Archive | March 10, 2015

“ኢህአዴግ የሚባል ውህድ ፓርቲ” የለም

ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ

ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡

ፓርቲው በላከው ደብዳቤ “በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም” ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡

ፓርቲው አክሎም “የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል” ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡

“ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡

የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም “ህወሓት-ኢህአዴግ”፣ “ብአዴን-ኢህአዴግ”፣ “ኦህዴድ-ኢህአዴግ” እና “ደኢህዴን-ኢህአዴግ” በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች “ኢህአዴግ” በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡ (ነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)

'"ኢህአዴግ የሚባል ውህድ ፓርቲ" የለም
ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ
http://www.goolgule.com/there-is-no-party-called-eprdf/

ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡

ፓርቲው በላከው ደብዳቤ “በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም” ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡

ፓርቲው አክሎም “የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል” ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡

“ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡

የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም “ህወሓት-ኢህአዴግ”፣ “ብአዴን-ኢህአዴግ”፣ “ኦህዴድ-ኢህአዴግ” እና “ደኢህዴን-ኢህአዴግ” በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች “ኢህአዴግ” በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡ (ነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)'

ሽሽት አያዋጣም

–  አማራ ሆነን አይደላችሁም ተብለን

– ከወግኖቻችን ጋር ተለያየን 

የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ

ethiopia

ችግርን መፍታት የሚቻለው ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ በመወያየትና የመፍትሄ ሃሳብ በመስጠትና በመፍታት ችግርን መቅረፍ እንጅ በመሸሸት በመደበቅ ከህዝብ ተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም አያዋጣምም :: ከሰሞኑ የወያኔ ጠቅላይ ሚንስቴር ኅይለማሪያም ደሳለኝን የወልቃይት ህዝብ በድህነት ቤቱ ካለው የኑሮ ውድነት በላይ ቤተሰቦቹን በአግባቡ ማስተዳደር እያቃተው ቢሆንም ከአለችው የዕለት ጉርስ በመቀነስ ለባለስልጣኑ የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት “መቸም ከአልበላ አይስቅ” ይላል የሃገሬ ሰው ሲተርት ሆዱን ሞልተን ከእሁን በፊት በተለያየ ጊዜ በፅሁፍ የአቀረብነው አቤቱታ የማንነት ጥያቄ ይህውም በባህል በወግ በልምድ በቋንቋ በኑሮአችን አንድ ሆነን በአማራነታችን ርግጠኛ ሆነን እያለን ወያኔ እኔ አውቅልህአለሁ አንተ ትግሬ እንጅ አማራ አይደለህም በማለት መብታችን በመግፈፍ ጥያቁ እያቀርብን ያለፍላጎታችን ወደትግራይ ተወስድን ይህም ለእኛ ታስቦ ሳይሆን የትግራይን መሬት ለማስፋፋት እንደሆነ ስለምናውቅ አእምሮችንም ሰለአልተቀበለው ለህዝብ ጥያቄ መጠበቅ በርሃብ ሲቀጣ ከመዋሉም በላይ ንቀቱ ከልክ ያለፈ በመሆኑ ህዝቡ ንዴቱና ምሬቱን በከፍተኛ ቁጣ የገለፀ መሆኑ ታውቁዋል::
By :- Hana Tadesse