Archive | December 2015

ዮናታን ረጋሳ ታሰረ

የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረውና ብዙ ጓደኞቹ እንደሚስማሙበት እጅግ ታታሪ የመብት ተሟጋች እና ፖለቲከኛ ዮናታን ረጋሳ በወያኔ ደህንነቶች ታፍኖ በታዋቂው የማእከላዊ እስር ቤት እንደሚገኝ ታውቋል። ቀደም ሲል ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችም በተመሳሳይ መታፈናቸው ይታወሳል።Yonatan Regassa of Blue party

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባን በማስፋት ስም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎችን መሬት ለመቀራመት ሲሰናዳ በተቀሰቀሰበት ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ በመደናገጥ ከመቶ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎችን ደግሞ በየማጎሪያ ካምፖቹ በማሰር ላይ ይገኛል።

የወያኔው አገዛዝ ሰሞኑን የአፈና ድርጊቱን አጠናክሮ በመቀጠል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮችንም ከያሉበት እንዲታፈኑ አድርጓል።

ወትሮውንም ጋዜጠኞችን እንደ ጦር የሚፈራው ወያኔ የነገረኢትዮጵያ ሪፖርተር ጌታቸው ሽፈራውንና ሌሎች ጋዜጠኞችንም በማሰር እና በማባረር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ወያኔ ከአስር ዓመት በፊት ምርጫ 1997ን ተከትሎ ተነስቶበት የነበረውን ህዝባዊ እምቢኝነት ለማዳፈን ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።

ይህ በዚህ እንዳል በኦሮምያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጨርሶ እንዳልበረደ የሚያሳዩ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ። ወያኔም በበኩሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ለማፈን ኦሮምኛም ሆነ አማርኛ ቋንቋን የማይናገሩ ገዳይ ወታደሮቹን ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ግድያና አፈናውን ተያይዞት ይገኛል።

ጨለማን ተገን አድርጎ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን በመቋረጥና ሂሊኮፕተሮችን በመጠቀም በድንገት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ የዘረገፋቸው ገዳይ ወታደሮቹ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል፣ ይህ ድርጊት እራሱን መንግስት እያለ የሚጠራው የወያኔ ቡድን እውነተኛ ማንነቱን የሚያሳይ ነው።

ሁኔታዎች ሁሉ እንደሚያመላክቱት ወያኔ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራ ቡድን ነው!

Advertisements

Ethiopia should “allow journalists to do their jobs” — Africa Times Editorial

Two journalists have been arrested by the government in Ethiopia as deadly demonstrations continue in the Oromia region. The Committee to Protect Journalists (CPJ), an independent nonprofit organization promoting press freedoms, on Sunday released a statement calling “on authorities in Ethiopia to release the editor-in-chief of Negere Ethiopia online newspaper, Getachew Shiferaw, who was arrested on Friday”.

The Federal Police arrested Getachew Shiferaw.

Shiferaw’s arrest on Christmas day comes after the arrest of Fikadu Mirkana, a news anchor for the state-run Oromia Radio and TV broadcaster. Mirkana was taken into custody from his home in Addis Ababa on December 19.

Sue Valentine, CPJ’s Africa Program Coordinator, said, “Ethiopia prides itself on development, but economic growth is a hollow achievement if the public does not enjoy fundamental human rights such as the right to receive and share information and divergent viewpoints.

“Authorities should immediately release Getachew Shiferaw, drop all charges against him, and allow journalists to do their jobs.”

After police were given permission to hold Shiferaw for 28 days when he appeared in court on Saturday, reports have suggested that he is likely to be charged under Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation. Police suspect the journalist of inciting violence by using social media as well as recruiting for the opposition party, Genbot 7, reported the online publication Negere Ethiopia.

Ethiopia’s 2009 anti-terrorism law has come under much international criticism as it is seen to prevent the freedom of the press. It criminalises any who are considered by the government to provide “expertise or moral support” for a terrorist act or organisation. Many have suggested that the proclamation enables the government to “criminalize independent political coverage and infringe on press freedom as guaranteed by the Ethiopian Constitution.”

The government, on December 24, has also ordered five members of the Zone 9 blog to appear in court on December 30 after they were acquitted of terrorism charges back in October. Soleyana, one of the five bloggers, told CPJ that the prosecution is appealing their acquittal.

In the midst of criticisms over the lack of press freedoms in the country the government continues to crack down on protestors.

The protests started when students began resisting the government’s idea to expand the capital’s administrative control into the Oromia region. The region spans across the country and houses a third of the Ethiopian population. Whilst to begin with the protests were sparked by students they have been joined by farmers and other residents from the area.  At least 87 protesters have been killed thus far however accounts of how many have died vary.

The ruling party which has been in power since 1991 has been accused of suppressing dissent in the past. “Authorities use arbitrary arrests and politically motivated prosecutions to silence journalists, bloggers, protesters, and perceived supporters of opposition political parties,” Human Rights Watch reported.

