|
Archive | April 2015
የምሥራች! የአንድ ደሮ ዋጋ የዐርባ አምስት በሬ ዋጋ ሆነ!
ክርስቲያን አንባቢዎቼ እንኳን ለ2007ዓ.ም የጌታችን የመድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፡፡ ሙስሊሞችና ሌሎችም እንኳን ለኛ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ለእናንተም በዓል(ላት) በሰላም እንዲያደርሰን የጋራ የሆነውን ፈጣሪን በጋራ እንለምነው፡፡
ይቺ የዘንድሮ የትንሣኤ በዓል ከቀደሙት ትንሽ ለዬት ሳትል አትቀርም፡፡ ይሄ ግፋፎ ብር እዬለየለት መጥቷል፡፡ የሰሞኑ ገበያ በጣሙን ተበሻቅጧል፡፡ መንግሥቶቻችን ሲያቀብጣቸው ብሩ ላይ የወፍ ስዕል አኑረውበት ብሩ በዓለማችን የመጨረሻው ፈጣን ወፍ ሆነ፡፡ ሲበር ፍጥነቱ ልዩ ነው፤ በሣይንሳዊ መሣሪያ እገዛ ካልሆነ በዐይን ብቻ አይታይም፡፡ አቶ ብሩ ጉድ አፍልቷል፡፡ በአብዛኛው ከሆዱ ባለፈ የማይጨነቅ የልምድ ነጋዴ በሞላባት ሀገራችን ውስጥ በአቋራጭ ለመክበር የሚስገበገበው ሰው በዛና አቅልን የሳተ የገንዘብ ግንኙነት ነግሦ ሁላችንንም አቅል እያሳጣን ከሰውነት ተራ እያስወጣን ይገኛል፡፡ የዛሬው አዋዋሌ ራሱ ከወትሮው የተለዬ ሆኖብኝ በጣም ሲገርመኝ ውሎ አመሸ፡፡ ከማን ጋር እንደማወጋው ጨንቆኝ ሳለ እናንተ ትዝ አላችሁኝ፡፡ እስኪ ተንፈስ ልበል፡፡
ትዳር ያደረገ ልጄ(በትግርኛ አማርኛየ ቅር አትሰኙም መቼም) – ለአቅመ-በግ ያልደረሰ በቅርብ ትዳር ያደረገ ልጄ ደሮ አጋዛኝ ብሎ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ይደውልልኛል፡፡ ወዲያውኑ እንገናኝና የካ ሚካኤል አካባቢ ወዳለው ሾላ የደሮ ገበያ እንሄዳለን፡፡ ትርምሱ ሌላ ነው፡፡ ከቤት የቀረ ሰው ያለም አይመስልም፤ በዚያም ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እዳር ተመካክሮ ሰው ከማፍራት ውጪ ተኝቶ የሚያድር አይመስልም፤ የሰው ፋብሪካ በየቤታችን የተከልን እንመስላለን – ብዛታችን ሲታይ፡፡ ለማንኛውም ከልጄን ጋር የተለያዩ ሸቀጦችንና ዕቃዎችን ዋጋ በእግረ መንገድ እየጠያየቅን ወደደሮ ተራ አመራን፡፡ የሁሉም ነገር ዋጋ ሰማይ ነው፤ ከምናውቀው ሰማይ በላይ ሌላ ሰማይ ካለም ከዚያም በላይ፡፡ የሁሉም ሸቀጥና ዕቃ ዋጋ ያስደነግጣል፡፡ ሁሉም ነጋዴ ቁጥር የሚያውቅ አይመስልም፡፡ ቁጥሩ ቀላል የማይባለው ሸማችም እንዲሁ ቁጥር የሚያውቅ አይመስልም፡፡ ነጋዴው ስምንት መቶ የሚለውን የቻይና አቃጣይ ጫማ – ከሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት ከሁለት መቶ በዘለለ የማይሸጠውን ጫማ ማለት ነው – ብዙም ሳይከራከር በሰባት መቶ ሃምሳ የሚሸምት ገዢ አለ፡፡ ተራዋ የላስቲክ ነጠላ ጫማ እንኳ ነፍስ አውቃ መቶና መቶ ሃምሳ ብር ስታወጣ ማየት ብርቅ ከመሆን አልፏል፡፡ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ደሞዝ ባለበት እየረገጠ የዕቃዎች ዋጋ በየሴከንዱ ሽቅብ እየተወነጨፈ እንዲህ ያለ ተናግዶት ማየት ገንዘቡ ከየት መጣ ያስብላል፤ አንዳንዱ ሰውማ ከቤቱ ውስጥ ገንዘብ ማተሚያ ማሽን ያለው ይመስላል፡፡
