Archive | May 4, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው

• በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል

• ‹‹የተጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው››

1186718_600650739977528_2059123344_n

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሀሙስ ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ከመስሪያ ቤት ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሚያዝያ 24/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተደረገውን አመጽ መርታችኋል፡፡›› በሚል ፖሊስ ክስ እንዳቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ማቲያስ መኩሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል፡፡ ማቲያስ፣ ብሌንና ተዋቸው ወረዳ 10 (ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ) ታስረው ይገኛሉ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደረገው እስርም ‹‹መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራ ሳይጨርስ በሀሰት 20 አባላትንና 6 አመራሮችን አስረናል ብለው ነበር፡፡ እነሱ የፈለጉት ይህን ሚዲያ ላይ ወጥተው በሀሰት የፈፀሙትን ውንጀላ ማሰመሰል ነው፡፡›› ሲል አቶ ዮናታን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

በሌላ ዜና በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደህንነትና ፖሊስ የሚፈፅመው ድብደባ አሁንም መቀጠሉ ተገልጾአል፡፡ በዛሬው ቀን የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሳብ ጌታቸው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ወረቀት በትነሻል›› በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀሙባት ተገልጾአል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

DSC_0469DSC_0384

By Alemayehu Tibebu

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ቅዳሜ በ 02/05/2015 በኑረንበርግ ከተማ በወቅቱ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን ኢትዮጵያንን ንጹሃን ዜጎች ሞት እና የኢትዮጵያን ህዝብ መሪር ሃዘን በማሰብ የ አንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ስብሰባውን ጀምሮዋል:: ትኩረቱንም በወቅቱ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስደትና በየቦታው የሚደርስባቸውን እንግልትና ስቃይ በማውሳት እንዲሁም ከአባላቱ መካከል ያላቸውን የስደትን አስከፊነትና ስቃይ ልምዳቸውን በማካፈል ይህ መከራና ስደት ሊቆም ይገባል ሰው እንደሰውነቱ ዜጋም እንደ ዜጋነቱ በሃገሩ ተከብሮ ሊኖር ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላለፈዋል::

DSC_0485

ላለፉት 23 አመታት በወያኔ የግፍ አገዛዝ ህዝቡን በመከፋፈል እና ነጻነቱን በመንፈግ ህዝቡ እንደልቡ እንዳይናገር እንዳይማር እንዳይሰራ ሃሳቡንም በነጻነት እንዳይገልጽ ጫና በማድረግ በማሰር እና በማሰቃየት ላለፉት 23 አመታት የዘለቀ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህን መከራ ሽሽት ወጣቱ ወደ ተለያየ የአለም ሃገራት እየተሰደደ ቢሆንም በየሄደበትም ሌላ ስቃየና መከራ ሲደርስበት ማየት እንደሚያሳምም በስብስባው ላይ የተገኙት አባላቶች ቁጭታቸውን ተናግረዋል::

የኢህአግዘ ዋና ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ልዑል ቀስቅስም ይህንን ችግር ልናቆመው የምንችለው በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔን ማስወገድ ስንችል ብቻ ነው ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል::

DSC_0630DSC_0353

የኢህአግዘ አባላት እና አመራር ከዚህ በፊት በተሻለና በጠነከረ መንገድ እየሄደ እንዳለ በስብሰባው ላይ የታዩት እና የተነሱት ሃሳቦች ምስክሮች ናቸው:: ይህ እየተጠናከረ የመጣው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብም ላለፉት ሁለት አመታት በትጋት ያገለገሉትን አመራሮች በማመስገን ለቀጣዩ አመታት ደሞ የተወሰን ማስተካከያና መተካካት ለማድረግ እጩዎችንም አሳውቆዋል:: ድርጅቱ በቀጣይ ሊሰራ ያቀዳቸውን ነገሮች በዝርዝር አቅርቦ ከአባላት የተነሱ ጥያቄዎችን በመመለስ ስብሰባው ተጠናቆዋል::

DSC_0432DSC_0439

DSC_0396 DSC_0390

DSC_0361DSC_0423