TPLF’s tribalism policy is unfolding in front of our eyes

Showing Solidarity is the answer!

by Ewnetu Sime

The Tigray People Liberation Front’s (TPLF) master plan that was designed without people participation has faced strong opposition in Oromia region. For past several weeks, the vast majority Oromo students have displayed peaceful legitimate defiance to the plan. The TPLF’s agaize troops and local riot police reacted with full force. They opened fire on peaceful protestors committing killing, in discriminate beating, torturing and arresting in attempt to crash the protest. Despite to this horrific situation a series of anti-TPLF rallies has continued in several places. Calling to disban the master plan implementation, to stop the ongoing land grab policy immediately, a transition to democracy and end to tyrannical single tribal rule are some of their demand. The regime brutality response to unarmed protestors shall be condemned by all freedom loving people.Ethiopians united

Regrettably, during this time some elements of diaspora community are occupied in different mission. As seen on social media they are busy in injecting anti Ethiopia unity rhetoric to misguide the protestor’s goals. The participants of this on line activities, they claim to be from “Oromo origin”. They have been engaging in one ethnocentric sentiment spreading hatred to other ethnic group rather supporting the current protest in a solidarity sprit. Are they the regime agents working hard to break the momentum of the protest or bunch of hardliner fanatics advocating ethnic ideology as answer for Ethiopia political problem? Are they using this opportunities to reap the benefits from student protest? If their messages are unchecked, it is a threat for solidarity and freedom of Ethiopian people. The peaceful majority cannot afford to sit back and let it happen. Who can forget the crime committed by TPLF’s ethnic policy in displacement of several people due to their ethnic origin from several places in the past 24 years? We must pay attention to these very few fanatic people that are systematically poising the current protest in the name of ethnic rights. We should not allow their intention to expand. The responsible free media and Ethiopian elites should continue providing clear views on ethnic rights and Ethiopia nationalism.

At this critical time any attempt to exploit the current defiance by hard liner of tribal proponent to rise to power must be rejected. Regardless our ethnic origin we should align with the protestors and show our outrage on the going brutalities. The focus must be to bring an end to ethnic based ruling regime from power. No one wants to see a repeat of the TPLF’s regime ethnic policy by its successor. The tribal elite campaign on line could pose trouble as they become an instrument of hate to other ethnic groups. Even more intriguing as they are attempting to rewrite the Ethiopian history, censuring Ethiopian flag on protest sites, exchange slurs etc…Ethiopian flag is a symbol of freedom, hope and unity to all Ethiopian people. It is a pride and honor to have a national flag. If the hardliner grip to the state power, they may be more ruthless than TPLF regime. They will be accomplices of TPLF’s tribal policy. Their deconstruction approach to divide Ethiopia must be exposed and condemned.

It is clear that these Oromo hardliner don’t speak for the majority. The majority is looking for genuine democracy, liberty and social justice for all. We should fight for interest of the oppressed mass of Ethiopia people. Tribalism should have no place in the country. Many of us we are dismayed and appalled as we see the ethnic rights principle is used as camouflage to distort the current protest. Oromo people are oppressed like the rest of ethnic groups with tyranny rule.

The TPLF troops are cracking down and committing mercilessly killing of young boys, girls, and peaceful by standers. It is a desperate attempt to brutally crash the protest and same time terrorize the public at large. This action is similar to the red terror dark period of Ethiopia history. At this horrific situation, it is important for us to stand together with the protestors.

It is no brainer encouraging narrow ethnic politics will further cements TPLF grip in power. Ethnic based extreme ideology brings nothing and will have no positive impact for the society peace and progress. Addis Ababa University students and the recent protest at Washington, D.C. area have demonstrated solidarity and should be encourage and joined by all freedom loving people. It is a fact that the opposition parties at home are prevented to have solidarity rally with protestors. TPLF’S policy has being played out the ethnic division rule the past 25 years. That is enough experience. Let speak out with one voice against divide and rule TPLF’S policy.

It is unfortunate to see TPLF’S tribalism policy ruining our beloved motherland. Unless it is countered by pro-democratic forces, it is bound to more tragic event. What we wish to see is all inclusive voice and then to turn around the defiance to lead it to de facto freedom. We should not only support the protest but also agitate for freedom, equality, and unity among Ethiopian people. The on line media should be used to galvanize the aspiration and interest of Ethiopian public opinion. We must learn from TPLF failed policy to prevent the rise of another version TPLF rule.

For years Ethiopia has crushed anyone who opposes its development plan. Now an ethnic uprising threatens to crash the country’s high-flying economy.

Revolt in an African Stasi State

by Jeffrey Smith, Mohammed Ademo

Ethiopia is hailed as one of the fastest-growing economies in the world. For the last decade, the East African nation has averaged around 10 percent annual GDP growth, far outpacing most of its neighbors on the continent. It recently launched a new light-rail system in the capital of Addis Ababa, the first of its kind in Africa, and the government is aggressively pushing several Chinese-funded hydroelectric and infrastructure projects to reduce agricultural dependence and accelerate manufacturing growth. Many experts — including those at the African Development Bank — expect the country’s upward trajectory to continue in 2016.

But despite the outward veneer of progress, all is not well in Africa’s second-most populous nation. Weeks of student protests have roiled the Oromia region, which is home to the Oromo, the country’s largest ethnic group and among its most marginalized. More than 80 people have been killed in a violent crackdown by security forces, according to opposition parties. Coupled with a devastating drought that will leave an estimated 20.3 million people in need of urgent assistance by January of next year, the mounting public discontent in Oromia offers the latest warning signal that the same top-down social and economic model that has powered Ethiopia’s rise could ultimately bring it crashing down.

Unlike most of its economic peers on the continent, Ethiopia follows a stringent growth model known as the “developmental state.” This model borrows heavily from the so-called Asian Tigers, whose state intervention in macroeconomic planning led to impressive economic growth in East Asia in the 1970s. Ethiopia’s late Prime Minister Meles Zenawi, the chief architect of the “developmental state” and the driving force behind its initial implementation, defended the decision to ditch the neoliberal paradigm in 2007: “[D]eveloping countries face formidable market failures and institutional inadequacies which create vicious circles and poverty traps, which can adequately be addressed only by an activist state,” he wrote.

But under Meles, the “activist state” became a euphemism for state repression — albeit under the guise of development. The ongoing protests in Oromia reflect growing public dissatisfaction with this experiment, as well as outrage over the routine and callous brutality demonstrated by the country’s security forces.

