ዮናታን ረጋሳ ታሰረ


የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረውና ብዙ ጓደኞቹ እንደሚስማሙበት እጅግ ታታሪ የመብት ተሟጋች እና ፖለቲከኛ ዮናታን ረጋሳ በወያኔ ደህንነቶች ታፍኖ በታዋቂው የማእከላዊ እስር ቤት እንደሚገኝ ታውቋል። ቀደም ሲል ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችም በተመሳሳይ መታፈናቸው ይታወሳል።Yonatan Regassa of Blue party

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባን በማስፋት ስም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎችን መሬት ለመቀራመት ሲሰናዳ በተቀሰቀሰበት ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ በመደናገጥ ከመቶ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎችን ደግሞ በየማጎሪያ ካምፖቹ በማሰር ላይ ይገኛል።

የወያኔው አገዛዝ ሰሞኑን የአፈና ድርጊቱን አጠናክሮ በመቀጠል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮችንም ከያሉበት እንዲታፈኑ አድርጓል።

ወትሮውንም ጋዜጠኞችን እንደ ጦር የሚፈራው ወያኔ የነገረኢትዮጵያ ሪፖርተር ጌታቸው ሽፈራውንና ሌሎች ጋዜጠኞችንም በማሰር እና በማባረር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ወያኔ ከአስር ዓመት በፊት ምርጫ 1997ን ተከትሎ ተነስቶበት የነበረውን ህዝባዊ እምቢኝነት ለማዳፈን ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።

ይህ በዚህ እንዳል በኦሮምያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጨርሶ እንዳልበረደ የሚያሳዩ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ። ወያኔም በበኩሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ለማፈን ኦሮምኛም ሆነ አማርኛ ቋንቋን የማይናገሩ ገዳይ ወታደሮቹን ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ግድያና አፈናውን ተያይዞት ይገኛል።

ጨለማን ተገን አድርጎ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን በመቋረጥና ሂሊኮፕተሮችን በመጠቀም በድንገት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ የዘረገፋቸው ገዳይ ወታደሮቹ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል፣ ይህ ድርጊት እራሱን መንግስት እያለ የሚጠራው የወያኔ ቡድን እውነተኛ ማንነቱን የሚያሳይ ነው።

ሁኔታዎች ሁሉ እንደሚያመላክቱት ወያኔ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራ ቡድን ነው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s