ሄሊኮፕተራችንስ መቸ ነው የምትመለሰው ??


hilikofeter
(አሌክስ አብርሃም)

ባለፈው ግምቱ ከ30 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ የኢትዮጲያን የጦር ሄሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ ገቡ የተባሉት ‹‹ከሃዲው››አብራሪና ረዳት አብራሪዎች …. ከብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት እና ከፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብር ሀይል ‹‹የተሰጣቸውን ተልእኮ›› ሲጨርሱ በሱዳን በኩል ወደአገራቸው እንደሚመለሱ ተስፋ አለኝ፡) አብራሪዎቹ ባይችሉ እንኳን ሄሊኮፕተሯን በፒካፕ መኪና በሱዳን በኩል ይላኩልን፡)

እንበልና ሄሊኮፕተራችን ስትመለስ ኢቢሲ ምናይነት ዜና ሊሰራ እንደሚችል እንጠርጥር እንዴ …
‹‹ የብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት እና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብር ሀይል ስለላውን በምድር እንዲሁም በአየር ለማቀላጠፍ ሆነ ብሎ ወደኤርትራ የላካት ሄሊኮፕተር ተልእኮዋን በመፈፀም በሱዳን በኩል ወደአገሯ በሰላም ገብታለች …በአሁኑ ሰዓት ኤርትራ የቀሩት …ሲሄዱ ‹‹ከሃዲ›› የሚል የሽፋን ስም የተሰጣቸው ዋና አብራሪውና አንዳንድ ረዳት ፓይለቶች ብቻ ናቸው››፡)

የቀልዱ ቀልድ ነው ….ወደቁም ነገሩ ስንመለስ ጥያቄም አለኝ … ይሄ ለኢትዮጲያ ሲሰልል ነበር የተባለው ደሚህት የተባለው ድርጅት በኢትዮጲያ አንዳንድ አካባቢዎች ጥቃት እያደረሰ ኢትዮጲያዊያ ውስጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ ሲባል ከዚህ በፊት ሰምተናል …ታዲያ በራሳችን ‹‹ሰላዮች›› ለደረሰብን ጉዳት ካሳ የሚከፍለን ማነው ….ከምር ፖለቲካ እንዲህ እቃቃ መሆኗ ይገርማል!!

ለማንኛውም መንግስታችን አቶ ሞላ እንደገና ‹‹የኢትዮጲያ ተልእኮውን›› ጨርሶ ወደኤርትራ እንዳይመለስ ጥንቃቄ እንዲያደርግልን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንጠይቃለን !! (የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ገፀ ባህሪ ስእላይ በርሄን ማስታወሱም ደግ ነው !!) እንግዲህ ጀግኖቻችንን እንቀበላቸው ዘንድ መስቀል አደባባይ ሰልፍ ብንጠራና ተሰልፈው ቢያልፉ በዛውም ከ‹‹ስምንት መቶ ጀግኖቻችን›› ምንም አለመጉደሉን በህዝብ አይን ቆጥረን ብናረጋግጥ ‹‹ህዝብን አስፈቅዶ ለሚወሰደው እርምጃ ›› ፈቃድ ለመስጠት ያመቸናል፡)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s