Until recently, many international observers — no doubt influenced by effective Ethiopian propaganda — assumed that the country’s development strategy was working just fine. As a result, donor countries eager for an aid success story — most notably, the United States — have largely ignored mounting concerns about the narrowing of democratic space and the unequal distribution of growth benefits. But such illusions have been shattered over the past month as the public protests in Oromia have burgeoned, creating the most significant challenge to the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) since it came to power in 1991.

Oromia is the largest of Ethiopia’s nine ethnolinguistic-based states, and it is no stranger to state-driven violence. The Oromo, who represent around 40 percent of the country’s 100 million people, have long suffered the brunt of the central government’s repression. The Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF), the kingmaker in the loose EPRDF coalition, dominates the central government. TPLF leaders and their coterie control key government institutions, the military, and much of the economy, a fact deeply resented by the Oromo and other oppressed groups throughout the country.

In theory, Ethiopia is a federation based on decentralized ethno-national representation. But the EPRDF’s top-down approach to development — and its refusal to fully implement the ethno-federalist system laid out in its constitution — has contributed to the growing estrangement of a number of minority groups from the capital. The Oromo experience is a case in point: Time and again, Addis Ababa has responded to the group’s calls for greater autonomy with disinterest and, at times, brute force.

Oromo protests have become something of a ritual over the past decade, as have the government’s heavy-handed responses to them. In April and May of last year, for instance, security forces fired live ammunition at protesters in order to suppress a popular uprising against government encroachment on Oromo lands. Activists estimate that there are at least 20,000 Oromo political prisoners in Ethiopia today, meaning that roughly one out of every 1,400 Oromo nationals is currently in jail. According to Amnesty International, at least 5,000 Oromos were arrested solely based on their actual or suspected opposition to the government between 2011 and 2014.

Unsurprisingly, EPRDF leaders in Addis Ababa have blamed the latest unrest in Oromia on what they deem anti-development forces. (Communications Minister Getachew Reda went as far as to refer to protesters as “demonic” and “terrorists.”) This refrain has been employed often to violate constitutionally protected civil liberties and justify the use of disproportionate force against perceived domestic opponents. On Dec. 17, Prime Minister Hailemariam Desalegn signaled his intention to continue the crackdown on demonstrators, threatening to use “merciless action” to disperse future crowds.

The current round of Oromo protests began on Nov. 12, when local students in Ginchi, a rural area 50 miles west of the capital, took to the streets to oppose a draft “master plan,” introduced by the central government, which aims to expand its administrative control over Oromia. Since then, the demands of the protesters have expanded to include calls for self-rule, more equitable development, and respect for the country’s ethnic-based federalist system, which in theory preserves the autonomy of regions like Oromia.

In essence, the protests have evolved into a full-scale revolt against Ethiopia’s highly centralized one-party state, which has closed off political space to the opposition, to religious groups, and to civil society. Not even individual households can escape the prying eyes of state authorities. In Oromia and a number of other regions, the government enforces a special hierarchical system of party informants, known as gott and garee, to monitor the everyday activities of Ethiopian citizens. This deeply ingrained spy network consists of one government informant for every five citizens.

Draconian national security laws have also become a cornerstone of the EPRDF’s efforts to keep citizens in check. For example, the 2009 Anti-Terrorism Proclamation includes overly vague language on the government’s powers of arrest, search, and seizure; allows courts to consider evidence obtained under torture; and enables authorities to detain citizens without charge for up to four months. Another key feature of this law defines terrorism as simply intending to “influence the government.”

Despite this track record of oppression, Ethiopia remains a veritable darling of the West. Nowhere is this more evident than in Washington, D.C., where Ethiopian autocrats have long been lauded, praised, eulogized, and rewarded with billions of dollars in foreign and development aid — of which less than 1 percent is currently allocated for human rights and democracy-related programming.

The capstone to Washington’s love fest with the EPRDF regime came in July, when President Barack Obama became the first sitting U.S. president to visit Ethiopia. While there, Obama twice referred to the one-party government as “democratically elected,” a darkly comedic remark that came barely two months after the EPRDF claimed all 547 parliamentary seats in a national election.

The United States does occasionally raise human rights concerns and acknowledge the shrinking democratic space in Ethiopia. In a Dec. 18 statement responding to the latest crackdown in Oromia, for instance, the State Department called for “dialogue” while expressing “condolences to the families of those who have lost their lives.” But given Washington’s preoccupation with Islamic terrorism in the Horn of Africa, and its view that Ethiopia is a stable bulwark against extremism, it has routinely stopped short of condemnation. Leaders in Washington have also declined to apply any meaningful pressure on the regime to reform, conveniently forgetting that it has half a billion dollars in annual aid to use as potential leverage.

It is clear that the majority of Oromo people, like most other oppressed groups in Ethiopia, are fed up with the EPRDF’s growing repression and its highly intrusive model of governance. Young people, especially, lack avenues to air their grievances, not to mention the basic democratic rights with which to demand a genuine platform to be heard. Instead of addressing their valid interests and concerns, Ethiopian authorities continue to respond with violence after their attempts to indoctrinate the youth fall short.

This cycle of violence will continue to tear at the fabric of Ethiopian society until the EPRDF regime allows genuine federalism to take root, thereby opening up the political environment and involving all of the country’s shareholders in the development process. The ongoing heavy-handed response to widespread discontent has already engendered a heightened ethnic self-awareness among Ethiopians and has contributed to a resurgent Oromo nationalism that is just now beginning to flex its collective muscle. Addressing the widening democratic deficit, as well as the country’s long-simmering ethnic grievances, remains the only sure way to safeguard Ethiopia’s stability and to sustain its recent economic trajectory.