ኑሯችን ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ተቆጣጣሪ ብሎ ነገር የለም፡፡ ያለውና የሌለው በምን ምክንያት እንዳለውና እንደሌለው ሊታወቅበት የሚያስችል አንድም ሕጋዊ መንገድ የለም፡፡ በሀገራችን መንግሥት አለ ማለት የሚያስችል ምንም ዓይነት ምልክት ደግሞ አይታይም፡፡ በኪነ ጥበቡ ውለን ከመግባታችን በስተቀር የመንግሥትን ቀርቶ የሕዝብን ኅልውና የሚያስረግጥ አንድም ነገር ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ዛሬ ሃያ ብር የሚሸጥ ነገር ነገ በትንሹ መቶ ብር ሲሸጥ ማየት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት የሚከብደው ሰው አይኖርም፡፡ የሀብት ክምችት እሽቅድምድሙ እንደመቶ ሜትር ሩጫ ፍጥነቱ ንፋሳዊና ብርሃናዊ ሆኗል፡፡ በዚህ ላይ ዳኛ የለ፤ ታዛቢ የለ፤ ሕግ የለ፤ አዳሜን እየረጋገጥህና እየረመረምክ ባዋጣህ መንገድ መሮጥና የምትፈልገው የሀብት ደረጃ ላይ ወጥተህ ፊጥ ማለት ነው፡፡ የመንግሥት አካላት ደግሞ አሯሯጮች ብቻ ሣይሆኑ ሯጮችም ናቸው፡፡ ስለዚህም በሩጫው ተረገጥኩ ብለህ የምታመለክትበት ቅሬታ ሰሚ ቢሮ የለም፡፡ ተጋግጠህ ከሩጫው ሜዳ ትወጣለህ ወይም እንደምንም ብለህ እዚያው ትንከላወሳለህ፡፡ እንዳሁኑ የጠበቀ ሕግ ሳይወጣለት በዱሮ ዘመን የእግር ኳስ ጨዋታም እንዲህ ነበር አሉ – ማንም ጉልበተኛ ኳሷን በጥበብ ሣይሆን በጉልበት ነጥቆ በመውሰድ እግብ የሚከትበት፡፡ በሀገራችን የአሁን ሁኔታ በገቢህ ላይ ምንም የተጨመረ ነገር ሳይኖር ዋጋዎች እንዲህ ሲንሩ ስታይ ሕይወትህ በነሲብ የሚነዳ እንጂ በህግና በሥርዓት የሚመራ አይመስልህም፡፡ ደናቁርት ደናቁርትን እየጎተቱ ወደ ገደል እየጨመሩ ናቸው፡፡
ዝኮነ ኮይኑ ልጄና እኔ ዶሮ ተራ ገባን፡፡ ከድስት የማይወጣ ጫጩት ዶሮ ዋጋው 250 ብር ይሉናል፡፡ እዚያም እዚህም ስንጠይቅ የተማከሩ ይመስል – ተማክረውም ሊሆን ይችላል – የሚጠሩትም ሆነ የሚሸጡበት ዋጋ አንድና አንድ ነው፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ – ብዙ ሰዎች ጫጩት ዶሮ በ200 ብርና ከዚያም በላይ በሆነ ዋጋ ሲገዙ አየን፡፡ አንዳንዱ ገዢማ ስለለመደው ይመስላል በዋጋው መናር ሲያቅማማ አይስተዋልም፡፡ እኛ ግን ደነገጥን፡፡ ሥጋ ቢኖረው ግዴለም፡፡ ግን ለወግና ባህል ሲባል ብቻ አንዲት ስትታረድ ከአየር ወርዶ መሬት የሚደርስ ደም እንኳን የሌላት ጫጩት ዶሮ በ200 ብር መግዛት ግፍ የሚሆንብን መሰለን፡፡ ልጄ ግን ሚስቱ አንደምትቆጣው አስረዳኝና እንደምንም ተከራክሮ በ190 ብር አንዱን ወንድ ጫጩት ገዝቶ በፌስታል ቋጠረው፡፡ ይህ እንግዲህ የድሆችን ዶሮዎች በሚመለከት የታዘብኩት ነው፡፡ የኮርማ ዶሮ ታሪክማ ሌላ ነው፡፡
