Archive | June 2015

እንደዘበት ወጥቶ መቅረት

ሳሙኤል አወቀን ይበልጥ የማውቀው በተለይ በመጣጥፎቹ ነበር፡፡ ለካ ነበር እንደዚህ ቅርብ ነው ነበር ያሉት እቴጌ ጣይቱ? ገና በግንባር ሳንተዋወቅ በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ተወቃቅሰንም ነበር፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት በመጣበት ወቅት እምላዕሉ ማለት አንተ ነህ ብሎኝ ስንተዋወቅ በጣም ፈጣን እና በተፈጥሮው በሳል ልጅ መሆኑን ለመረዳት ትንሽ ደቂቃ እንኳን አልፈጀብኝም ነበር፡፡ ቅምም ያለ ቀልጣፋ ልጅ ዳግም ላናየው እንደፅጌረዳ በሰው እጅ ተቀጠፈ፡፡ ከአሰፋ ማሩ ጎን በአርያም ሆኖ ሊፋረደን ከአለት የጠጠረ አደራውን ትቶልን እንደወጣ ቀረ፡፡ እነሆ ሃገር እንደ ድመት ልጆቿን እንደምትበላ የምናስመሰከርበት አርባኛ አመታችንን ሳሙኤልን እንደሻማ ለኩሰን አከበርንላት፡፡ ሰው እንዴት ወገኑን፣ያገሩን ልጅ፣ ያውም ወደፊት ለትውልድ አርአያ ሊሆን የሚችል ጎረምሳ በአጭር ሲያስቀር ህሊናው እረፍት ይሰጠዋል? ምን የሚሉት እርግማን እና ልክፍት ተጣብቶን ይሆን አርባ አመት ሙሉ እንደጅብ እርስ በርስ እየተበላላን እንደማሽላ ፍሬ ብቅ ብቅ ያለውን ከነተስፋው የምንቀጨው? የምን ሾተላይ ይሆን? በምድር ጽዋችን ሞልቶ ሲቃችንን የሚያይ እምባችንን የሚያብስ በደላችንን የሚሰማ አምላክ እውነት ከወዴት ይሆን የሚኖረው? ለምንስ ይሆን ዝም ያለን??????????
እህህ…….
ምርር ስቅስቅ ብዬ አላነባው ነገር፣
ሲቃም አመጽ ተብሎ እንዳልጠረጠር፣
እምባዬን እንደህል ሲያንቀኝ እየዋጥኩት፣
ለቆሰለው አንጀቴ ቀለብ አደረኩት፡፡