Source: Foreign Policy

ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች ተቀጣጥሎ ይገኛል

ከኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም ትናንትና ዛሬ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል ::

ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት አሳፍሪ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሴት ተማሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:፡

Ambo

 

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/11448#sthash.cZTsi4kX.dpuf

ኢትዮጵያ የማን ናት? (ከአንተነህ መርዕድ)

ከአንተነህ መርዕድ

“ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው” ( ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ)
“ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም” (ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ)

ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት የብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የልብ ህመም ሆኖ የቆየው የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ዛሬም በኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ጥያቄ ቢኖር የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሆነ በጨለማ ለመግዛት የተነሱት ጣልያንም ሆነ ወያኔ ለአላማቸው ማስፈፀምያ የዚህን ታላቅ ህዝብ ጥያቄ ነበር ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚጠቀሙበት። ከላይ በጥቅስ ያስቀመጥኋቸውን ሃሳቦች የተናገሩት በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ ትፅዕኖ ፈጣሪና ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከአስራ አራት ዓመት በፊት በሞት የተለዩን ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳን ንግድ ማተምያ ቤት አጠገብ ባለው መኖርያ ቤታቸው ለጦቢያ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ልናደርግላቸው አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ጋር ሄደን ነበር። ሜጫና ቱሉማን በመመስረትና ለኦሮሞ መብት በመታገል ኢትዮጵያዊ መፍትሄ እንዲያግኝ በመልፋት የሚታወቁት እኒህ አንጋፋ አባት አመሻሽ እድሜአቸው ላይ ሆነው ያዩት ሁሉ አላስደሰታቸውም።ethiopia

አክራሪ ፅንፍ የያዙ የኦሮሞ ኤሊቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን መለየትን እንደመፍትሄ በግልፅ በሚሰብኩበትና ለተግባራዊነቱ በሚገፉበት፤ ወያኔም ይህንኑ አጀንዳ አስጨብጦ በሚያራግብበት ፈታኝ ወቅት ነበር የሄድንባቸው። አምቦ አካባቢ ግንደበረት ተወልዶ ከማደጉም በላይ የኦሮሞን ህብረተሰብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጋሽ ሙሉጌታ ከኮሎኔሉ ጋር ያላቸውን መግባባትና መከባበር ስመለከት ተገርሜያለሁ። በርካታ አገራዊና የግል ጥያቄዎችን ያቀረብንላቸው ቢሆንም በቁጣ ስሜት የመለሱት ለኦሮሞ ችግር ከኢትዮጵያ መገንጠል መፍትሄ ይሆናልን? የሚለውን ጥያቄአችንን ነበር። “ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው?” በማለት ነበር ጥያቄአችንን በጥያቄ የመለሱት።

ኦሮሞ የኢትዮጵያ እምብርት ብቻ ሳይሆን ከሰሜን ጫፍ እስከ ትግራይ፣ በደቡብ እስከ ኬንያ፤ በምስራቅ ኦጋዴንን ነክቶ በምዕራብ ሱዳን ድረስ ሲያጣቅስ በመሃል ከአብዣኛው ኢትዮጵያውያን ተዛንቆ፣ ተዋልዶ፣ ተዋህዶ በመኖሩ እድሉ የኢትዮጵያ ባለቤት መሆን እንጅ ጊዜው እንደወለዳቸው ፖለቲከኞች ቁራሽ መሬት ይዞ መወሰን አይደለም የህዝቡ ፍላጎት። ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳም የገለፁት ይህንኑ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ነበር። ቃለ መጠይቁን ለህትመት አብቅተን ኮሎኔል ዓለሙን ደግመን ስናገኛቸው ያየሁትና የሰማሁት ለብዙ ጊዜ አሳዝኖኛል። የጊዜው የፖለቲካ አራጋቢዎች ትልቅ የመንፈስ ስብራት ፈጥረውባቸው ነበር። “ዛሬ በሽምግልናዬ ቤት ውስጥ ተወስኜ ሞቴን በጸጋ በምጠብቅበት ሰዓት የአገር ጉዳይ ጠልቆ ያልገባቸው ወንድሞቼ በእኔና በቤተሰቤ ያሳደሩብኝ ጫና ቀላል አይደለም። ቀሪ ጊዜዬን በሃዘን እንዳልቋጨው ታገሱኝ” አሉን። እኛም ታገስናቸው።

ዛሬ ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳና አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት የሉም። ጋሽ ሙሉጌታ ሊለየን ትንሽ ሰዓታት ሲቀረው “ለዘመናት ወጣቱ ላይ የነበረኝን ወቀሳ አንስቻለሁ፤ አገሩን የሚታደግ ወጣት በማየቴ ኮርቻለሁ። በሉ ተነሱ ሰልፍ የጀግና ነው፣ ድል የእግዜብሄር ነው” ሲል ተስፋውንና ጥሪውን ገልፆ አልፏል። የኦሮሞ ህዝብና ቀሪው ኢትዮጵያዊ ባንድ ቁሞ ታላቋን ኢትዮጵያን የመገንባቱ ተስፋ እየለመለመ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ባለቤት ለመሆን አገራዊ አጀንዳ ይዞ እየተነሳ ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ኤሊቶች) እንደ ኦሮሞ ህዝብ ሰፊ ልቦናና ኢትዮጵያዊ ባለቤትነትን ካላቀፉ ለጠባቡና ለጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ ራሳቸውን ወስነው መነሳት እንደማያዋጣቸው የተረዱ ይመስላል። ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ሌንጮ ለታና ጓዶቻቸው፣ ከወጣቶቹም ጁአር ሞሃመድና ሌሎችም ሰሞኑን ያሳዩት ሁሉን አቃፊ (አኮሞዳቲቭ) አቋም ያየ፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሞን ህብረተሰብ በሚመጥን ደረጃ ለመገኘት መንቀሳቀሳቸውን ወይንም መፈለጋቸውን ይገነዘባል። ያድርግልን። ከሰሞኑ የህዝብ አመፅ በኋላ የአማራውና የኦሮሞው አንድነት ጥሪ በሰፊው ተሰብኳል። አመፁን ተከትሎ የመጣ በረከት ይመስላል (ፈረንጆች ኤ ብሌሲንግ ኢን ዲስጋይዝ እንደሚሉት)። አመፁን ወደ እውነተኛ አንድነት እንዲያድግ ከተፈለገ አጀንዳው ከክልላዊነት ወጥቶ ወደ አገራዊነት መለወጥ አለበት።