ወደ ሀብታም ሰዎች የደሮ ግዢ ደግሞ ልውሰዳችሁ፡፡ አንዱ ሀብታም ሁለት ወፋፍራም ዶሮዎችን አነሳና ዋጋቸውን ጠየቀ፡፡ ለያንዳንዳቸው 375 ብር ተባለ፡፡ ብዙም አልተከራከረም፡፡ 700 ብር ውልቅ አድርጎ ከፈለና ሁለቱንም ገዝቶ እመኪናው ጀርባ ሸጉሮባቸው ሸመጠጠ፡፡ ያለው ማማሩ አልኩ – በልቤ፡፡ ወደሌላ የዶሮ መሸጫ ቦታ አመራሁ፡፡ የኔ ቤት ድስት የማይችለውን አንድ ዶሮ አንዷ ሴት ሀብታም ብድግ አደረገችና ዋጋውን ጠየቀች፡፡ አምስት መቶ ብር ተባለች፡፡ እንደነገሩ ተከራከረችና በአራት መቶ ሃምሳ ተስማምታ ይዛው እብስ አለች፡፡ አንድ ዶሮ አራት መቶ ሃምሳ ብር! ይህን ትክክለኛ መረጃ ከሌላ ቦታ የምታገኙት አይመስለኝም፡፡ አንድ ዶሮ አራት መቶ ሃምሳ የኢትዮጵያ ብር ሲሸጥ እቦታው ነበርኩ፡፡ ጉድ ነው፡፡ ዶሮው ግን እንዳልኳችሁ ፍሪዳን ያስነቃል፡፡ ቢሆንም ግን ዶሮ ነው፡፡ በሬ ወይም በግና ፍየል አይደለም፡፡ እናም ዶሮ 450 ብር ሲያወጣ አየሁ፡፡ በዱሮው ዘመን አሥር ብር ፍሪዳ ይገዛ ነበር፤ እናም ዘንድሮ አንድ ዶሮ የተገዛበት ብር በዱሮው ዘመን ዐርባ አምስት ፍሪዳ ይገዛበት ነበር ማለት ነው፡፡ የሒሣብ ዕውቀቴ ወንዝ ባያሻግርም ከዚች የዶሮ ግዢ ነጥብ አንጻር የገንዘባችን ግሽበት 4500% ይመስለኛል፡፡ ዱሮ በግራም ሁለትና ሦስት ብር ይሸጥ የነበረውን የ18 ካራት ወርቅ ከአሁኑ ሰባት መቶና ስምንት መቶ ብር ዋጋው ጋር ስታነጻጽሩትም ግሽበታዊ ሥሌቱ በድንጋጤ ደም ቀጥ ያደርጋል፡፡ በ“ሰው በላው ሥርዓት” በኪሎ አንድ ብር ይሸጥ የነበረው ቅቤ ዛሬ 210 ብር ሲሸጥ ዕድገታችንን ለመለካት ምን መሣሪያ መጠቀም እንዳለብን ለማወቅ ወያኔን መጠየቅ ነው፡፡ ዱሮ በ120 ብር የሚሸመተውና ማንም ተራ ዜጋ የሚለብሰው የእንግሊዝ እውነተኛ ከሱፍ የተሰፋ ሙሉ ልብስ ዛሬ ሌላ ነገር ተቀያይጦበት በአሥራዎቹና ሃያዎቹ ሺዎች ሲገዛና የደረጃ መለያ ሲሆን ዕድገታችን የደረሰበትን ጫፍ ማሰብ እንችላለን፡፡ በቅርብ በደርግ ዘመን እንኳን በሦስት ሺህ ይገዛ የነበረ ያማሃ ሞተር ሣይክል ዛሬ ከመቶ ሺ ብር በላይ ሲገዛ የገንዘባችንን “ጥንካሬ” ያሳያል – ሊያውም እኮ በወረፋ ለወራት ጠብቀህ፤ መኪናውም እንዲሁ ነው፡፡ አሁን ለጥገና ብቻ የምታወጣው ገንዘብ ዱሮ ብዙ መኪናዎችን ሊገዛልህ የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ አሁን አንድ ቤት ለመሥራት አስበህ ለምስማር ብቻ የምታወጣውን ወደዱሮው ብትመነዝረው ያኔ አንድ ቪላ ቤት ሊሠራልህ ይችላል፡፡ ዱሮ አሥር ብር መንዝረህ ለመጨረስ “የጓደኛ ያለህ” እንዳላልክ ዛሬ አሥር ብር አንዲት ቡትሌ ቢራ እንኳን የማይገዛ ከንቱ ወረቀት መሆኑን ስትረዳ ሀገርህ ከየት ወዴት እያመራች እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ይታይሃል፡፡ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ሚስቱ ልጅ ስለወለደችለት ፈረስ በሚያስጋልብ አዳራሽ ቅልጥ ያለ ድግስ ደግሶ ከአልማዝና ዕንቁ ውድ ስጦታዎች በተጨማሪ የ2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት!) ሚሊዮን ብር መኪና ቁልፍ ለሚስቱ በስጦታ መልክ የሚያበረክት የትናንት ሙልጭ ድሃ የዛሬ ወፍዘራሽ ከበርቴ በቀየህ ትታዘብና የት እንዳለህ ታውቅ ዘንድ ዐይንህን ብታሽ ከድቅድቅ ጨለማ ውጭ የሚታይህ ሌላ ነገር የለም፡፡ ጥሬ እውነት ነው እየነገርኩህ ያለሁት – ለሥነ ጽሑፍ ውበት ብዬ ያጋነንኩ እንዳይመስልህ፡፡ …
