋዝ፡፡እኛ ኣገር ቢቆፈር የሚወጣው የሰማእታት ኣጽም ብቻ ነው፡፡
በቅርብ ጊዜ ያለው የኢትዮጵያ ገጽታ በሚከተለው መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡የተገለበጠ መኪና -ተጀምሮ ያላለቀ ኣውራ ጎዳና-በፖሊስ ቆመጥ የቆሰለ ሰልፈኛ-ቦርጫም የቲቪ ጋዜጠኛ-ቀጫጫ ተሸላሚ ኣርሶ ኣደር-ሁለት ኣገጭ ያለው ወታደር-በኣሸናፊው እስር የሚጠናቀቅ ክርክር-ከእድሜ የሚረዝም መፈክር-የቻይና እዳ- ከጀሪካን ሰልፍ የተሰራ ግድግዳ፡፡
ሰልፍ ያማራችሁ ተሰለፉ፡፡ብቻ እኔ ወክ በማረግበት በኩል ኣትለፉ፡፡እኔና ቢጤዎቼ በየጓሮው የፖሊስ ቆመጥ እንደ ሸንኮራ ሲበቅል ኣይተናል፡፡ የዛሬ ፖሊስ የሚበትነው ቢያጣ የታክሲ ሰልፍ ይበትናል፡፡
ባለፈው ኣመት ልደቴን በማስመልከት ሚስቴ ቮልስዋገን ገዝታ ኣበረክታልኝ ነበር ፡፡ዘንድሮ ደግሞ ኣስፓልት ልትገዛልኝ ኣቅዳለች፡፡ ታድያ የት ሄጄ ልንዳ ?መኪናችንን የምንጠቀምበት ለመብራት ነው፡፡ማታ ቮልሳችንን ከሳሎናችን በር ፊትለፊት ገትረን በፍሬቻው ብርሃን ራት እንበላለን፡፡መንዳት ኣይታሰብም፡፡ያዲስ ኣበባ ሰው መሄጃ ስላጣ መኪናውን ጥግ ኣስይዞ ይቅማል፡፡ትራንስፎርሜሽን ማለት መኪና ወደ መቃምያ ቤት መቀየር ነው እንዴ? ትራፊክ ፖሊሶችም ነገሩን ለምደውት ቃሚ ኣይቀጡም ኣሉ፡፡ባይሆን በየጋቢናው በር ብቅ እያሉ “እስቲ በርጫውን የገዛህበት ደረሰኝ ኣሳየኝ”ይላሉ፡፡
ያ ባቡር በመጣና እንዴት ኣባቱ ኣድርጎ እንደሚሄድ ባየሁት፡፡ሃዲዱ የቤቴን ግድድዳ ታክኮ ነው የተዘረጋው፡፡ራሱን ለመግደል ከባቡሩ መስኮት የሚወረወር ሰው ምኝታ ቤቴ ውስጥ መውደቁ ኣይቀርም፡፡ወይ እቶጵያ ድንቅቅ የምትል ኣገር፡፡ ወደብ ባይኖራትም መርከብ ኣላት፡፡ኤሌክትሪክ ባይኖራትም የኤሌክትሪክ ባቡር ኣላት፡፡

እስቲ ባቡሩ ከለገጣፎ ሲነሳ ኣስቡት፡፡የባቡሩ ወያላ ተሳፋሪው ሁሉ ገብቶ ማለቁን ካረጋገጠ በኋላ እንዲህ የሚል ይመስለኛል”ውድ ተሳፋሪዎቻችን በኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት ጉርድ ሾላ ላይ ልናድር ስለምንችል ታጣፊ ኣልጋ መያዝ እንዳትረሱ፡፡”
ከብረትና ከጥቅስ የተሰራው የኣዲስኣበባ ምኒባስ በስንት ጣሙ፡፡ በነገራችን ላይ ፣ኣሜሪካ ውስጥ ታክሲ ውስጥ ያለው ወሳኝ እቃ ጂፒ ኤስ ሲሆን የኢትዮጵያ ታክሲ ወሳኝ እቃ ጥቅስ ነው፡፡ወያላው በግራ መስታውት”ከሾፊሩ ጋር የምትጨቃጨቁ ፡በኢቦላ እለቁ”የሚል ርግማን ለጥፎ በቀኝ መስታውት በኩል ጽዋ የያዘ የመላእክ ስእል ይለጥፋል፡፡ በጥቅሱ ሃጢኣት ሰርቶ ፡ ከመላእኩ ስእል ኣካማኝነት ንስሃ ገብቶ ወደ ቤቱ ይገባል፡፡
(እኔ ከቀጠልኩ ይቀጥላል)

መስታውት በኩል ጽዋ የያዘ የመላእክ ስእል ይለጥፋል፡፡ በጥቅሱ ሃጢኣት ሰርቶ ፡ ከመላእኩ ስእል ኣካማኝነት ንስሃ ገብቶ ወደ ቤቱ ይገባል፡፡

(እኔ ከቀጠልኩ ይቀጥላል)