ለኢትዮጵያ ህልውናና እድገት የህዝቦቿ መተባበር፤ በተለይም የኦሮሞውና የአማራው በአንድነት መቆም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጠው ለመግዛት የሚያልሙ የውጭ ሆነ የውስጥ ጠላቶች እነዚህን ጉልህ የህዝብ ክፍሎችን የጥቃታቸው ኢላማ የሚያደርጉት። አድዋ ላይ አባቶቻችን ያንበረከኳትና በዓለም ፊት ያዋረዷት ጣልያን የሽንፈቷ ምክንያት የኢትዮጵያውያን ህብረት መሆኑን ከውድቀቷ ተምራለች። ከአርባ ዓመት በኋላ ቂም ቋጥራ ዳግም ስትመጣ፤ መጀመርያ የተሰማራችው ተባብረው የደቆሷትን አማራና ኦሮሞን በመለያየት ላይ ነው። ብዙ ክፍተት ለጊዜው ብትፈጥርም እንዳልተሳካላት ሌላውን የኦሮሞ የጀግንነት ምሳሌ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ታሪክእንቃኝ። የበጋው መብረቅ የሚባሉት የጀግናው የጄኔራል ጀጋማ ኬሎ አጎት ናቸው። ፊታውራሪ አባዶዮ ዋሚ ገሮ ይባላሉ። አባ ዶዮ የፈረስ ስማቸው ነው። ጣልያን አማራንና ኦሮሞን ለመከፋፈል በሰፊው ሠርቶ ስለነበር፤ ይህ ሰበካ እውነት የመሰላቸው ታላላቅ ሰዎች የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮን ምክርና ይሁንታ ለመሻት ቤታቸው ሄዱ። “አማራ የሚበድለን ስለሆነ ከአካባቢያችን ልናስወጣ አስበናል ምን ይመክሩናል?” የሚል ሃሳብ አቀረቡላቸው። እንግዶቻቸውን አብልተው አጠጥተው፣ በነገሩም አሰላስለው ቆዩና ለእያንዳንዳቸው እፍኝ እፍኝ ሙሉ ሰርገኛ ጤፍ እንዲሰጣቸው አዘዙ። ጤፉም ለእንግዶቹ ተሰጠ። “በሉ ቀዩን ከነጩ ጤፍ ለዩልኝ” አሏቸው። ግራ የተጋቡት እንግዶች “አባ ዶዮ ይሄማ እንዴት ይቻላል?” በማለት እንደማይሆን ነገሯቸው። “ያቀረባችሁልኝ እኮ እንዲህ ያለ ጥያቄ ነው። ከአማራ ያልተጋባ፣ ያልወለደ፣ ያልተዛመደ ማን አለ? እንዝመት ካላችሁ በራሳችን፣ በቤታችን እንጀምር። ይህንን ደግሳ ያበላቻችሁ የልጆቼ እናት አማራ ናት። ልጆቼንና ልጆቿንም፣ እሷንም ጭምር ግደሉ፤ እናንተም በየቤታችሁም ሂዱና የአማራ ደም ያለበትን አጥፉ። ይህ እንዲሆን አይደል የምትጠይቁኝ” አሏቸው። በርግጥም ከአማራ ያልተዛነቀ ኦሮሞ፤ ከኦሮሞ ያልተዋለደ አማራ ጥቂት ነው። ጥፋታቸውን የተረዱት መልዕክተኞች የጣልያንን ተልዕኮ አከሸፉ። በነገራችን ላይ ዶክተር መረራ ጉዲናም አንዳንድ ፅንፈኛ የሆኑትን ፀረ አማራ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃንን “ማታ ቤታቸው አማራ ሚስቶቻቸውን ታቅፈው እያደሩ ቀን ስለእነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መለያየት ይሰብካሉ” ሲሉ ከሃያ ዓመት በፊት መተቸታቸውን አስታውሳልሁ።

ታሪኩ በዚህ አያበቃም። የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮ ወንድም የአባ ኬሎ ገሮ ልጅ ጀጋማ ኪሎ ጣልያንን ገና በአስራ አራት አመታቸው ጀምሮ ነው በጥይት እየቆሉ መውጫ መግቢያ አሳጥተው ነፃነታችንን ያጎናጸፉን። የጣልያንን ሴራ ብቻ ሳይሆን ሰላቶን ከነባንዳው አይቀጡ ቅጣት የቀጡት ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ ከአምሳ አምስት ዓመት በኋላ የባንዳ ልጆች የሆኑ የወያኔ መሪዎች በአማራውና በኦሮሞው ልዩነት ፈጥረው ለማፋጀት ሲነሱ አጎታቸው ዘንድ ለምክር እንደሄዱ መልዕክተኞች የህወሃትን መርዝ ይዘው ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ሲያቀነቅኑ ልባቸው በሃዘን ተነክቷል። አዛውንቱ ፖለቲከኛ ቡልቻ ደመቅሳ “ለኦሮሞ መገንጠል ይበጀዋል ወይ?” ብለው ለጠየቋቸው “ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም” ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም ብለው እንደመለሱላቸው ሰምቻለሁ። ዛሬ ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ የ95 ዓመት አዛውንት ናቸው። የኦሮሞ አድባር፣ የኦሮሞ ዋርካ፣ የአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ዋርካ በህይወት እያሉ ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ስንት ጊዜ ተጠቃች? ስንት ጊዜ አፈር ልሳ ተነሳች?