በዕድሜየ ቆዳ መልስ ሁለትና ሦስት ብር በግና ፍየል ሲሸጥ አይቻለሁ፡፡ በዚያን ዘመን አንድ አነስተኛ ከብት(በሬ/መሲና) በግልም ሆነ በቡድን ለማረድ በትንሹ አሥር ብር ያስፈልግ እንደነበር ቀድሜ እንደጠቆምኩት እኔ ራሴ ኅያው ምሥክር ነኝ፡፡ ያኔ ከአሥር ብር እስከ ሃምሳ ብር ይሸጥ የነበረው በሬ ዛሬ እስከ ሃያ ሺህ ብርና ከዚያም ባለፈ እስከ ስልሣ ሺህ ብር ድረስ መቸብቸቡን፣ ያኔ ከ12 ዕንቁላሎች ጋር 10 ወይም 15 ሣንቲም ይሸጥ የነበረው ዶሮ ዛሬ ያለ አንዲትም ዕን
በቤተመንግስት አካባቢ አለመተማመኑ በገሃድ እየታየ ነው * የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች በሙሉ ወደ ቤንሻንጉል ተላኩ
(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት በሚያስተዳድረው መንግስት ውስጥ እርስ በ እርስ በባለስልጣናቱ መካከል ያለው አለመግባባት እና አለመተማመን እያየለ መሄዱ ቤተመንግስትም መድረሱ ተሰማ:: በተለይም የመለስን ራዕይ ገደል ይግባ የሚለው የአቶ አርከበ ቡድን ሃይለማርያም ደሳለኝን ይዞ እያየለ መሄዱና በሌሎች የሕወሓት አባላት ላይ ያለው አለመግባባት ወደ አለመተማመን ደርሶ የቤተመንግስት ጠባቂዎችን እንዳስቀየረ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋለጡ::
ቤተመንግስቱን ሲጠብቁ የነበሩ የሕወሓት ተላላኪ ወታደሮች በጠቅላላ ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ መላካቸውን ያጋለጡት የዘ-ሐበሻ ምንጮች እነዚህ ጠባቂዎች ደግሞ የአየር ሃይል አባላት መሆናቸው ጉዳዩን ከረር አድርጎታል:: ሕወሓት በሚመራው አየር ኃይል ውስጥ ያለው መታመስና በርካታ የአየር ሃይል አባላትም እየከዱ ወደ ጎረቤት ሃገራት መሰደድና ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ያስደነገጠው መንግስት የአባይን ግድብ ትጠብቃላችሁ በሚል ሰንካላ ምክንያት መሳሪያቸውን በጠቅላላ አስቀምጠው ወደ ቤንሻንጉል እንዳዘዋወራቸውና በምትካቸውም ጆሮዋቸውን ቢቆርጧቸው ያለውን መከፋፈል የማያውቁ ወታደሮችን በቤተመንግስቱ አካባቢ አስፍሯል::
በገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለው መከፋፈል ወደ እርስ በ እርስ መበላላት ሊያደርስ እንደሚችል ከውስጣቸው የሚወጡ መርጃዎች ይጠቁማሉ::
መደበኛ የስብሰባ ጥሪ ለኢህአግ ዘብ አባላት በሙሉ
‹‹በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል›› ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
