የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር በክልሉ ንጹሃንን የገደሉትን የፌደራል ፖሊሶች አመሰገኑ


muktar
(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በሰላማዊ መንገድ ሰልፍ የወጡ ንጹሃን ዜጎችን የገደሉትን የፌደራል ፖሊሶች አመሰገኑ::

በአሁኑ ወቅት በርካታ ዜጎች በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ሕዝባዊ ጥያቄ የተነሳ ቆስለው በህክምና ላይ ሲሆኑ ከአንድ መቶ የማያንሱ ሰዎችም በፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ይታወሳል:: እነዚህን ዜጎች የገደሉትን ወታደሮች ለወሰዱት እርምጃ አመስግነው በክልላችን ሰላምን ለማምጣት የወሰዱት እርምጃ ነው ብለውታል::

“በሰሞኑ አመጽ የመከላከያና የፖሊስ ኃይሎቻችን አፈጻጸማቸው ለሕዝብ ደህንነት በጽናት የቆሙ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው:: በዚህ አጋጣሚ ለጸጥታ አካላት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በራሴ ስም ታላቅ ምስጋና ላቀርብላቸው እወዳለሁ።” ያሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር ይህ አነጋገራቸው በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን እንደቀሰቀሰ ተገልጿል::

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሞ ተማሪዎች ያደረሱት ሕዝባዊ ቁጣ ለአዲስ አበባው ቤተመንግስት 20 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ሕወሓት የሚመራው መንግስት አቅጣጫውን በመቀየር የኦህ ዴድ መሪዎች ከሕዝብ ጎን እንደቆሙ በማስመሰል “ፌደራል ፖሊሶች ክልላችንን ለቀው ይውጡ ሲሉ የኦህዴድ ባለስልጣናት ገለጹ” ሲል ዜና ማስነበቡና ሕዝቡን ለማደናገር መሞከሩ ይታወሳል:: ይህ ሳያንስ አቶ አባ ዱላ ገመዳም ሆን ተብለው በዛሚ ኤፍ ኤም ላይ ቀርበው መንግስትን በይፋ እንዲተቹና ከሕዝብ ጎን እንደቆሙ ለማስመስል ፕሮፓጋንዳ ተሰርቷል:: አሁን ነገሮችን ያረጋጉ ሲመስላቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር እንዲህ ያለውን ምስጋና ለገዳዮች ማቅረባቸው ሕዝቡን አስቆጥቷል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s