“በኦሮሚያ ግጭትና ተቃውሞ ከ400 በላይ ሰዎች ሞተዋል” ሂውማን ራይትስ ዎች


death-toll-rises-to-140-in-ethiopia-protests-against-urban-expansion-1452276969

Written by Alemayehu

የ314 ሟቾች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል
በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ በነበረው ተቃውሞና ግጭት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የገለፀው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከ300 በላይ የሚሆኑ የሟቾችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረበው የምርመራ ሪፖርቱ፤ 28 የፀጥታ ኃይሎችና የመንግስት ሹማምንትን ጨምሮ 173 ሰዎች በግጭቱ መሞታቸውን መግለፁ የሚታወስ ሲሆን፤ የፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊና ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰዱት ማለቱ አይዘነጋም፡፡ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ፤ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ከመጠን በላይ የኃይል እርምጃ ወስደዋል ብሏል ከትናንት በስቲያ ባወጣው ሪፖርት፡፡
በግጭቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መቁሰላቸውን፣ በ10ሺዎች የሚገመቱ ለእስር መዳረጋቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የደረሱበት አልታወቀም ብሏል፡፡ አብዛኞቹ በግጭቱ የተገደሉት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ሙዚቀኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርና አባላት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና ከፀጥታ ኃይሎች የሚሸሹ ተማሪዎችን ያስጠለሉ ግለሰቦች ለእስር መዳረጋቸውን አመልክቷል፡፡
የተቋሙ የምርመራ ቡድን ሪፖርቱን ለማጠናቀር ከ17 የኦሮሚያ ዞኖች 125 ሰዎችን ማነጋገሩ የተጠቆመ ሲሆን የተለያዩ ግለሰቦች፣ ተጎጂዎች፣ የአይን እማኞች፣ የመንግስት ሹማምንትና፣ የሚዲያ ባለሙያዎች ቃለ ምልልስ ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርቱ ማጠቃለያ፤ የታሰሩ ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ለተጎጂዎች ድጋፍ እንዲደረግ እንዲሁም ወንጀል የፈፀሙ ለህግ እንዲቀርቡ መንግስትን ጠይቋል፡፡

click heir :- 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s