በአሜሪካ ከሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት ለፍሕትና ለዴሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ አባላት ጋር በተለያዩ ስቴቶች ለመወያየት ወደዚያ ለማቅናት ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ያመሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ባላወቁት ምክንያት ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው ጉዟአቸው እንደስተጓጎለ ገለጹ፡፡
መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ወደ አሜሪካ ለመብረር ሁሉን ነገር አሟልተው ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የአውሮፕላን መሳፈሪያ ሰዓት እስከሚደርስ ሊሸኟቸው አብረዋቸው ከነበሩ ጓደኞቻችው ጋር ሲጨዋወቱ አምሽተው ወደ ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
የመጨረሻውን ፍተሻ አልፈው ወደ አውሮፕላን መግቢያ በር ለማምራት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ፍተሻ ጋ ሲደርሱ ፓስፖርታቸውን ሰጥተው የይለፍ ማረጋገጫ ለማግኘት እየተጠባበቁ ሳሉ የኦፕሬሺን ሠራተኛዋ ‹‹ከዚህ ቀደም ሌላ ፓስፖርት ነበረዎት?›› የሚል ጥያቄ እንዳቀረበችላቸው ገልጸዋል፡፡ እንደነበራቸውና ከዚህ በፊትም ወደ አሜሪካ ለመሄድ እዚያው ፍተሻ ላይ ሲደርሱ ‹‹ከፓስፖርትዎት መካከል አንድ ገጽ ጎድሏል፤›› ተብለው መመለሳቸውን እንደነገሯት አክለዋል፡፡ ለ20 ደቂቃ ያህል በኢንተርኔት ላይ አንዳንድ ነገሮችን ስታነብ የነበረችው ሠራተኛዋ፣ ‹‹አለቆቼን ላነጋግር›› ብላቸው ወደ ቢሮ መግባቷንና ወዲያው በፍጥነት ተመልሳ ሥራዋን በመቀጠል ‹‹ይጠብቁ እያዩት ነው›› እንዳለቻቸውና ለ50 ደቂቃዎች ያህል መጠበቃቸውን ኢንጂነር ይልቃል ገልጸዋል፡፡
ከረዥም የደቂቃዎች ቆይታ በኋላ አንድ ሰው ከቢሮ ወጥቶ ‹‹እርስዎ ዛሬ መሄድ አይችሉም፤›› ብሏቸው ስማቸው፣ ዜግነታቸውና የፓስፖርት ቁጥራቸው ተጽፎ፣ የታገዱበት ምክንያት ያልተገለጸበት ወረቀት እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲጠይቁ ‹‹እኛ የኦፕሬሽን ሠራተኞች ነን፣ ምክንያቱን አናውቅም፡፡ ነገ መጋቢት 24 ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ መጥተው ከአለቆቻችን ምክንያቱን ያውቃሉ፤›› ብለዋቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
በማግሥቱ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲሄዱ ‹‹በዚህ ወረቀት መግባት አትችሉም፡፡ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ሄደው ይጠይቁ፤›› ብለው እንደመለሷቸውም አስረድተዋል፡፡ ኢንጂነር ይልቃል በዕለቱ ወደ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መምሪያ ዋና መሥሪያ ቤት የሄዱ ቢሆንም፣ ‹‹ሰዓቱ መሽቷልና ነገ ጠዋት ይመለሱ፤›› ተብለው ሳይሳካላቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡
መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠዋት ሦስት ሰዓት ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት የሄዱ ቢሆንም፣ ፓስፖርቱ እንዳልደረሳቸው ሠራተኞቹ ነግረዋቸው በስልክ እየደወሉ እንዲጠይቋቸው ስልክ ሰጥተዋቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ ማታ ሲደውሉ ፓስፖርቱ እንዳልመጣ ነገር ግን እነሱ እንደሚደውሉላቸው ነግረዋቸው ስልካቸውን መውሳደቸውን አስረድተዋል፡፡ ፓስፖርታቸውን አለማግኘታቸውንና የታገደቡበትን ምክንያት ሳያውቁ ጉዟቸው ተስተጓጉሎ መቀመጣቸውን የሚናገሩት ሊቀመንበሩ፣ በፕሮግራማቸው መሠረት ሄደው ቢሆን ኖሮ መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. (ቅዳሜ) ከዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም ጋር በዋሽንግተን ከደጋፊዎቻቸው ጋር ይገናኙ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
የዋሽንግተን ነዋሪዎችን ጨምሮ በሰባት ስቴቶች ከሚኖሩ የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲዎች ደጋፊዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎችን ያደርጉ እንደነበር የገለጹት ኢንጂነር ይልቃል፣ ጊዜ ካላቸው ካናዳ ቶሮንቶ ከሚገኙ ደጋፊዎቻቸውም ጋር ለመገናኛት ዕቅድ እንደነበራቸው አስታውቀዋል፡፡
በአጠቃላይ የሚቆዩት ለአንድ ወር እንደነበር የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ በእንግሊዝ ፕሮግራም ይዘው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ ስብሰባው በሁለቱ ፓርቲዎች ደጋፊዎች የተዘጋጀ ስለነበር ለየት ያለና በጉጉት ይጠበቅ የነበረ ዝግጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሰዎችን ልብና አዕምሮ መያዝ በመቻሉ፣ ብዙዎች እየተቀላቀሉትና በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች መታየት የጀመረ ፓርቲ በመሆኑና በገዥው መንግሥት ስላልተወደደ እንቅፋቶቹ እየበዙ ናቸው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ወቅቱ የምርጫ በመሆኑ በአገር ውስጥ ዝግጅቶችን በማድረግ ሁኔታ ወደ ውጭ መሄድን ለምን እንደመረጡ ተጠይቀው፣ ‹‹የእኔ እንቅስቃሴ ድርጅቱን የሚያሳድግና የድርጅቱን አቅም የሚያጠናክር ነው፡፡ ይኼም ትግል ነው፡፡ የምሄደው ለሥራ ነው፡፡ እዚያም ያሉትን ደጋፊዎቻችንን እናነቃቃለን፡፡ አዳዲስ አባላትንም እናገኛለን፡፡ የምሄደው ሰማያዊ ፓርቲን ይዤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆኜ ነው፤›› ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኢንጂነር ይልቃልን ጉዳይ በመለከተ ከመንግሥትም ሆነ ከሚመለከተው አካል እስከ ዓርብ ሌሊት ድረስ ምንም የተሰጠ መግለጫ አልነበረም፡፡
ፎቶና ዜና ሪፖርተር ጋዜጣ
