Archive | July 31, 2016

ሰበር ዜና . . . በጎንደር የአማራ ልዩ ሐይልና የአካባቢ ሚሊሻ ህዝባዊነት እያሳዩ ነዉ ተባለ

ethiopian-army
በጎንደር ተሰማርቶ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የልዩ ሐይልና የአካባቢ ሚሊሻ ባጠቃላይ ነገ የሚካሄደዉን የጎንደርን ሰልፍ ተነተርሶ የተሰጣቸዉን ሰላማዊ ሰልፍ የማክሸፍ ሴራ ያለማቀበላቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ደርሰዉናል።
·         ከየትኛዉም መንደሮች ወደ መሰብሰቢያ ቦታዉ የሚወስዱ መንገዶች በጸጥታ ሐይሎች እንዲዘጉ።
·         ሰልፉን ያስተባብራሉ ይመራሉ ይቀሰቅሳሉ የሚባሉ ግለሰቦች ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ማድረግ…… ትእዛዝ (( )) ይህ ሁኔታ የጸጥታ ሐይሎችን በመጠቀም ማስገደድንም ይጭምራል
·         የስረአቱን ቀንደኛ ደጋፊ ብአዴኖችን በመጠቀም ጥቆማዎችን አይነተኛ መሳሪያ አድርጎ ማባበያ (መደለያ) እና ማዘናጊያ እቅዶችን ማስፈጸም!!
·         ይህ ካልሆነ በጸጥታ ሐይሎች ተጠቅሞ እርምጃዎችን በተጠና ሁኔታ መዉሰድ>>>> የሚሉ ሲሆኑ እነዚህና የመሳሰሉት ሂደቶች ዉጤታማ ስይሆኑ ቢቀሩና ሰልፉ ቢካሄድ የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ እንዲሁን ትእዝዝ ቢተላለፍም ባጠቃላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የጸጥታ ሐይሎች ብሎም የአካባቢ ሚሊሻ . . . . . ” አንዳችም ሰዉ ላይ ጉዳት አናደርስም ” አፈና አናካሄድም! ህዝቡ መብቱን በሰላማዊ መንገድ እየገለጸ ከመካከላችን አንዳች ስህተት ቢሰራ ዝም ብለን አንመለከትም! በማለት አቋማቸዉን የገለጹ ሲሆን በተለይም የአካባቢ ሚሊሻዎች በተለየ ሁኔታ ከህዝቡ ጎን መቆማቸዉን በድፍረት ተናግረዋል።
እነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ ገደል በገደል የሆኑበት የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን ሰሜን ጎንደር አይከል አካባቢ ያሰፈረዉን የአጋዚ ጦር ወደ ጎንደር እያስገባ ከመሆኑ በተጨማሪ በባሕር ዳር ስምሪት ላይ የነበረ የልዩ ሐይል ወደ ጎንደር እንዲንቀሳቀስ የተደረገ ሲሆን
….  በጎንደር የልዩ ሐይልና የአካባቢ ሚሊሻ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ምድቦች ማንም ይምጣ ማን ይህን ህዝብ ይንኩና እንተያያለን በማለት እርስ በእርሳቸዉ ተፋጠዉ ይገኛሉ።
ዜና -በልኡል አለም