አብዛኞቹ የህወሃት መሪዎች ለጣልያን ያደሩ የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ከገብረመድህን አርዓያ የበለጠ ምስክር አንሻም። Rኡቅ ሳንሄድ የህወሃት ሴራ ባለቤት የመለስ ዜናዊ አያት የጣልያኑ ደጃዝማች አስረስ በርካታ ህዝብ ያስፈጁ አገር የሸጡ ባንዳ መሆናቸውን ሁሉም ያውቀዋል። ታድያ እነመለስና ጓደኞቻቸው ከአባቶቻቸው የተማሩት አገርን መታደግ ሳይሆን ማፍረስ ነው። ጀግናው አፄ ዮሃንስ ከበርካታ የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋር(የትግራይን ጨምሮ) አንግታቸውን የተሰውበትን መሬት ሳይቀር ለሱዳን ሲሰጡ ሃፍረት የማያውቁ ከሃዲ ወንጀለኞች ናቸው። በመሆናቸውም ነው መሃል ኢትዮጵያን አፍኖ ለመግዛት አማራና ኦሮሞን ለመለያየት የባንዳ አባቶቻቸውን ጌቶች ፖሊሲ የተከተሉት። ይህ ተንኮል ከጣልያን የበለጠ ለእነሱ ሰርቷል። ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከሁለቱ ህዝብ ፅንፈኛ የሆኑና ለፍርፋሪ የሚያድሩትን በማግኘታቸው ዙፋናቸው ላይ እስከአሁን ተደላድለዋል።

አማራው በየሄደበት እንደ አውሬ ታድኗል። ዐይኑ እያየ ገደል ላይ ተጥሏል። ይህንን ደግሞ ሃውዜን ላይ በትግራይ ህዝብ ሲፈፅሙት የተካኑ በመሆናቸው በፊልም እየቀረፁ “ኦሮሞው አማራውን እንዲህ አድርጎ ነው የገደለው” ብለው በአደባባይ በማሳየት እስከዛሬ የሠራላቸውን የመከፋፈል ሴራ ውጤታማ አድርጎታል። ተንኮላቸው በሁለት በኩል ስለት እንዳለው ቢላዋ ባንድ በኩል ኦሮሞውን ከአማራ ለመለያየት ሲያገለግላቸው፤ ሌላኛው ስለት ኦነግን የፖለቲካ ሞት እንዲሞትላቸው ማድረጋቸውን የዚህ ተንኮል መሃንዲስ ከሆነው መለስ ዜናዊ ጋር በቅርብ የሠሩትና አጥርተው የሚያውቁት ሊንጮ ለታ ዛሬ በአዛውንት እድሜአቸውና በሰከነ አእምሮአቸው ቢመሰክሩ ደስ ይለናል። ለትናንት የፖለቲካ ዓላማ ባይጠቅምም፤ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ትምህርት ይሆነዋል።

ኦሮሞው በየቦታው ሲሰደድ፣ ሲገደልና የአገሪቱን እስር ቤቶች ሲያጨናንቅ፤ አድር ባይ ልጆቹ ወያኔ የሰጣቸውን የመቶ ዓመት ታሪክ ሲቆፍሩና ተጠያቂ ሲፈልጉ፣ ዛሬ የሚፈጸመውን ዐይን ያወጣ በደልና ግፍ እነሱም ዐይተው እንዳላዩ፣ ህዝቡም እንዳያይ ብዙ የከፋ ወንጀል ሠርተዋል። ቢዘርፉ የማይጠረቁ የወያኔ መኳንንት አዲስ አበባን ጨርሰው የአካባቢውን ገበሬ ሲያፈናቅሉ “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ጅል ተመክሮአቸው ህዝቡን አጥንቱ እስኪቀር ትንሽ ፍርፋሪ እያገኙ አስግጠውታል። ዛሬ ፅዋው ሞልቶ ሲፈስና ህዝቡ ከዳር ዳር ሲነሳ በድንገት ባነኑና የህዝብ ደጋፊ ነን ለማለት በአዳራሽ ተሰብስበው ወያኔ ላይ መፎከራቸውን ከኢሳት ሰምተናል። ልጃገረዷ አረገዘች የሚል ሃሜት ሲናፈስ “እስቲ ታገሱ፤ እህል ከሆነ ይጠፋል፣ ሽል ከሆነም ይገፋል” እንዳሉት ኦህዴዶቹ ከልባቸው ከሆነ የምናየው ነው። ጌታቸው ወያኔ ሳይቀድሙት በመቅደም አባዜ የተካነ ነውና ቀበቶአቸውን ጠበቅ ሊያደርጉ ይገባል። የስምንት ዓመት ልጅ በጥይት ከሚደፋ፣ አስከሬን ለወላጅ በሺህ ብር ከሚሸጥ፣ አገርን ቆርሶ ከሚቸበችብ አምባገነን ጋር ከመስራት የከፋ ወንጀል አለ? ርህራሄ የሌለው ህወሃት ለዚህ ድፍረታቸው በመቶ ሺዎች አሳልፈው ከሰጧቸው፣ እስር ቤት ከሚገኙ ወንድሞቻቸው ጋር ለማጎር አይሳሳም። ደርግ መኢሶንን ተጠቅሞበት ደመኛ ጠላቶቹ ከሆኑት ኢህአፓዎች ጋር በአንድ እስርቤትና በአንድ ጉድጓድ እንዳገናኛቸው ሁሉ ወያኔም ይህንኑ እንደሚያደርግ ግልፅ ነው። ኦህዴድ ሆይ! በአገሪቱ በተለይ በኦሮሞው ላይ ለተሠራው ሁሉ ወንጀል ሃላፊነቱን በግልፅ በመውሰድና ከህዝብ ጎን በመቆም ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት ካልታገላችሁ ይህ ሙት ስርዓት ይዟችሁ ይሞታል።