እምላዕሉ ፍስሃ

1505152_1428343147489663_4996375091015041984_n

ምርጫ ሲባል…..መሳይና አስመሳይ……

ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

ethiopia_election

ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ፡፡
ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል ይሆናል፤ አንድ የሁለት ጓደኞች የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ፤ አንዱ ስሙ መሳይ ነው፤ ፊታውራሪ ነው፤ ሌላው ስሙ በፈቃዱ ነው፤ ሀኪም ነው፤ አንድ ቀን በፈቃዱ መሳይን ሲያገኘው በፊታውራሪነቱ ለማሾፍ ፊታውራሪ መሳይ አለ፤ መሳይን ጫን ብሎ፤ መሳይም ሲመልስ በዶክተርነቱ እያሾፈ ዶክተር በፈቃዱ ብሎ ዶክተርን ጫን ብሎ መለሰለት! የኛን ምርጫ-መሳይ ምን ብለን፣ አንዴት ብለን እናሹፍበት? ያውም ማሾፍ ከተፈቀደ! በባህላችን በጣም የተወደደ ምግብ አለ፤ ያንን ምግብ አቅርበው መሣሪያው ሲነፍጉ ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን መንሣት ይባላል፤ ንፉግነት ብቻ አይመስለኝም፤ ክፋትም አለበት፤ የደርግና የወያኔ ምርጫ-መሳዮች በአለማወቅና በንፉግነታቸው ይመሳሰላሉ፤ በክፋት ግን አይመሳሰሉም፡፡
ደርግም ሆነ ወያኔ ከሌኒን ለመማር አልቻሉም እንጂ አስመስለዋል፤ ምርጫ-መሳዩንም ያገኙት ከዚያው ነው፤ ሌኒን ጉሮሮን ግጥም አድርጎ በብረት ሰንሰለት አስሮ ነጻ ነህ ይላል! መገንጠል ትችላለህ! ይላል፤ ወያኔም ሲሉ ሰምቶ መገንጠል-መሳይ ሕግ-መሳይ አወጣ!
ችግር ነው ጌትነት! ዱሮ ተረት ነበር፤ ዛሬ ግን በእውነት ሲቸግር እያየን ይመስለኛል፤ አንድ ሰው ራሱ ባፈራው ሀብትና በደረሰበት የጌትነት ደረጃ ችግር አይሰማውም፤ ሀብቱ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት እንደመጣ፣ ምን ያህል ልፋት እንዳስከተለ መገመት ይቻላል፤ በተዘረፈ ሀብት ጌትነት ሲመጣ ግን ችግርን አዝሎ ነው፤ አንድ ሰው አራት ሚልዮን ብር ወድቆ ቢያገኝ አራት መቶ ካሬ ሜትር መሬት ቢገዛበት አያስደንቅም፤ የገንዘብ አያያዝን ስለማያውቅና በስጋት ስለሚከሳ መሬቱ ላይ መቀመጥ አስተማማኝ መስሎ ይታየዋል፤ ከካስትሮ በፊት የነበረውን የኪዩባ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን የሚያውቅ በዛሬው ጊዜ በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነቱን ለመረዳት አያዳግትም፤ በኪዩባም ሆነ በኢትዮጵያ በተዘረፈ ሀብት ጌትነትን ያስፋፋው አሜሪካ ነው፤ ሕዝብ የሚደኸየውና የሚከብረው በጉልበትና በዝርፊያ ብቻ በሆነበት አገር ጊዜውን ጠብቆ ከሁለት አንዱን አርግዞ ይወልዳል፤ ወይ ዘራፊዎችን ሁሉ ዘርፎ ሙልጭ የሚያወጣቸው ጉልበተኛ ይመጣል፤ ወይ በሕጋዊ መንገድ ከዘራፊዎች እየገፈፈ ሀብትን ለሕዝብ የሚያደላድል ሕጋዊ ሥርዓት ይመሠረታል፤ ሁለቱንም በማስረገዝ ላይ ያሉት በግፍ ሀብታም የሚሆኑት ናቸው፡፡
ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ምርጫ መሳይ አለ፤ ሕዝብ የሀብት ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ግን ትንሽ ያስቸግራል፤ በኮንዶሚንየም ለማስመሰል ቢሞከርም አልሆነም፤ ለሎሌዎች ሹሞችም አልተዳረሰም!
በምርጫ መሳዩ ማሸነፍ ቀላል ነው፤ እንዲያውም መቶ በመቶ ማሸነፍ ይቻላል፤ ችግሩ የሚመጣው ከዚያ በኋላ ነው፤ ደካሞች የፖሊቲካ ቡድኖችንና ደካማውን ሕዝብ ማሸነፍ እንደሚቻል ጉልበተኛው አስመስክሯል፤ ሌላው ቀርቶ ‹‹የኔ›› የሚላቸውን ቡድኖችም አፈር ላይ ሊያስተኛቸው ይችላል፤ እንዲያውም አፈሩ ምቹ ፍራሽ ነው ብለው በደስታ እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው ይችላል፤ አሁን የጉልበተኛው መድረክ እየጠበበ መጣ፤ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ የጠበበው መድረክ ውስጥ ባሉት ጉልበተኞችና ጉልበተኛ መሳዮች ነው፤ በአንድ በኩል በጉልበተኞች መሀከል፣ በሌላ በኩል በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፤ በሌላ በኩል በጉልበተኞችና በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፣ ይህ ትግል ዳካማዎች የፖሊቲካ ቡድኖችን እንደማሸነፍ ቀላል አይደለም፤ በአጥር ላይ እየተንጠለጠሉ የጣሉትን ለመልቀም እየተሻሙ ነው፤ በጉልበተኞቹ መሀከል ክፉ የሥልጣን ችጋር ገብቷል ማለት ነው፤ ጦር መማዘዝ ኪስን እንደሚያራቁት ያውቃሉ፤ ያለሥልጣን ኪስ ሙሉ እንደማይሆንም ያውቃሉ፤ ታዲያ ምን ይሻላል?

