የኢህአግዘ ጁላይ 16/2016 በአሻፍንበርግ ከተማ በየሶስት ወሩ የሚያካሂደውን መደበኛ ስብሰባ አካሂዱዋል ::


By Alemayehu Kidanewold /Reporter

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ጁላይ 16/2016 በጀርመን ሃገር አሻፍንበርግ ከተማ በየሶስት ወሩ የሚያካሂደውን መደበኛ ስብሰባውን ከ መቶ በላይ አባላቱ በተገኙበት አካሂዱዋል ::IMG_1656

በስብሰናው ላይ በወቅቱ የሃገራችንን ሁኔታዎች በማንሳት ሰፊ ውይይት አካሂዱዋል:: በአሁኑ ሰአት የወያኔ ስርአት አልባ አገዛዝን በመቃወም አደባባይ የሚወጡትን ንጹሃን ዜጎችን በጥይት በመጨፍጨፍ ህዝቡን ከድህነቱ ፣ ከርሃቡና ከመቸገሩ ጋር ሌላ ፣ ሊቁዋቁዋመው የማይችል ቁስል በመጨመር ግፉን አጠናክሮ መቀጠሉን ያነሱት ተሰብሳቢዎቹ በተጨማሪ ቤተሰብ ያለ ጡዋሪ ሃገርም ያለ ተተኪ ትውልድ እንዲቀር ሰላማዊውን ህዝብ ያለ ምንም ርህራሂ በየጎዳናው እያረገፈው መሆኑን በእልህና በቁጭት ተናግረዋል::

ከዚህ በፊት በኦሮምያ ክልል በተነሳው አመጽ ቁጥራቸው ከ 350 በላይ የሆኑ ሰዎች መጨፍጨፉ እንዳለ ሆኖ አሁን ደግሞ በ አማራው ክልል በጎንደር ከተማ ሌላ ደም ማፍሰሱን ስለቀጠለበት ይህም በስብሰባው ላይ እንደ አንድ ርዕስ ሆኖ አባላቱ በሰፊው ተወያይቶበታል ::

ተሰብሳቢውም በምን መልኩ ትግሉን ማገዝ እና መቀላቀል ይቻላል?” በሚለው ዙሪያ ሃሳብ አንስቶ የተወያየ ሲሆን ይህን የወያኔ ፋሺስታዊ አገዛዝ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንደሚቆሙ  ለመላው አለም ለማሳወቅ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ከስምምነት ላይ ተደርሶዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጀርመን ሃገር ለአሻፍንበርግ ከተማና አካባቢው ያሉትን አባላት ከ 3 አመት በላይ ያገለገሉትን ሊቀ መንበር በአዲስ መተካቱን ያሳወቀ ሲሆን በመጨረሻም በድርጅቱ ውስጥ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚያገለግሉ አባላትን በመሸለም እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ሊቀ መንበር አቶ ልኡል ቀስቅስ የመዝጊያ ንግግር በማድረግ የስብሰባው ፍጻሜ ሆንዋል ::

 

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s