የኦሮሞ ህዝብ ልበ ሰፊ ነው። አስተዋይና አዋቂም ነው። ይህንን ትልቅነቱን ሰሞኑን በሚገባ አሳይቷል። በውስጡ ያሉትን አማሮችና ሌሎችንም እንዲተነኩስ ዘረኞች ቢሰብኩትም በልበ ሰፊነት ሰላማዊ ትግል እያደረጉ ልጆቹ ለሰላምና ለፍቅር ሲሉ ወድቀዋል። አምናም ዘንድሮም የወደቁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ሰማዕታት ናቸው። ለጠባብ አላማ አልወደቁም። ይልቅስ ገዳዮቻቸው ወራዳ ታሪክ ፈፅመዋል። የኦሮሞ ህዝብ በትልቅነቱ ልክ አባቶቹ በደማቸው የአቆዩአትን አገር ባለቤት ሆኖ ነፃ ሊያወጣት ከወንድሞቹ ጋር ይሰለፋል እንጂ ፖለቲከኞች በሰፉለት አርቲፊሻልና ጠባብ ዓላማ ራሱን ወደ ትንሽነት አይቀይርም። ለዚያውም የትግራይን ህዝብ የካዱ የባንዳ ልጆች መጠቀምያ አይሆንም። ለኦሮሞ ህዝብ እንኳን ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካ ትጠበዋለች። “ኢትዮጵያ የማን ሁና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው” ያሉት ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ ምንኛ ተስፋቸው በለመለመ። “ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም” ያሉት ጀግናው ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ እንደልብ መስማት ባዳገታቸው በዚህ የሽምግልና ወቅት አሁን በምልክትም ቢሆን የኦሮሞን ህዝብ እንቅስቃሴ መረዳታቸው አይቀርምና የመጨረሻ ዘመናቸው በሃዘን እንዳይቋጭ መትጋት ያስፈልገናል።

የእኛ ያልሆነን ሶሻሊዝም ለማፅደቅ የብዙ ኢትዮጵያውያን ደም ፈስሶ ስር ሳይሰድ ቀርቷል። የልዩነትና የጎሳ ፖለቲካም አፍላው ያለፈበትና የመሸበት አስተሳሰብ መሆኑን እንደሶሻሊዝሙ ብዙ ከፍለንበት ተምረናል። ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ካለንበት ጨለማ ለመውጣት በጋራ ካልተነሳን ተስፋ የለንም። በተለይም ከአማራውና ከኦሮሞው የወጡ ጽንፈኞች በህዝቡ ስም በመነገድ አምባገነኑና ዘረኛው የውያኔ አገዛዝ እድሜ እንዲኖርው ከማገዝ እንዲቆጠቡ በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል። በዘውግ ፖለቲካ ተጨፍነን እያለ፣ ለከተማ መሬት ስናዝን፣ የአግሪቱ ለም መሬት ለሱዳን እየተሰጠ ነው። በጉርሻ ስንጣላ የህልውናችን መሰረቱ ራትና ምሳችን ሊሄድ ነው። መተማ ላይ የአፄ ዮሃንስን አንገት የቀላ ሰይፍ ድንበሯን አናስነካም ያሉትን ንፁሃን በመቁረጥ ላይ ነው። ሰይፉ ከሁለት አቅጣጫ ተደቅኖብናል። ከሱዳንና ከህወሃት። ሰሞኑን የሱዳኑ መሪ አልበሽር ሰራዊታቸው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲንቀሳቀስ አዝዘዋል። በኢትዮጵያ ምንግስት በኩል ደግሞ ኃይለማርያም ደሳልኝ ኢትዮጵያውያንን ሱዳንን የሚያጠቁ ሽፍቶች ሲሉ በፓርላማው ፊት ወንጅለዋል። ይህም ይህወሃት ሰራዊት ከሱዳን ጋር ተባብሮ ዜጎቹን ለመውጋት መዘጋጀቱን ያመለክታል። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዚህ ያለ ለህልውናዋ ጠላት የሆነ መንግሥት አጋጥሟት አያውቅም።

ይህን ጽሁፍ በማጠቃለል ላይ እያለሁ ወያኔዎች በቀለ ገርባንና ሌሎችንም እያደኑ ማሰራቸውን ሰማሁ። ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እጣ መሆኑን ያላወቀ ካለ አንድም የዋህ ነው፣ ያለዚያም የስርዓቱ አገልጋይ ነው። በቀለ ገርባን የመሰለ የተረጋጋ፣ ሰላም ፈላጊና ትልቅ የዓላማ ሰው አገሪቷ እንዳይኖራት ወያኔ ተግቶ መሥራት የጀመረው አሁን አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አሰፋ ማሩን፣ ተስፋዬ ታደሰን….ገድሏል፤ የቅንጅት መሪዎችን፣ አንዱዓለም አራጌንና ሺህ የኢትዮጵያ ተስፋዎችን አስሯል። በአራቱም ማዕዘናት ወጣትና ሽማግሌ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል። አገርንና ህዝብን እንደጠላት ኢላማ አድርጎ ከተነሳ ስርዓት በጎ ነገር የመጠበቅ የዋህነት አብሮ የመግደልን ያህል ወንጀል ከሆነበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያውያን ሌት ተቀን መስራት ያለብን በቀለ ገርባንና ተመስገን ደስአለኝን ከመሰሉ ጀግኖች ጎን መቆምና እነሱን የመሰሉ ሺዎችን ከመካከላችን ማፍራትና መንከባከብ መሆን አለበት። ዳር ቆሞ ሌሎችን በመተቸት የተጠመደው ልሂቃን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ተገቢ ዋጋ እየከፈሉ ባለበት ሰዓት የጥርጣሬና ያለመተማመን ዲስኩሩን ያቁምና የትግሉ አካል ይሁን።

ኢትዮጵያ የቅን ልጆቿ ሁሉ የጋራ ናት!