Ethiopian in Germany protest in munich against hailemariam Desalegn at the G7 summit.

በጀርመን እየተካሄደ ባለው የ ቡድን ሰባት G7 ሃያላን ሃገሮች ስብሰባን ከሚቃወሙት ከ 30,000 በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞች ጎን ኢትዮጵያውያንም መንግስታቸውን ተቃውመዋል።የተለያዩ ሃገራት ሚዲያዎች ሳይቀሩ እንደዘገቡት ኢትዮጵያውያኑ በሙኒክ ጀርመን በተደረገው ሰልፍ ከፊት ለፊት በመገኘት የወያኔን ስርኣት አጋልጠዋል።የታሰሩ ይፈቱ ፥የመሬት ቅርምቱ ይወገድ፥ የጂ7 መንግስታት ለ ኢትዮጵያ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ ኣሳስበዋል።

ከጁን 4 የተጀመረውን ይሄን ደማቅ አለም ኣቀፋዊ ተቃውሞ ሰልፍ ሌሎቹም የ ኒውክለር፥የ አለም ሙቀት መጨመርን የሚመለከቱ መልዕክቶች ላንድ ሳምንት ያህል እያሰሙ ይገኛሉ።

G7 111391503_647503408715565_8979004781643535858_n

11403349_647503348715571_3198543849543016173_n

Mehr als 30.000 Menschen demonstrieren gegen G7-Gipfel

Mit einer Großveranstaltung haben Gegner des G7-Gipfels in Elmau ihre Proteste gegen das Treffen der sieben wichtigen Industrienationen eingeläutet. In München gingen nach Polizeiangaben 34.000 Menschen auf die Straße.
Demonstranten auf dem Münchner Stachus (Foto: AFP/Getty Images)
Die Demonstranten zogen nach der Auftaktkundgebung unter dem Motto “TTIP stoppen – Klima retten – Armut bekämpfen” durch die Münchner Innenstadt. Zu Zwischenfällen kam es bislang nicht. Rund 3000 Polizisten sind im Einsatz.
An dem Protestzug, zu dem diverse Parteien und Nichtregierungsorganisationen aufgerufen hatten, nahmen auch Politiker von Linkspartei und Grünen teil. Zu schaffen
machte den Demonstranten nach Angaben der Polizei die große Hitze. Viele Teilnehmer hätten Kreislaufprobleme gehabt.
Auf Plakaten und Transparenten im Demonstrationszug hieß es etwa “Yes we can – Stopp TTIP!” und “Jedes Kind, das an Hunger stirbt, wurde ermordet”. Am Hauptbahnhof entrollten Demonstranten ein großes Plakat mit der Aufschrift: “G7-Gipfel blockieren!”

ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት

የኢትዮጵያ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን የጭካኔ እርምጃ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የታሰረው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት፡፡ ዛሬ 25/2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውንያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩን ገልጾአል፡፡

natinael

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንጋይ በመወርወር ሰልፉን አውካችኋል›› የተባሉ ሌሎች አምስት ወጣቶች ለሰኔ 4 የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ተቀጥረዋል፡፡ በሰልፉ ሰበብ ተይዘው የታሰሩት ወጣቶች በቤተሰብ እንዳይጠየቁ መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