በሁሉም አቅጣጫ መስዋዕት በሚከፍሉ ልጆቿም በቅርቡ ጨለማው ይገፍላታል!!

በአንድነት የተነሱ ታጋዮቿ ይታደጓታል!!

Amerid2000@gmail.com

ከኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ የተሰጠ መግለጫ

EPPFG Stamp 2
በኣሁኑ ወቅት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እያካሄደ ያለውን ህዝባዊ ማእበል እንደግፋለን። ህብረተሰባችን በራሱ ተነሳሽነት እያደረገ የሚገኘውን ወያኔን የመጋፈጥ እንቅስቃሴ የራስ የማድረግ ስራ ግን እንቃወማለን።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ባለፉት 25 ኣመታት በዘረኛው የወያኔ መንግስት ስር ወድቆ የሰላም፣ የፍትህ እና መልካም ኣስተዳደር እጦት ወስጥ እንደሚገኝ ኣለም የሚያውቀው ነው። ይህ ግፍና መከራ የበዛበት ጀግናና ትእግስተኛ ህዝብ ግን ኣንድ ቀን ትግስቱን ጨርሶ በጨቋኙ ላይ እንደሚነሳ ይጠበቅ የነበረ ጉዳይ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብም ይህ ኣይነት ስር ነቀል እምቢ ባይነት እና ህዝባዊ ማእበል በወያኔ ቡድን ላይ እንዲመጣ የራሱን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል።
ይኸው እውን ሆኗል። ዛሬ በመላው ኦሮሚያ እና በሰሜኑ ያገራችን ክፍል በጎንደር ኣካባቢ የተፋፋመ ህዝባዊ ኣመጽ እየተካሄደ ነው የሚገኘው።
ወያኔም የሚያደርገው ጠፍቶት የተለመደ የጭካኔ ዱላውን ተቃዉሞውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በሚወጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያሳረፈ ይገኛል። ይህም ሆኖ ትግሉ ላይ ማፋፋሚያ ነዳጅ ይጨምርበት እንደሆነ እንጅ እሳቱን እንደማያዳፍነው የታመነ ነው።
ያም ሆኖ ግን ትግሉ የተናጠል ሳይሆን የመላ ህዝባችንን የጋራና ኣንድነት ትግል የሚጠይቅ ነው። ስለዚህ የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ኣያካሄዱ ያሉትን ፍትሃዊ ተቃዉሞ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲቀላቀለው እና ድጋፉን እንዲገልጽ ጥሪ እናቀርባለን።
ለዘመናት ተከብራ የኖረችው ኣገራችን ድንበር ተቆርሶ ለሱዳን ኣይሰጥም ብሎ የሞት ሽረት ተጋድሎ እያደረገ ያለው የጎንደር ህዝብንም የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ እንደተለመደው ከትግሉ ጎን መቆሙን ይገልጻል።
የወልቃይት ና ጠገዴ ህዝብ ያለፍላጎቱ በትግራይ ስም የኖረበትን ዘመን ሽሮ ወደ ኣማራነቱና ጎንደሬነቱ ለመመለስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴም ኣንደግፋለን። መላው ኣገር ወዳድ የሃገራችን ህብረተሰብም ከጎንደር ህዝብና ከኦሮሞ ህዝብ ጎን በመሆን የራሱን ኣገራዊና ታሪካዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን። ይህ ካልሆነ ግን ምን ኣልባትም ኣሁን እየተቀጣጠለ ያለው ፍትሃዊ እምቢባይነት ወደ ግቡ ለመድረስ ጊዜ ይወስድበታል። ኢህኣዴግ ከመከፋፈል ምን ያህል እንደተጠቀመ ህዝባችን ባለፉት ኣመታት በሚገባ ተረድቶታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ህዝባችን በራሱ ተነሳሽነት እና መሪነት እያደረገ ያለዉን ህዝባዊ ኣመጽ ከሩቅ ሆነው የሚመለከቱና እጃቸው የሌለበት ኣንዳንድ ሃይሎችና ግለሰቦች የነሱ ስራ እንደሆነ ኣድርገው የሚሰጧቸውን መግለጫውች የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ በጥብቅ ይቃወማል። ምክንያቱም ይህ ህዝባዊ ማእበል ጊዜውን ጠብቆ የተፈጠረ ህዝባዊ ኣመጽ ነው። ይህን ታሪካዊ እንቅስቃሴ ከህዝብ ወስዶ ወደራስ ማስጠጋት የህዝብን ትግል እንደመንጠቅ ይቆጥራል።
ለኢትዮጵያ ኣንድነት ሳይሆን ለሃገሪቱ መበታተን ሃይማኖትንና የመሳሰሉትን ሽፋን በማድረግ የባእዳን ኣገር ተልእኮን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ኣካላትንም ድርጅታችን በጽኑ ያወግዛል።
ለመብታቸው መከበር እጅና ኣእግራቸውን ይዘው በወጡ በኦሮሚያና በጎንደር ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየተካሄደ ያልው ዘግናኝ ግድያና እስራትም ባስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
ድል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ። ቀብር ለወያኔ።
ከኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ ፕሬስ ክፍል።